Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በመከላከያ ቆይታዬ ውሌን አራዝሜ እቀጥላለሁ እንጂ እለያያለው ብዬ ፈፅሞ አልጠበቅኩም ነበር”በሀይሉ ግርማ /ሰበታ ከተማ/

 

የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ካፒቴን ሆኖ በበርካታ ግጥሚያዎች ላይ ተሰልፏል። ቡድኑ ከወረደበት ከፍተኛው ሊግ ወደ ነበረበት ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እንዲያልፍ ከክለቡ ተጨዋቾች ጋርም ጥሩ አስተዋፅኦውን አበርክቷል። ያም ሆኖ ግን የውል ጊዜው በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ሲጠናቀቅ ይኸው ተጨዋች ለረጅም ጊዜ ግልጋሎትን ከሰጠበት ክለቡ ጋር በመለያየት በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪኖ/ ሊሰለጥን ወደተዘጋጀው አዲሱ ክለቡ ሰበታ ከተማ ሊያመራ ችሏል።

በመከላከያ ክለብ ውስጥ በፕሪምየር ሊግ ደረጃም ሆነ ክለቡ ወደታችኛው ሊግ በወረደበት ሰዓት ለቡድኑ ተሰልፎ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚታወቀው የአማካይ ስፍራው ተጨዋች በሀይሉ ግርማ  በቡድኑ ቆይታው ዳግም ውሉን በማራዘም ከመከላከያ ጋር ስለመቀጠል እንጂ  ከክለቡ ጋር እለያያለው ብሎ ፈፅሞ እንዳላሰበ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን ከክለቡ ጋር ስለተለያየበት  ሁኔታም ሀሳቡን ሲሰጥ “አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ ለመጪው የውድድር ዘመን ሊገነቡት ለፈለጉት ቡድን እኔን የዕቅዳቸው አካል ስላላደረጉኝ ነው፤ ቢፈልጉኝ ኖሮ ድርድር ውስጥ ይገቡ ነበር”  ካለ በኋላ እኔ ግን ለመከላከያ ቡድን ከሰጠሁት ጥሩ ጥቅም አኳያ  ከክለቡ ጋር  ውሌ ተራዝሞ  አለመቀጠሌ  የሚያስቆጨኝና ያልጠበቅኩት ነው፤ ከቡድኑ በመውጣቴ የተገፋው ያህልም ነው የተሰማኝ ሲልም ተጨማሪ አስተያየቱን አክሎ  ገልጿል።

በመከላከያ የነበረውን የውል ጊዜ ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ሰበታ ከተማ ካመራው የአማካይ ስፍራው ተጨዋች በሀይሉ ግርማ ጋር የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ቆይታን አድርጎ ተጨዋቹ የሰጠው ምላሽ እንደሚከተለው ይቀርባል።

ሊግ፦ መከላከያና በሀይሉ ግርማ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዘንድሮ ተለያዩ፤ ይህ ይሆናል ብለህ ጠብቀህ ነበር?

በሀይሉ፦ በፍፁም፤ ምክንያቱም በዚህ ቡድን ውስጥ  የነበረኝ ቆይታ በአብዛኛው የውድድር ዓመታቶች የአማረና የተሳካም ወቅት ነበርና። መከላከያ እኔን ፈልጎ እስካሁን ሲያጫውተኝ የነበረ ቡድን ነው። በዚህ ቡድን ሳለውም ጥሩ ከመጫወቴ ባሻገር በስነ-ምግባር ደረጃም የቡድኑ ግዴታዬን ስወጣም የነበርኩኝ ነኝ። ከዛ ውጪም ክለቡ ወደ ታችኛው ሊግ ሲወርድም አብሬ ወርጄም በካፒቴንነት ዳግም ወደነበረበት ሊግ እንዲመለስ  ያደረግኩኝ ተጨዋችም ነኝ። ክለቡ ካደረጋቸው ግጥሚያዎች ውስጥም  በአሰልጣኙ እምነት ተጥሎብኝ የመጨረሻዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሲቀሩ በቀይ ካርድ ወጥቼ ካለመጫወቴ በስተቀር  በአጠቃላይ  ጨዋታዎች ላይም በቋሚነት ልጫወት የቻልኩኝ ነኝ። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ዘንድሮ የውል ጊዜዬ ከክለቡ ጋር ሲጠናቀቅ አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ  እኔን የመጪው የውድድር ዘመን የቡድኑ እቅድ አካል ሊያደርገኝ ስላልፈለገና  ስላልተደራደረኝ ከመከላከያ  ጋር  ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተለያይቼ ወደ አዲሱ ቡድን ሰበታ ከተማ ለማምራት ችያለሁ። በመከላከያ  በነበረኝ ቆይታዬ ጥሩ ጊዜን ለማሳለፍ ችያለሁ። ከክለቡ ጋርም  ዳግም ውሌን አራዝሜ እቀጥላለሁ ብዬም ጠብቄ ነበር።  ያ አልሆነም። ፈፅሞ ባልጠበቅኩት ሁኔታም ነው ከክለቡ ጋር የውል ጊዜዬ እንደተጠናቀቀ የተለያየሁትና ለቡድኑ ከሰጠሁት ግልጋሎት አንፃር  የተገፋ ተጨዋች ያህል ስሜት ነው የተሰማኝ።

ሊግ፦ ከመከላከያ ብትለያይም ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ አልፋችኋል፤ ያን ስሜት እንዴት ትገልፀዋለህ?

በሀይሉ፦ መከላከያ ወደታችኛው ሊግ ሲወርድ እኔ የቡድኑ ካፒቴን ነበርኩ፤  ይህን ትልቅ ክለብ ወደነበረበት ሊግ ዳግም መመለስ አለብን በሚል የቁጭት ስሜት  ውስጥ  ሆነን ሁላችንም የቡድኑ ተጨዋቾች  በጥረታችን ክለቡን ለስኬታማነት ስላበቃነው እኔንም ሆነ የቡድናችንን አጠቃላይ አባላቶች በጣም ነው ደስ ያለን።

ሊግ፦ ከመከላከያ እንደተለያየ የቅድሚያ ምርጫ እንዴት ሰበታ ከተማ ሆነ?

በሀይሉ፦ መጀመሪያ ላይ ከሰበታ ውጪ ሌሎች አማራጮች  ነበሩኝ። ያም ሆኖ ግን ሰበታ ከተማን በሀላፊነት ከሚመራው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ጋር ከዚህ ቀደም  በመከላከያ ክለብ ውስጥ በነበረኝ ቆይታ አሰልጥኖኝ ያለፈና ከእሱም ጋር በስራ ሂደት ጥሩ ጊዜን ስላሳለፍን ከዛ ውጪም ከሚከተለው አጨዋወት ጋር እኔም የምጣጣም ተጨዋች ስለሆንኩኝም የሁለታችን ድርድር ሊሳካ ችሎ  የቡድኑ የአዲሱ ዓመት ተጨዋች መሆኔን በፊርማዬ አረጋግጬያለው።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  በሚኖርህ የሰበታ ከተማ ክለብ ቆይታህ አንተን እንዴትና በምን መልኩ እንጠብቅህ?

በሀይሉ፦ ሰበታ ከተማ ለአዲሱ የውድድር ዘመን በርካታ ተጨዋቾችን ለቅቆ ነው አሁን ላይ ለቡድኑ ሊጠቅሙ የሚችሉ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኘው። ከእነዛ መካከልም እኔን ጨምሮ መከላከያን ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ ካደረጉት ተጨዋቾች መካከል በምድባችን በተደረገው ጨዋታ በርካታ ግቦችን ያስቆጠረው ዘካሪያስ እና ሳሙሄል ሳሊሶ እንደዚሁም ደግሞ ወጣቱ ተጨዋች መሀመድ ም ይገኙበታል። ሌሎችም ጥሩ ተጨዋቾች ቡድኑን እየተቀላቀሉና አሰልጣኙ ደግሞ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ወላይታ ዲቻን መሀል ላይ በመረከብ ጥሩ ቡድን ከመስራቱ ባሻገር በውጤትም ወደላይ ከፍ እንዲል ስላደረገው የእኔም የአዲሱ ዘመን የቡድኑ ቆይታዬ የአማረ እንደሚሆንና ክለባችንም ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣ እርግጠኛ ነኝ።

ሊግ፦ ላሳደገህ ሙገር ጨምሮ የመከላከያ ክለብ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ቆይታን አድርገህ ተጫውተሃል፤ ወደ ብዙ ክለቦች ያላመራህም ተጨዋች ሆንሃል። በዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

በሀይሉ፦ የእውነት ነው የኳስ ጊዜዬን በአብዛኛው ያሳለፍኩት በሁለቱ ክለቦች ውስጥ ነው። ሙገር እኔን አሳድጎም ለዛሬው ደረጃ እንድደርስ ያደረገኝና እንጀሬ ያወጣልኝ የምወደው ክለቤም ነው። ወደ መከላከያ ስገባም ብዙ ነገሮችን እንዳውቅ ክለቡ አስችሎኛልና የእነዚህ ቡድኖች ቆይታዬ ረጅሙን ጊዜ ወስዶ ወደ ሌሎች በርካታ ክለቦች እንዳላመራ ያደረገኝ እግር ኳሱን ስጫወት በጥሩ ስነ-ምግባር ለስፖርቱ ተገዥ ሆኜ ለቀጠረኝ ክለብ የሚጠበቅብኝን ግልጋሎት ስለምሰጥና ብዙም ግጭት ውስጥ ስለማልገባ ከዛ ውጪ ያለኝ ፀባይም ከሰዎች ጋር የሚያግባባኝ ስለሆነም በዚህ መልኩ ነው ቆይታን ያደረግኩት።

ሊግ፦ አሳዳጊ ክለብህ ሙገር ሲፈርስ ስሜትህ የቱን ያህል ነበር?

በሀይሉ፦ ሙገር መፍረስ ያልነበረበት ተወዳጅ ክለብ ነው። ቡድኑ በአንድና በሁለት ሰዎች ምክንያት ያውም ምንም አይነት መግለጫ ባልተሰጠበት ሁኔታና  እስከዛሬ ድረስም የፈረሰበት ሁኔታ ሳይታወቅ ይህን ለእኛም ሆነ ለሀገር ትልቅ አገልግሎት የሰጠ ክለብ ሲፈርስ ሳይ የተሰማኝ ሀዘን በጣም ከፍ ያለ ነበር። ሙገር ታዳጊ ተጨዋቾችን በማፍራት በጣም የሚታወቅ ቡድን ነበር። በቡድኑ ውስጥ የነበረው ፍቅርም የሚገርምና የፍቅር ቤትም ተብሎ የተነገረለትም ስለነበር የዚህ ቡድን አለመኖር ሁሌም ያሳዝነኛል፤ የፈረሰበትን ሁኔታም ባውቅ በጣም ደስ ይለኛል።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በዲ. ኤስ. ቲቪ  የምትታይበትን እድል ለማግኘት ከጫፍ ደርሰሃል። በዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

በሀይሉ፦ ዘንድሮ ኳስን የተጫወትኩት በታችኛው ሊግ ነበርኩና ብዙ ጓደኞቼ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ሲታዩ በጣም ደስ ይለኝ ነበርና  እኔስ መቼ ይሆን ይህን እድል የማገኘው በሚል የቁጭት ስሜት ከራሴ ጋር በመነጋገርም ላይ ነበርኩና አሁን ላይ እኔም ለዚህ እድል ልበቃ በመዘጋጀቴና  በዛ ደረጃ መጫወት ስለሚያስገኘው ጥቅምም ብዙ ልምዶችን  ከጓደኞቼ የወሰድኩባቸው አጋጣሚዎች ስላሉም ከወዲሁ ጥሩ ስሜት ነው እየተሰማኝ ያለው። ዲ ኤስ ቲቪ የሀገራችንን እግር ኳስ ለማሳደግ እየጣረ ያለ ድርጅት ነው። ከዛ ውጪም ለእኛ ተጨዋቾች ችሎታችንን በማሳደግ በኳሱ የላቀ ደረጃ ላይ እንድንደርስም ስለሚያደርገን ይህን ሁኔታ ወደ አገራችን እንዲመጣ ላደረጉት የሊግ ካምፓኒው አመራሮች በዚሁ አጋጣሚ ምስጋናን ማቅረብ እፈልጋለሁ።

ሊግ፦ የክረምት ወራቱ የእረፍት ጊዜ እንዴት እየታለፈ ነው?

በሀይሉ፦ የውድድር ዘመኑን ጨዋታ እንዳጠናቀቅኩኝ መጀመሪያ ላይ ከቤተሰቦቼ ጋር ለረጅም ጊዜያት ተለያይቼ ስለነበር ከባለቤቴና ከልጄ ጋር ነበር  የእረፍት ወቅቱን ያሳለፍኩት። ከዛ በኋላ ደግሞ ለአዲሱ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ለፈረምኩለት ክለብ ሰበታ የሚጠበቅብኝን ግልጋሎት ለመስጠትና አሁን ካለኝ ብቃትም ከፍ ባለ ደረጃ ላይ መቀመጥን ስለምፈልግ እንደዚሁም ደግሞ በኳስ ተጨዋችነት ዘመኔም እኔ በምፈልገው  ደረጃ ላይ ባለመድረሴም የቁጭት ስሜትም ስላለብኝ በግል ከጓደኞቼ ጋር በመቀጣጠር ከወዲሁ ልምምዴን በመስራት ላይ ነው የምገኘው።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P