Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቤትኪንግን የምንወዳደረው ለተሳትፎ ሳይሆን ለሻምፒዮናነት ነው”ብሩክ በየነ /ሐዋሳ ከተማ/



ሐዋሳ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን በ1996 እና በ1999 ለሁለት ጊዜ በማንሳት ኢትዮ-ኤሌክትሪክን በክብሩ ተጋርቶታል፤ 14 ጊዜ ካነሳው ቅ/ጊዮርጊስ በመቀጠል ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ይኸው ቡድን በዘንድሮው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ውድድር ላይም ወደ ተሳትፎው የሚገባው “ለጠንካራ ተፎካካሪነት ሳይሆን የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት” እንደሆነም የቡድኑ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ብሩክ በየነ ለሊግ ስፖርት ዝግጅት ክፍል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ሐዋሳ ከተማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀድሞው የቡድኑ ስኬታማ ተጨዋች እና ካፒቴን እንደዚሁም ደግሞ የብሔራዊ ቡድናችን ረዳት አሰልጣኝ በነበረው ሙልጌታ ምህረት በመመራት እየሰለጠነ ባለበት የአሁኑ ወቅት ክለቡ የቀድሞ ስሙንና ዝናውን ለመመለስም ጠንካራ ተሳትፎን እንደሚያደርጉም ብሩክ በየነ ተጨማሪ አስተያየቱን የሰጠ ሲሆን ከእዚህ ተጨዋች ጋር አጠር ባለ ሁኔታ ስለ ቤትኪንግ የሊጉ ተሳትፎአቸው፣ ከእሱ ጋር ስለተያያዙት ጉዳዮች እንደዚሁም ደግሞ በቅርቡ ለኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ተመርጦ በመጫወት ተሳትፎ ስላደረጉበት የሴካፋ የውድድር ተሳትፎአቸው ተጨዋቹ የሚለን አለና እሱን እንዲከታተሉት ጋብዘንዎታል፡፡
ሐዋሳ ከተማ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከማድረጉ በፊት ሲሰራው ስለነበረው የፕሪ-ሲዝን ዝግጅት
“ሐዋሳ ከተማ ለእዚህ ዓመት የውድድር ተሳትፎው እስካሁን እያደረገ የነበረው ዝግጅት በጣም ጥሩ ነው፤ ቡድናችን ይሄን ልምምድ እየሰራ የነበረውም በአብዛኛው ወጣትና ጥቂት ልምድ ያላቸውንና ነባር ተጨዋቾችንም ይዞ ነው፤ አሰልጣኛችን ሙልጌታ ምህረትም እነዚህን የያዛቸው ተጨዋቾችን ክለቡን በጥሩ ሁኔታ ሊጠቅሙ በሚችሉበት መልኩም ልምምዱን በማሰራትና ከእኛ ነባሮቹም ጋር በደንብ በማግባባት ወደ ውድድሩ ሜዳም እንድናመራም ሆነ ወደተቀናጀውም እንቅስቃሴ እንድንገባም እያደረገን ይገኛልና የአሁን ሰዓት ላይ ያለንበት ሁኔታ ጥሩ የሚባል ነው”፡፡
ሐዋሳ ከተማ በቢትኪንግ የፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎው ዘንድሮ ስለሚያመጣው ውጤት
“በውድድሩ ተሳትፎአችን ጥሩ እና በወጣቶች የተገነባን ቡድን ነው ይዘን የቀረብነው፤ ያ ስለሆነም የእዚህ ዓመት ጨዋታዎቻችንን የምናደርገው ለተሳትፎ ሳይሆን የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እና የክለቡን የቀድሞ ስምና ዝናንም ለመመለስ ነው”፡፡
በሐዋሳ ከተማ ክለብ ውስጥ ስላለው የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው
“ሐዋሳ ከተማን በመቀላቀል ስጫወት አሁን ላይ ሁለተኛ ዓመቴን ይዤ እገኛለው፤ ዓምና ወደ ቡድኑ ባመራሁበት የመጀመሪያው ዓመት የውድድር ተሳትፎዬም ላይ ኮቪድ ወደ ሀገራችን ገብቶ ሊጉን እስካቋረጠበት ሰዓት ላይ ለክለቤ 9 ግቦችንም ለማስቆጠር ችያለውና ይሄን ስመለከት ከጅማሬዬ የቡድኑ ቆይታዬን በመልካምነቱ ነው ላነሳው የምፈልገው”፡፡
ወደ ሐዋሳ ከተማ ከማምራቱ በፊት ስለተጫወተበት ቡድንና ስለነበረው የሜዳ ላይ ተሳትፎ
“ሐዋሳ ከተማን በተጨዋችነት ለማገልገል ከመምጣቴ በፊት አስቀድሜ ስጫወትበት የነበረው ቡድን ወልቂጤ ከተማ ነበር፤ ያኔ የቡድኑ አሰልጣኝ የነበረውም አዲሴ ካሳም ነበርና በእሱ ምርጥ ስልጠና እየተመራው ነበር ስጫወት የነበርኩት፤ በእዚሁ ቡድን የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬም ለሁለት ዓመታት በቡድኑ ቆየውና የመጀመሪያው ዓመት ላይ በ6 ጨዋታ 9 ግቦችን በሁለተኛው ዓመት ላይ ደግሞ በ3 ጨዋታ 9 ግብ አስቆጥሬና ጥሩ ጊዜንም በቡድኑ ውስጥ አሳልፌ ወደ ሐዋሳ ከተማ በሁለተኛው ዙር ላይ ለማምራት ቻልኩ”፡፡
ለሐዋሳ ከተማ በእዚህ ዓመት የሜዳ ላይ ተሳትፎው ምን ጥቅምን ሊሰጥ እንደተዘጋጀ
“ይሄ ቡድን የሊጉ ሻምፒዮና እንዲሆን በጣም እፈልጋለው፤ ከዛ በመነሳት ይህ ውጤት ሊገኝ የሚችለው ደግሞ ሁሉም የቡድኑ ተጨዋች በጥሩ አቋም ላይ ሲገኝ ነውና እንደ ራሴ በግል ቡድኑን ለመጥቀም በሚገባ ተዘጋጅቻለው፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ዓምና ከነበረኝ ብቃት የተሻለ ተጨዋች ለመሆንና ብዙ ግብም የማገባ ተጨዋች እንደምሆን አምናለው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነቱ አርአያ ስለሚያደርገው ተጨዋች
“ለእግር ኳስ በነበረኝ ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ወደ ተጨዋችነቱ ሳመራ አርአያ ያደረግኩት ተጨዋች አንድ ሳይሆን ሁለት ናቸው፤ እነዚህም ሽመልስ በቀለ እና ጌታነህ ከበደ ይባላሉ፤ ለሁለቱ ተጨዋቾች ጥሩ አድናቆት አለኝ፤ አይቼያቸው ስላደግኩ ሁለቱንም ተምሳሌቴ /ሞዴሌ/ አድርጌያቸዋለሁ”፡፡
የእግር ኳስ ተጨዋችነት ጉዞው በምን እንዲጠናቀቅ እንደሚፈልግ
“አሁን ላይ የእግር ኳስን መጫወት ጀምሬዋለሁ፤ አበረታች የሚባል እንቅስቃሴንም በሜዳ ላይ ማሳየት ጀምሬያለው፤ በእዚሁ ተሳትፎዬ ጥሩ ጉዞን ከወዲሁ እያደረግኩም ነው የምገኘው፤ ይህን ካልኩ ከእዚህ በኋላ በሚኖረኝ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ የኳስ መዳረሻዬን ማጠናቀቅ የምፈልገው የመጀመሪያው ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ በመጫወት ስኬትን መጎናፀፍ እና ደማቅ ታሪክን ማስፃፍ ከእዛ ውጪ ደግሞ ከምጫወትበት ቡድን ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት መቻልና እንደ ግል ደግሞ የሀገሪቱ ከፍተኛ ግብ አግቢ በመሆን ታሪካዊ ተጨዋች እና በፕሮፌሽናል መልኩም የተጫወተ ተጨዋች ተብዬ ነው የኳስ ጉዞዬን ማጠናቀቅ የምፈልገው”፡፡
በመጨረሻ…
“የእግር ኳስን ስጫወት በፍጥነት ራሴን እዚህ ደረጃ ላይ አደርሳለው ብዬ ፈፅሞ አልጠበቅኩም፤ ያም ሆኖ ግን በፈጣሪ እርዳታ ይሄ ሊሆን ችሏልና በመጀመሪያ አምላኬን በመቀጠል ደግሞ ቤተሰቦቼንና ከእዚህ ቀደም አሰልጥነውኝ ያለፉትን አዲሴ ካሳንና በወጣት ብሔራዊ ቡድን ደረጃ ጭምር ያሰለጠነኝን ተመስገን ዳናን ላመሰግናቸው እፈልጋለውኝ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P