Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ ነበረብኝ፤ የግድ ግን ልግባ አልልም”ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን /ኢትዮጵያ ቡና/

“ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ ነበረብኝ፤ የግድ ግን ልግባ አልልም”
“ኢትዮጵያ ቡና ብዙ ተጨዋቾችን ባለማስፈረሙ አይጎዳም፤ ያሉን ተጨዋቾች በቂ ናቸው”
ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን /ኢትዮጵያ ቡና/


የኢትዮጵያ ቡና የአማካይ ስፍራን በመምራት ይታወቃል፤ ከዛ በፊት በነበረው የኳስ ጨዋታ ዘመኑ ደግሞ ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ለሐዋሳ ከተማ ክለቦች በአብዛኛው በቋሚ ተሰላፊነት በመጫወት እና ችሎታውንም እያሻሻለ በመምጣት የአሁን ሰዓት ላይ ለሚጫወትበት ቡድን ጥሩ ግልጋሎቱንም እየሰጠ ይገኛል፤ በሀሰላ ከተማ የተወለደው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ተጨዋች የነበረው ታሪኩ ስምኦን ደግሞ አጎቱ እንደሆነ የሚናገረው ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን /ችምስ/ ከሊግ ስፖርት አዘጋጅ ከሆነው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ጋር የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ከመጀመሩ በፊት ቡድናቸው እያደረገ ስላለው የፕሪ-ሲዝን ዝግጅት፣ ቡና በሊጉ ምን ውጤት እንደሚያመጣ፣ ከራሱ እና ከሌሎች ከኳስ ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች ዙሪያ አውግቷልና፤ ቆይታችን ይሄን ይመስላል፤ ተከታተሉት፡፡
በፕሪ-ሲዝን እያደረጉ ስላለው ዝግጅት
“እስካሁን አንድ ወር ከ7 ቀን ለሚደርስ ጊዜ ተዘጋጅተናል፤ በእዚሁ ጊዜ የዝግጅት ጊዜ ልምምዳችንም ከኳስ ጋር የተያያዙ ስራዎችን በመስራት ላይም ነው ያለነው፤ ከዛ ውጪም አሁን ላይ ደግሞ በእዚሁ ዝግጅት ወቅት በብሔራዊ ቡድን ውስጥ የነበሩትም ተጨዋቾቻችን ተቀላቅለውን ልምምድን እየሰሩና የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችንም በማድረግ በአሁን ሰዓት ላይ ወደ ሜዳ ስንገባ ራሳችንን በምን መልኩ አዘጋጅተን እንደምንመጣ መመልከትንም ጀምረናልና ይሄ ነው የእስካሁኑ የዝግጅታችን አካል፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ሌላ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ለበርካታ ወራቶችም ከኳሱ ርቀንም ነበርና አሁን ላይ በእዚህ መልኩም ወደምንወደው እና ለእኛ ደግሞ ህይወታችን ወደ ሆነው የእግር ኳሳችንም ስለተመለስን በጣም ነው ደስ ያለኝ”፡፡
ዘንድሮ ካለፈው ዓመት የተሻለና ጥሩ ቡድንን ይዘው ይቀርቡ እንደሆነ
“ይሄ ሊገጥመን እንደሚችል ከወዲሁ አስባለው፤ ምክንያቱም ያለፈው ዓመት ሁለተኛው ዙር ከገባ በኋላ ቡድናችን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ይታይ ነበር፤ የሊጉን ውድድር ኮቪድ አቋረጠው እንጂ ቡና ከእዛም በላይ ይጓዝ ነበር፤ስለዚህም ዘንድሮ በሚኖረን የሊጉ ተሳትፎ ቡድናችን ያን ጥሩነቱን አስቀጥሎ እንደሚመጣና የሊጉንም ዋንጫ ለማንሳት እንደሚጫወት ከፍተኛ እምነት ነው ያለኝ”፡፡
በፕሪምየር ሊግ ተሳትፎአችሁ እንደ ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነትህ ምን ውጤትን እናመጣለን ብለህ ነው ያቀድከው?
“ኢትዮጵያ ቡና ምንጊዜም የሚጫወተው የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ነው፤ ይሄን ከላይም ገልጬዋለሁ፤ እንደ አንድ ተጨዋችም ልናገር የምፈልገው ክለባችን ጥሩ የሚባል ውጤትን እንዲያመጣልን ሁላችንም እንፈልጋለን፤ እኛ ያለምንም ጫና ከተጫወትን፣ በአሰልጣኞቻችን የሚሰጡንን ስራዎች ተግተን በመስራት ካከናወን፣ የያዝነውን አጨዋወት ካለቀቅን እና እንደዚሁም ደግሞ የሊግ ውድድሮቹ ሳይቆራረጡ ከቀጠሉ የውድድሩ ሻምፒዮና የማንሆንበት ምንም አይነት ምክንያት የለም”፡፡
በፕሪምየር ሊጉ የዝውውር መስኮት በስፋት አለመሳተፋቸው ይጎዳቸው እንደሆነ
“ክለባችን ዘንድሮ በነበረው የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት በርካታ ተጨዋቾቹን ካለመልቀቁ እና ያሉትንም ተጨዋቾች የውል ጊዜ አራዝሞ ከማቆየቱ አንፃር እንደሌሎች ቡድኖች በርካታ ተጨዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች ባለማምጣት የተጓዘበት መንገድ ለእኔ ይጎዳዋል ብዬ ፈፅሞ አላስብም፤ ምክንያቱም ቡና ባለፈው ዓመት የሰራው ቡድን ጥሩና ጠንካራ ነበር፤ ከዛ ውጪ ስብስቡንም ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ተጨዋቾች ከመያዙ አንፃር የወደድኩትና የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን የጨዋታ ታክቲክ ከመላመዱም ጋር በተያያዘ መልካም ጉዞን እያደረገ ያለ ቡድን ስለሆነም ነው፤ ከዛም ባሻገር ደግሞ ቡድናችንን በለቀቀው ፈቱዲን ጀማል ምትክ አበበ ጥላሁንን ስላገኘን በአህመድ ረሺድ /ሺሪላ/ ምትክ ደግሞ የሚተካ ተጨዋች ስለሚኖረን እንደዚሁም ደግሞ ቡና የሚጫወተው እንደ ህብረት በጋራ በመንቀሳቀስ እንጂ እንደ ግል ስላልሆነም ምንም የምንጎዳበት ነገር የለም”፡፡
ኢትዮጵያ ቡና የነባር ተጨዋቾቹን ውል ለአራት ዓመታት ስለማራዘሙ
“ክለባችን በእዚህ ዙሪያ የሰራው ነገር በጣም ጥሩ ነው፤ ምክንያቱም ጥቅሙ ለእሱም ለተጨዋቾቹም ነውና፤ ቡና ከእዚህ ቀደም ያሉትን ተጨዋቾች በማሰናበት አዳዲስ ቡድንን ነበር በየጊዜው የሚሰራው አሁን ግን ያሉትንና በጨዋታ እንቅስቃሴም የተላመዱትንና የተግባቡትን ተጨዋቾች በማቆየት በቡድን ግንባታው ላይ በማተኮሩ ወደ ተሻለ አካሄድ እያመራ እንደሆነ ያመላክታል፤ ወደ ተጨዋቾቹ ጋር ስትጓዝም ለእዚህን ያህል ጊዜ ፊርማቸውን ሲያኖሩ ቡድኑን በጥሩ መልኩ ለማገልገል ጠንክረው ነው የሚሰሩት፤ ነገ ክለብ አጣለው ወደሚል ስሜትም አያመሩም፤ ጥሩ አሻራን ለሚጫወቱበት ክለብም ማሳረፍ ስለሚፈልጉም የቡናን አሰራር ወድጄዋለው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ራስህን ለመስጠት ዘንድሮ በምን መልኩ ተዘጋጅተሃል?
“የእግር ኳስን ስትጫወት ሁሌም ቢሆን ካለፉት ዓመታቶች አቋምህ አንፃር በደንብ ተሻሽለህ እና የተለየ ተጨዋች ሆነህ መቅረብ ያስደስታል፤ ያ ስለሆነም እኔም በዘንድሮ የውድድር ዘመን ላይ ከእዚህ በፊት የነበሩብኝን አንድአንድ ድክመቶች በማሻሻልና የራሴን ችሎታም በሚገባ አድሼ በመምጣት ከዛ ውጪም የእኔ ስራ መጫወት ቢሆንም አሰልጣኜም በእኔ ላይ የሚጨምርልኝ ነገር ስላለ ከዛ በመነሳት ክለቤን ኢትዮጵያ ቡናን በጣም ለመጥቀም እና ውጤታማም ለማድረግ እየተዘጋጀው ነው የምገኘው”፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ቡና ካመራ በኋላ እያሳለፈ ስላለው ጊዜ
“ኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀልኩበት ያለፈው ዓመት ጊዜ አንስቶ እያሳለፍኩት ያለው ቆይታ በጣም ጥሩ እና ደስተኛም ያደረገኝ ነው፤ በእዚህ ቡድን ስቆይም ለቡድኑ ጎል ከማስቆጠር እና ለጓደኞቼም ኳስ ከማቀበል ባሻገር በምፈልገው አይነት መልኩም የእግር ኳስን ልጫወት ችያለሁ፤ ከዛም ባሻገር ኮቪድ ሊጉን አቋረጠው እንጂ በአቋም ደረጃ ለቡድኔ ብዙ ጥቅሞችን የምሰጥበት እድልም ነበረኝ”፡፡
በፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎአችሁ ጥሩ እግር ኳስን እየተጫወትን ነው ብለህ ታስባለህ?
“ለእኔ አዎን፤ ምክንያቱም ቡና እየተጫወተ ያለው አጨዋወት የጋራ እንጂ የግል ስላልሆነ ነው፤ በእዚህም እንቅስቃሴ ውስጥ ቡድናችን ሲጫወት አንድ ተጨዋች ለብቻው ተነጥሎ በሚንቀሳቀስበት መልኩ ሳይሆን ሁሉም ተጨዋች እኩል ደክሞም የኳስ ንክኪ በበዛበት መልኩም አዝናኝ የሆነን እግር ኳስ የሚጫወተውና ያ ለእኛ የተለየ ጣህም አለው፤ አጨዋወታችንም ድካምን የሚቀንስልንም ስለሆነ ያንንም በጣም ወድጄዋለው”፡፡
በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያ ቡና ያለ ደጋፊው ሲጫወት ይጎዳ እንደሆነ
“ይሄን በሁለት መልኩ ነው የማየው፤ ደጋፊዎቻችን በሌሉበት መጫወታችን በፋይናንስ ደረጃ ክለባችን በጣም ተጎጂ የሚሆንበት ነገር አለና ይሄን ጥሩ ባልሆነ መልኩ ነው የምመለከተው፤ ከሜዳ ላይ እንቅስቃሴ አንፃር ደግሞ የእነሱ አለመኖር ለእኛ ከፍተኛ ድጋፍንና ብርታትን የሚያሳጣን ነገር አለና ይሄም ተጎጂ ያደርገናል፤ እንደዛም ሆኖ ግን አሁን ላይ ኳሱ የሚካሄደው የግድ ያለ ደጋፊና ተመልካች በመሆኑ እኛን ሊጠቅመን የሚችለው ነገር ቢኖር ቡድናችን ከሌሎች ተወዳዳሪ ክለባቶች አንፃር የራሱ የሆነ አጨዋወት ስላለው ያን ሳይለቅና አጠናክሮም ማስጓዝ ከቻለ በእዛ እንቅስቃሴው በውጤት ደረጃ ተጠቃሚ የሚሆንበት ነገር አለ”፡፡
በኮቪድ ከእግር ኳሱ ርቆ ስለመቆየቱ እና ዳግም ስለመመለሱ
“የእግር ኳሳችን በተቋረጠበት እና ከኳስ ጨዋታውም በራቅንበት ሰዓት እኔም ሆንኩ ሌሎች ተጨዋቾች ያሳለፍነው ጊዜ በጣም ከባድ ነበርና ያ ወቅት ተመልሶ እንዲመጣ መቼም ቢሆን ፍላጎትን አላሳድርም፤ ምክንያቱም እግር ኳሱ ሲቋረጥ ከብዙ ሰዎች ጋር እንዳልገናኝ ከዛም ውጪ ከወዳጅ ዘመዶቼ እና ጥሩ ከሆኑም ጓደኞቼ ጋር ሻይ ቡና እየተባባልን እንዳልጨዋወት አድርጎኛል፤ አሁን ላይ ግን ኳሳችን ዳግም ወደነበረበት ሊመለስ የወራት ዕድሜ የቀረው እና የዝግጅት ጊዜ ልምምዳችንንም ሆነ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎቻችንን ሁላችንም የቡድናችን ተጨዋቾች ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምርመራ ፈጣሪ ይመስገን ነፃ በሆንበት መልኩ የጀመርንበት ሁኔታ ስላለ ያ በጣሙን ሊያስደስተኝ ችሏል”፡፡
በእዚህን ወቅት ምን ናፍቆሃል
“ወደ ኳሱ መመለሳችን ተረጋግጧል፤ የናፈቀኝ ግን የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ወደ ስታድየም መጥቶ እየዘመረ እና እየጨፈረ የሚደግፈንን ጊዜ ነው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ የተጠባባቂ ስፍራ ተጨዋች ሆኖ ያውቅ እንደሆነና ቢሆን ኖሮ ይበሳጭ እንደሆነ
“ባለፉት ስድስት ዓመታት የእግር ኳስን ለኤሌክትሪክ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለሐዋሳ ከተማ እና ለኢትዮጵያ ቡና ስጫወት ምንአልባት ወይ በጉዳት፣ ካልሆነ ደግሞ በአምስት ቢጫ ካርድ እንደዚሁም ደግሞ በአዲስ መልክ ወደ አንድ ቡድን ስገባ የመጀመሪያ ሁለት እና ሶስት ጨዋታዎቼን የክለቡን እንቅስቃሴ ከመመልከት አኳያ ለተወሰኑ ወቅቶች ተሰልፌ ሳልጫወት ቀርቼ ልሆን እችላለው እንጂ ለአንድም ጊዜ ግን ተጠባባቂ ተጨዋች የሆንኩበትን ጊዜ ፈፅሞ አላስታውስም፤ ከዛ ውጪ ለእነዚህ ቡድኖች ስጫወት ተጠባባቂ ተጨዋች ልሆን ብችል እንኳን አቋሜ ከሌሎች ተጨዋቾች ያነሰ ከሆነ አልበሳጭም ነበር፤ ምክንያቱም አንድ ተጨዋች ሊበሳጭ የሚገባው ጥሩ ችሎታ ኖሮትና ለክለቡም ከሌሎች ተጨዋቾች በተሻለ መልኩ መጥቀም እየቻለ አሰልጣኞች ሊጠቀሙበት ካልቻሉ ብቻ ነው የሚል እምነት ስላለኝ ነው”፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አለመጠራት መቻሉ እና የእግር ኳስ ሜዳው ላይ ሲንቀሳቀስ ድብቅ እና የማይታይ አይነት ችሎታ አለው ስለመባሉ
“ከእዚህ ቀደም ለብሔራዊ ቡድን የመመረጥ ዕድሉን አግኝቼና ስሜም ተላልፎ ከቆየ በኋላ ጥሪው ዳግም ሳይደርሰኝ የቀረሁበትን ጊዜ በሚገባ አስታውሳለው፤ ከዛ በኋላና በፊት ደግሞ ካለኝ ጥሩ ችሎታና በሜዳ ላይም ከማሳያቸው ጥሩ እንቅስቃሴዎች አኳያ ለብሔራዊ ቡድናችን መመረጥ እየተገባኝ ሳልመረጥ ስቀር የተቆጨሁባቸው ጊዜያቶች አሉ፤ እነዛን የመመረጥ እድሎችን ግን በወቅቱ ስላላገኘው ወደ ብሔራዊ ቡድኑ የግድ ልግባ ወይንም ደግሞ በቡድኑ ውስጥ ልኑር አልልምና፤ ለብሔራዊ ቡድን የማልመረጥበትን ምክንያት እስካሁን ላውቅ አልቻልኩም፤ እንደ አንድ አንድ ሰዎች ምልከታ ከሆነ ግን አንተ የማትመረጠው ለብዙ ሰዎች ድብቅና የማይታይ ምርጥ ችሎታ ስላለህ ነው፤ ስለዚህም አንተን በደንብ የሚመለከትና ችሎታህን በደንብ የሚረዳ አካል ያስፈልግሃል ይሉኛል፤ ይህን በሚነግሩኝ ጊዜም እስከዛሬ የብሔራዊ ቡድናችን ለተጨዋቾች ምርጫ የሚሄድበት አካሄድ ልክ እንዳልነበርም የተረዳሁበት ሁኔታ ስላለ ከእዚህ በኋላ ደግሞ ይሄን የመመረጥ እድል ለማግኘት ሙከራዬን እቀጥላለሁ፤ ከተጠራው ደስተኛ እሆናለው፤ ካልተጠራው ደግሞ አንድ ቀን እድሉን ማግኘቴ ስለማይቀር የሚያሳስበኝ ነገር የለም”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶ እንደሆነ
“እስካሁን ለአንድም ጊዜ ወጥቼ አላውቅም፤ በ5 ቢጫ ካርድ ግን አንድ ጨዋታን አርፌያለው”፡፡
በዲ.ኤስ.ቲቪ ፕሪምየር ሊጋችን ሊተላለፍ መሆኑ
“ይሄ ለእኛ ሀገር እግር ኳስም ሆነ ለተጨዋቾቻችን የሚያስገኝልን ከፍተኛ እና ትልቅ ጥቅም ስላለ ያገኘነውን አጋጣሚ በሚገባ ነው ልንጠቀምበት የሚያስፈልገን፤ የሊግ ጨዋታዎቹ በእኛ ሀገር ደረጃ ላይ መተላለፋቸው እኛን እድለኛ እንድንሆን ነው የሚያደርገን፤ ከእዚህ በላይም ሌላ ጥሩ እድል የለም፤ ምክንያቱም እነዚህ ጨዋታዎች የሚተላለፉት በበርካታ ሀገራት ስለሆነና ተጨዋቾቻችንም የሚታዩበት አጋጣሚ የሰፋ ስለሆነ ከወዲሁ የሚያስፈልገው እንግዲህ ወገብን ጠበቅ አድርጎ መስራት እና ባለህ ችሎታ ላይም የተሻሉ ነገሮችን ጨምረህም መምጣት ነውና ዲ.ኤስ.ቲቪ ለተጨዋቾቻችን ለከፈተላቸው በር ምስጋና ሊቸረው ይገባል፤ ፈጣሪ በእዚህ በኩልም ስለረዳን ለእሱም ምስጋና ያስፈልገዋል”፡፡
ወደ ትዳር ዓለሙ መግባትህን ሰማን
“አዎን፤ ገብቻለው፤ ይሄ የሆነውም ከአንድ ወር በፊት ነበር፤ ወደዚህ ጣፋጭ እና በጣም አስደሳች ወደሆነው ህይወት ስለገባውም በጣም ተደስቻለው”፡፡
ከባለቤትህ ጋር ስለነበራችሁ ትውውቅ እና ስለ እሷ የምትለው ካለ
“ባለቤቴ ረድሄት ተሾመ ትባላለች፤ እሷ የደብረዘይት ልጅ እኔ ደግሞ የሀሰላ ልጅ ሆነን ነው በአጋጣሚ ሁለታችንም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ስለነበርን በቸርች ውስጥ የተዋወቅነው፤ እሷ የልጅነት ዕድሜ ጓደኛዬም ነች፤ ስለ እሷ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር የጓደኝነትም ሆነ የፍቅር ህይወትን ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ በጣም ተሳስበን፣ ተከባብረን፣ ተፈቃቅረን የምንኖርበትን ሁኔታ ከማመቻቸት አንስቶ ለእኔ የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወት ኳስ ባትወድም ስራዬን ግን በማክበር ትልቁን አስተዋፅኦ ያበረከተችልኝ ስለሆነች ስለ እሷ ብዙ ለማውራት ቃላቶች ናቸው ያነሰኝ እና በጣሙን ላመሰግናት እፈልጋለው”፡፡
ስለ ቤተሰቦቹ
“ቤተሰቦቼ ከልጅነት ዕድሜዬ አንስቶ ኳስን እንድጫወት የሚፈልጉ ነበሩ፤ ከዛም ውጪ በብዙ ነገሮች እየደገፉኝ ያበረታቱኝም ነበር፤ በተለይ ደግሞ ወላጅ አባቴ የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዋቂ ተጨዋች ታሪኩ ስምኦን ወንድም ነበርና የአጎቱን ፈለግ ሊከተል ነው ብሎ ስለ እሱ ይነግረኝ ነበርና እነዚህ ነገሮች ጭምር ናቸው በኳሱ ላይ በርትቼ በመስራት ለዛሬው የኳስ ተጨዋችነት ህይወቴ የጥርጊያውን በር የከፈተልኝና ይሄን መቼም ቢሆን አልረሳሁም፤ ቤተሰቦቼ ላደረጉልኝ ነገርም ከፍተኛ ምስጋናን አቀርባለውኝ”፡፡
በቤተሰባቸው ቀልደኛው ማን እንደሆነ
“በቤተሰባችን ከሚገኙት ወንድሞቼና እህቶቼ መካከል ቀልደኛው ልጅ እኔ ነኝ፤ ቀልደኛ የሆንኩትም ቀልድ ስለምይዝና ስለማወራላቸውም ነው”፡፡
ችምስ ተብሎ ስለሚጠራበት ቅፅል ስሙ
“በሰፈር ደረጃ የወጣልኝ ስም ነው፤ ያኔ ልጅ ሳለሁ በአጥቂ ስፍራ ላይ ነበር የምጫወተው፤ የማገኛቸውን ኳሶችም ሁሉ በጎሎች ላይ አሳርፍ ነበርና ይህን የተመለከቱ እና ግብ ላይም አይምሬ መሆኔን የተረዱ ሰዎች ናቸው በአንድ ጨዋታ ላይ ያ ግቡን የሚቸምሰው ልጅ ወደሜዳ ይግባና ግቡን ይቸምሰው ተባልኩ፤ ከዛ በኋላም ነው ጭምስ የሚለው ስም መጠሪያዬ የሆነው”፡፡
የውሃ ዋና ካለመቻሉ ጋር በአንድ ወቅት ስላጋጠመው ነገር
“ይሄ ሁኔታ በትምህርት ቤት ህይወቴ ጊዜ ያጋጠመኝ ነው፤ ያኔ ጥሩ ጊዜን እያሳለፍኩ ነበር፤ አንድ ጊዜ ታዲያ ጓደኞቼ ዋና እንድዋኝ ከትምህርት ላይ በግድ አስኮብልለውኝ ወደ ዋና ቦታ ወሰዱኝ፤ እኔ ግን ዋና አልችልም ነበርና ወደ ውሃው ውስጥ እንደገባው በሚያሰምጠኝ መልኩ ልንደፋደፍ ቻልኩ፤ ያኔ እነሱ በእኔ ላይ ሙድ እየያዙብኝ ነበር፤ የዋና ቦታው እኮ በጣም አጭር እና እኔን ሊያስቆመኝ እና ምንም ነገር ሊያደርገኝ በማይችል መልኩ ነበርና የተሰራው ያንን ገጠመኜን መቼም ቢሆን አልረሳውም”፡፡
ባህሪይውን በተመለከተ
“በእዚህ በኩል ሰዎች ስለ እኔ ቢያወሩ ደስ ይለኛል፤ ያም ሆኖ ግን መናገር ካለብኝ መቀላለድ እወዳለው፤ ሲሪየስም ነኝ፤ ከዛ ውጪ ደግሞ እኔ ላይ እንዲደረግብኝ የማልፈልገውን ነገር ሰዎች ላይ እንዲደረግም ፈፅሞ አልፈልግም”፡፡
በመጨረሻ…
“በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ ሁሌም ደስተኛ ሆኜ ነው እያሳለፍኩ ያለሁት፤ ብስጩም አይደለሁም፤ ለእዚህ ደግሞ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ፤ ይሄን ካልኩ ከፈጣሪ ቀጥሎም ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃም ብዙ ሰዎች አሻራቸው አለበት እና እነሱንም ማመስገን እፈልጋለው፤ ከዛ ውጪ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር እንደ ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነቴ ለእዚህ ክለብ ጥሩና የተሻለ ነገር በመስራት በደጋፊው በኩል የሚያስመሰግነኝን ስራ መስራትም ዋንኛው እቅዴም ነውና በአሁን ሰዓት እዛ ላይም ነው አተኩሬ ያለሁት”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P