Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በኳሱ ብዙ ውጣ ውረድ ባሳልፍም ያንን ተቋቁሜ አልፌ ወደ ብቃቴ መመለሴ አስደስቶኛል” ተስፋዬ አለባቸው /መቻል/

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ መስከረም 20/2015 ቀን ሲጀመር ጠንካራ የሊጉ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት ክለቦች መካከል አንዱ መከላከያ ነው፤ ይኸው ቡድን የመጪው ዓመት ውድድሩን ሲከፍትም በቀድሞ መጠሪያ ስሙ “መቻል” በመጠራትም ይጫወታል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ስመ ገናና ከሆኑት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነውና በውጤታማነቱም የሚታወቀው መቻል ለአዲሱ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ስም ያላቸውንና ጥሩ ችሎታ ያላቸውን ትላልቅ ተጨዋቾችን በማስፈረም ላይ ሲገኝ ከእነዛም መካከል በሀድያ ሆሳዕና ክለብ ውስጥ በውድድር ዘመኑ ጥሩ ብቃቱን በማሳየት ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈውን ተስፋዬ አለባቸውን /ቆቦ/ ሊያስፈርምም ችሏል።

መቻል ለቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጪው ዓመት የውድድር ዘመን ተሳትፎው ሊያስፈርመው የቻለው ተስፋዬ አለባቸው /ቆቦ/ በተጨዋችነት ዘመኑ ለሰበታ ከተማ፣ ለቅ/ጊዮርጊስ፣ ለወልዲያ ከተማ፣ ለወላይታ ድቻ እና ለሀድያ ሆሳዕና ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በእነዚህ የተጨዋችነት ዘመን የውድድር ዘመን ቆይታው በአብዛኛው ጥሩ ጊዜያትን ከማሳለፍ አልፎ ከቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ለአራት ጊዜያት የሊጉን ዋንጫ፣ ለአንድ ጊዜያት የጥሎ ማለፍ ዋንጫን ሊያነሳ ችሏል፤ ከመቻል አዲሱ ፈራሚ ተስፋዬ አለባቸው /ቆቦ/ ጋር የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ስላሳለፋቸው የኳስ ህይወቱ፣ ስለ ራሱ የግል ብቃት፣ በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ወደ አዲሱ ክለቡ ስላደረገው ዝውውር እና ሌሎችንም ጥያቄዎች አቅርቦለት ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶታል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በተለያዩ ክለቦች ውስጥ ተጫውተህ አሳልፈሃል፤ በኳሱ ባለፉት ህይወቶችህ ደስተኛ ነህ?

ተስፋዬ፦ አዎን፤ በጣም፤ በኳስ በእርግጥ ብዙ ውጣ ውረድ ይኖራል፤ ይሄ ደግሞ በእግር ኳስ ብቻ አይደለም በህይወትህ ጭምርም የሚያገኝህ ነገር ነው፤ እነዚህ ሁኔታዎች ደግሞ የህይወትህ ማጣፈጫዎች እና ቅመሞች ስለሆኑ እነዚህን ነገሮች ተቋቁሞ ማለፍ እና አሜን ብሎም መቀበል የግድ ስለሆነ ባሳለፍኳቸው የኳስ ህይወቶቼ ደስተኛ ነኝ።

ሊግ፦ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥለሰበታ ከተማ ስትጫወት ነበር አንተን እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ኤፊ ኦኔራ ለዋልያዎቹ በመጥራት ወደ እውቅናው መድረክ ሊያመጡህ የቻሉት፤ እሳቸው በአንተ አንደበት በምን መልኩ ነው የሚገለፁት?

ተስፋዬ፦ በእግር ኳስ ህይወት ቅድሚያ የሚሰጥህ ሁልጊዜ አሁን ለምሳሌ እኔን ወደ ሰበታ ከተማ እንድመጣ ያደረገኝ አሰልጣኝ ደረጄ በላይ ነው፤ እሱን አባት ነው የምትለው፤ ታውቀዋለህ፤ ከእሱ በኋላ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን የመረጠኝና በራሴ ተማምኜም እንድጫወት ያደረገኝ አሰልጣኝ ኤፊ ኦኔራ ነውናእሱም ለእኔ ልክ እንደ አባት የምመለከተው ጥሩ ሰውም ነበር።

ሊግ፦ ኤፊ ኦኔራ በያዘው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ ነበርክና የእዛን ጊዜ ተሳትፎአችሁን እንዴት ተመለከትከው?

ተስፋዬ፦ በወቅቱ ጥሩ እና አሪፍ ጊዜን ነበር ያሳለፍነው፤ ብዙዎቻችንም አስራ አንድ እና አስራ ሁለት የምንደርሰው ተጨዋቾችም አዳዲስ ነበርን፤ ደረጃ ውስጥ ሁሉ ገብተን መጫወታችንም የማይረሳኝ ነበርና  በወቅቱ ኦኔራ ጥሩ ቡድን በመስራቱ የአማረ የውድድር ጊዜን ነው ልናሳልፍ የቻልነው።

ሊግ፦በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታህ ላይ ኳሶችን ከባላጋራ ተጨዋቾች ላይ ከመንጠቅ ባሻገር በጥሩ ሁኔታ የምታቀብልበትንም ሁኔታ ለመመልከት የቻልንባቸውም ወቅቶች ነበሩ፤ ያም ሆኖ ግን እነዚህ ብቃቶች ኖረውህ አግሬሲቭ እና ስሜታዊ የምትሆንባቸውም ወቅቶች አሉና በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያዎች የምትላቸው ነገሮች ካሉ?

ተስፋዬ፦ በእንደዛ መልኩ ኳሶችን የምጫወተው አልሸነፍ ባይነቱ በውስጤ ስላለ እንጂ ሌላ ነገር እና ምክንያት ኖሮኝ አይደለም፤ መሸነፍን ማንም ሰው አይወድም፤ አውቀዋለሁ፤ አንድ አንድ ሰው ላይ ግን የሚገንበት እና የሚለይበት ነገር አለ፤ እኔም የእዛው ተጠቂ ሆኜ ነበር ኳሱን ስጫወት የነበረው።

ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታህ ላይ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር የተለያዩ የዋንጫ ድሎችን ለማሳካት ችለህ ነበር፤ ያን ወቅት በምን መልኩ ታስታውሰዋለህ?

ተስፋዬ፡- አዎን፤ በቡድኑ ውስጥ በነበረኝ የያን ዘመን ቆይታዬ አራት የፕሪምየር ሊግ ድሎችን፣ አንድ የጥሎ ማለፍ እና አንድ የሱፐር ካፕ ዋንጫን ላገኝ ችያለሁ፤ በአጠቃላይ በሊጉ ያላገኘሁት ስኬትም የለም፤ ይሄም ነው ደስተኛ ያደረገኝ፤ ከዛ ውጪም በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎአችንም ስምንት ውስጥ ለመግባት አሪፍ ጊዜን ያሳለፍንና ያስደሰተን ቢሆንም ያን እልም በመጨረሻ ግን አለማሳካታችን ብቻ ይቆጨኛል።

ሊግ፦ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ዘመንህ ቆይታህ ላይ ከአጠገብህ ከበርካታ ተጨዋቾች ጋር የመጫወት አጋጣሚውን ለማግኘት ችለሃል፤ ኳሱን ስትጫወት በጣም ምቾት የሰጠ ተጨዋች ማን ነው?

ተስፋዬ፦ የእውነቱን ለመናገር ከብዙዎቹ አጠገብ ጋር ሆኜ ኳሱን ስጫወት ጥሩ ጊዜያትን ያሳለፍኩ ቢሆንም ከእነዛ መካከል ምረጥ ከተባልኩ ደግሞ በጣም ምቾትን ሰጥቶኝ የተጫወትኩት ተጨዋች ለጥቂት ጊዜም ቢሆን የተገናኘነው በቅ/ጊዮርጊስ በነበርኩበት ሰዓት ላይ ከፋሲካ አስፋው አጠገብ ጋር ሆኜ ኳሱን ስጫወት ነው።

ሊግ፦ ለቅ/ጊዮርጊስ በምትጫወትበት ሰዓት ጥሩ ጊዜያትን እንደማሳለፍህ ሁሉ  በአንድ ወቅት ደግሞ ህመም አጋጥሞህ ከሜዳ የራቅክበትም ጊዜ ነበር፤ ያን ወደ ኋላ መለስ ብለህ ስታስታውሰው በምን መልኩ ነው የምትገልፀው?

ተስፋዬ፦ በቅ/ጊዮርጊስ ያሳለፍኳቸው ዓመታቶች የእውነት ለመናገር ከስኬት ጋር የተገናኘ ጭምር ስለነበር በጣም ጥሩ እና ደስ የሚሉ ጊዜያቶች ነበሩ፤ በተቃራኒው ደግሞ ለእዚህ ቡድን ስጫወት ለእኔ ጥሩ ያልነበሩትና እንደ መጥፎ አጋጣሚ የተመለከትኳቸው ደግሞበመጨረሻዎቹ ማለትም በ2009 ላይ ከግማሽ ዓመታቶች ጀምሮ የውድድር ዘመኑ እስኪያልቅ ድረስ የነበሩትናቸው፤ ያኔ እንደ ማንኛውም ተጨዋች አሞኝ ስለነበርና ለመጫወት ስላልቻልኩ ነው ያሳለፍኩትን ጊዜ ጥሩ አይደለም የምለው፤ በአዲሱ ዘመን ተመልሼ ስመጣ ደግሞ ተሸሎኝ ስለነበርም ጥሩ የውድድር ጊዜን ላሳልፍ ቻልኩ።

ሊግ፦ ቅ/ጊዮርጊስን ከለቀቅህ በኋላ ያሳለፍከውን የኳስ ጊዜ እንዴት ትገልፀዋለህ? ለማን ለማን ቡድኖችስ ተጫወትክ?

ተስፋዬ፦ቅ/ጊዮርጊስን ከለቀቅኩኝ በኋላ መጀመሪያ ያመራሁት ወደ ወልዲያ ከተማ ወደ አደግኩበት አካባቢ ነው ለመጓዝ የቻልኩት፤ በእዛም ቡድን ቆይታዬ ጥሩ ጊዜን ለማሳለፍ ብችልም ለቡድናችን ደግሞ ነገሮች በሚፈልገው መልኩ ሳይሄድለት መቅረቱን አስታውሳለው፤  በመቀጠል ደግሞ የተጓዝኩት ወደ ወላይታ ድቻ ነው፤ በእዛም ቡድን ቆይታዬ ደህና የሚባል ጊዜን አሳልፌያለሁ፤ ከሁሉም በበለጠ ደግሞ ራሴን አግኝቼበታለሁ፤ እንደ አዲስም ተወልጄበታለው ብዬ የምናገርለት ቡድን ደግሞ ሀድያ ሆሳዕና ነው።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ውስጥ መልካም የሚባል የውድድር ጊዜን አሳልፈሃል፤ ስለ ውድድር ዘመን ተሳትፎአችሁ ምን የምትለው ነገር አለ?

ተስፋዬ፦ ሀድያ ሆሳዕና ልክ እንደ ቤቴ ክለብ ነው፤ ከኮሚቴዎቹ ጋርና ከተጨዋቾቹም ጋር እንደ ቤተሰብም ያህል ሆነን ነው ያሳለፍነው፤ ተመካክረን ነበር ስራችንን ስንሰራም የነበርነው፤ አሪፍ ጊዜንም አሳልፈናል።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የሀድያ ሆሳዕና ክለብ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታህ ላይ የቡድናችሁ ጥሩ እና ክፍተት ጎን የነበረው የቱ ነው?

ተስፋዬ፦የውድድር ዘመኑ ቆይታችን ላይ የእኛ ችግርና ክፍተት ነበር ብዬ የማስበው ትኩረት መስጠት እና ያለመስጠት ጉዳይ ላይ ነው፤ ትኩረት የምንሰጣቸውን ግጥሚያዎች ካየካቸው በሜዳ ላይ የእንቅስቃሴ ብልጫ አለን፤ ጨዋታዎቹን ማሸነፍም ይገባናል፤ ትኩረትን ስናጣ ደግሞ ብዙ ጨዋታዎች ላይ ውጤትን እንድናጣ ያደርገናል፤ ተጋጣሚን አውርደን ስንመጣም ያልሆነ ጎሎች እንዲቆጠርብንም ምክንያት ይሆናል፤ ችግራችን እነዚህ ብቻ ናቸው፤ በጥሩና በጠንካራ ጎንነት የምናነሳቸው ነገሮች ደግሞ ብዙ ናቸው፤ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴያችን ጥሩ መሆናችን አንዱ ጥሩ ጎናችንም ነው።

ሊግ፦ ውጤትን ለማጣት ከአስተዳደራዊ ችግር ጋር በተያያዘስ አንድአንዴ ደመወዝም የማይከፈላችሁ ወቅትም ነበርና ይሄስ ሁኔታ በክፍተት ጎን ደረጃ አይነሳም?

ተስፋዬ፦ ይሄ ነገርማ ይኖራል፤ ግን ኳስ ጨዋታው ስራችን ነውና ስራህን እየሰራ ነው መጠየቅ ያለብህ፤ ደመወዝህ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ መከፈሉ አይቀርም፤ አይደለም የአሁኑ ዓመትን ያለፈው ዓመትን ሊከፍሉም እየተደራደሩና እየተዘጋጁም ነው፤ እኛ ይሄን ነገር እንደ ምክንያት አድርገን ውጤትን ልናጣም አይገባም።

ሊግ፦ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ተጫውተህ እንደ ማሳለፍህ በራስህ ላይ ምን ለውጦችን እየተመለከትክ ነው? በቀጣዩ ዓመት ላይስ በምን መልኩ ከአዲሱ ክለብህ ጋር እንጠብቅህ?

ተስፋዬ፦ እግር ኳስ ሂደትን ይፈልጋል፤ በእዛ ሂደት ውስጥ ደግሞ አልፌያለሁኝ፤ ማናችንም ደግሞ በወጥ አቋም ላይ እግር ኳስን ተጫውቶ የጨረሰ እና ያሳለፈ ተጨዋች ዓለም ላይ የለም፤ ጉዳት ይኖራል፤ መውጣትና መውረድም ይኖራል፤ በእዚህ ሰርክል ውስጥ ያለፍኩ ተጨዋች ብሆንም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ተቋቁሜ በማለፍ ወደ ብቃቴ ስለተመለስኩ በጣም ደስተኛ ነኝ። ከአሁን በኋላ በሚኖረኝ የኳስ ህይወት ቆይታዬ ደግሞ እግዚአብሄር ይርዳኝ፤ ጤናም ይስጠኝ ነገሮችን በማስተዋልና በመንቀሳቀስ ጥሩ የውድድር ጊዜያቶችን አሳልፋለው ብዬ አስባለሁ።

ሊግ፦በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት መቻልን /መከላከያን/ አዲሱ ክለብህ አድርገሃል፤ ቡድኑን እንዴት የቅድሚያ ምርጫህ አደረግክ? ከሌሎች ቡድኖችስ ጥሪ አልመጣልህም?

ተስፋዬ፦ መጥቶልኛል፤ ከራሴ ክለብ ሀድያ ሆሳዕናም ጋር ውልህን አራዝምና እኛ ጋር ቆይም ተብዬ ድርድር ቀርቦልኛል፤ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ስደራደር ብዙ ነገሮችን አስቤ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን እነሱ ካቀረቡልኝ የፊርማ ክፍያ ጋር በተያያዘ ልንስማማና ልንግባባ ስላልቻል ወደ መቻል /መከላከያ/ አመራው፤ ወደ እነሱ ሳመራ ብዙ ነገሮችን ተመልክቼ ነው፤ የቡድኑን የተጨዋቾች ስብስቡን፣ ጥሩ ክፍያን ስላቀረቡልኝና አጠቃላይ ፋሲሊቲውን /እንክብካቤያቸውን/  በመመልከት እና ጥያቄያቸውን ካቀረቡልኝ ቡድኖች መካከልም በብዙ ነገሮች የተሻለም ስለሆነ ነው።

ሊግ፦ ስለ አዲሱ ክለብህ መቻል /መከላከያ/ የቱን ያህል የምታውቀው ነገር አለ? ለክለቡ ስትፈርምስ ስለ ቡድኑ ታሪኮች የተነገረክስ አለ?

ተስፋዬ፦ በፊርማው ስነ-ስርዓት ጊዜ በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ አላወራንም፤ ያም ሆኖ ግን ስለ ቡድኑ ታሪክ በተወሰነ መልኩ የማውቃቸው ብዙ  ነገሮች  አሉ፤ መቻል ትልቅ ቡድን እንደነበርና ያን የቀድሞ ስሙን በመጠበቅ መጫወት እንዳለብንና ዳግም ታላቅ ስሙን በመመለስ ለስኬት መጫወትም እንደሚኖርብን ነው ያስተዋልኩት።

ሊግ፦ በዝውውር መስኮቱ ለመቻል እየፈረሙ ስላሉት ተጨዋቾችስ ምን አልክ?

ተስፋዬ፦ እኔም አዲሱ ፈራሚ እንደመሆኔ ወደ ቡድኑ በመምጣት ላይ ያሉትን ተጨዋቾች ከነባሮቹ ጋር ጭምር ስመለከታቸው ተጨዋቾቹን ነጥረው የወጡ ጥሩ ተጨዋቾች ነው የምላቸው፤ ከአመራሮቹና ከኮቺንግ ስታፉ ጋር በመሆንም ይህ ስብስብ የተሻለ የሚባል ውጤትን ከክለቡ ጋር ያስመዘግባል ብዬም ነው የማምነው።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ መቻል በማርሽ ባንድ ታጅቦ ነው ሲደገፍ የተመለከትነው፤ ይህን አንተም አይተካል፤ ለአዲሱ ቡድንህ ስትጫወት አንተን ጨምሮ ሌሎቹም ተጨዋቾች በእዚህ መልኩ ልትደገፉ ነውና ስሜቱን እንዴት ነው የምትገልፀው?

ተስፋዬ፦ ድጋፍ በጣም ነው የሚያስደስተው፤ እንደዚህ ደግሞ በተጠናና ድጋፉም በማርሽ ሲሆን ደግሞ የተሻለ የጨዋታ ድባብ ነው በሜዳ ላይ የሚታየው፤ በእዛ መልኩ ስትጫወትም የመነቃቃት ስሜት ይኖርሃል፤ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በእዛ መልኩ መደገፉም መልካም ነው ብዬም ነው የማስበው።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጋችን በዲ. ኤስ. ቲቪ መተላለፍ ከጀመረ አሁን ሁለተኛ ዓመቱን ይዟል፤ በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

ተስፋዬ፦ ይህ ውድድር ከመጣና ጨዋታዎቹም የቀጥታ ስርጭትን አግኝተው መተላለፍ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በእኛ ላይ ያላደረገብን ነገር ምንም የለም፤ በተለይ በቴክኖሎጂ ደረጃ፤ ውድድሩ የእያንዳንዱን ተጨዋቾች የኳስ ብቃት በሚገባ ቁልጭ አድርጎ ያሳይሃል፤ ወደ ሜዳ ስትገባም የአንተ ችሎታ እንደ በፊቱ በወሬ ብቻ አይደለም የሚለካው በእይታ ጭምርም ነው፤ ከዚህ በፊት የእኛ ኳስ በሬዲዮ ብቻ ነበር የሚተላለፈው፤ አሁን ላይ ግን ዲ. ኤስ. ቲቪ ወደ እኛ ሀገር ከመጣ ጀምሮ ኳሳችን ላይ የተሻለ ነገርን አምጥቶልናል፤ የኳስ እይታችንንም አሳድጎልናል፤ ገበያ ላይ እንድንወጣም አስችሎናል፤ ከእዛ ውጪ ደግሞ ከገቢ አንፃርም ክለቦቻችን ኳሱን ሲጫወቱ ገቢያቸውንም ጭምር እየተመለከቱ ነውና የተሻለ ነገርን ፈጥሮልናል።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዘንድሮ ሲጠናቀቅ ሻምፒዮናው ክለብ የመጨረሻው ቀን ውድድር ላይ ነበር የታወቀው? አንዱ ወራጅ ቡድንም ጭምር፤ በእዛ መልኩ የውድድሩን መጠናቀቅ አስመልክተህ ምን የምትለው ነገር አለ?

ተስፋዬ፦በቅድሚያ የውድድሩ ፍፃሜ አንገት ለአንገት በሆነና በእዛ መልኩ ሊያልቅ በመቻሉ ለሻምፒዮናውም፣ ለሁለተኛውም፣ ለመሀል ሰፋሪውም ሆነየወራጅ ቀጠናው ላይ ለነበሩት ቡድኖች ደስ በሚል ሁኔታ ነው ግጥሚያዎቹ ሊጠናቀቁ የቻሉት፤ የ1ዘንድሮው ውድድር አሸናፊው ቡድን እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ አልታወቀም ነበር፤ ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላም ነው አሸናፊው ቡድን ታውቆ ሲደሰትና ወራጅ ቡድኑም ታውቆ ሊከፋ የቻለው፤ እግር ኳስ እንግዲህ እንዲህ ያሉ ትህይንቶችን ነው የምታስተናግደው፤የጨዋታው ፍፃሜም እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ እንዲህ አጓጊ እና ደስ በሚል ሁኔታ በመጠናቀቁም ብዙዎችም ነው ሊደሰቱ የቻሉት፤ እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ከአሁን በኋላ በሚኖሩት ውድድሮችም የሊጉ አሸናፊ ቡድን አስቀድሞ የሚታወቅ አይመስለኝም፤ ምክንያቱም የውድድሩ የቀጥታ ስርጭትን ማግኘት ተጨዋቾችን ራሳቸውን ገበያ ላይ ለማውጣት ስለሚያስችላቸው እና ክለቦችም ዋንጫን ካገኙ ከሚያገኙት ገቢ አንፃርም ተጠናክረው ስለሚመጡ ወድድሩ የበለጠ እያማረም ይሄዳል።

ሊግ፦ የዘንድሮ ውድድር በቅ/ጊዮርጊስ ሻምፒዮናነት ነበር የተጠናቀቀው?

ተስፋዬ፦ የሻምፒዮናነቱ ዋንጫ ለእነሱ ይገባቸዋል፤ እንደውም ለሁለት ወራት ያህል ሊጉን ይመሩ ስለነበርም ቀድመውም ነበር ማረጋገጥ የነበረባቸው።

ሊግ፦ አቡበከር ናስር ዓምና ዘንድሮስ ለአንተ የቱ ተጨዋች ጎልቶ ወጥቷል?

ተስፋዬ፦ ብዙዎች አሉ፤ በእኔ እይታ ግን ከፊት ያስቀመጥኳቸው ተጨዋቾች የፋሲል ከነማ ተጨዋቾች የሆኑትን በዛብህ መላዮ እና በረከት ደስታን ነው፤ ከእነሱ በመቀጠል ደግሞ የውድድር ዘመኑ ኮከብ ተጨዋች ጋቶች ፓኖምም ጥሩ የውድድር ጊዜን አሳልፏል።

ሊግ፦ ብዙዎች አንተን ብቸኝነትንና ዝምታን ይመርጣል ይሉሃል?

ተስፋዬ፦ ሂደቱ ነው እንደዛ ሊያስብላቸው የቻለው፤ ብቻዬን የምሆንበት ጊዜ አለ፤ ከሰዎች ጋር የምሆንበት ጊዜ አለ፤ ለምሳሌ ወደ ሜዳ ገብተህ ኳስ በምትጫወትበት ሰዓት ብቸኝነትን አትመርጥም፤ ከጓደኞችህ ጋር ታወራለህ፤ ከእዛ ውጪም ቢሆን ማውራት ባለብህ ነገር ላይ ከሰዎች ጋር ታወራለህ፤ ዝምታን የምትመርጥበትም ወቅት አለ እና የእኔን ባህሪያቶች የሚገልፁት የነገሮችሂደቶች ናቸው።

ሊግ፦ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም ወደ ብሔራዊ ቡድን ተመልሶ እና ተመርጦ ስለመጫወቱ ምን እያሰብክ ነው?

ተስፋዬ፦ ለብሔራዊ ቡድን መጫወትን የማይፈልግ ሰው ማንም የለም፤ ምርጫው ደግሞ የአሰልጣኙ እይታ ነው፤ ከአንተ የሚጠበቀው ደግሞ ሁሌም ቢሆን ራስህን በብቃት ማዘጋጀት መቻል ነውና የቀጣዩ ጊዜ ምርጫ ሲኖር ያንን የመመረጥ እድል እጠብቃለው።

ሊግ፦ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በተያያዘ አንድ ጥያቄን ላንሳልህ፤ ግብፅን ማሸነፍ ችለን ነበር፤ ሌሎች ጨዋታዎችን ደግሞ እየተጠባበቅን ነው የምንገኘው፤ ለአፍሪካ ዋንጫው የማለፍ ተስፋችን የቱን ያህል ይሆናል ብለህ ትጠብቃለህ? ስለ ቡድናችን ተጨዋቾች እና አቋምስ ምን ትላለህ?

ተስፋዬ፦ ለቡድናችን የተመረጡትን ተጨዋቾች በተመለከተ አሪፍ አሪፎች ናቸው፤ የታክቲካል ዲስፕሊን አጨዋወትን በደንብ አድርገው እየተገበሩ ያሉም ናቸው፤ በአቋም ደረጃም ቡድኑ ላይ ያለው ነገር በጣም ጥሩ ነው፤ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ለአፍሪካ ዋንጫው በማለፋችን ተስፋ ላይ እድላችንን በሚመለከት እንድናልፍ ምኞቴ ቢሆንም በፐርሰንት ደረጃ ይህን ያህል አልልህም።

ሊግ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአፍሪካ ዋንጫው ላይ ሲጫወት ከሌሎች ትላልቅ ሀገራት ጋርአነፃፅረህ ልዩነታችንን በተመለከተ ምን ትላለህ? ምን ብንሰራስ በታላቅ የእግር ኳስ ደረጃ ላይ መገኘትን እንችላለን?

ተስፋዬ፦ እኛ ኢትዮጵያኖች የራሳችን የሆነ ነገር አለን፤ ኳስ ፖሰስ ላይ ነው ከመጀመሪያው አንስቶ ተመስርተን መስራት ያለብን፤ ኳሊቲያችንን ማወቅ አለብን፤ ተጋፍተን መጫወት የለብንም፤ ከግብፅ ጋር ስንጫወት እንደታየነው ኳሱን መስርተን ስለተጫወትን ነው ያሸነፍናቸውና በእዚህ መልኩ ከተጫቀወትን ለትልቅ ደረጃ መድረስ እንችላለን።

ሊግ፦ እናጠቃል?

ተስፋዬ፦ በእኔ የእግር ኳስ ህይወት ውስጥ ብዙ ሰው አለ፤ የቱን ስም ጠርቼ የቱን እንደምጥልም አላውቅም፤ በመጀመሪያ ግን ፈጣሪዬን እዚህ ደረጃ ላይ ስላደረሰኝ አመሰግንዋለው፤ ከእዚህ በላይም እንዲያኖረኝ፤ ሲቀጥል ቤተሰቦቼን ወንድሞቼንና ጓደኞቼን ሁላችሁንም በእኔ ህይወት ውስጥ ያላችሁትን ፈጣሪ ያክብርልኝ አመሰግናችኋለሁ፡፡

 

spot_img
የቀደሙ ጽሁፎችሊግ ስፖርትን እንደተለመደው በቅዳሜ እትሟ ጠብቋት ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት 20ኛ ዓመቷን ልትይዝ እየተቃረበች ትገኛለች፤ ዘወትር ቅዳሜ ለንባብ የምትቀርበው ይህቺው ተወዳጇ ጋዜጣዎ ነገ እንደተለመደው በገበያ ላይ ስትውልም በሀገር ውስጥ እትሟ ከሀድያ ሆሳዕና ወደ መከላከያ የተዘዋወረው ተስፋዬ አለባቸው /ቆቦ/ ስላሳለፈው የኳስ ህይወት ወደ አዲሱ ክለቡ መከላከያ ስላደረገው ዝውውርና ሌሎችንም ጉዳዮች አንስተንለት ምላሾቹን ሰጥቶናል። ተስፋዬ ለሊግ ስፖርት ከሰጣቸው አስተያየቶች ውስጥም “ብዙ ውጣ ውረድ ባሳልፍም፤ ወደ ብቃቴ መመለሴ አስደስቶኛል” ይላል።
ቀጣይ ጽሁፎችሊግ ስፖርት፤ ሊግ ስፖርት፤ ሊግ ስፖርት ተወዳጇን ጋዜጣችን ነገ ቅዳሜ ጠብቋት ሊግ ስፖርት ጋዜጣ 20ኛ ዓመቷን ልትይዝ ተቃርባለች፤ ዘወትር ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ይህቺው ተወዳጇ ጋዜጣ ነገ እንደተለመደው ገበያ ላይ ስትውልም በሀገር ውስጥ እትሟ ለኢትዮጵያ ቡና በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከወልቂጤ ከተማ በመምጣት ፊርማውን ለማኖር የቻለው ጫላ ተሺታ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሰጥቷል።
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P