Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ችሎታዬን በማድነቅ የውስጥ እግሬን የሳመ ደጋፊ አጋጥሞኛል” ዳዊት ተፈራ(ኦዚል)/ሲዳማ ቡና/

በመሸሻ ወልዴ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን መቀላቀሉን እውን ካደረገበት ጊዜ አንስቶ በውድድሩ ተሳትፎው ላይ በጠንካራ ተፎካካሪነቱም ሆነ የደረጃ ተወዳዳሪም ሆኖ ለማሳለፍ የቻለው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በእዚህ ዓመት ላይ ዓምና ለጥቂት ያጣውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ዘንድሮ ለማንሳት እንደሚጫወት የቡድኑ ስኬታማና ወጣት ተጨዋች ዳዊት ተፈራ /ኦዚል/ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ተሳትፎው ቅዱስ ጊዮርጊስን፣ ፋሲል ከነማን፣ መቐለ 70 እንደርታን በመከተል በአራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የቡድኑ ተጨዋች ዳዊት ከእነዚህ ክለቦች መካከል ከሁለቱ ጋር ማለትም ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያደርጉት የሁለተኛው ዙር ጨዋታ በሜዳቸው ከመሆኑ አንፃር እና በመከላከሉም ላይ የነበረባቸውን የመጀመሪያው ዙር ክፍተቶች ሙሉ ለሙሉ የሚቀርፉበት ሁኔታም ሊኖር ስለሚችል የሊጉን ዋንጫ ሊያነሱም የሚችሉበት እድሉ እንደሚኖራቸውም ሀሳቡን ጨምሮ ገልጿል፡፡
የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቱን ተወልዶ ባደገበት የሻሸመኔ ከተማ ውስጥ በልጅነት ህይወቱ መጫወት የጀመረው ዳዊት በክለብ ደረጃ ለመከላከያ ተስፋ ቡድን በመቀጠል ደግሞ ለጅማ አባቡናና አሁን ላይ ደግሞ ለሲዳማ ቡና በመጫወት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለኢትዮጵያ ተተኪ ብሔራዊ ቡድንም ተመርጦ ተጫውቷል፡፡
በቤተሰቦቹ ውስጥ ከሚገኙት ሶስት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች መካከል በአሁን ሰዓት እግር ኳሱን በብቸኝነት እየተጫወተ የሚገኘው ዳዊት በቁመቱ ሜትር ከ65 ሲረዝም ኪሎው ደግሞው አሁን ባይመዘንም ለብዙ ጊዜያት ከ45 ኪሎ አንስቶ እስከ 55 ኪሎ ድረስ እግር ኳስን መጫወቱን ይናገራል፤ ከዚህ ተጨዋች ጋር በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያም ቆይታ አድርገን ምላሹን ሰጥቶናል፡፡


ሊግ፡- የሲዳማ ቡና የአንደኛው ዙር ተሳትፎው ምን ይመስላል? የነበራችሁ ጠንካራና ደካማ ጎንስ?
ዳዊት፡- የፕሪምየር ሊጉ ላይ በመጀመሪያው ዙር የነበረን ተሳትፎ ከሞላ ጎደል ጥሩ የሚባል ነው፤ በእዚሁም ጊዜ ቆይታችን በድክመት ደረጃ የምጠቅሠው ነገር ቢኖር ይኸው ዙር ሊጠናቀቅ ሶስትና አራት ጨዋታዎች እስከቀሩበት ጊዜ ድረስ በመከላከሉ ላይ የተቸገርንበት አጋጣሚዎች የነበሩበት ሲሆን በጠንካራነቱ የምገልፀው ደግሞ የፊት መስመሩ ላይ ስናጠቃና የመሃል ክፍሉም ላይ ኳስን ስንጫወትና ከአጥቂው ክፍሉም ጋር ተናበን ስንንቀሳቀስ ያለን ጥምረት በርካታ ጎሎችን እስክናስቆጥር ያደረሰን በመሆኑ ይሄ በጥሩ መልኩ የሚገለፅ ነው፡፡ በአጠቃላይ በእዚህ ዙር የነበረን አቋም ሲታይም ቡድናችን የያዘው ጠንካራ ጎን የበለጠ ስለሚያመዝን የቀጣዩ ዙር ላይ ብዙ ተጠናክረንና ባለፉት ባሸነፍንባቸውም የመጨረሻዎቹ ሶስት ጨዋታዎች ላይ የነበረንን ጥሩ አቋም የበለጠ አሳድገን ለሁለተኛው ዙር ላይ በስኬታማነት እንደምንቀርብ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- እንደሲዳማ ቡና የፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ተሳትፎው ያስመዘገባችሁት ውጤትም ሆነ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴያችሁ ለእናንተ በቂ ነው ማለት ይቻላል?
ዳዊት፡- በጣም በተጋነነ መልኩ ውጤታችን በቂ ነው ወይንም ደግሞ ጥሩ ነው ለማለት ባይቻለንም በአብዛኛው ጨዋታዎቻችን በእንቅሰቃሴው ደረጃ ቡድናችንን እንደተመለከትኩት ደካማ የሚባልም አልነበረም፤ በመከላከሉ ላይ የነበሩብን ክፍተቶቻችንም ናቸው ቢያንስም ሆነ ቢበዛ በሊጉ የውድድር ተሳትፎአችን ላይ ጠብቀን ለነበረው የሁለተኛነት ደረጃና የመሪነትም ስፍራ ላይ እንዳንቀመጥ ያደረገን፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ሲጠናቀቅ ለአንተ ከተቃራኒ ቡድን ምርጡ ተጨዋች እና ምርጡ ቡድን ማን ነው?
ዳዊት፡- ለሲዳማ ቡና ተሰልፌ በተጫወትኳቸው በርካታ ጨዋታዎች ለእኔ የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ሆኖ በምርጥ ብቃቱ ላይ ያገኘሁት ተጨዋች ማንም የለም፤ እንደ ቡድን ለመናገር ከሆነ ግን አዳማ ከተማ የእኛ ሜዳም ላይ ሲጫወቱ በደንብ ተመልክቼያቸው እና ስለ እነሱም አቋም ጥሩ መሆን የሰማሁት ነገር ስላለ እነሱን ነው በምርጥነት የምገልፀው፡፡
ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ ከሲዳማ ቡና ተጨዋቾችስ የትኛው ተጨዋች በጥሩ ብቃቱ ይገለፃል?
ዳዊት፡- የእኛን ቡድን ተጨዋቾች ነጥሎ መጥራቱ ይከብደኛል፤ ብዙዎቹ ተጨዋቾች ጥሩ ነበሩ ብል ይቀለኛል፡፡
ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ ላይ አዲስ ፊት ሆነውስ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳዩ ካሉ ተጨዋቾች መካከል?
ዳዊት፡- ለፋሲል ከነማ በመስመር ስፍራ ላይ የሚጫወተው ተጨዋች እና ከእኛ ቡድን ውስጥ ደግሞ ዓምና እየተቀየረ የሚገባው ዘንድሮ ደግሞ ለቡድናችን በቋሚ ተሰላፊነት በመጫወት ቡድናችንን እየጠቀመ የሚገኘው አጥቂያችን ይገዙ ቦጋለን በጥሩ ተጨዋችነቱ ተመልክቼዋለሁ፤ የቡድናችንን ይኸው ተጨዋችም በርታ ልለው እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾች አንተን በጣም የፈተነህ እና ያስቸገረህ ተጨዋች ማን ነው?
ዳዊት፡- የመቐለ 70 እንደርታው አሚን ነስሩ፤ ያን ዕለት ከእነሡ ጋር በሜዳችንና በደጋፊዎቻችን ፊት ስንጫወትና ሲያሸንፉን በስኪመር ስፍራ ላይ ተጫውቶ ነበርና ማርክ አድርጎኝ በምፈልገው ደረጃ ጥሩ እንዳልጫወት ስላስቸገረኝ እሱን ነው የምጠቅሰው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙርን በምን መልኩ ትገልፀዋለህ?
ዳዊት፡- የፕሪምየር ሊጉን የመጀመሪያው ዙር እንደ አጠቃላይ ፉክክር ሳየው ከአምናው ትንሽ ደከም ቢልብኝም ውድድሩ ሊጠናቀቅ በተቃረበባቸው ጨዋታዎች ላይ ደግሞ ጥሩ መሻሻልን አሳይቶ በመምጣቱ አሁን ላይ የሁለተኛው ዙር ውድድሩ እንደ አለፈው ዓመት ጥሩ ፉክክር እንደተደረገበት የውድድር ዓመት ሊሆን የሚቃረብ ይመስለኛል፡፡
ሊግ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን መምራት የእነ ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ በተከታታይ ደረጃ ላይ መገኘት በሊጉ ልታስመዘግቡ ካሰባችሁት ውጤት አንፃር ለእናንተ ስጋት ይሆኑባቹኋል?
ዳዊት፡- የእነሡ በእዛ ደረጃ ላይ መገኘት ፈፅሞ ስጋት ይሆንብናል ብዬ አላስብም፤ አሁን በአንደኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው፤ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚከተሉት ደግሞ ፋሲል ከነማና መቐለ ናቸው፤ ይሄ በመሆኑም የሁለተኛው ዙር ላይ ክለባችን ከመቐለ 70 እንደርታ ውጪ ቅዱስ ጊዮርጊስንም ሆነ ፋሲል ከነማን የሚያገኛቸው በሜዳው ላይ ስለሆነና እነሱንም የሚያሸንፍበት ሰፊ እድሉ ስላለው ምንም የሚያሰጋው ነገር የለም፡፡
ሊግ፡- ሲዳማ ቡናን ግለፀው ብትባል ምን አይነት ቡድን ነው?
ዳዊት፡- ሲዳማ ቡና በሊጉ ደስ የሚልና የሚወደድ አይነት ቡድን ነው፤ ብዙ ሲኒየር ተጨዋቾች የሌሉበት እና በወጣት የተገነባም በመሆኑ ክለቡ የሚጓዝበት መንገድ ይበል የሚያሰኝ ነው፤ ከዛ ውጪ ሁሉም ተጨዋቾችም በከፍተኛ ወኔና ፍላጎትም ኳስን የሚጫወቱበት መንገድም ስላለ ቡድኑ እንከን የማይወጣለት እና ምርጥ ቡድንም ነው ብዬ አስባለው፡፡
ሊግ፡- የሲዳማ ቡናው አሠልጣኝ ዘርአይ ሙሉ እንዴት እና በምን መልኩ የሚገለፅ ባለሙያ ነው?
ዳዊት፡- አሠልጣኝ ዘርአይ ሙሉን በሚመለከት ደስ የሚለው ነገር እኛ ልምድ ያለን ተጨዋቾች እንዳልሆነው ሁሉ እሡም ገና ጀማሪና በወደፊቱም የሙያው ቆይታው ላይ ራሱን ለማሳደግ ብቅ ያለ እና ታታሪም የሆነ አሰልጣኝ በመሆኑ በልዩ መልኩ የምንገልፀው እና ሁሌም በጥሩ ጎኑ የምናነሳው አሰልጣኝ ነው፤ እሱ እኛን ተጨዋቾቹንና ሰዎችን የሚረዳበት አካሄድ በጣም የሚገርም ነው፤ እንደ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን እንደወንድም ነው የሚቀርበን እና ነገሮችንም የሚያወያየን፤ ለሠውም ጥሩ የሚያስብ መልካም የሚባልም አሠልጣኝ ነው፤ ከዚህ አኳያ በክለቡ ቆይታውም እሱ ከእኛ ጋር እንደዚሁም ደግሞ እኛም ከእሱ ጋር ደስተኛ ሆነን እየሠራን ነውና እንደጀማሪ አሰልጣኝነቱ አሁን እየሰራ ያለው በጎ ስራ ሊያስደንቀውም የሚገባ ምርጥ አሰልጣኝ ነው፡፡
ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር ያስደሰታችሁ እና ያስቆጫችሁ ጨዋታ የትኛው ነው?
ዳዊት፡- ለእኛ አስደሳች እና ጣፋጭ የሆነልን ግጥሚያ ወልቂጤ ከተማን ድል ያደረግንበት ነው፤ ምክንያቱም ያ ጨዋታ ከሜዳችን ውጪ ያደረግነውና የእነሡ ሜዳ ደግሞ እንደ እኛ ኳስን ተቆጣጥሮ ለሚጫወት ቡድን ለእንቅስቃሴው አስቸጋሪ ሆኖበት ግጥሚያውን በአሸናፊነት ሊወጣው በመቻሉ ነው፤ ለክለባችን አስቆጪውና የተከፋንበት ጨዋታ ደግሞ በሜዳችን ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያከናወነውና ነጥብ የጣልንበትን ጨዋታ ነው፤ ይሄን ጨዋታ በአሳዛኝነቱ መቼም ቢሆን ከውስጣችንም አይጠፋም፡፡ ይህንን ልልህ የቻልኩት ድሬዳዎች ያን እለት ሲጫወቱ የፕሪምየር ሊግ ቡድን ስለማይመስሉና የሚያገኙትን ኳስ ሁሉ ወዳገኙበት ቦታ ሁሉ ይጠልዙት ስለነበር ነው፡፡ ከዛ ውጪ እኛም በመጨረሻ ሠአት ላይ ያገኘነውን የፍፁም ቅጣት ምት ከመሳታችን ባሻገር በጨዋታው ላይ በርካታ የግብ ሙከራዎችንም አድርገንና በእነሱም ተመልሶብን አንዷን እንኳን ለግብ ልናበቃት አለመቻላችንና እነሱም ባላሰብንበት ሰዓት በመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ግብ ያስቆጠሩብን ሁኔታ ስለነበር ያን ወደ ኋላ ተመልሼ ሳይ ያስቆጨኛል፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሜዳ እና ከተመልካቾች ድባብ አንፃር ወደ የትኛዎቹ ስታድየሞች መጥተህ ስትጫወት በጣም ደስ ይልሃል?
ዳዊት፡- በሜዳዎች ደረጃ ሃዋሳ ስቴድየም፣ ፋሲል ስቴድየም፣ ባህር ዳር ስቴድየም፣ መቀሌ ስቴድየምና የአዳማ ስቴድየም ላይ መጥተን ስንጫወት በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ከድባብ አኳያ ደግሞ ወደ ሸገር መጥተህ ከኢትዮጵያ ቡናና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መጥተህ የምታደርጋቸው ጨዋታዎች የተለየ ስሜት እንዲሰማህ ያደርግሃል፡፡ ሸገር ላይ ከሁለቱ ቡድኖች ጋር ስትጫወት አሸንፍክም ተሸነፍክም ጥሩ ከተጫወትክ ይደግፉሃል፡፡ እነሡ ያን ለማድረግም ምንም አይነት ችግር የለባቸውም፤ ጥሩ ጎንህን ይነግሩሃል፤ ጥሩ ካልሆንክም ደካማነትን ያስቀምጡልሃልና ኳስን የሚያውቁ ደጋፊ ስለሆኑ በጣምም ደስ ይሉሃል፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ተጫውተህ ባሳለፍከው የእስካሁን ህይወትህ ደስተኛ ነህ?
ዳዊት፡- በአብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቱ ቆይታዬ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባም ለመጀመሪያ ጊዜ መጥቼ ለመከላከያ ተስፋ ቡድንም መጫወቴ ነው በብዙ ነገሮች ጠቅሞኝ ለደስታዬም የጥርጊያ መንገዶቹ ሊከፈቱልኝ የቻሉት፤ ለመከላከያ ስጫወት ቡድናችንን የአዲስ አበባ የተስፋ ቡድኖች ሻምፒዮና አድርገን ነው ወደ ዋናው ቡድን ያደግኩት፡፡ ያን ጊዜ ታድያ የቡድኑ አሠልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ በክለቡ ብቆይ ተቀይሬ እገባ እንደሆነ እንጂ በቋሚነት የመጫወት እድሉ ክለቡ ከያዛቸው ልምድ ያላቸውና ጥሩም ተጨዋቾች አንፃር አናሳ ሊሆን እንደሚችል ስለነገረኝ እና እኔ ደግሞ ተሠልፌ መጫወትን ስለፈለግኩና መከላከያም ሊለቀኝ በመቻሉ ወደ ጅማ አባቡና ክለብ አምርቼ እዛ ጥሩ የሚባል ጊዜን አሳለፍኩ፡፡ በመጀመሪያው አመት የውድድር ቆይታዬም ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማሳልፍ ከጫፍ ደርሰንና እርግጠኞችም ሆነን በድሬዳዋ ከተማ በመሸነፍ ሳንገባ ስንቀር በጣም ተቆጭቼና ከፍቶኝ ነበር፤ ያኔ ቡድኑን ወደ ላይ ለማሳለፍ ባንችልም በቀጣዩ አመት ግን ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲገባ ስላደረግኩት ደስተኛ እና ጥሩ ጊዜን ነው ያሳለፍኩት፡፡
ሊግ፡- መከላከያ አንተን ያሳደገህ ቡድን ነው፤ በዋናው ቡድን ደረጃ ዘልቀህ አለመጫወትህ አያስቆጭህም?
ዳዊት፡- ያስቆጨኛል እንጂ፤ ለመከላከያ መጫወትን እፈልግ ነበር፤ አለመጫወቴም ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል፡፡ ያም ሆኖ ግን በጊዜው በቡድኑ ውስጥ የነበረው ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ ለእኔ በቋሚነት ተሠልፎ ለመጫወት ስላላስቻለኝ ያ እድል አምልጦኛል፤ ቢሆንም ግን መከላከያን ለአንድ ቀንም ቢሆን ወደፊት ባገለግላቸው በጣም ደስ ይለኛል፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ችሎታህ የት ደረጃ የመድረስ ራዕይ አለህ? በችሎታህ ጥሩ የቴክኒክ ብቃት እንዳለህ ማሳየት ችለሃል፤ ይሄ ብቃት እንዴት መጣ?
ዳዊት፡- የእግር ኳስ ችሎታዬን ከዚህ በኋላ በሚኖረኝ የተጨዋችነት ቆይታዬ በጣም እያሳደግኩት የመሄድና ወደፊት ደግሞ ወደተሻሉ ሌሎች ቡድኖችም በመግባት ለታላቅ ደረጃም የመድረስ ከፍተኛ እልምና ፍላጎት አለኝ፡፡ የእኔን የኳስ ብቃት በተመለከተ አሁን ላለኝ ችሎታ ልበቃ የቻልኩት ዝም ብዬ አይደለም በክረምት ወራት ወደ ሀገሬ ሻሸመኔ በሄድኩ ቁጥር የራሴን ልምምድ ጠንክሬ እሠራለሁ፤ የውጪ ኳሶችንም በደንብ እመለከታለሁ፡፡ ተጫውቼ ያሳለፍኳቸውን የራሴንም ጨዋታዎች መልሼ በማየትም ችሎታዬን እገመግማለሁ፡፡ የውጪ ኳሶችንም በዲኤስቲቪ ሳይ ሁሌም በትኩረት የምመለከተው በራሴ ቦታ ላይ የሚጫወቱ ተጨዋቾችንም ነውና እኔስ ለምን እንደእነሡ አላደርግም በሚልም ለራሴም እለማመዳለሁና በዚሁ ነው ችሎታዬን እያሻሻልኩ ያለሁት፡፡
ሊግ፡- ከባህር ማዶ ክለቦች የአርሠናል ደጋፊ ነህ?
ዳዊት፡- አዎን፤ ቡድኑንም በጣም ነው የምወደው፡፡
ሊግ፡- ኦዚል የተባልከው አርሠናልን በመደገፍህ ነው?
ዳዊት፡- ከዛ አኳያ እንኳን አይደለም፤ የጅማ አባቡና ተጨዋች እያለሁ ደጋፊው ነው የእኔን አጨዋወት በማድነቅና ግራኝም ስለሆንኩ እንቅስቃሴዬን አይተው ኦዚልን ነው የምትመስለው በማለት ስሙን ያወጡልኝ፡፡
ሊግ፡- አርሰናል ውጤታማ መሆን አልቻለም፤ ምን ትላለህ?
ዳዊት፡- አዎን፤ አሁን ላይ በእዚያ የታደለ አይደለም፡፡ ያም ሆኖ ግን አሠልጣኙ አርቴታ ከጋርድዮላ ጋር የሠራ እንደመሆኑ የሚቀጥለው አመት ላይ ጥሩ ቡድንን ይዞ ሰርቶ የሚመጣ ይመስለኛል፡፡
ሊግ፡- ከኳስ ውጪ የእረፍት ጊዜህን የት ነው የምታሳልፈው?
ዳዊት፡- ብዙ ጊዜ በቤት ወይንም ደግሞ በካፌ ውስጥ ነው የማሳልፈው፤ ከዛ ውጪ ደግሞ የውጪ ኳስን በመመልከትና ፕሌስቴሽንም በመጫወት አሳልፋለሁ፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ለአንተ ሞዴልህ ወይንም ደግሞ ተምሳሌትህ ተጨዋች ማን ነው?
ዳዊት፡- ለእኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጫወት በደንብ ባላየውም ሽመልስ በቀለን የብሄራዊ ቡድን ላይ ሳየው በደንብ ነው ያደነቅኩት፤ ከእሱ ውጪም ዳዊት እስጢፋኖስ እና ፍሬው ሰለሞንም /ጣቁሩን/ አደንቃቸዋለውና እነሱ ናቸው ተምሳሌቶቼ፡፡
ሊግ፡- በዓለም ላይስ በቀዳሚነት ደረጃ በጣም የምታደንቀው ተጨዋች?
ዳዊት፡- ለእኔ ከሊዮኔል ሜሲ ውጪ ማድነቅ በጣም ከባድ ቢሆንብኝም እንደ እነ ሮዝኪይ አይነት ተጨዋቾችንም ብቃታቸው ስለሚያስደስተኝ ለእነሱም በቀጣይነት ስፍራው አድናቆት አለኝ፡፡
ሊግ፡- ለሲዳማ ቡና እንደ አምናው ዘንድሮ የሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ሆኖ መፈፀም ይስማማዋል?
ዳዊት፡- እኔ በዛ ደረጃ አላስብም፤ የእዚህ አመት ላይ አሁን ጥቃቅን ችግራችን መከላከሉ ላይ ነው፤ ለእዛም ዜጋ ተጨዋቾች ወደ ቡድናችን መጥተው ሙከራ እያደረጉ በመሆኑ እነሱ ጥሩ ሆነውልን ከተገኙ እና አሁን ላይ ደግሞ በቦታው ላይ የሚጫወቱት ተጨዋቾች መሻሻልን እያሳዩ በመሆኑ ቡድናችን ከአምናው የተሻለ የሚባል ውጤትን ያመጣል፤ ይሄ ውጤትም እኛ እስከመጨረሻው ጨዋታችን ድረስ ጥሩ እንሁን እንጂ የሊጉን ዋንጫ የማናመጣበት ምንም አይነት ምክንያት እንደማይኖር ፈፅሞ አልጠራጠርም፡፡
ሊግ፡- ለሲዳማ ቡና ስንት ጎሎችን አስቆጠርክ?
ዳዊት፡- 3 ግቦች፡፡
ሊግ፡- የጎሉ ቁጥር በቂ ነው?
ዳዊት፡- ብዙ ጊዜ ለጓደኞቼ የግብ ኳሶችን በማቀበል ስለምጠመድ ነው እንጂ ያስቆጠርኳቸው ግቦች ለእኔ በቂ ናቸው ብዬ ፈፅሞ አላስብም፡፡ የሁለተኛው ዙር ላይ ግን ከወዲሁ ከመጀመሪያው ዙር በተሻለ ስንት ጎሎችን ለቡድኔ አስቆጥራለሁ ብዬ ነው ስራዬን አቅጄ የጀመርኩት፡፡
ሊግ፡- ቤተሰቦችህ እንዴት ይገለፃሉ?
ዳዊት፡- ቤተሠቦቼ ለእኔ ሁሉም ነገሬ ናቸው፤ ምክንያቱም መጀመሪያ ላይ ትምህርቴን እንድማር ይፈልጉ የነበሩ ቢሆንም ኳስን መጫወት ስጀምርም ጠንክረህ ስራም ይሉኝ ስለነበር ነው የእነሱ ድጋፍ ታክሎበትም ለዛሬው ደረጃ ላይ የደረስኩትና ለእነሱ ከፍተኛ ምስጋና አለኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮስ?
ዳዊት፡- የእግር ኳስን ስጫወትም ሆነ ሳልጫወት በፊት የእንጨት ስራ ባለሙያ ነበርኩ፤ በተለይ ደግሞ ብዙ ሶፋዎችን እሰራም ነበር፤ በእዚህ ሙያም ላይ ሆኜ ከጓደኛዬ ጋር በመሆንም ኮንትራት እየተቀበልኩ እሰራም ነበር፤ ከእሱ ውጪም ቀደም ሲል በኦሮሚያ የትምህርት ቤት ደረጃም ከራሴ ወንድም ጋር አብረን ኳስ እየተጫወትን ከወንድሜም ጋር ስራውን እንሰራ ነበርና የእዚሁ ሙያ ባለቤትም ነኝ፤ ወንድሜ አሁንም ይሄን ስራ እየሰራ ነው፡፡
ሊግ፡- በተደጋጋሚ ጊዜ የእግር ኳስ ሜዳው ላይ የያዝከውን አነስተኛ ኪሎና ቁመናህን ተመልክተው ኳስን በጥሩ ሁኔታ ስትጫወት ብዙዎች ያደንቁሃል፤ በእዚህ ደረጃ ከመጫወትህ አንፃር ያጋጠመህ የተለየ ነገር አለ?
ዳዊት፡- አዎን፤ የእኔን ችሎታ አስመልክቶም ለብዙዎችም ጥያቄ ነው የሚሆንባቸው፡፡ አንዳንዶች የእኔን ተክለ ሰውነት እና ቁመናን ከውጪ ያዩና ሜዳ ስገባና በማሳየውም እንቅሰቃሴ ሲያዩኝ በጣም ነው የሚገረሙት፡፡ በአንድ ወቅትም አስታውሳለሁ ለጅማ አባቡና ቡድን ሱፐር ሊግ ላይ እያለን ስንጫወት አንድ ትልቅ ሰውዬና የቡድናችን ደጋፊ ናቸው ጨዋታው አልቆ ከሜዳ ስንወጣ ጫማዬን አውልቄ በሸበጥ እየሄድኩ ሳለ ነበር ሰውዬው ወደ እኔ በመጠጋት ካልሲዬን አውልቀው የውስጥ እግሬን ሲስሙት በጣም ነው የተገረምኩት፤ እሳቸው እግሬን ከሳሙት በኋላም እንደአንተ አይነት ተጨዋች አይቼም አላውቅም የትም መጫወትም ትችላለህ ብለውኝም ነው አድናቆት የቸሩኝ፤ ከዛ ውጪም አሁን ድረስ አንተ በእዚህ ኪሎ መጫወትህ ይገርማል በማለትም የእኔን ኪሎ የሚመኙም አሉና ለእኔ ሁሉም ነገር በዚህ በኩል ጥሩ እየሆነልኝ ነው፡፡
ሊግ፡- ከአንተ መነሻነት በአነስተኛ ኪሎ ወደፊት ወደ እግር ኳሱ ለሚመጡ ተጨዋቾች ምንን ትመክራለህ?
ዳዊት፡- የምመክራቸው ነገርማ አለ፤ የእግር ኳስን በሰፈር ደረጃ ላይ በምጫወትበት ሰዓት የሻሸመኔ ከተማ ክለብ የብሔራዊ ሊግ ላይ ይጫወት ነበር ያኔም አንድ አንድ ልጆች ወደ እኔ ይመጡና ችሎታዬን በማየት የኳስ አቅምህ ከባድ ነው አንተን አንድ ትልቅ አሰልጣኝ መጥቶ ቢያይህ የግጭት ጨዋታ ስለሚበዛበት ሱፐር ሊግ አይደለም የፕሪምየር ሊግ ላይ ነው የምትጫወተው ይሉኝ ነበርና ወደ መከላከያ ተስፋ ቡድን ካመራው በኋላ የእኔ መገኛ የነበረው ግን በሱፐር ሊግ ላይ መጫወት ነውና በእዛ ደረጃ መምጣቴ ለእኔ ጥሩ ሆንልኛል፤ ፕሪምየር ሊጉም ለእኔ ከሱፐር ሊጉ አኳያ በጣምም ቀሎኛል፤ ከዚህ በመነሳት እንደ እኔ ላሉት በኪሎ አነስተኛ ለሆኑ ተጨዋቾች እኔ ልመክር የምፈልገው፤ እኔ የደረስኩበት ደረጃ ለመድረስ ምንም ችግር የለውም፤ ዋናው ነገር ሁሉንም ነገር በትህግስት ጠብቁ፤ ትህግስተኛ ካልሆንም ኳስ ተጨዋች መሆን አንችልም፤ እኔም ትህግስተኛ ስለሆንኩ ነው ለዚህ ደረጃ የደረስኩትም ነው የምላቸው፤ አንዳንዶቹ እንደውም በጣም አጭር ነህ ሰውነትም የለህም፤ ኳስ ግን በጣም ትችላለህ እንዴት ብለን እንደአንተ እንሁን የሚሉኝም የሰፈር ልጆችም ነበሩና ትህግስት ወሳኙ ነገር ነው ልላቸው ነው የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….?
ዳዊት፡- የእግር ኳስን መጫወት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ ለእኔ እዚህ ደረጃ መድረስ ትልቁን አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ሁሉ አመሰግናለው፤ የመጀመሪያውም ተመስጋኝ ፈጣሪዬ ነው፤ ከዛም ቤተሰቦቼ በመቀጠል ደግሞ በልጅነቴ ሻሸመኔ ሳለው ለውድድር ይዞኝ ይሄድ የነበረው አሰልጣኜ መስፍን በመከላከያ ቡድን ውስጥም በተስፋ ቡድን ደረጃ ጥሩ ጊዜን ካሳለፍኩ በኋላ ለዋናው ቡድን የመጫወት እድሌ አነስተኛ መሆኑን ሲነግረኝ እኔ ደግሞ መጫወትን ስለምፈልግ ውል ያለኝ ተጨዋች እንደመሆኔ በገንዘብ ደረጃ ብዙም ባልጠቀመም የውል ማፍረሻ ብር 500 ሺ ከፍዬ ከቡድኑ እንድለቅ ላደረገኝ አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌና አሁን ለምጫወትበት የሲዳማ ቡና አጠቃላይ አባላቶች ከፍተኛ ምስጋና አለኝ፡፡ ሌላው ማስተላለፍ የምፈልገው መልህክት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተመርጦ የመጫወት ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ፤ ለእዛም ጠንክሬ እሰራለውኝ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P