Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለእኔ የዓመቱ ኮከብ ተጨዋች ያሬድ ባየህ ነው””ፋሲል ከነማ ያነሳው ዋንጫ ጅማሬ እንጂ ፍፃሜ አይደለም፤ በአፍሪካ የውድድር መድረክ ገና እንነግሳለን”ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ /ፋሲል ከነማ/

 

ለፋሲል ከነማ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሀላፊነት ዘመን ወደ ዋናው ቡድን አድጎ በመጫወት በአሁን ሰዓት ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ አበረታች የጨዋታ እንቅስቃሴውን እያሳየ ይገኛል። በዘንድሮ የውድድር ዘመንም በ20  ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎም ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል። ሶስት ኳሶችን አሲስት አድርጓል። ለቡድኑ አንድ የፍፁም ቅጣት ምትንም ለማስገኘት ችሏል።

የፋሲል ከነማ እግር  ኳስ ቡድን የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ሲሆን በድሉ ከፍተኛ የደስታ ስሜት እንደተሰማው የሚናገረው ወጣቱ ተጨዋች ናትናሄል ገብረ ጊዮርጊስ  ለፋሲል ከነማ አሁን ላይ ምንም ነገርን አላደረግኩለትም፤ በቀጣዩ ጊዜ የኳስ ህይወቴ ግን ቡድኑን ስኬታማ በማድረግ ለታላቅ ደረጃና ውጤት አበቃዋለው” ሲል ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር ባደረገው ቃለ-ምልልስ ምላሹን ሰጥቷል።

ለኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆናቸው ብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ ከቻለው ናትናሄል ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ መድህን ጋር ያደረግነው ቆይታም የሚከተለውን ይመስላል፤ ተከታተሉት።

ስለ ውልደቱና እድገቱ

“የተወለድኩትና ያደግኩት በጎንደር ከተማ ፒያሳ ሰፈር ላይ ነው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ሰፈር ስንቀይር  18 ቀበሌ አካባቢ መኖር ጀመርኩኝ”።

ስለ እግር ኳስ ጅማሬው

“የኳስ ጅማሬና መነሻዬ ወደ 18 ሰፈር ቀይሬ ከመጣው በኋላ ነው። እዛም ነበር ልጅ ሆኜ መጫወት የጀመርኩት። ለኳሱም ጥልቅ ፍቅሩ ስለነበረኝ በርትቼ እየሰራው በመምጣት ለዛሬው የተሻለ ደረጃ ላይም ልደርስም ቻልኩኝ”።

የውልደትህ እና የእድገትህ አካባቢ ስላወጣቸው ተጨዋቾች

“በተጋነነ ደረጃ ስሙን የምጠራልህ ተጨዋች እስካሁን ባይኖርም አሁን አሁን ግን እኔና ዓለም ብርሃን አለን። ወደፊት ደግሞ እኛን ተመልክተው ሌሎች ተጨዋቾች ይወጣሉ ብዬ አስባለው”።

በልጅነት ዕድሜው አድንቆት ስላደገው እና ተምሳሌቱ ስለሆነው ተጨዋች

“የእኔ አርአያዬና ሞዴሌ የሆነው ተጨዋች አብዱራህማን ሙባረክ /ግሪዳው/ ነው። እንደ ፋሲል ከነማ ደጋፊነቴ እሱን ለፋሲል ከነማ ሲጫወት ጀምሮም ነው ሳደንቀው የኖርኩት”።

ከባህርማዶ ስለሚያደንቀው ተጨዋችና ስለሚደግፈው ክለብ

“የምደግፈው ማንቸስተር ዩናይትድን ነው። ቀንደኛም የምባል ደጋፊ ነኝ፤  የማደንቀው ተጨዋች ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ነው”።

እግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮ

“ወደ ትምህርቴ ነበር  የማመራው። ያም ሆኖ ግን የኳሱ ስሜት ከፍ አለብኝና ኳስ ተጨዋች ሆንኩኝ”።

በቤተሰባችሁ ውስጥ የእግር ኳስ ተጨዋቹ አንተ ብቻ ነህ? ስንት ወንድምና እህትስ አለ?

“የእግር ኳስ ተጨዋቹ እኔ ብቻ አይደለሁም፤ ወላጅ አባቴ አሁን መጫወቱን አቆመ እንጂ ጎንደር ውስጥ በሚካሄዱ የእግር ኳስ ውድድሮች በተለያዩ ክለቦች ውስጥ ይጫወት ነበር። በእኛ ቤተሰብ ውስጥ ያሉኝ ወንድምና እህቴ በአጠቃላይ ስድስት ናቸው። አምስቱ ወንዶች ሲሆኑ አንዷ ሴት ናት። በአጠቃላይ አንድ ቡድን ልንሰራም ሁለት የቤተሰብ አባል ቀርቶናል”።

በልጅነት ዕድሜህ የእግር ኳስን ስትጫወት ተፅህኖ ነበረብህ?

“በፍፁም፤ ይሄ ሊሆን የቻለውም አባቴ ኳስን ተጫውቶ በማሳለፉ ነው። በእናቴ በኩል ብቻ መጀመሪያ አካባቢ ልከለከል ብችልም ወዲያው ግን የሰፈር ልጆች ችሎታዬን እያዩ ይጫወት ፍቀጂለት ሲሏት እሺ አለችና በጥሩ ሁኔታና ደስተኛም ሆኜ ኳሱን መጫወት ቀጠልኩኝ”።

የእግር ኳስን መጫወት ስትጀምር መነሻህ የት ነበር?

“መጀመሪያ ላይ በሰፈር ደረጃ ከተጫወትኩኝ በኋላ በቀጥታ ያመራሁት በጎንደር ዩንቨርስቲ ውስጥ ለተቋቋመው የፕሮጀክት ቡድን ለመጫወት ነው። እዛም በሰፈርና በትምህርት ቤት ደረጃም ስጫወት ያውቀኝና በችሎታዬም ያደንቀኝ በነበረው መኮንን ገብሬ አማካኝነት ተመልምዬ ስልጠናን ወሰድኩና በዛው ዓመት ላይ ለፕሮጀክት ቡድኑ ከመጫወት አልፌ ለጎንደር ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ለሆናቸው  ቡድን ተጫወትኩ። ቀጥዬም ለጎንደር ምርጥ ቡድንም ተመርጬ በመጫወት ነው የኳስ ጅማሬዬ የነበረው”።

የእግር ኳስን በየቱ ስፍራ ላይ ሆኖ መጫወት እንደጀመረ

“የፊት አጥቂ ሆኜ ነው መጫወት የጀመርኩት። አሰልጣኝ መኮንንም ነው በዛ ስፍራ ላይ እንድጫወት አድርጎኝም ለእሱ ቡድን ጎሎችን ሳስቆጥርለትም የነበርኩት”።

የእግር ኳስ ተጨዋች በመሆኑ ስለተፈጠረበት ስሜትና  ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ  ልጅ እያለ ስለነበረው ግንዛቤ

“የእግር ኳስ ተጨዋች ሆኜ ማደጌ ጥልቅ የሆነ የደስታ ስሜት ነው እንዲሰማኝ ያደረገው። ኳስ ተወዳጅ ስፖርት ስለሆነም ነው ደስታዬን ከፍ እያደረገውም ያለው። ስለ አገራችን የኳስ ግንዛቤ ላልከው በፊት ላይ ምንም አይነት ግንዛቤውም ሆነ እውቀቱ አልነበረኝም። ዳሽን ቢራ ልክ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ሲገባ ግን ብዙ ነገሮችን ከማወቅ አልፌ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ለመጫወት በጣም እንደጓጓሁኝ አስታውሳለው። ያንን የመጫወት እልሜንም አሳክቻለው”።

ለየትኛው ቡድን መጫወት ነበር የአንተ ዕልምህ?

“ለፋሲል ከነማ ነዋ! ፋሲል ከነማ የጎንደር ከተማ ትልቁና እኔ ደግሞ እየደገፍኩት ያደግኩት ቡድን ስለሆነ ለእሱ ነበር ልጫወት ያሰብኩት። ከዛም ለቡድኑ መጫወቴን እውን አደረግኩት”።

ወደ ቡድኑ የገባክበትን ሁኔታ ጀባ ብትለን….?

“ይቻላል፤ መጀመሪያ ላይ በፕሮጀክት ደረጃ ስጫወት ታይቼ ነው በአሰልጣኝ ታደሰ አማካኝነት የሙከራ ዕድል ተሰጥቶኝ ምርጫውን በማለፌ ለወጣት ቡድኑ ልያዝ የቻልኩት። ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላም ቡድኑ ግርማይ ኪሮስ የተባለን ሌላ አሰልጣኝ ካስመጣ በኋላም በእሱ ስር ሰለጠንኩና ለአማራ ምርጥ ቡድን በመጫወት ሐዋሳ ከተማ ላይ ለተደረገው የክልል ምርጥ ቡድኖች ውድድር ላይ በመጫወት ሻምፒዮኑን የደቡብ ክልልን ተከትለን ውድድራችንን በሁለተኛ ደረጃ ሆነን ልናጠናቅቅ ቻልን”።

ወደ ፋሲል ከነማ የዋናው ቡድን ስላደገበት ሁኔታ

“በፋሲል የወጣት ቡድን ውስጥ ለሁለት ዓመታት ያህል ከቆየው በኋላ የዋና ቡድኑን ልቀለቃል የቻልኩት በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሀላፊነት ዘመን ነው። እሱ የቢ ቡድናችን ወደ ብሔራዊ ሊግ በሚያስገባው የአማራ ክልል የውስጥ ውድድር ላይ ይሳተፍ ስለነበር በዛ ላይ ተመልክቶኝና ችሎታዬንም አድንቆ ነው በደንብ መበርታት እንዳለብኝ ጭምር ነግሮኝ ሊያሳድገኝ የቻለው። በዚህ አጋጣሚም ውበቱ በታዳጊ ወጣት ተጨዋቾች ላይ ያለው እምነት ከፍተኛ ስለሆነም ጭምር ላመሰግነውም እወዳለው”።

ለፋሲል ዋናው ቡድን አንተ ብቻ ነው ያደግከው?

“አይደለም፤ ዓለምብርሃንን ጨምሮ 4 ልጆች ነበርን ልናድግ የቻልነው”።

ለፋሲል ከነማ ስላደረገው የመጀመሪያ ጨዋታው

“ከሐዋሳ ከተማ ጋር ሐዋሳ ላይ 3-2 በሆነ ውጤት ስንሸነፍ ያደረግኩት ጨዋታ ነው። 3 ደቂቃ ሲቀርም ነው ተቀይሬ ልገባ የቻልኩት”።

ለፋሲል ከነማ በርካታ ግጥሚያዎችን ስላደረገበት ዓመት እና ስለ ቡድኑ ቆይታው

“በፋሲል ከነማ ያለኝ ቆይታ ደስ የሚልና የአማረ ነው። ከዚህ ቡድንና ከልጅነት ዕድሜዬም አንስቶ ከደገፍኩት ቡድን ጋር ገና ወጣት ተጨዋች ሆኜ የሊጉን ዋንጫ ስላነሳው በጣም ደስ ብሎኛል። በፋሲል ቆይታዬ ሌላው በርካታ ግጥሚያዎችን ያደረግኩት ዘንድሮ ነው። ዓምና ውድድሩ በኮቪድ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ 18ቱ ውስጥ እገባ ነበር። በዚህ ዓመት ላይ ግን እስከ 20 በሚደርሱ ጨዋታዎች ላይ አብዛኞቹን ተቀይሬ በመግባት ሶስት ያህሉን ደግሞ በቋሚነት በመሰለፍ  አድርጌያለው። በዚሁ ጊዜ ቆይታዬም ሁለት ጎሎችን ሳስቆጥር ሁለት የግብ ኳሶችን ደግሞ አቀብያለው /አሲስት/ አድርጌያለው። ከዛ ውጪም ለቡድኑ የፍፁም ቅጣት ምትም ለማስገኘት ችያለው”።

የፋሲል ከነማ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮንነት እና የተገኘው ስኬት እንደ ቡድኑ ተጨዋችነትህ ስለፈጠረብህ ስሜት

“ድሉን በተመለከተ በትክክልና ከበቂም በላይ የሚገባን ሆኖ ነው ያገኘሁት። 4 ጨዋታ እየቀረንም ነው ሁሉንም ቡድኖች ባሳመነ መልኩም  ሻምፒዮና ልንሆን የቻልነው። የእዚህ ስኬትም እንደ አንድ የቡድኑ ተጨዋች እኔ ውስጥ የፈጠረብኝ የደስታ ስሜት በጣም ከፍተኛ ነው። ገና በዚህ የወጣትነት ዕድሜዬ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማግኘት መቻል ዕድለኝነትንም ይጠይቃልና በጣም ነው የተደሰትኩት”።

ሻምፒዮና ሲሆኑ የመጀመሪያውን ስልክ የደወለው

“ለእህቴ ሰናይት ነበር የደወልኩት። እሷ እኔን በኳሱ ሁሌም የምታበረታታኝ ናት። በመቀጠል የደወልኩት ደግሞ ጓደኛዬ ሙስጠፋ ጋር ነው”።

ለፋሲል ከነማ እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት

“ፋሲል ከነማን አሁን ላይ ገና አልጠቀምኩትም። ከዚህ ቡድን ጋር ብዙ እልም አለኝ። ለራሴም ለክለቤም ጥሩ ነገርን መስራት ስለምፈልግ በቀጣዩ ጊዜ የኳስ ህይወቴ የማሳያቸው ነገሮች ይኖሩኛል”።

ፋሲል ከነማ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አነሳ፤ በቃ!

“ምን ይበቃል? ለእሱ ይህ ብቻ ድል በቂ አይደለም፤ ክለቡ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ይወዳደራል።  ቡድናችንን በውድድሩ ለማንገስ እንጫወታለን። ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታቶች ከተሳትፎ የዘለለ ውጤት አልነበረንም አሁን ግን ከዛ የተሻለን ውጤት ቡድኑ ይጠብቃልና በዛ ደረጃ ነው የምንወዳደረው። ከዛ ውጪም ሌሎች በርካታ የሊግ ዋንጫዎችንም በወደፊቱ ተሳትፎዎቻችን ላይ ልናገኝ እና በአንድ ድል ብቻ መቆም እንደሌለብንም ልንረዳም የግድ ይለናልና ልንበረታ ይገባል”።

ፋሲል ከነማን ሻምፒዮና ያደረገው ዋናው ሚስጥር

“ሊጉን አሳምነን አይደል ያሸነፍነው። ለዛ ያበቃን ሁላችንም በየጨዋታውና ልምምድ ላይ እንደማመጥ ነበር። ከዛ ውጪ ደግሞ በአሰልጣኙ የሚሰጠንን ታክቲክም በአግባቡ ከመተግበር ባሻገርም ስህተት በሚኖርበት ሰዓት አይዞህ አይዞህ እየተባባልንም ስለተጓዝን ይህ ሁኔታ ለድል አብቅቶናል”።

በዲ ኤስ ቲቪ ሊጋችን መተላለፉ

“በጣም ነው ደስ ያለኝ። ይሄ የሆነውም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ጨዋታዎቹን ደጋግመህ የማየት እድሉ ስላለህም ችሎታህን ከዛ በመነሳት ታሻሽልበታለህ”።

የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር የኮከብ ተጨዋችነት ሽልማትን ወስዷል፤ እሱ የአንተም ምርጫ ነው?

“አቡበከር ጥሩ ተጨዋች እንደሆነ አምናለው። ብዙ ሰዎችም ስለ እሱ ብዙ ብለዋል።  ያም ሆኖ ግን ለእኔ የዚህ ዓመት ኮከብ ተጨዋች ይሆናሉ ብዬ የገመትኳቸው ተጨዋቾች ሻምፒዮና ከመህናችንም አንፃር ያሬድ ባየህ እና ሽመክት ጉግሳን ነበር። በተለይ ደግሞ የእኔ ኮከቡ ተጨዋች ያሬድ ባየህ ነው። እሱም ነበር ኮከብነቱን ማሸነፍ የነበረበት”።

የአቡበከርን በኮከብ ተጨዋችነት መመረጥ ስትሰማ እኔንስ ወደፊት ይሄ ይጠብቀኛል አልክ?

“እንዴት አልልም። አንድ ሰው ከሰራ የልፋቱን ውጤት ያገኛል። በዘንድሮ ዓመትም  አቡኪ ካገኘው ሽልማት ውጪ እኔ እጩ በነበርኩበት የተስፈኛ ተጨዋች ሽልማትንም የሐዋሳ ከተማው ወንድማገኝ በመመረጥ አግኝቶ ነበርና እንዲህ ያሉ ሽልማቶች ጠንክረህ እንድትሰራ ስለሚያደርግህ ወደፊት ይህን ማግኘቴ የማይቀር ነው”።

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ /u-23/ ለመመረጥ መቻሉ ስለፈጠረበት ስሜት

“ሀገርን በሚወክል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመርጬ የነበረው በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሀላፊነት ዘመን ላይ ለወጣት ቡድን ነበር። ያኔ በፓስፖርት ችግር ቀረው። ዘንድሮ ግን ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆነው ቡድን ልመረጥ ስለቻልኩ እና ሀገርንም ወክለህ ለመጫወት በመዘጋጀት ላይ መገኘት በጣም ደስተኛ እና ዕድለኛ እንድሆም ነው ያደረገኝ”።

ስለ እልሙና ግቡ

“የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ድልን ከክለቤ ፋሲል ጋር በማንሳት እልሜን ለማሳካት ችያለው። ቀጥሎ  ደግሞ ለብሄራዊ ቡድን ተመርጦ  በመጫወት  እና ወደ ውጪ ሀገርም በመውጣትና  በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት በመጫወት የሀገሬን ስም የማስጠራት እቅድ አለኝ”።

ባህሪህ

“ወደ ሜዳ ስገባ ሽንፈትን ስለማልወድ እበሳጫለው፤ እቆጣለው። ከዛ ስወጣ ግን መሳቅና መጫወትን አዘወትራለው”።

በፋሲል ከነማ አዝናኙ /ኮሜዲው/ ተጨዋች

“ሽመክት ጉግሳ ነው። እሱ ካለ አይደብረንም”።

በችሎታው ማስተካከል ያለበት

“የእግር ኳስ ተጨዋች ስትሆን ሙሉ አትሆንም። ክፍተቶቼን እየተመለከትኳቸው ነው። ያ ስለሆነም በሜዳ ላይ ያሉብኝን ስህተቶቼን ቀንሼና አርሜም በመምጣት በመጪው ዓመት ላይ የተሻለ ነገር ለመስራት  በምርጥ አቋሜ እመጣለው”።

ፋሲል ሻምፒዮና ከሆነ በኋላ በተለየ ሁኔታ ስለተመለከተው ነገር

“በጎንደር የተደረገልንን አቀባበል ነዋ! ዕድሜ ልኬን እንደዚህ አይነት ድባብን ከዚህ በኋላ የምመለከትም አይመስለኝም”።

ክብደቱና ቁመቱ

“70 ኪሎ ግራም ስመዝን ቁመቴ ደግሞ 1ሜትር ከ80 ነው”።

የሚወደው ምግብና መጠጥ

“ከሚበላ ጥብስን ስወድ ከሚጠጣ ደግሞ ጁስ በተለይ ደግሞ ማንጎን ነው የምወደው”።

በመጨረሻ

“በእግር ኳሱ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሱኝን ላመስግን፦ መጀመሪያ ፈጣሪዬን ከፊት አስቀድማለው። ሲቀጥል ቤተሰቦቼን ያሰለጠኑኝን አሰልጣኞች እንደዚሁም ደግሞ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎችን አመራሮችንና የቡድን አጋር ጓደኞቼን ብዙ ነገርን አድርገውልኛልና አመሰግናቸዋለው”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P