Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቅ/ጊዮርጊስን ማሸነፋችን ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሮልናል፤ እኛ ለእነሱ ብቻ የምንዘጋጅ አይደለንም” አዲስ ተስፋዬ /ሰበታ ከተማ/

“ከኮሮና ቫይረስ ፈጣሪ ይጠብቀን”
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/


በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ17ኛው ሳምንት ጨዋታ ሰበታ ከተማ ቅ/ጊዮርጊስን በአስቻለው ግርማ ብቸኛ ግብ 1ለ0 አሸንፏል፤ አስቻለው ግቧን እንዲያስቆጥርም የአማካይ ስፍራው ተጨዋች ዳዊት እስጢፋኖስ ለተጨዋቹ ያቀበለበት መንገድ ከፍተኛ አድናቆትን እንዲሰጠውም አድርጎታል፤ ሰበታ ከተማ የዐርቡን ጨዋታ ለማሸነፍ እንዲችል የቡድኑ ተጨዋቾች ከፍተኛ ትግልን ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህ ተጨዋቾች መካከልም ክለቡን በተከላካይ ስፍራው ላይ በጥሩ ብቃቱ በማገልገል እየተወደሰ የሚገኘው አዲስ ተስፋዬ በጨዋታው አሸናፊነታቸው መደሰቱን ገልጾ ውጤቱም የሚገባቸው እንደሆነም አስተያየቱን ለዝግጅት ክፍላችን ሰጥቷል፡፡
ቅ/ጊዮርጊስን ስላሸነፉበት ጨዋታ፡- “ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያደረግነው ጨዋታ ቡድኑ የሀገሪቱ ትልቅ ክለብ ከመሆኑ አኳያ እና የእያንዳንዳቸው የጨዋታ ውጤቶችንም እነሱ ለሻምፒዮናነት ከሚያደርጉት ፉክክር አንጻር በጣም እንደሚፈልጉት ስለምናውቅ ከዛ ውጪም ለእኛም የደረጃ መሻሻልን እንደሚያመጣልንም ስለምንረዳ ጠንክረን በመግባት ነው ግጥሚያውን ያደረግነው፤ በፍልሚያውም ቡድናችን ከእነሱ በተሻለ መልኩ ተንቀሳቀሶም ነበርና በመጨረሻም የጨዋታው አሸናፊ ልንሆን ችለናል”፡፡
በጨዋታው የተመዘገበው የ1ለ0 ውጤትና ድሉ በቂ እንደሆነ፡- “ለእኛ ውጤቱ በፍጹም በቂ ነው ብለን አናስብም፤ በተለይ ደግሞ ሳላዲን ሰይድ በቀይ ካርድ ከሜዳ ከወጣ በኋላ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር የምንችልበት እድሉም ነበረንና እነዛን ሳንጠቀምበት መቅረታችን የግብ ቁጥሩን እንዳናሰፋው አድርጎናል፤ ከዚህ በመነሳትም ጨዋታውን ቢያንስ 2ለ0 ወይንም ደግሞ 3ለ0 ማሸነፍ ነበረብን”፡፡
ከጨዋታው በኋላ ለቅ/ጊዮርጊስ ብቻ ነው በደንብ ተዘጋጅታችሁ የመጣችሁት ስለመባላችሁ፡- “ይሄን ሀሳብ በፍጹም እኛ አንቀበለውም፤ ምክንያቱም በሊጉ ውድድር ዘንድሮ የተዘጋጀነው ለ15ቱም ክለቦች እንጂ ለእነሱ ብቻ አይደለምና ፤ ብዙ ጊዜ ግን ከእነሱ ጋርም ሆነ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስትጫወት በርካታ ደጋፊዎች ስላላቸውና የሀገሪቱም ትላልቅ ቡድኖች ስለሆኑ በእዚያ ጨዋታ ላይ ግጥሚያህን ስታደርግ ለማሸነፍ የሚኖርህ መነሳሳት /ሞቲቬሽን/ ከሌሎች ጨዋታዎች አኳያ የሚጨምርበት ሁኔታ ስላለ ያ ነው ለእነሱ ብቻ ተዘጋጅታችሁት የመጣችሁት የሚያስብለው”፡፡
ስለዚህ ዓመት የሊግ ጉዞአቸው…. እንደዚሁም ደግሞ ስለ ጠንካራና ክፍተት ጎናቸው፡- “በሊጉ ያለን የእስካሁኑ ተሳትፎ ጥሩ የሚባል ነው፤ በውድድሩ ላይም ጠንካራው ጎናችን 95 ፐርሰንት ያህል የሜዳችን ላይ ጨዋታን ማሸነፍ መቻላችንና ለማሸነፍም በጥሩ ስነ-ልቦና ላይ ለመገኘት መቻላችን ነው፤ እንደ ክፍተት የምንቆጥረው ደካማ ጎናችን ደግሞ የሜዳ ውጪ ጨዋታዎቻችን ላይ ጥቃቅን የሆኑ የራሳችንና በውሳኔ አሰጣት ላይም የዳኝነት ችግር ነበርና ይሄን ብቻ ነው መጥቀስ የምፈልገው”፡፡
ሰበታ ከተማ ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን ነው ወይንስ በተቃራኒው…? በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ላይስ የት ላይ እንጠብቃችሁ፡- “በአንደኛው ዙር የሊጉ ተሳትፎአችን በምንፈልገው መልኩ እግር ኳስን አልተጫወትንም፤ በሁለተኛው ዙር ላይ ደግሞ ከበፊቱ ግጥሚያዎቻችን ብዙ የተማርናቸው እና ያስተካከልናቸውም ነገሮች አሉና የሰበታን ምርጡን ቡድን እስከውድድሩ ማጠናቀቂያ ድረስ ይዘን እንቀርባለን፤ ሊጉንም ከአንደኛ እስከ አራተኛ ባለው ደረጃ ውስጥ ሆነንም እናጠናቅቃለን”፡፡
የፕሪምየር ሊጉን አጠቃላይ ፉክክር አስመልክቶ፡- “የእዚህን ዓመት የሊግ ውድድር ከዓምናውና ከካቻምናው አንጻር ስመለከተው በሁሉም መልኩ ጥሩና የተሻለ ነው፤ ሻምፒዮና የሚሆነውና ወራጁ ቡድንም ገና አልተለየም፤ ከዛ ውጪም በስፖርታዊ ጨዋነቱም ከሜዳ ውጪ የምታደርጋቸው ጨዋታዎች በስርዓት እና እግር ኳስንና እግር ኳስንም በሚሸቱ ነገሮች ብቻ እየተከናወኑና የባላጋራ ቡድን ደጋፊዎችም ጥሩ የሆነ አቀባበልን ለየተጋጣሚዎቻቸው ቡድኖች እያደረጉም ጨዋታዎቹ ሰላም በሰፈነበት መልኩ እየተከናወኑ ስለሆነ ይሄ ሊጉን በእዚህ ዓመት ለየት አድርጎታል፤ በዚሁ አካሄድም ሊቀጥልም ይገባል”፡፡
አስቆጪው እና በጣም የተደሰታችሁበት ጨዋታ፡- “በሊጉ ካከናወናቸው የእስካሁኑ ግጥሚያዎቻችን በጣም የተደሰትንበት ጨዋታ ቢኖር ቅ/ጊዮርጊስን ዐርብ ዕለት ድል ያደረግንበት ነው፤ ይህን ያልንበት ምክንያትም አለን፤ ይኸውም የመጀመሪያው ዙር ላይ ሊጉን ከጨረስንበት ደረጃ አንጻር ጨዋታውን ማሸነፍ መቻላችን በደረጃው ሰንጠረዡ ወደ ላይ ከፍ እንድንል አድርጎናልና፤ በጣም ያስቆጨን ጨዋታ ደግሞ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ባህርዳር ላይ ያደረግነው ነው፤ ከእነሱ ጋር ስንጫወት 2ለ0 ተመርተን ነበር፤ በኋላ ላይ አንድ ግብ አስቆጠርንና ውጤቱን አጠበብን፤ በድጋሚም 3ለ1 ተመራን፤ መልሰን ደግሞ ጎል አስቆጠርንና 3ለ2ም ሆንን በስተመጨረሻም ግጥሚያው እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ሌላ ተጨማሪ ጎል ለማስቆጠርና አሸናፊ ለመሆን ያ ካልተሳካ ደግሞ አቻ ለመውጣት ብርቱ ትግል አድርገን ለመጫወት ብንሞክርም ያ ሊሳካልን ባለመቻሉ ለሽንፈት ተዳርገናልና የዛ ጨዋታ ሽንፈት ያስቆጨኛል”፡፡
ለሰበታ ከተማ ክለብ እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት፡- “በእዚህ ዓመት በሜዳ ላይ ለክለቤ እያበረከትኩ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፤ ከአንድ ጨዋታ በስተቀርም በሁሉም ግጥሚያዎች ላይ ቡድኔ የሚፈልገውን ስኬት እንዲያስመዘግብም የሚቻለኝን ሁሉ ጥረት አድርጌያለው፤ የሁለተኛ ዙር ላይም ከወዲሁ የተሻለ ብቃትን በመያዝ ቡድኔን እየጠቀምኩት ባለሁበት ደረጃ ላይ ስለምገኝም አጠቃላይ አቋሜን በአበረታችነቱም ነው የምጠቅሰው”፡፡
ስለቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቱ፡- “የእግር ኳስን ወደ ውጪ በመሄድ በፕሮፌሽናል ተጨዋነት ደረጃ መጫወትን አልማለው፤ እነዛን እድሎችንም ከወዲሁ ለማግኘትም ጠንክሬ በመስራት ጥረትን አደርጋለው”፡፡
በፕሪምየር ሊጉ ስለሚፈራው አጥቂ፡- “እስካሁን የምፈራው አጥቂ ማንም የለም፤ ወደፊትም ማንም ይምጣ ልፈራው አልችልም፤ እንደዚሁም እነሱ ቢፈሩኝም ነው የሚሻለው”፡፡
በፕሪምየር ሊጉ ተስፋ ሰጪን እንቅስቃሴ እያሳየ ያለ ተጨዋች፡- “ብዙዎቹን ተጨዋቾች በተደጋጋሚ የማየት አጋጣሚውን ባላገኝም እስካሁን ካየዋቸው ግን በችሎታው ከፍተኛ ተስፋ የጣልኩበት ተጨዋች የእኛውን ሀይለሚካኤል አደፍርስ /ቼሪን/ ነው፡፡
በዓለም ላይ የኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ ስለመሆኑ፡- “በሽታውን በተመለከተ ብዙ ነገሮችን እየሰማን ነው፤ በውጪው ዓለም ሰዎችም በቫይረሱ እየተጠቁ ይገኛልና እኛም ሀገር የገባ በመሆኑ ሁላችንም ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል፤ ከዛ ውጪም ይሄን ቫይረስ አስመልክቶም የተለያዩ ሀገር የሊግ ውድድሮችም እየተቋረጡ ነውና እንደ እኛ ባሉት ሀገራት ደግሞ ይሄ ህመም ከተስፋፋ ከፍተኛ ችግር ሊያስከትል ስለሚችል ሊግ ኮሚቴው ስለውድድሩ ሊያስብበት ይገባል”፡፡
ስለ ቤተሰቡ፡- “ጥሩ ቤተሰብ አለኝ፤ ባለቤቴም ሀዊ ተስፋዬ ትባላለች፤ እሷም ለእኔ የዛሬ እግር ኳስ ተጨዋችነት እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ትልቁን አስተዋፅኦ ያደረገችና ነፍሰ ጡር ሆና ጭምርም አሁን ድረስ በኳሱ የምታበረታታኝ ነችና ምስጋናዬን ላቀርብላት እፈልጋለው”፡፡
በመጨረሻ…፡- “የሰበታ ከተማ ደጋፊዎች ለክለባችን የሚያደርጉትን ማበረታታት በጣም አደንቃለው፤ ስለዚህም ሊመሰገኑ ይገባል፤ ከዛ ውጪ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ለእኔ የእግር ኳስ ተጨዋችነት አሁን ላይ ለውጥን እንዳመጣ እያደረጉኝ ያሉትን መጀመሪያ ፈጣሪዬን ከዛም አሁን ላይ ትምህርት ቤት የገባው ያህል እያሰለጠነኝ ያለውን ውበቱ አባተን እና ቤተሰቦቼን እንደዚሁም ጓደኞቼን አመሰግናቸዋለው”፡፡
?
https://t.me/Leaguesport

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P