Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለብሔራዊ ቡድን ለምን አልተመረጥኩም ብዬ ራሴን አላስጨንቅም” “መጪው ጊዜ የእኔ ነው” ብሩክ በየነ /ሐዋሳ ከተማ/



በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ዘንድሮ በክስተት ተጨዋችነት በመቅረብ ለክለቡ 9 ግቦችን አስቆጥሯል፤ ይሄ የግብ ቁጥሩም ለኮከብ ግብ አግቢነቱ ከእነ ሙጂብ ቃሲምና ከሌሎች ተጨዋቾች ጋርም እያፎካከረው ይገኛል፤ ተጨዋቹ ብሩክ በየነ ሲባል፤ በብዙዎቹ ዘንድ ደግሞ አቡሌ ተብሎም ይጠራል፤ ከዚህ ተጨዋች ጋር ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ሐዋሳ ከተማ በሊጉ እያደረገው ስላለው ፉክክርና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቆይታን አድርጎ ተጨዋቹ ምላሽን ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡
የሐዋሳ ከተማን የፕሪምየር ሊግ ጉዞ በተመለከተና ስለሁለተኛው ዙር አጀማመራቸው
“የመጀመሪያው ዙር የሊጉ ተሳትፎአችን እንደ ቡድን ለእኛ ጥሩ ውጤት ያስመዘገብንበት ነበር፤ በግሌም በእዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ ላይ ከወዲሁ በጣም ለምወደው ክለቤ ዘጠኝ ያህል ጎሎችን ያስቆጠርኩበትና የስኬታማነትንም ጊዜ እያሳለፍኩበት ያለ በመሆኑ ብዙ ነገሮች መልካም በሆኑ መንገዶች እየሄዱልኝ ነው የሚገኙት፡፡ የፕሪምየር ሊጉን የሁለተኛ ዙር አጀማመራችንን በተመለከተ ደግሞ ምንም እንኳን ግጥሚያችንን በሽንፈት ብንጀምርም ይሄን የውጤት ማጣት በፍጥነትና በእርግጠኝነት እናስተካክለዋለን ከዛ ውጪም ጠንካራም የፕሪምየር ሊጉ ተፎካካሪ እንሆናለን”፡፡
ሐዋሳ ከተማን በፕሪምየር ሊጉ ጎድሎታል የምትለው ነገር
“የፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎአችን ላይ ቡድናችንን ጎድሎታል ብዬ የማስበው ነገር ከሜዳ ውጪ የምናደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ ውጤትን ማስጠበቅ የማንችልበትን ሁኔታና ጎል እንዳይቆጠርብንም ማድረግ አለመቻላችን ነው፤ በሜዳችን ስንጫወት ደግሞ እስካሁን ያለንን ጨዋታ አለመሸነፍ መቻላችን በጥሩ ጎን የሚታይ ስለሆነ ከሜዳ ውጪ ለምናደርጋቸው ጨዋታዎች ከእዚሁ የሜዳችን ላይ ጨዋታዎች ትምህርት በመውሰድና ጠንክረንም በመስራት ጠንካራ ቡድንን ለመገንባት ተዘጋጅተናል”፡፡
የሐዋሳ ከተማ የተጨዋቾች ስብስብ በወጣት የተገነባ ነው ማለት ይቻላል?
“ከምነግርህ በላይ አዎን፤ ብዙ ታዳጊና ወጣት ተጨዋቾችም ናቸው በስብስባችን ውስጥ ያሉት፤ ክለባችን እንዲህ ያሉ ተጨዋቾችንም ከበፊት አንስቶም ያፈራልና ይሄ የእግር ኳሳችንን ለማሳደግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ በመሆኑም ያለው አሠራር ሊደነቅ የሚገባው ነው”፡፡
ሐዋሳ ከተማ ለሁለት ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና ሆኗል፤ ይሄን የክለቡን ስምና ዝና ምን ያህል ያውቅ እንደሆነ
“ሐዋሳ ከተማ በፕሪምየር ሊጉ የከዚህ ቀደም ተሳትፎው ስለነበረው ስም እና ዝና እንደዚሁም ደግሞ ስለ ውጤታማነቱ እኛ አሁን ላይ ብቅ ያልነው ወጣት ተጨዋቾች ብዙ ነገሮችን ቀደም ሲል ያሰለጥነን ከነበረው አዲሴ ካሳም ሆነ የአሁኑ አሠልጣኛችን ብርሃኑ ወርቁ /ፈየራ/ በሚገባ የተነገረን ጥሩ ጥሩ ነገር አለ፤ ከእነዛ ውስጥ ለምሳሌ ቡድኑ ስለነበረው ምርጥ የተጨዋቾች ስብስብና ወጣት ተጨዋቾችም እንደሚበዙበትም ይነግሩን ነበርና እኛም ያንን የቀድሞ የቡድኑን ስምና ዝና ለመመለስም መዘጋጀታችንን እንነግራቸዋለን”፡፡
ሐዋሳ ከተማ የሚያፈራቸው በርካታ ተጨዋቾች ለብሄራዊ ቡድናችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ይመረጡ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ይሄ ብዙ እየሆነ አይደለም፤ አያስቆጭህም?
“በጣም ያስቆጨኛል እንጂ፤ ስለዚህም ያንን በፊት ለብሄራዊ ቡድናችን በርካታ ተጨዋቾችን የምናስመርጥበትን ወቅትና ጊዜ አሁን ላይ ያለነው እኛ ወጣት ተጨዋቾች በደንብ ስለማናውቅ በህብረት ጠንክረን እየሠራንና እኛስ መቼ ነው ለብሔራዊ ቡድንስ የምንመረጠው በሚለውም ላይ እየተነጋገርበት ስለሆነ ያንን ታሪክ የምናስመልስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም”፡፡
የሐዋሳ ከተማ ክለብ ውስጥ ባለው የተጨዋችነት ቆይታ ደስተኛ ስለመሆኑና የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛው ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ ለብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ አለመቻሉ
“ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተጨዋቾች ምርጫ ላይ በመነሳት አሁን ላይ ለቡድኔ በርካታ ጎሎችን ስላስቆጠርኩ ብቻ ለምን አልተመረጥኩም ብዬ የምጓጓ አይነት ተጨዋች አይደለሁም፤ አሁን ላይ ባለኝ ወቅታዊ አቋምም ገና ወጣትና ብዙ ተስፋ የሚጣልብኝም ተጨዋች ነኝ፤ ስለዚህም በመጪው ጊዜም ብሩህ ተስፋን የማይና ብዙ ነገሮችም ከፊቴ የሚጠበቅብኝ ተጨዋች እንደሆንኩ ስለማውቅ ለብሄራዊ ቡድን አሁንም በድጋሚ መናገር እፈልጋለው ከወዲሁ ለምን አልተመረጥኩም ብዬም ራሴን በሚገባ አላስጨንቅም፤ የእግር ኳሱ ላይ ደስተኛ ነህ ወይ ለተባልኩት አዎን በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ወደፊትም ደስተኛ እሆናለው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ባለው ብቃት ራሱን በምን ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጥ
“በእግር ኳስ አሁን ላይ ገና ጅማሪ ተጨዋች ነኝ፤ ወደፊት ግን የሀገሪቷ ትልቅ ተጨዋች እንደምሆን በጣም እርግጠኛ ነኝ”፡፡
የእግር ኳሱ ላይ ከማን ጋር ተጣምሮ ቢጫወት ደስ እንደሚለው
“የእግር ኳሱ ላይ እስከአሁን የመጫወት እድሉን አብሬው ባላገኝም አብሮኝ እንዲጫወት የምመኘው ተጨዋች የልጅነት እድሜዬ ላይ በጣም አድንቄው ያደግኩት ጌታነህ ከበደ ነው፤ ከእሱ ጋር ብጫወት በጣም ደስ ይለኛል”፡፡
ከሐዋሳ ከተማ ተጨዋቾች ውስጥ የቡድን አጋርህ የሆነው መስፍን ታፈሰ ለዋልያዎቹ ተመርጧል፤ በእሱ መመረጥ ምን እንደተሰማው
“የሐዋሳ ከተማው መስፍን ታፈሰ ገና ታዳጊ እና ጎበዝም ተጨዋች ነው፤ ከወዲሁም ለብሔራዊ ቡድን በመመረጡም በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ በእሱ የሜዳ ላይ ብቃትም ከፍተኛ እምነትም ስላለኝ ዋልያዎቹን ወደፊት ብዙ ይጠቀማቸዋልም እላለው”፡፡
ሐዋሳ ከተማ የበፊት አሰልጣኙን ከኃላፊነት አንስቶ በአዲሱ አሰልጣኝ እየተመራ ይገኛል፤ በስራ ላይ ልዩነት አይተህባቸዋል?
“የበፊቱ አሰልጣኛችን አዲሴ ካሳ በእግር ኳሱ ላይ በሚያጋጥም አይነት ሁኔታ ከሃላፊነቱ ቢነሳም የአሁኑ አሰልጣኛችንም ብርሃኑ ቡድኑን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ እንደአዲሴ ሁሉ የእሱን የስልጠና አካሄድ ባላቀቀ ሁኔታ ቡድናችንን በጥሩ ሁኔታ እያሰለጠነ ይገኛልና ብዙም ያየንባቸው ልዩነቶች የሉም፤ ሁለቱም ጥሩ አሰልጣኞች ናቸው”፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለየቱ ቡድን የተለየ አድናቆትና ፍቅር አለህ?
“የሊቨርፑል ደጋፊነቴ እንዳለ ሆኖ ባርሴሎናንም በጣም ነው የምወደው፤ በተለይ ደግሞ ባርሳን የወደድኩት ለሊዮኔል ሜሲ ስል ነው፤ እሱ የተለየ እና የአለማችንም የምንጊዜው ምርጡም ተጨዋች ነው”፡፡
ሊቨርፑል በአትሌቲኮ ማድሪድ ተሸንፎ ከአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ውጪ ስለመሆኑና ስለነበረው ፉክክር
“በሊቨርፑል ሽንፈት በጣም ተናድጃለው፤ ምክንያቱም ክለቡ እንዳለው ጥንካሬ ከዚህ ውድድር መውጣት አልነበረበትምና፤ ግን ኳስ ነውና ያ ነገር አጋጠመው፤ የሁለቱ ቡድኖችን ጨዋታ በተመለከተ ግጥሚያው በጣም ጠንካራና ከባድ ነበር፤ አትሌቲኮዎች ውጤት አስጠብቀው ለመውጣት ነበር የመጡት፤ በኋላ ላይ ግን የመልሶ ማጥቃት አጨዋወታቸው ጠቅሟቸው ጨዋታውን ሊያሸንፉ ቻሉ”፡፡
የአንተ የተለየ ባህሪህ
“በጣም ዝምተኛ ነኝ፤ ይሄ ይገልፀኛል”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ዘመንህ መድረስ የምትፈልገው ስፍራ
“የመጀመሪያው ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን በመመረጥ በስኬታማነት ማገልገል፤ ቀጥሎ ደግሞ ፕሮፌሽናል ተጨዋች ሆኜ የሀገሬን ስም ማስጠራት”፡፡
የእግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮ?
“እሱን ፈጣሪ ነው የሚያውቀው፤ ሌላ ነገርን መቼም ቢሆን አስቤ አላውቅም”፡፡
ወደ ሐዋሳ ከተማ መጥቶ መዝናናት ለሚፈልግ ሰው አስጎብኝ ብትባል
“መጀመሪያ የፍቅር ሀይቅን ነው የማሳየው፤ ያንን ካስጎበኘሁት በኋላም ዓሳን እጋብዘዋለው”፡፡
የክለባችሁ አዝናኝ ተጨዋች
“ሁሉንም ስትቀርባቸው አዝናኝና አስቂኞችም ናቸው፤ በዚህ ነጥለህ የምትጠራውም ተጨዋች የለም”፡፡
በቡድናችሁ ዝምተኛው ተጨዋችስ
“ዳንኤል ደርቤ ነዋ! እሱን ብዙም ሲያወራ ተመልክቼውም አላውቅም”፡፡
የእግር ኳስን ስትጫወት በተለየ መልኩ የማትረሳው ነገር አለ?
“አዎን፤ ያኔ ልጅ ሆኜ ሐዋሳ ከተማ በሚገኘው ቀበሌ 02 ሜዳ ላይ ኳስን ስንጫወት የወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ የነበረው አዲሴ ካሳ እስከ እረፍት ድረስ ስንጫወት ተመልቶኝ ነበርና ከዚህ ይዤህ ልሂድ ለወልቂጤ ከተማም ላጫውትህ ሲለኝ በጣም ገርሞኝና ደንቆኝ ነበር፤ ወዲያውንም ወደ ወልቂጤ ወስዶና ክለቡ ውስጥ አስገብቶም ለቡድኑ አጫወተኝ ያን መቼም የማልረሳው ነው፤ ለእኔም የተለየው ቀን ያ ነበር”፡፡
የልጅነት እድሜህ ላይ ፀበኛ ነበርክ… ወይንስ በተቃራኒው?
“ፀበኛ እንኳን አይደለሁም፤ ሜዳ ውስጥ ስገባ ግን በጣም እልኸኛ ነኝ”፡፡
እግር ኳስን ከመጫወት ውጪ ለመዝናኛነት የምትመርጣት ከተማ
“መቐለ ከተማ ናታ፤ እሷ ከተማ በጣም ትመቸኛለች፤ ሀገሯ በጣም ፍቅርም የሆነች ነች”፡፡
በእግር ኳስ ማሻሻል የምትፈልገው
“ለሐዋሳ ከተማ ስጫወት ብዙ ጊዜ አንድ ወይንም ደግሞ ሁለት ጎልን ነው የማገባው፤ ይሄን የጎል ቁጥር ወደ ሀትሪክ መስራትና ከዛ በላይም በማስቆጠር ማሳደግም እፈልጋለሁ”፡፡
የፕሪምየር ሊጉን የእስካሁን ጉዞ በተመለከተ
“የፕሪምየር ሊጉን ውድድር በፉክክር ደረጃ እንደተመለከትኩት በሜዳህም ሆነ ከሜዳ ውጪ ስትጫወት አሁን ላይ በጣም ከባድና ጠንካራ ፉክክር እየተደረገበት ነው፤ ቡድኖች ካላቸው የተቀራረበ ነጥብ አኳያም ሻምፒዮናውም ሆነ ወራጅ ክለቡ ገና አልተለየም፤ ለመለየትም የሚያስቸግር ነው፤ ስለዚህም ይሄ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ በተለይ በዳኝነት ላይ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ብዙ ነገርን ሊሰራ ይገባዋል፤ ክለቦችም የማንም እገዛ ሳያስፈልጋቸው በላባቸውም ብቻ የጨዋታ አሸናፊ ሊሆኑ ይገባል”፡፡
በቅርቡ ዓለም ላይ የኮሮና ቫይረስ ተስፋፍቶ ህዝቡን እያሳመመውና እየገደለውም ይገኛል፤ ምን ትላለህ?
“በሽታው በጣም ከባድና የሚያስፈራም ነው፤ ማለት የምችለው ነገር ቢኖር ፈጣሪ ይጠብቀን ነው”፡፡
በአለም ላይ ካሉ ሰዎች ማግኘት የምትፈልገው
“ሊዮኔል ሜሲን ነዋ! እሱ ልዩ ሰው ነው፤ በጣምም ነው የምወደው”፡፡
በመጨረሻ….
“የእግር ኳሱ ላይ አሁን ለደረስኩበት ደረጃ ብዙ ሰዎችን ማመስገን እፈልጋለሁ፤ መጀመሪያ ግን ለምስጋናው ፈጣሪዬን ነው የማስቀምጠው፤ ከዛ በመቀጠል ደግሞ አሰልጣኜና ብዙ ነገር ያደረገልኝን አዲሴ ካሳ በእኔ ህይወት ውስጥ ብዙ ቦታ ስላለውም እሱንና አሰልጥነውኝ ያለፉትን በሙሉ አመሰግናቸዋለው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P