Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በእግር ኳሱ ታላቅ ደረጃ ላይ መድረስ የቅርብ እልሜ ነው” ሄኖክ ዱልቢ /ሐዋሳ ከነማ/

የሐዋሳ ከተማ ውስጥ ቧንቧ ሰፈር
ወይንም ደግሞ ሐረር ሰፈር በሚባለው
አካባቢ ነው ከአባቱ አቶ ዱልቢ መሐመድ
እና ከእናቱ ወ/ሮ ወርቄ ካሳ በመወለድ
ወደዚህች ምድር ብቅ ያለው፤ የሐዋሳ
ከተማ እግር ኳስ ክለብ ውስጥ የ25
ቁጥርን በማጥለቅ በመሃል ሜዳ ላይ
የሚጫወተው ይኸው ወጣት ተጨዋች
በሚሰለፍባቸው ግጥሚያዎች ላይ አበረታች
የሚባል ብቃቱን ሲያሳይ የተስተዋለ ሲሆን
ተጨዋቹ አሁን ላይ የያዘውን እንቅስቃሴ
አጠናክሮ ከቀጠለም በእግር ኳሱ ወደፊት
ትልቅ ደረጃ ላይ ይደርሳል የሚል ግምትን
በብዙዎች ዘንድ አግኝቷል፡፡
የሐዋሳ ከተማ ክለብ ውስጥ ተወልዶ
በማደግ በቤተሰቦቹ ውስጥ ከሚገኙት 5
ወንድሞቹ እና አንድ እህቱ መካከል
ብቸኛ ስፖርተኛ እንደሆነ የሚነገርለት
ሄኖክ ዱልቢ የአሁን ሰአት ላይ 64
ኪሎ ግራም ሲመዝን 1.72 ሜትር
ቁመትም አለው፤ ይሄን ወጣት ተጨዋች
ስለ እግር ኳስ ህይወቱ ጅማሬው፤ ስለ
ቡድናቸው ሐዋሳ ከተማ፣ ከፋሲል ከነማ
ጋር ስለሚያደርጉት የነገው የጥሎ ማለፍ
የፍፃሜ ጨዋታና ሌሎችንም ጥያቄዎች
አስመልክተን ላቀረብንለት ጥያቄዎች
ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቶናል፤
ተከታተሉት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ጅማሬህ ምን
ይመስላል?
ሄኖክ፡- የእግር ኳስ ጅማሬዬ
እንደማንኛውም የአገራችን ተጨዋቾች ልጅ
ሆኜ በሰፈር ደረጃ ኳስን በመጫወት ሲሆን
ትንሽ አደግ ስልም የተለያዩ የፕሮጀክት
ቡድኖች ውስጥ በመግባት የሜዳ
ላይ እንቅስቃሴዬን እንዴት ቦታዬን
ጠብቄ መጫወት እንዳለብኝም የተለያዩ
ልምዶችን ቀስሜም ነው ኳሱን በአግባቡ
ልጫወትበትም የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ልጅ ሆኖ
መጫወት በብዙ ቤተሰቦች ዘንድ ፈቃድን
አያሰጥም ነበር፤ ለአንተስ በእዚህ በኩል
ችግር አላገጠመህም?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ
ውስጥ የታዳጊነት ዕድሜ ላይ ሆነህ
ኳስን ስትጫወት ልክ ነህ ብዙ ቤተሰቦች
ለትምህርት ቅድሚያን እንድትሰጥ
ከመፈለግ ኳሱን እንዳትጫወት የተለያዩ
ተፅዕኖን ያደርጉብሃል፤ በእኔም ቤተሰብ
ዘንድ ያኔ ኳስን እንዳልጫወት ትንሽ ጫና
የነበረብኝ ቢሆንም ከቤተሰቦቼ አካላት
ውስጥ አንዷ የሆነችው ወላጅ እናቴ ግን
የእኔን ኳስ መጫወት በጣም ትፈልገው
እና ኳስንም እንድጫወት ታበረታታኝና
ትገፋፋኝ ስለነበር ለዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ
መድረሴ የእሷ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነበርና
በእዚህ አጋጣሚ ላመሰግናት እፈልጋለሁ፡

ሊግ፡- በፕሮጀክት ደረጃ የእግር
ኳስን ስትጫወት ለማን ለማን ቡድኖች
ተጫወትክ?
ሄኖክ፡- በፕሮጀክት ደረጃ እኔ
የተጫወትኩባቸው ክለቦች መጀመሪያ
ሙሉ ወንጌል ተብሎ ለሚጠራው
የቸርች ቡድን ነው፤ በመቀጠል ደግሞ
ለሜሪስቶፕስ ተጫወትኩ በኋላ ላይ
ደግሞ ባለፈው ዓመት ላይ የኢትዮጵያ
ታዳጊ ብሄራዊ ቡድንን ያሰለጥን የነበረው
ተመስገን ዳና የራሱን የግል ፕሮጀክት
ቡድን አቋቁሞ ስለነበር የእሱ ቡድን ውስጥ
ገብቼም በመሰልጠን ልጫወት ችያለሁ፡፡
ሊግ፡- ከቤተሰባችሁ መካከል የእግር
ኳስን የምትጫወተው አንተ ብቻ ነህ?
ሄኖክ፡- አዎን፤ እኔ ብቻ ነኝ፡፡
ሊግ፡- ሐዋሳ ከነማ ለአንተ የመጀመሪያ
ቡድንህ ነው፤ ወደ እነሱ እንዴት ልታመራ
ቻልክ?
ሄኖክ፡- ሐዋሳ ከነማን በወጣት ቡድኑ
ደረጃ መጀመሪያ ልቀላቀል የቻልኩት
የተመስገን ዳና የፕሮጀክት ቡድን ውስጥ
ኳስን በምጫወትበት ሰዓት በሜዳ ላይ
የማደርገው እንቅስቃሴ በሚገባ ታይቶልኝ
ነው፤ በጊዜው ጥሩ እና አበረታች የሚባል
ችሎታው ነበረኝና መጀመሪያ ለወጣት
ቡድን ታጨሁኝ፤ እዚያም ለሁለት ዓመት
ያህል ለሚቃረብ ጊዜ ልምምዴን እየሰራሁ
እና ለቡድኑም እየተጫወትኩ ከታየሁ
በኋላ የ2009 ዓ.ም ላይ የዋናውን ቡድን
ተቀላቀልኩና በክለብ ደረጃ የእኔ የኳስ
ህይወት ጅማሬዬ የሚመስለው ይሄንኑ
ነው፡፡
ሊግ፡- የታዳጊነት ዕድሜህ ላይ ኳስን
ስትጫወት ለአንተ ተምሳሌት የሆነህ እና
አድንቀህ ያደግከው ተጨዋች ማን ነው?
ሄኖክ፡- ሙሉጌታ ምህረትና ሙሉዓለም
ረጋሳ፤ እነዚህ ሁለት ተጨዋቾችን
ያለምክንያት አላደነቅኳቸውም፤ መጀመሪያ
ስለተጨዋቾቹ እሰማ የነበረው በሚዲያ
ደረጃ ከሚነገረው ነገር በመነሳት ነበርና
በኋላ ላይ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴያቸውን
ስመለከት ከዚያ ውጪም ከችሎታቸው
ባሻገርም በዲሲፕሊን ላይ ያላቸውን ጥሩ
ነገር ስመለከት የበለጠ እንዳደንቃቸውና
በስተመጨረሻም ከእነሱ ጋር የመጫወት
አጋጣሚንም ስላገኘሁ ይሄ እኔን እድለኛ
እንድሆንም አድርጎኛልና በዚህ በኩል
በኳስ ተጨዋችነቴ በጣም ደስተኛ
እንድሆንም አድርጎኛል፡፡
ሊግ፡- ከባህር ማዶ ተጨዋቾች
መካከልስ ለአንተ ተምሳሌት የሆነህ
ተጨዋች የለም?
ሄኖክ፡- አለ እንጂ፤ የማንቸስተር
ዩናይትድ ደጋፊ ስለሆንኩ ሳይሆን የፖል
ስኮልስ አጨዋወት ሁሌም በጣም ይመቸኝ
ስለነበር እሱን አድንቄ ነው ያደግኩት፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
የመጀመሪያ ግጥሚያህን እና የመጀመሪያ
ጎልህን ታስታውሳለህ፤ በእዚያ ዙሪያስ
የምትለው ነገር ካለ?
ሄኖክ፡- የሐዋሳ ከተማ ክለብ ውስጥ
ሆኜ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ኳስን ስጫወት
የመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታዬ ከሀድያ
ሆሳዕና ጋር ያደረግነው ነበር፤ ያኔ ገና
ከስር ያደግኩበት እና ብዙም ልምድ የሌለኝ
ተጨዋች ስለነበርኩ መጠነኛ ድንጋጤ
ተፈጥሮብኝ በ25ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሬ
የወጣሁበት አጋጣሚን አስታውሳለሁ፡፡
የሐዋሳ ከነማ ክለብ ቆይታዬ ላይ በእኔ ስም
የተመዘገበችው ግብ ደግሞ የዘንድሮው
የውድድር ዘመን ላይ ደደቢትን 5ለ2
ስንረታ ያስቆጠርኳት የመጀመሪያው ግቤ
ናትና ያቺን ግብ በማስቆጠሬ በጣም ደስ
ሊለኝ ችሏል፡፡
ሊግ፡- ሐዋሳ ከነማ ከእዚህ ቀደም
በውጤታማነት ይታወቅ ነበር፤ ከብዙ
ዓመታቶች በፊትም ለሁለት ጊዜያት ያህል
የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አንስቷል፤ የጥሎ
ማለፍ ዋንጫንም ከዚህ ቀደም አግኝቷል፤
አሁን አሁን ላይ ግን ውጤቶች
ርቀውታልና በእዚህ ዙሪያ ምን ማለት
ትፈልጋለህ?
ሄኖክ፡- ሐዋሳ ከነማ እንደከዚህ ቀደሙ
ውጤታማ ሊሆን ያልቻለው የወደፊት
ቡድኑ መሰረት ጥሎ እንዲያልፍና ጠንካራ
ክለብም እንዲሆን ከመፈለግ የታዳጊ
ወጣቶች ላይ እየሰራ በመሆኑ ነው፤ ይሄን
ጅማሬ ደግሞ ለሀገር እግር ኳስ እድገት
ማሰብ ከተፈለገ ሌሎች ክለቦችም ሊከተሉት
የሚገባ ነው፤ ሐዋሳ ከነማ አሁን ላይ
በወጣቶች በማመን እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ
ስራውም ቡድኑ ላይ ካለፉት ዓመታት
ውጤት አንፃር በዚህ ዓመት ለውጦች
እየታዩ ይገኛልና በጊዜ ሂደት ደግሞ
ቡድናችንን ወደምንፈልገው ውጤታማነት
ላይ በእርግጠኝነት የምናመጣው
ይመስለኛል፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር
ሊግ የውድድር ተሳትፎ ለሐዋሳ ከነማ
ስትጫወት ተስፋ የሚጣልበት እና
አበረታች የሚባል እንቅስቃሴን ማሳየትህ
ተስተውሏል፤ እንደ ቡድኑ ተጨዋችነትህ
ያለፉትን ጥቂት ዓመታት ጉዞአችሁን በምን
መልኩ ታየዋለህ? አንተስ በቅድሚያ
እንዴት ወደ ዋናው ቡድን የማደግ እድሉን
አገኘኸ? በሜዳ ላይ የምታሳየውን
ጥሩ እና አበረታች እንቅስቃሴንስ ከምን
በመነሳት ልታሳይ ቻልክ?
ሄኖክ፡- ሐዋሳ ከነማ በወጣት
ተጨዋቾች ላይ ማመን የሚለውን የራሱን
ፖሊሲ መጠቀም ከጀመረበት የቅርብ ጊዜ
አንፃር በቡድኑ ላይ የሚታየው የሜዳ ላይ
እንቅስቃሴ ለውጥ እየታየበት ያለና
ጥሩም የሚባል ነው፤ በውጤት ደረጃ
ስታይም ከቅርብ ዓመታቶች ተሳትፎው
አኳያ የተሻለ ነገርን እየተመለከትንና
በታዳጊዎች ላይም መሰረትን እየጣልንም
ስለሆነ ካለፉት ጥቂት ዓመታት አንስቶ
አሁንም ድረስ ለብዙ ነገሮች ማሳያ የሆነ
ነገርን ማስመልከት ችለናል፡፡
ወደ ሐዋሳ ከተማ የዋናው ቡድን
ውስጥ ስለማደጌ ለእኔ ምክንያት የሆነኝና
ትልቁን አስተዋፅኦ ያደረገልኝ አሰልጣኝ
ውበቱ አባተ ነው፤ ያኔ እሱ ከስር ወደ
ዋናው ቡድን እንዳድግ በመፈለግም ነው
በሜዳ ላይ የተሻለ የሚባል ብቃትን በሜዳ
ላይ ስላሳየሁት እንዳድግ ያደረገኝና በእዚሁ
አጋጣሚ በወጣት ተጨዋቾች ላይ ከፍተኛ
እምነት ላለው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
ምስጋናዬን ልገልፅለት እፈልጋለው፡፡
የሐዋሳ ከነማ ክለብ ውስጥ የመሰለፍ
እድሎችን ባገኘሁባቸው ጨዋታዎች በሜዳ
ላይ አበረታች የሚባል እንቅስቃሴዎችን
ለማሳየት የቻልኩት በተፈጥሮ የተሰጠኝ
የራሴ የሆነ ችሎታ ስላለኝ እና
የአሰልጣኞችም ስልጠና ታግዞበት ነውና
ይሄንን ችሎታዬን ወደፊትም ጠንክሬ
በመስራት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስን
እፈልጋለሁኝ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን
እየተጫወትክም እየተመለከትክም
በቆየክባቸው አጋጣሚዎች በችሎታው
ቀልብህን ስቦ ያደነቅከው እና በኳሱ ያዝናና
ተጨዋች ማን ነው?
ሄኖክ፡- በሜዳ ላይ እንቅስቃሴው
ኳስን ሲጫወት ችሎታው ስቦኝ እኔን
የሚያዝናናኝ ተጨዋች ታፈሰ ሰለሞን /
ሜሲ/ ነው፤ የእሱ የኳስ ብቃት ይለያል፤
ሌላው የማደንቀው ተጨዋች ደግሞ
ሽመልስ በቀለ ነው፡፡
ሊግ፡– በእግር ኳስ ህይወትህ በጣም
የተደሰትክባቸው እና የተከፋክባቸው
አጋጣሚዎች የትኛዎቹ ናቸው?
ሄኖክ፡- የሐዋሳ ከተማ ክለብን
በተጨዋችነት በተቀላቀልኩበት የቅርብ
ዓመታት ላይ በጣም የተደሰትኩበት ቀን
በደቡብ ሲቲ ካፕ የዋንጫ ውድድር ላይ
ሲዳማ ቡናን አሸንፈን ዋንጫውን ስናነሳ
ሲሆን፤ የተከፋሁበት እና ያዘንኩበት
አጋጣሚ ደግሞ እስካሁን ድረስ ምንም
የለም፤ በእግር ኳሱ ህይወቴ ተደስቼ እንጂ
ለአንድም ቀን ተከፍቼም አላውቅም፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ
አሁን ላይ ያለህበትን ደረጃና ብቃት
እንዴት ትገልፀዋለህ?
ሄኖክ፡- የእግር ኳስን አሁን ላይ ገና
አልተጫወትኩም፤ ለኢትዮጵያ እግር
ኳስም ገና አሁን ነው የተወለድኩት፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳሱ የወደፊት ምኞትህ
ምንድነው?
ሊግ፡- እንደማንኛውም ተጨዋች
የቅድሚያ ዋና ምኞቴ ለብሄራዊ
ቡድን ተመርጦ መጫወት ቢሆንም
በተጨማሪነት ግን ሌላ የማስባቸው ነገሮች
አሉ፤ ለብሄራዊ ቡድን ከተመረጥኩ በኋላ
ሀገሬን ኢትዮጵያ ወደተሻለ ደረጃ ላይ
ማድረስን እፈልጋለሁ ያኔም ነው የእኔ
ደስታ ከፍተኛ የሚሆነው፤ ከዛ ባሻገር
የኢትዮጵያ እግር ኳስ እንዲያድግም በግል
ማድረግ ያለብኝን ነገር ሁሉ ለማድረግም
ዝግጁ ነኝ፡፡ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት
ደረጃም መጫወት ቀጣዮቹ እቅዶቼ እና
እልሞቼ ናቸው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ አሁን ላይ
በየሜዳዎቹ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቶች
እየታዩበት አላስፈላጊ ወዳልሆኑ ነገሮች
እያመራ ይገኛል፤ በዚህ ዙሪያ ለእግር ኳሱ
ሰላምና ለውጥ መሻሻል ምን የምትለው
ነገር ይኖርሃል?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ጥሩ
ባልሆነ መንገድ እየተጓዘ ይገኛልና አሁን
ላይ በጣም ታሟል፤ ሁሉም ጋር ወደ
ክልል ወጥቶ መጫወትም ከፍተኛ ስጋት
እና አስፈሪም ሆኗል፡፡ በሜዳ ላይ ባለህ
ችሎታና ብቃት ተጠቅመህም ነጥብ ይዘህ
መውጣትም ከባድ የሆነበት ጊዜም ነው
ያለውና በቅድሚያ ይሄንን ችግራችንን
እንድንፈታው ፈጣሪ ይርዳን፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ የአሁን ሰአት
ላይ በብሄር፣ በዘርና በፖለቲካ ደረጃ
በመከፋፈል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ
ሆኖ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ ሁኔታ
ውስጥ ከምንም ነገር ነፃ የሆነውን እግር
ኳስ ለእነዚህ ነገሮች መጠቀሚያ ማድረጉ
ተገቢ እና ትክክል ባለመሆኑ ለእነዚህ
ነገሮች የውድድሩ አዘጋጅ አካላቶች ጥሩ
ነገር እንዲመጣ እልባት ሊሰጡት ይገባል፤
እኔም በመጨረሻ ማለት የምፈልገው
ፈጣሪ ሰላሙን አውርዶልን የምንወደውን
እግር ኳስ በአገራችን ላይ እንድንመለከት
ብቻ መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ
ጨዋታን ነገ እሁድ ከፋሲል ከነማ
ጋር ታደርጋላችሁ፤ ለእዚህ ጨዋታ
ያደረጋችሁት ዝግጅት ምን ይመስላል?
የዋንጫው ባለቤትስ ማን ይሆናል?
ሄኖክ፡- ከፋሲል ከነማ ጋር ላለብን
የነገው የፍፃሜ ጨዋታ ቡድናችን በጥሩ
መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡ የነገው ተፋላሚያችን
ዘንድሮ ካሳየው አቋምም አንፃር ጠንካራ
ቡድን እንደሆነ ስለምናውቅ ይሄን
ተረድተንና የእኛም ቡድን አሁን ላይ ከጊዜ
ወደ ጊዜ በከፍተኛ መሻሻል ላይም ስለሚገኝ
ከእነሱ ጋር የምናደርገውን ጨዋታ
በአሸናፊነት ለመወጣት እየተዘጋጀን ነው
የሚገኘው፡፡ እንደ ሐዋሳ ከነማ ቡድን
ተጨዋችነቴ ከፋሲል ከነማ ጋር የሚኖረን
የዋንጫ ጨዋታ በሁለታችንም መካከል
ጥሩ ፉክክር የሚደረግበት ነው፤ በእዚህ
ጨዋታም የዋንጫው አሸናፊ ሆነንና
እኔም በታሪክ የመጀመሪያውን ዋንጫ
ማግኘትን በጣም ስላለምኩ ለቡድኔ
ውጤታማነት ከወዲሁ የምችለውን ነገር
ሁሉ አደርጋለሁ፡፡
ሊግ፡- ከእግር ኳስ ውጪ ጊዜህን የትና
በምን መልኩ ነው የምታሳልፈው?
ሄኖክ፡- የእግር ኳስን ከተጫወትኩ
በኋላ የእረፍት ጊዜዬን የማሳልፈው
የተለያዩ ስፖርቶችን እና ጂምን በመስራት
ሲሆን ከዛ ውጪ ደግሞ እቤት ስሆን
ፊልሞችን በማየት እና ሌላው ደግሞ
አልፎ አልፎ የፕሌይ ስቴሽን ጨዋታን
በመጫወት ነው፡፡
ሊግ፡- የደቡብ ክልል ተወላጆች
በአመጋገብ ላይ ጥሬ ስጋ ወይንም ደግሞ
ዓሳ በመብላት ይታወቃሉ፤ በእዚያም
አይደራደሩም፤ አንተም እንደ እነሱ ነህ?
ሄኖክ፡- እኔ እንኳን በዚህ የምለይ
ይመስለኛል፤ ጥሬ ስጋም ብዙ አልበላም፤
በአመጋገብ ላይ ግን ሌሎች ያገኘሁትን ነገር
ከመብላት ውጪ ምግብን ብዙ የመምረጥ
ችግር የለብኝም፤ ምናልባት ግን ወደፊት
የራሴ የሆነ አመጋገብ ሊኖረኝ ይችላል፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ መጫወቱ ላይ
አንተ የምትኖርበት አካባቢ እነማንን ታዋቂ
ተጨዋቾች አፈራ?
ሄኖክ፡- በሐዋሳ ከተማ ውስጥ እኔ
በምኖርበት አካባቢ የእግር ኳሱ ያፈራቸው
ተጨዋቾች ብዙ ናቸው፤ በጥቂቱ መጥቀስ
ካስፈለገም ለዓለም ብርሃኑ፣ ማናዬ ፋንቱ፣
ሄኖክ አየለ እና ቢኒያም አድማሱ /
አይናማው/ ሊጠቀሱ የሚችሉ ተጨዋቾች
ናቸው፡፡
ሊግ፡- የሄኖክ ባህሪይ ሲገለፅ?
ሄኖክ፡- ብዙዎች ፀባየኛ እና ዝምተኛ
ነው የሚሉኝ፤ አስቸጋሪ ባህሪይ አለኝ
ብዬም አላስብም፡፡
ሊግ፡- ከዋናው ስምህ ሌላ የምትጠራበት
ተቀፅላ ስም አለህ? ለምንስ ተባልክ?
ሄኖክ፡- በቅፅል ስም ደረጃ አዎን ታላቅ
ወንድሜ ሰዋለም ያወጣልኝ “አሙዬ”
የሚል የመጠሪያ ስም አለኝ፤ ይሄንን
ስም ወንድሜ ሊያወጣልኝ የቻለውም
በአንድ ወቅት ኳስን አብረን በሰፈር ደረጃ
ስንጫወት ከአፉ አምልጦት በድንገት
ሊጠራኝ በመቻሉ ነው፤ የስሙን ትርጓሜ
ግን አሁንም ድረስ ላውቀው አልቻልኩም፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ሜዳ ላይ
ስትጫወት ምን አይነት ኳስ ያዝናናሃል?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ አብዛኛው
የእግር ኳስ ተጨዋች አሁን ላይ እያየ
ያደገው የውጪ ሀገር እግር ኳስን
ነው፤ በዚህ ምልከታም በሜዳ ላይ እኔን
የሚያዝናናኝ ጨዋታ ልክ ማንቸስተር
ሲቲ እንደሚያሳየው እንቅስቃሴ አንፃር
የቲኪታካን ጨዋታ ነው፤ አንድ ቡድን
ኳሱን ተቆጣጥሮ መስርቶና ኳሱን በመያዝ
የባላጋራ ቡድንን በልጦ የሚያሸንፍበት
አጨዋወት ደስ ይለኛልና ያ አጨዋወት
ነው የእኔ ምርጫዬ፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘልቄ ከገባሁባቸው
ጊዜ አንስቶ ለእኔ በተጨዋችነት
እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የተለያዩ
አስተዋፅኦን ያደረጉልኝን ሁሉ ማመስገን
እፈልጋለሁ፤ መጀመሪያ ለሁሉም ነገር
ፈጣሪ ቅድሚያውን ይወስዳልና እሱን
አመሰግናለሁ፤ በመቀጠል ከፕሮጀክት
አንስቶ እስከ ክለብ ድረስ ያሰለጠኙኝን
ተመስገን ዳናን፣ መልካሙን፣ መድኃኒትን፣
ሙሉጌታ ምህረትን፣ ውበቱ አባተን፣ አዲሴ
ካሳን፣ የሐዋሳ ከተማ ክለብ አጠቃላይ
አባላቶችን ደጋፊዎቻችንን፣ ቤተሰቦቼን፣
እኔ የምኖርበት አካባቢ ያሉትን ጓደኞቼን
እና ጥሩ ነገር እያደረገልኝ ያለውን
የሐዋሳ ከተማ ክለብን በጣም ላመሰግን
እፈልጋለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P