Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በኮንፌዴሬሽን ካፑ መሳተፍ ብቻ አይደለም ቡናንም ሀገርንም የሚያኮራ ውጤት እናስመዘግባለን”ሬድዋን ናስር /ኢትዮጵያ ቡና/

 

 “የጣምራ ኮከብነቱን ሽልማት ማግኘት ከፈለግክ እንደ አቡኪ በጣም መልፋትና መትጋት አለብህ”

ሬድዋን ናስር /ኢትዮጵያ ቡና/

ኢትዮጵያ ቡና በመስከረም ወርላለበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ተሳትፎውናበመጪው ዓመት ላይ ለሚካሄደው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ውድድር የፕሪ-ሲዝን ዝግጅቱን ከአንድ ሳምንት በፊት የጀመረ ሲሆን ልምምዱንም በተሳካ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን የቡድኑ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሬድዋን ናስር ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር በነበረው ቆይታ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ የሻምፒዮና ውድድር ላይ ፋሲል ከነማን በመከተል ሊጉን በሁለተኝነት ደረጃ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና ለእነዚህ ከፊቱ ላሉበት ሁለት ውድድሮቹ ነባሮቹን ተጨዋቾች ጨምሮ አዳዲሶቹን  በማካተት ከኳስ ጋር የተያያዘ ጠንከር ያለ ልምምድን እየሰሩ መሆኑንም የሚናገረው ሬድዋን ናስር በእነዚህ የውድድር ተሳትፎዎቻቸውም መሳተፍ ብቻ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ውድድር የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት በኢንተርናሽናሉ ጨዋታ ደግሞ የመጀመሪያው እልማችን ከዚህ ቀደም የእኛ ቡድን ቡናም ሆነ ቅ/ጊዮርጊስ ለመጨረሻ ጊዜ አስመዝግበውት የነበረውን 16 ቡድኖች ውስጥ የገቡበትን ውጤት በማሻሻል የምድብ ድልድል ውስጥ ለመግባትና ከዛ በዘለለም ቀጥሎ ያለው እልማችን ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ከዚህ ቀደም ተሳትፎ ባደረገበት እና አሁን በቀረው የካፍ ካፕ ውድድር ላይም አራት ውስጥ ለመግባት ከፍተኛ ፍላጎታቸው መሆኑንም ይናገራል፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና የመሀል ሜዳው ላይ በጥሩ ብቃቱ በመጫወት የሚታወቀው ሬድዋን ናስርን ሊግ ስፖርት ጋዜጣ በጋዜጠኛዋ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አማካኝነት ስለ ፕሪ-ሲዝን ዝግጅታቸው፣ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ ስለሚኖራቸው የውድድር ተሳትፎና ሌሎችንም ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎችን እያነሳንለት የሰጠን ምላሽ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችሁን ጀምራችኋል፤ ምን ይመስላል?

ሬድዋን፡- በቅርቡ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ላይ የምንሳተፍ እንደመሆናችን  እስካሁን እየሰራን ያለው ልምምድ በጣም ጥሩና ጠንከር ያለም ነው፤ ከኳስ ጋር የተያያዘ ስራንም ነው እየሰራን የምንገኘው፡፡

ሊግ፡- አዳዲስ ተጨዋቾችንም በቡድኑ ውስጥ አካታችሁ ነው እየተለማመዳችሁ የሚገኘው፤ እነሱስ ክለቡንና የሚሰጠውን ልምምድስ እየተላመዱት ነው?

ሬድዋን፡- እየሰራን ካለነው ልምምድ በመነሳት እነዚህ ተጨዋቾች አዎን ክለቡን እየተላመዱት ነው ማለት ይቻላል፤ ተጨዋቾቹን በማላመድ ረገድም ብዙ ጊዜ ስፖርተኛ ሲገናኝ ለመቀራረብ ችግር የሌለበትና ከውጪም ሆነን የምንተዋወቅበት ሁኔታም ስላለ አሁን ላይ ቡናን እየተላመዱት ነው የሚገኘው፤ ከዛ ውጪ ያለውን የፕሪ-ሲዝን ዝግጅትን በተመለከተም ደግሞ እነዚህን ተጨዋቾች አሰልጣኙ አምኖና ለእኔም የጨዋታ እንቅስቃሴ ይሆናሉም ብሎ ያመጣቸውና የመረጣቸው ተጨዋቾችም ስለሆኑ ከሚሰሩት ልምምድ በመነሳት ለመናገር የምፈልገው ቡና የሚከብዳቸው ክለብ አይሆንም፡፡

ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና የፕሪ-ሲዝን ዝግጅት ከልምምዱ ባሻገር የካምፕ መንፈሱስ ምን ይመስላል?

ሬድዋን፡- እስካሁን በጣም ጥሩ ነገርን እየተመለከትን ነው፤ አዲሶቹም ነባሮቹም ተጨዋቾች እርስበርስ በፍጥነት በመግባባት ጥሩ ጊዜያቶችንም እያሳለፍንም ነው የምንገኘው፤ አሁን ደግሞ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን ጨምሮ ሌሎችም የአውሮፓ ሊግ ጨዋታዎች የተጀመሩ በመሆናቸውም ያንን በመመልከት ጭምርም ነው የካምፑን መንፈስ በጣም ጥሩ እያደረግነውም የሚገኘው፡፡

ሊግ፡- የአሁኑየፕሪ-ሲዝን የመጀመሪያው ዝግጅታችሁ በቅርቡ ለሚጠብቃችሁ የኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታችሁ ነው፤ በዚህ የውድድር ተሳትፎአችሁ ላይ ቡናን በምን ውጤት እንጠብቀው?

ሬድዋን፡- አዎን፤ አሁን ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየተዘጋጀን የሚገኘው ከላይ እንደገለፅከው ለእዚህ ከ9 ዓመታት በኋላ ለተመለስንበት የኢንተርናሽናል ውድድር ተሳትፎአችን ነው፤ በጥሩ መልኩም ነው እየተዘጋጀን የሚገኘው፤ በዚህ ከኡጋንዳው ክለብ ጋር ላለብን የደርሶ መልስ ጨዋታም ይህን ግጥሚያ በስኬት አጠናቀን ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍና ከዚህ ቀደምም የእኛው ቡድን ኢትዮጵያ ቡናና ቅ/ጊዮርጊስም ለመጨረሻ ጊዜ አስመዝግበውት ከነበረውና 16 ቡድኖች ገብተውበት ከነበረው ውጤት ላቅ ባለ መልኩም የአሁኑ የቡና ቡድን ይህን ድል እንዲቀዳጅም እንፈልጋለን፤ እንደ አጠቃላይ ኢትዮጵያ ቡና ለእዚህ ውድድሩ የቀረበው ለተሳትፎ ብቻ አይደለም፤ ቡናንና ሀገሩን የሚያኮራ ውጤትም እንደሚያስመዘግብ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ሊግ፡- ስለ ኢትዮጵያ ቡና ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ክለቦች ደረጃ ስላስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በቂ ግንዛቤው አለ?

ሬድዋን፡- አዎን፤ በ1990 ዓ/ም ላይ ቡና በነበረው ምርጥ ቡድን የአፍሪካ ሀያሉን የግብፅ ክለብ አል-አህሊን አሸንፎ ወደ 16 ቡድኖች ደረጃ የገባበትን ውጤት በሚገባ አውቃለው፤ የምድብ ድልድል ውስጥ ሊገባም ከጫፍ ደርሶም ነው ከውድድሩ የተሰናበተውና የአሁኑ የእኛ ቡድን ያንን ታሪክ ወደ ኋላ በመመልከትም ጭምር ነው ሪከርዱን ለማሻሻልም እየተዘጋጀን የምንገኘው፤ በዚሁ የውድድር ተሳትፎአችን የእኛ የመጀመሪያው ምኞታችን ይሄና የፕሪምየር ሊጉንም ዋንጫ ማንሳት ቢሆንም በኢንተርናሽናል የውድድሩ መድረክ ላይም በታሪክ እንደሰማሁት ኢትዮጵያ መድን በአፍሪካ ካፍ ካፕ የውድድር ተሳትፎው ላይ ከዚህ ቀደም እንዳስመዘገበው የግማሽ ፍፃሜ ድረስ የመግባት ራዕይም ነው ያለን፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ዋንጫውን አጥቶ ነው ውድድሩን በሁለተኝነት በማጠናቀቁ ለኮንፌዴሬሽን ካፑ ያለፈው እነዚህን ሁለት ስሜቶች እንዴት ነው ያስተናገድካቸው?

ሬድዋን፡- አስቀድመን አልመን የነበረውን የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ በማጣታችን በጣም ብከፋም በሌላ ጎኑ ስመለከተው ደግሞ ቡድናችን ከራቀበት የኢንተርናሽናል  የውድድር መድረክ ላይ ከ9 ዓመታት በኋላ ዳግም በእኛ የተጨዋችነት ዘመን ሊመለስ በመቻሉ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ይሄ እኔን ብቻ ሳይሆን በዚህ ውድድር ላይ ክለባችን እንዲሳተፍ አጥብቀው ይፈልጉ የነበሩትን ደጋፊዎቻችንንም ሁሉ ያስደሰተም በመሆኑ በኋላ ላይ እጥፍ ድርብም ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል፡፡

ሊግ፡- በኮንፌዴሬሽን ካፑ የኡጋንዳውን ክለብ ዩጋንዳ አር ኤ ነው የምትገጥሙት፤ ስለ ክለቡ ምን መረጃ አላችሁ?

ሬድዋን፡- እስካሁን ያወቅነውም የተመለከትነውም ነገር የለም፤ ከዚህ በኋላ ምንአልባት ልናውቅ እንችል ይሆናል፡፡

ሊግ፡-የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አጥታችሁ ነው የሊግ ውድድሩን በሁለተኝነት ያጠናቀቃችሁት፤ ይሄ ውጤት ለእናንተ በቂ ነበር? ለዛ ውጤት ማጣታችሁ ምክንያት የምታደርገውስጉዳይ ነበር?

ሬድዋን፡- አዎን፤ እንደ ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነቴ ዘንድሮ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ካሳየነው ጥሩ ብቃትና በተጋጣሚዎቻችን ላይም ከነበረን የኳስ ብልጫ አኳያ እኛ ያስመዘገብነው ውጤት በቂ የሚባል አይደለም፤ ውጤቱም ያንሰናል፤ ግን የኳስ ነገር ሆነና ዋንጫውን አጣን፤ በዘንድሮ ውድድራችንም እኛ የሊጉን ዋንጫ ያጣነው በሰራናቸው ጥቃቅን ችግሮችም ነው፤ በተለይ በቆመ ኳስ ላይ በጣም ቸልተኞች ነበርን፤ በግብ ክልላችን ላይም የምንፈፅማቸው ስህተቶች ጭምርም ግቦች በቀላሉ እንዲገቡብን ያደርጉ ነበርና እነዚህ ውጤቶች አሳጥተውናል፤ ከዛ ውጪ ፋሲሎች በወኔ ደረጃ ከእኛ የተሻሉም ነበሩ፤ እነሱ ጋር እያንዳንዱን ጨዋታም ማሸነፍና ማሸነፍ በሚል ውጤት ላይ ብቻ ባተኮረ መልኩ ተጨንቀውም  ይንቀሳቀሱ ነበር፤ እኛ ጋር ስትመጣ ግን ከውጤቱ ባሻገር ለያዝነው የጨዋታ እንቅስቃሴም በመጨነቅና እንቅስቃሴውንም እያሳደግን ለመሄድም እንፈልግም ስለነበር ያ ልዩነትም ነው ዋንጫውን ሊያሳጣን የቻለው፡፡

ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና በመጪው የውድድር ዘመን ተሳትፎው ለየት ባለ መልኩ ይቀርባል?

ሬድዋን፡- ከጨዋታ እንቅስቃሴ አንፃር ከሆነ የያዘውን አጨዋወት ይበልጥ አሳድጎትና ስህተቶቹን ቀንሶ ይመጣል እንጂ የያዘውን አጨዋወት ፈፅሞ አይለቅም፤ ለየት ብለን የምንቀርበው ይሄ ደጋፊ የሊጉን ዋንጫ አጥብቆ ይፈልጋልና ጠንክረን ሰርተን በመቅረብ እነሱን በውጤት ልናስደስታቸው ይገባናል፡፡

ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና በሚበረከተው አስተዋፅኦ ከአንተስ በአዲሱ ዓመት ምን እንጠብቅ፤ በቋሚ ተሰላፊነት ለመጫወት የሚኖረው ፉክክርስ ምን ይሆናል ብለህ ትጠብቃለህ?

ሬድዋን፡- በኢትዮጵያ ቡና በሚኖረኝ የመጪዎቹ ዓመታት የተጨዋችነት ቆይታ ከእኔ ብዙ ነገሮች እንደሚጠበቁ አውቃለውና ለዚህ ቡድን ጥሩ ነገሮችን ለመስራት እያሰብኩ ነው፤ ለመሰለፍ የሚኖረው ፉክክርም ጥሩ ስለሆነ ያን እድል ለማግኘትም እታገላለው፡፡

ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና ለሶስት ዓመት ውልህን ከማራዘምህ በፊት ክለቡን ለመልቀቅ ተዘጋጅተህ ነበር?

ሬድዋን፡- ኸረ በፍፁም፤ ይሄን ያለው ማነው? ቡና እኮ ለእኔ ብዙ ነገር ያደረገልኝ ክለብ ነው፤ በዛ ላይ ምርጥ ደጋፊም አለው፤ በወቅቱ ለእኔ በሚደረገው ነገር ላይ እየተነጋገርን ነበር፤ ከዛ መስማማት ቻልን፤ ቀጠልኩኝ፡፡

ሊግ፡- ወንድምህ አቡበከር ናስር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የጣምራ ሽልማቶችን ወስዷል፤ በዛን ወቅት ምን አልክ?

ሬድዋን፡- በጣም ደስ ብሎኛል፤ እንደ እሱ ይህን አይነት ሽልማት ለማግኘትም በጣም መልፋትና መትጋት ይኖርብሃል፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ..?

ሬድዋን፡- በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ የታላቁን ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን መለያ አጥልቄ በመጫወቴ በጣም ደስ ብሎኛል፤ ከዚህ ቡድን ጋር ታሪክ መስራትም እፈልጋለውኝ፤ አሁን ሌላ የማስበው ደግሞ ክለቤ ላይ ደርሶብኝ በነበረው ጉዳት ምክንያት ለብሔራዊ ቡድን ተመርጬ ከዛም ከእነሱ ጋር ሳልቀጥል ቀርቼ ነበርና መልሼ ለብሔራዊ ቡድን መመረጥን እፈልጋለው፤ ይህን ካልኩ በኳሱ እስካሁን ለመጣሁበት መንገድ መጀመሪያ ፈጣሪዬን ዓላ ቀጥሎ እናትና አባቴን፣ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌና ሙሉ የኮቺንግ አባላቶችን፣ ከዛ ውጪ ደግሞ አሰልጣኝ እስማሄል አቡበከርንና ሁሌም ስልክ እየደወለ የእኔን ብቃት በማየት የሚያበረታታኝን አሰልጣኝ ይገዙ ሻንቆንና እንደዚሁም የቡና ደጋፊዎችንና አመራሮችንና የጉቶ ሜዳ ልጆችን ለማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P