Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

መሀሪ መና /ሲዳማ ቡና/ “የአቻ ውጤቱ አይገባንም፤ ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፍ ነበረብን”

መሀሪ መና /ሲዳማ ቡና/
“የአቻ ውጤቱ አይገባንም፤ ኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፍ ነበረብን”
“አስፈሪው ሲዳማ ቡናን በሁለተኛው ዙር ላይ እንመለከታለን”
“በእግር ኳሱ የእኔ ደካማው ጎን በአንድ እግሬ ብቻ ኳሱን መጫወቴ ነው”
በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የሁለተኛው ዙር የመጀመሪያው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በአዳማ ከተማ ላይ ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቋል። ለሲዳማ ቡና መሀሪ መና ቀዳሚ ያደረገቻቸውን ግብ ቢያስቆጥርም ኢትዮጵያ ቡናዎች በአቡበከር ናስር አማካኝነት ያስቆጠሩት ግብ አቻ ሊያስለያያቸው ችሏል።
በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሲዳማ ቡና አሁን ላይ ከመሪው ቅ/ጊዮርጊስ በ 8 ነጥብ ዝቅ ብሎ በ5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይነት በሚኖሩት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ ክለቡ አስፈሪውን የቀድሞ ቡድኑን ዳግም እንደሚያስመለክት የግራ መስመሩ የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች መሀሪ መና ከጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል።
ከመሀሪ መና ጋር የነበረንም ቆይታ በሚከተለውም መልኩ ቀርቧል። ተከታተሉት።
ኢትዮጵያ ቡናን ተፋልመው አቻ ስለተለያዩበት ጨዋታ
“መጀመሪያ እኛ ወደ ሜዳ ስንገባ በድሬዳዋ ከተማ በነበረን ቆይታ ያገኘነውን ተከታታይ የስኬት ውጤት ለማስቀጠል በመፈለግ ከአሰልጣኞቻችን ጋር ተነጋግረን ነው ከመጀመሪያው 45 ደቂቃ ጀምሮ እነሱን ለማሸነፍ ተጭነን ስንጫወት የነበርነው፤ በእዛ እንቅስቃሴ ውስጥም አጥቅተን ስንጫወት ብዙ ኳሶችንም ለመሳት ችለናል፤ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደግሞ በቡድናችን ተጨዋቾች ላይ መዳከሞች ቢታዩም ከቡናዎች በተሻለ የግብ ማስቆጠር እድሎችንም ፈጥረናልና ለማሸነፍ ፈልገን የነበርነውንና ማሸነፍም የነበረብንን ግጥሚያ ሳይሳካልን ቀርቶ አቻ ለመለያየት ችለናል”።
የአቻ ውጤቱ አይገባችሁም ማለት ነው…..?
“ለእኛ አዎን፤ ጨዋታውን ማሸነፍ ነበረብን ምክንያቱም እነሱ ከእኛ በላይ የግብ እድሎችን ለመፍጠር አልቻሉም ነበርና እኛም ነን ከእነሱ በተሻለ መልኩ የግብ እድሎችን የፈጠርነው። በጨዋታው ቡናዎች ኳሱን ይዘው በመጫወት የእኛን የግብ በር ለማስከፈት ጥረት እያደረጉ የነበሩ ቢሆንም የእኛ የተከላካይ ክፍል መስመር በጥንቃቄ ይጫወት ስለነበርና የመጫወቻ ስፔስም ስለከለከልናቸው ከውጤት አንፃር የእኛንም ጎሎችን የመሳት ሁኔታ ጨምሬ የተመዘገበውን የአቻ ውጤት ስመለከተው ለእኛ የሚገባን ሳይሆን ማሸነፍ የነበረብን ነው”።
በኢትዮጵያ ቡና ላይ ሐሙስ ዕለት በነበረው ጨዋታ ቀዳሚ የሆናችሁበትን ግብ ለማስቆጠር ችለህ ነበር፤ ከአንተ ግብ ማስቆጠር ጋር በተያያዘ ምን የምትለው ነገር አለ….?
“ከእዚህ በፊት በነበረኝ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ወደፊት አጥቅቶ መጫወት በጣም ያስደስተኝ ስለነበር ጎል አስቆጥር ነበር። በተለይም ደግሞ ከቅ/ጊዮርጊስ ይልቅ በባንኮች ቡድን ውስጥ ሆኜ ስጫወት፤ ቅ/ጊዮርጊስም እያለው በእዛ ውስጥ ተሳትፎን አድርጌያለሁ። ይሄን ልምዴን ወደፊትም ማስቀጠል እፈልጋለው እና አሁን ቡና ላይ ግብ ማስቆጠሬ ለእኔ ከፍተኛ ተነሳሽነትንም ነው የሚፈጥርልኝ”።
በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሲዳማ ቡና የውድድር ዘመኑ ሲጀመር ምንን አቅዶ አሁን ላይ ደግሞ ምን ውጤትን ሊያስመዘግብ ተዘጋጅቷል…?
“የፕሪ-ሲዝኑን ልምምድ እንደጀመርን የእኛ ዋንኛው ፍላጎት የነበረው ዋንጫውን ባናነሳ እንኳን ሊጉን እስከ ሁለተኛ ባለው ደረጃ ላይ ሆነን በማጠናቀቅ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር ላይ መሳተፍን መፈለጋችን ነው። ለእዛ አሁን ጊዜውም አልረፈደም። ከእዛም በመነሳት በእዚህም ዙር የሚጠቅመንን ተጨዋችን ስላስፈረምን የምንፈልገውን ውጤት እናመጣለን”።
እስካሁን ስለነበራቸው ጥንካሬና ክፍተት ጎን
“ጠንካራው ጎናችን በህብረት እናጠቃለ፤ በህብረት እንከላከላለን። ትንሹ ድክመታችን ደግሞ ፊት መስመራችን ላይ በአንዱ አጥቂያችን ይገዙ ቦጋለ ብቻ የምንጫወትበት ሁኔታ ስለነበር አሁን ላይ ሳላህዲን ሰይድ ለእኛ ክለብ ከመፈረሙ ጋር በተያያዘ የአጥቂው ክፍላችን ይበልጥ የሚጠናከርበትና ተደጋጋሚ ጎል ማስቆጠር የምንችልበት ሁኔታም ስለሚኖር ያ ክፍተታችን የሚሻሻልና አስፈሪውን ሲዳማ ቡናን የምንመለከትበትም ሁኔታ ይሆናል”።
በሲዳማ ቡና የውል ዘመንህ ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ጊዜ ዳግም ውልህን ልታድስ ችለሃል፤ ከእዚህ ጋር በተያያዘ የምትለው ነገር ካለ
“ወደ ሲዳማ ቡና ቤት ስመጣ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ነው ለአንድ ዓመት እንድጫወት ብሎ ያስፈረመኝና እንድጫወት ያደረገኝ አሁን ላይ ውሌ ወደመጠናቀቁ በተቃረበበት ሰዓት ላይ ደግሞ ካለኝ አቋም በመነሳት በክለቡ ውስጥ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ለሚደርስ ጊዜ ቆይታን እንዳደርግና ውሌም እንዲራዘም ስላደረገ ከቡድኑ ጋር ጠንክሬ በመስራት የተሳካ ጊዜያትን ለማሳለፍ እየተዘጋጀው ነው”።
በእግር ኳሱ ከእዚህ ቀደም ስላሳለፈው ህይወት
“ቅ/ጊዮርጊስን ከለቀቅኩኝ በኋላ ትንሽ ተቸግሬ ነበር። ይኸውም የእኔን የጤንነት ሁኔታ ሳያጣሩ ወደየትኛውም ክለብ እንዳላመራ አንዳንዶች ያልሆነ አሉባልታን ያወሩብኝ ነበር። ያም ሆኖ ግን አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የእኔን ሁኔታ በደንብ ካወቀ በኋላ በፊትም የእኔን ማንነት ያውቅ ነበር እምነቱን ጥሎብኝ እና ወደ ቡድኑም አስመጥቶኝ ማንነቴን እንዳሳይ ስላደረገኝ ከባድ የነበረውን ወቅት በጥሩ ሁኔታ እንዳሳልፍ ነው ያደረገኝ”።
በአንተ ላይ ይወሩ የነበሩትና ወደሌላም ክለብ እንዳታመራ አድርገውህ የነበሩት ምክንያቶች ምን ነበሩ?
“እነዛ ሁኔታዎች በቅ/ጊዮርጊስ እያለው የቡድኑ የቦርድ ሊቀመንበርና ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀል ደርሶብኝ ከነበረው ጉዳት አኳያ እኔን አሳክመውኝ ነበር። የቡድኑ ደጋፊዎችም ከጎኔ ነበሩ። በእዚሁ አጋጣሚም አቶ አብነትንና የቡድኑን ደጋፊዎችንም ማመስገን እፈልጋለሁኝ። ይህ ሆኖ ሳለም ከክለቡ ጋር ለመቀጠልም ፈልጌ ነበር። በኋላ ላይ ከእነሱ ጋር ስለያይ የሌላ ቡድን አሰልጣኞች እኔ ክለቡን የተለያየሁበትን ሁኔታ ጉዳት አለበት ከሚል የጥርጣሬ ስሜት ጋር አያይዘውት ስለነበርና ብዙ አሰልጣኞችም እኔን ሊቀበሉኝም ስላልፈለጉ በስተመጨረሻ አሰልጣኝ ገብረመድህን ነው እኔን ስለሚያውቀኝና ጤንነቴንም ስላረጋገጠ ጠርቶኝ ለቡድኑ ሊያጫውተኝ የቻለው”።
በቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወትህ የተሳካ ጊዜያትን ታሳልፋለህ?
“በሚገባ ነዋ! ለእዛም ቡድኑ ወደሚፈለግበት ደረጃ ላይ እንዲመጣም ጠንክሬም ነው የምሰራው። ከእዛም ውጪ ከቡድን አጋር ጓደኞቼም ጋር ሆኜ የቡድኑን ውጤት ከፍ ወዳለ ስፍራ ለመውሰድ እና የሁላችንም ምኞት ወደሆነውም የኢንተርናሽናል ውድድር ላይም ለመሳተፍ ጥረትን እናደርጋለን”።
ሲዳማ ቡናን ከሌሎች ቡድኖች አንፃር የሚለየው
“በሜዳ ላይ ጠንካራ ህብረት አለን፤ ጠንካራ የአሰልጣኞች ስብስብም አለን፤ ሌላው ደግሞ አልሸነፍ ባይነታችን፣ ከመከላከል ይልቅ አጥቅተን መጫወትን መምረጣችን፣ ቡድኑ በወጣት ተጨዎቾች የተገነባ እና ለማንም የማይሳሳ መሆኑም ካለው የቡድኑ መንፈስ ጋር ተዳምሮ ክለቡን ከሌሎች ለየት እንዲል ያደርገዋል”።
አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ሲገለፅ
“የእውነቴን ነው የምልህ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም
ከማደንቃቸው አሰልጣኞች መካከል አንዱ እሱ ነው። በየጊዜው እኛ ተጨዋቾች እንድንለወጥ ከመፈለግ በጣም ይለፋል። እንደ ወንድምና አባት ሆኖም እየተቆጣ ጥሩ ልምምድን ከማሰራት በተጨማሪም ይመክረናልና ከእሱ የማሰልጠን ችሎታ አኳያ አሁን ላይ እያስመዘገብን የሚገኘው ውጤት ለእሱ የሚያንሰው ነው፤ ከሚያሰራውም የልምምድ አይነት አንፃርም እኛ በፈለግነው መንገድ ስላልሄድንለት በውጤቱ ገና አልረካም፤ ከእዚህ በኋላ በሚኖረን የጨዋታ ጉዞ ግን ጥሩ ውጤትን በማስመዝገብ እሱን ለማስደሰት ዝግጁ ነን”።
ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በመጨረሻው ቀን ሲጠናቀቅ ዋንጫውን ማን ከፍ አድርጎ ያነሳዋል?
“አሁን ላይ እሱን መወሰን አይቻልም፤ ጊዜው ሲደርስም መልሱን ብናየው ይሻላል”።
ባሳለፍነው ዓመት የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በሁሉም መልኩ ጎልቶ የወጣ ተጨዋች ነበር፤ ዘንድሮ ማንን እየተመለከትክ ነው?
“እንደ አቡበከር ባይሆንም ዓምና የእኛውን ተጨዋች ይገዙ ቦጋለን ከተጠባባቂ ወንበር እየተነሳ የሚያሳየውን ጨዋታ ስመለከትና ዘንድሮም ለቡድናችን ውጤት ማማር እያደረገ ያለውን አስተዋፅኦ በድጋሚ ሳይና በኮከብ ግብ አግቢዎች ፉክክር ውስጥም የሚገኝም ስለሆነ ይሄ ተጨዋች ገና ወጣት በመሆኑ ጭምር ለእኔ ጥሩ ሆኖ ያገኘሁት ተጨዋች እሱን ነው”።
ደጋፊዎቻችሁ ይለያሉ?
“አዎን፤ የእኛ ደጋፊዎች ሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሜዳ ውጪም በደንብ አድርገው ይደግፉናል። በምንሄድበትም ቦታም ሁሉ ነው ድጋፋቸውን የሚሰጡን። እነሱ ለእኛ እንደ 12ኛ ተጨዋች ሆነውም ነው የሚያገለግሉን”።
ለሐዋሳ ከተማ፣ ለቅ/ጊዮርጊስ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫውተህ ከማሳለፍህ ባሻገር በአሁን ሰዓት ለሲዳማ ቡና እየተጫወትክ ነው የሚገኘው። በኳሱ ቆይታህ ድክመቴ የምትለው ነገር ምንድን ነው?
“በእግር ኳስ ተጨዋችነት የህይወት ዘመን ቆይታዬ የእኔ ደካማ ጎን ብዬ የማስበው የአንድ እግር ተጨዋች መሆኔን ነው፤ ብዙ ጊዜ በአንድ እግሬ ነው ኳስን የምጫወተው”።
በመጨረሻ……?
“ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በዲ. ኤስ. ቲቪ ደረጃ መተላለፍ መጀመሩና ወደ እኛ ሀገር መምጣቱ ወደፊት ብዙ ወጣት ተጨዋቾች የሚፈሩ ከመሆኑ አኳያ ለሀገራችን እግር ኳስ ትልቅ ጠቀሜታና ምርጥ ታሪክንም ነው የሚያስገኝለት። የጨዋታዎቹ በዓለም ደረጃ መተላለፋቸውም ተጨዋቾቻችን የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እድልንም ስለሚያስገኝላቸው ለእግር ኳሳችን ለውጥንና ከፍ ያለ ጠቀሜታን የሚያስገኝለት ስለሆነ ይህ እንዲመጣ ላደረጉ አካላቶች ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል በሚል ነው መልዕክቴን መቋጨት የምፈልገው”።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P