Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

አማኑኤል ተርፉ /ቅ/ጊዮርጊስ/ “የቅ/ጊዮርጊስ ተጨዋች ሆነህ ውጤት ማጣት በጣም ያማል”

“ፕሪምየር ሊጉ እንደበፊቱ ጊዜ ቀላል አይደለም፤ በጣም የለፋና የደከመ ቡድን  ዋንጫውን ያነሳል”

ለቅ/ጊዮርጊስ  የመሰለፍ ዕድሎችን ባገኘባቸው ጨዋታዎች  ከተተኪው ቡድን  አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ጥሩ ብቃት እንዳለው  ለማሳየት ችሏል፤ በዚህ ብቃቱሞ ለኢትዮጵያ የታዳጊና የወጣት ብሄራዊ ቡድኖች ተመርጦም ተጫውቷል።

በቤንሻንጉል በመወለድ ከሶስት ዓመቱ ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ዓመቱ ድረስ ወላጅ አባቱ ለስራ በሚገኙበት ኡጋንዳ ሀገር እድገቱን ያደረገው እና የቅ/ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድንን በታዳጊነት ዕድሜው ሊቀላቀል የቻለው አማኑሄል ተርፉ  ቡድናቸው በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ ሻምፒዮና ውድድር ባስመዘገበው ውጤት በጣም ማዘኑንና መቆጨቱን በመግለፅ ይህ ውጤት  ክለባቸውን  ቅዱስ ጊዮርጊስን በፍፁም የማይመጥነው እንደሆነም ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል።

የቅ/ጊዮርጊሱ አማኑሄል ተርፉ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ ውድድር እንደ በፊቱ ቀላል እንዳልሆነና በጣም የለፋና የደከመ ቡድን ብቻ የሊጉን ዋንጫ እንደሚያነሳም ሀሳቡን ጨምሮ በመግለፅ ቡድናቸው ለመጪው  የውድድር ዘመን  ከወዲሁ ከፍተኛ ትኩረትን ሰጥቶ በመምጣት የቡድኑን የቀድሞ ስምና ዝና መመለስ እንዳለባቸውም እየተናገረ ይገኛል።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ ውድድር ለቅ/ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን የመሰለፍ እድልን አግኝቶና ተስፋ ሰጪ የሚባልን እንቅስቃሴም አሳይቶ በመሀል ጉዳትን ካስተናገደና ከሜዳ ከራቀ በኋላ ተመልሶ በመዳን ክለቡን ሲያገለግል የነበረውንና ለኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ22 ዓመት በታች ለሆናቸው ተተኪ ብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ የቻለውን ይህን ወጣት ተጨዋች ሊግ ስፖርት  በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግራው ለሁሉም በቂ ምላሽን ሰጥቷታል።

ሊግ፦ ለኢትዮጵያ ታዳጊና ወጣት ቡድን ከዚህ በፊት አሁን ላይ ደግሞ ለተተኪው ብሄራዊ ቡድን ለመመረጥ ቻልክ፤ ስሜቱ እንዴት ነው?

አማኑሄል፦ በሁለቱም ጊዜያቶች ውስጥ እነዚህን የመመረጥ እድሎችን ሳገኝ ፈፅሞ ያልጠበቅካቸው ስለነበሩ በጣም ነው ደስ ያለኝ። ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የወጣት ቡድን ውስጥ ስመረጥ ከክለቤ ጋር ዝግጅት ላይ ሆኜ ነበር ባላሰብኩበት ሁኔታ የተመረጥኩት። ከዛ በፊት ተመስገንና ደረጄ ተስፋዬ /አንገቴ/ በያዙት የታዳጊ ቡድን ውስጥ ለካ ጥሩ ተንቀሳቅሼም ነበርና ያ አቋሜ ጭምርም ነበር ሊያስመርጠኝ የቻለው። በአሁን ሰዓት ላይ ደግሞ ብዙ ሲኒየር ተጨዋቾች ባሉበት ቡድን ውስጥ ሀገሬን ወክዬ ልጫወትበት ወደምችልበት ደረጃ ለተስፋው ቡድን ልመረጥ መቻሌ ትልቅ ዕድል እንዳገኘው ነው የምቆጥረውና የራሴን አቅምና ብቃት ለማሳየት  ብሎም ደግሞ ከዚህ በላይም ከፍ ወዳለ ስፍራም ለመጓዝ እንድችል መለኪያም የሚሆነኝ ነውና ለቡድኑ ለመመረጥ በመቻሌ ለየት ያለ የደስታ ስሜት ነው እየተሰማኝ ያለው።

ሊግ፦ ለቅ/ጊዮርጊስ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን አሳይተህ ጉዳትን አስተናግደህ ነበር፤ ተመልሰህ ድነህ መጥተህ ደግሞ ቡድንህን ለማገልገል ችለሃል። ስለዚያን ጊዜ ስሜቶችህ ምን ትላለህ?

አማኑሄል፦ ጉዳትን ማንም ተጨዋች ፈፅሞ አይፈልገውም፤  በውድድር ዘመኑ ወጥ የሆነ አቋሜን  እስከመጨረሻው ጨዋታዎች ድረስ በማሳየት ክለቤን በሚገባ እጠቅመዋለው በምልበት ሰዓት ላይ ባልጠበቅኩት ሁኔታ ይህንን ጉዳት ሳስተናግድ ስችልና ከዳንኩ በኋላም ለቡድኔ ለመሰለፍ ሳልችል ስቀር በጣም ነው የተቆጨሁት። ያም ሆኖ ግን በእንደዛን በነበርኩበት ሁኔታ ላይ የቡድኔ ተጨዋቾች ስሜቴን በመመልከት ያበረታቱኝና አይዞህም ይሉኝ ስለነበር ያ ለእኔ ትልቁ መፅናኛ ሆኖኛል።

ሊግ፦ ከጉዳትህ ድነህ ስትመጣ ተጠባባቂ ነበርክ፤ ውድድሩ ሊያልቅ ሲል ደግሞ በቋሚ ተሰላፊነት ተጫውተህ ጎልም ማስቆጠር ቻልክ። በዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

አማኑሄል፦ በእግር ኳስ ጨዋታ ማንም ተጨዋች የራሱን ብቃት አውጥቶ ማሳየት ስለሚፈልግ መቀመጥን አይፈልግም፤ እኔም አልፈልግም። ሆኖም ግን ጉዳትን አስተናግጄና ከህመሜም ድኜና አገግሜ በመጣሁበት ሰዓት ላይ በእኔ ስፍራ ላይ ለመጫወት የቻሉት ተጨዋቾች በቦታው ላይ በጥሩ ፐርፎርማንስ ላይ ይገኙ ስለነበሩ ያን ሰብሮ ለመግባት አስቸጋሪ ነበር የሆነብኝ በኋላ ላይ ግን የውድድር ዘመኑ ሊጠናቀቅ ሁለት ግጥሚያዎች በቀሩበት ሰዓት ላይ  ከሰባትና ስምንት ሳምንታት ግጥሚያዎች በኋላ ዳግም ወደ ሜዳ በመመለስ በአዳማ ከተማ ክለብ ላይ ጎል እስከማስቆጠር ደረጃም ላይ ደርሼ ነበርና ወደዚሁ ሁኔታ በመመለሴ በጣም ነው ደስ ያለኝ።

ሊግ፦ አዳማ ከተማን ስታሸንፉ ጎል ያስቆጠርከው በግንባርህ በመግጨት ነው፤ እንደዚህ አይነት የማግባት ሙከራን ከዚህ ቀደም በነበረ ጨዋታም ላይ ለማሳየት ችለሃል። በዚህ የተካንክ ነህ?

አማኑሄል፦ የእግር ኳስን ከበፊት አንስቶ ስጫወት የቴስታ ኳስን መግጨት በጣም እወዳለው። ሳልፈራም ነው የግብ አጋጣሚዎችን ለመጠቀምም ስል ኳሷን ለመምታትም የምንደረደረውና ይሄ ጥረቴ ወደፊትም የሚቀጥል ነው።

ሊግ፦ የበርካታ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮና ክለባችሁ ዘንድሮም ለተከታታይ አራት ዓመታት ዋንጫውን አጥቷል፤ በዚህ ምን አይነት ስሜት እየተሰማህ ይገኛል?

አማኑሄል፦ እንዲህ ያለ የውጤት ማጣት በእንደዚህ ባለ ታላቅና ድልን በተደጋጋሚ ጊዜ በለመደ ቡድን ውስጥ ሲያጋጥም ከፍተኛ የሚደብር አይነት ስሜት ነው  የሚፈጠርብህ።  የውጤት ማጣት  አይደለም  በእኛ ለወራጅነት በሚጫወት ክለብ ውስጥ ራሱ አይፈለግም። ተቀባይነትንም አታገኝም። ለታሪክ ልታስቀምጠው በምትችለው መልኩ ስታሸንፍ ብቻም ነው ተቀባይነትን የምታገኘውና  ይሄን የውጤት ማጣት በመጪው የውድድር ዘመን አስተካክለነው ወደምንታወቅበት የስኬታማነት ዘመን እንመለሳለን።

ሊግ፦ ቅዱስ ጊዮርጊስን በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ምን ጉዳዮች ዘንድሮ ውጤት አሳጣው?

አማኑሄል፦ ይህ ጥያቄ ይለፈኝ።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ዋንጫውን በመጪው ጊዜ ለማንሳትስ በምን መልኩ መቅረብ ያስፈልጋል?

አማኑሄል፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እንደ በፊቱ የኳሳችን ጊዜ አሁን ላይ ቀላል አይደለም። ሻምፒዮናው ቡድንና ወራጅ ቡድኑም ተፈታትነውም ሲጫወቱ ታይቷል።  ያ ስለሆነም ይህን ድል ለመጎናፀፍ  ለፍተህ፣ ደክመህና ጠንክረህም መምጣት ይጠበቅብሃልና እኛም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ በዚህ መልኩ ለመገኘት ስራችንን ከወዲሁ የምንሰራ ይሆናል።

ሊግ፦ ቅ/ጊዮርጊስ  የቀድሞ ስምና ዝናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይመልሳል?

አማኑሄል፦  ብዬ አስባለው፤  ከላይ እንደገለፅኩት ፕሪምየር ሊጉ አሁን ላይ እንደበፊቱ  ውድድር ጊዜ  ቀላል አይደለም፤ በጣም የለፋና የደከመ ቡድንም ነው እስከመጨረሻው ጨዋታዎች ድረስ ተፋልሞ ዋንጫውን የሚያነሳው አንተ ጣር እንጂ ይህን ድል መጎናፀፍ ይቻላል። ቡድናችን አሁን ላይ ካለፉት ጊዜያቶች ብዙ ትምህርትን ያገኘ ይመስለኛል። ዘንድሮ በነበረን ውድድር የተወሰኑ ጨዋታዎች እስኪቀሩ ድረስ ዋንጫውን የማግኘት ዕድሉ ነበረን ከዋንጫው ስንርቅ ደግሞ በጣም ስሜታዊ ሆነን ተናደድን አሁን ስለቀጣዩ ጊዜ ነው ማሰብ ያለብን። የምናደርጋቸውን እያንዳንዳቸውን ጨዋታዎች በማሸነፍም ነው በመጪው ጊዜ ደጋፊዎቻችንንና የቦርድ አባላቶቻችንን ማስደሰት የምንፈልገው።

ሊግ፦ በቅ/ጊዮርጊስ ቆይታህ ደስተኛ ነህ? ለቡድኑስ በቂ ግልጋሎትን ሰጥቼያለው ትላለህ?

አማኑሄል፦  በቡድኑ ቆይታዬ በጣም ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም ለታላቁ እና  የሀገሪቱ ምርጥና ታዋቂ ተጨዋቾች ተጫውተው ባሳለፉበት ቡድን ውስጥ ለመጫወት መቻል መታደል ነውና  ይህ ነው ትልቁ ጉዳይ እንደዛም ሆኖ ግን በእንደዚህ ያለ ቡድን ውስጥ ስትጫወትም ውጤት ማምጣት ዋንኛው አስፈላጊው ጉዳይ ነውና ያን ማሳካትም የግድ ይላል።

የቅ/ጊዮርጊስ ቆይታዬ ላይ ቡድኑን ጠቅሞ ከመጫወት ጋር በተያያዘ አሁን ላይ እኔ በሚገባ ክለቡን እየጠቀምኩት ነው ብዬ አላስብም። ካለኝ ብቃት አኳያ ገና ጫፉንም አላሳየሁትም። ብዙ ነገር ይጠበቅብኛልና ያን በቀጣይ ጊዜ ለማሳየት ነው በመዘጋጀት ላይ የምገኘው።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጋችን በዲ.ኤስ.ቲቪ መተላለፉን አስመልክተህ ምን አልክ?

አማኑሄል፦ መታየቱ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ያልታዩ ተጨዋቾች ብቃታቸውን አውጥተው ለመጫወት ሲሞክሩ ይስተዋላሉ። በተለይ ደግሞ ለወጣት ተጨዋቾች ወደ ውጪ ሀገር አምርተው እንዲጫወቱም ትልቅ ዕድልን የሚፈጥርላቸውም ስለሆነ የዚህ ስራ ተግባር ሊበረታታ ይገባል። ሌላው የሊጉ ጨዋታዎች በዲ ኤስ ቲቪ መታየቱ ወደ ሜዳ በመምጣት የአገራችንን ኳስ ጨዋታ ለመመልከት ላልቻለው ህዝባችንም በኳሱ ያለንበትን ሁኔታ እንዲያውቅም ስለሚያደርገው ይህን ሁኔታ ላመቻቹት አካላቶች ምስጋናዬ ከፍ ያለም ነው።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  ዘንድሮ ምን የተለየ ነገርን ተመለከትክ?

አማኑሄል፦ በሊጉ ወጣት ተጨዋቾች ላይ በሚገባ ከተሰራ አገራችን ብዙ አቅም ያላቸው ተጨዋቾች እንዳሏት ነው የተረዳሁት። ስለዚህም ለእንደእነዚህ አይነት ተጨዋቾች የመሰለፍ ዕድሎች ቢሰጣቸው ጥሩ ነው።

ሊግ፦ የኢትዮጵያ ቡናው አቡበከር ናስር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ደምቆ በርካታ የኮከብ ተጨዋችነትን ሽልማቶች ጠቅልሎ ወስዷል፤ ምን አልክ?

አማኑሄል፦ አቡበከር ዘንድሮ የወሰዳቸው ሽልማቶች በጠቅላላ ብዙ ለፍቶአልና ይገባዋል። አንድ ሰው ደግሞ የልፋቱን ሲያገኝ እና ለዛም ሽልማትም ሁሉም ሰው ምስክርነትን ሰጥቶለት ተገቢውን ክብር ሲጎናፀፍም በጣም ደስ ይላልና እኔንም ደስ ሊለኝ ችሏል። ከዛ ውጪም አቡኪ ዘንድሮ ባሳየው ምርጥ ብቃትም እንደልፋቱ ከተለያዩ ሀገራት የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እድሉም እየመጣለት ስለሆነና በዚህ ደግሞ እሱ ወደ ውጪ ሲያመራ ለሌሎች ተጨዋቾችም ብዙ እድሎች ስለሚፈጠርላቸው  ለእዚህና  ለኮከብ ተጨዋችነት ተሸላሚነቱ እንኳን ደስ ያለህ ልለውም እወዳለው።

ሊግ፦ አበቡከር በኮከብ ተጨዋችነት እንደተሸለመ ሁሉ ከእሱ ውጪ ደግሞ የሐዋሳ ከተማው ወንድማገኝ ሀይሉም ተስፋ ሰጪ ተጨዋች ተብሎ ተሸልማል፤ እኔስ አላልክም?

አማኑሄል፦  እንዲህ ያሉ ሽልማቶችን ተጨዋቾች ሲያገኙማ አንተም እኮ ትጓጓለህ። የእኔስ ተራ መች ይሆናል የሚል ትንሽ የመንፈስ  ቁጭት ስሜትማ  ይፈጥርብሃልና  የተሻለ ብቃትን አሳይተህ የዛ ተሸላሚ ለመሆን ጥረትን ታደርጋለህ። በዘንድሮ ውድድር ከአቡኪ ውጪ የተሸለመው ወንድማገኝ በታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ አብረን ነበርን የእሱም እንዲሁም የአቡኪም መሸለም እኔም በቦታው እንደሆንኩ ያህል ተሰምቶኛልና በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ ልላቸው እወዳለሁ።

ሊግ፦ ፋሲል ከነማ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ውድድር ከመጠናቀቁ በፊት  አራት ጨዋታዎች እየቀሩት ነው ዋንጫውን ያነሳው፤ ምን አልክ?

አማኑሄል፦ ፋሲል ከነማ ትልቅ ቡድን ነው። እንደ ቡድን  በመጫወትና በመልፋትም ነው ዋንጫውን ያገኘው።  ለእዚህ ድሉም ተገቢነትና ትክክለኝነት ጨዋታዎቹ በዲ ኤስ ቲቪ የተላለፉ በመሆናቸውም እነሱንም እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እፈልጋለው።

ሊግ፦ የእግር ኳስ ግብህ የት ድረስ ነው?

አማኑሄል፦ እልሜ በሀገር ውስጥ ብቻ መጫወት አይደለም። ወደ ባህርማዶ ወጥቼ መጫወት እፈልጋለው። ይህን ለማሳካትም ብዙ ነገር ይጠበቅብኛልና በአጭር ጊዜያቶች ውስጥ ሙሉ ተጨዋች ለመሆን ጥረትን አደርጋለው።

ሊግ፦ ቤትኪንጉ ተጠናቀቀ፤ በምን ሁኔታ ጊዜያቶችህን እያሳለፍክ ነው?

አማኑሄል፦ ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ከቤተሰቦቼ ጋር ነው ጊዜያቶቼን እያሳለፍኩ ያለሁት። እነሱ በተለይ ለቤቱ የመጀመሪያውም ወንድ ልጅ ስለሆንኩና የእኔን በኳስ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሴም ያጓጓቸው ስለነበርም በሁሉም ነገር ደስ እያላቸውም ነበር ውድድር ጨርሼ ወደ ቤት ስመጣ እያቀፉኝ ጭምር በምክራቸው በርታ ሲሉኝም የነበሩትና በቀጣዩ ጊዜ ከአሁን በተሻለ መልኩ ጥሩ ነገርን አሳያቸዋለሁኝ። ወደ ቤተሰቦቼ ካመራው በኋላና  ለአራትና ለአምስት ቀናቶች እረፍት ካደረግኩኝ በኋላ ሌላ ያደረግኩት ነገር ቢኖር  ወደ ልምምድ በመመለስ የኤሮቢክስ እና የሲት ሀፕ ልምምዶችን በመስራት ላይ ነበርም የቆየሁት። ይህን መስራቴም አሁን ለተመረጥኩበት የኢትዮጵያ የተስፋ ብሄራዊ ቡድን ሊጠቅመኝ የሚችል ነው።

ሊግ፦ የእግር  ኳስን ከቤተሰብ በመራቅ ነው የምትጫወተው። ውድድሩ ልክ እንደተጠናቀቀ አሁን?

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  አቡበከር ምርጡ ተጨዋች ተብሏል። ከእሱ ውጪ ለአንተ ሌላ ምርጡ ማነው?

አማኑሄል፦ የእኛው ክለብ ግብ ጠባቂ ባህሩ ነጋሽ ነዋ! እሱን የመረጥኩት የቡድኔ ተጨዋች ስለሆነ አይደለም። ባህሩ የውጪ ሀገር ግብ ጠባቂዎች በተደጋጋሚ ጊዜ ወደ ቡድናችን እየመጡ በማይሰለፍበት ሁኔታ ውስጥ ለሁሉም ነገር ትዕግስትን አድርጎ አሁን ላይ ዕድሉን ሲያገኝ በጥሩ ብቃት አጋጣሚውን ተጠቅሞበታልና ያ ስላስደሰተኝ ነው ልክ እንደ አቡበከር ሁሉ እሱም ምርጫዬ የሆነው።

ሊግ፦ ከባህር ማዶ የየቱ ክለብ ደጋፊ ነህ?

አማኑሄል፦ ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን ስለማደንቅ የማንቸስተር ሲቲ ደጋፊ ነኝ።

ሊግ፦ ማንቸስተር ሲቲ የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ አጣ?

አማኑሄል፦ በጣም ተናድጄያለው። ነገር ግን በእግር ኳስ መሸነፍና ማሸነፍ  ያለ ስለሆነ ተቀብያለው።

ሊግ፦ የአውሮፓ ዋንጫ ትናንት ምሽት ተጀመረ፤ ድጋፍህ ለማን ነው?

አማኑሄል፦ ለፖርቹጋል፤ ስብስባቸው በጣም ደስ ይላል። አዳዲስ ተጨዋቾች አሉ። የማንቸስተር ሲቲው እነ ሩቢን ዲያስን ጨምሮ ዝነኛውን ክርስቲያኖ ሮናልዶን የያዘና ጥሩ ኳስን እንድትመለከትም የሚጋብዙ ተጨዋቾች ስላሉ የውድድሩን የአሸናፊነት ግምት ሁሉ ለእነሱ ልሰጣቸውም ችያለሁ።

ሊግ፦ ከምግብ ምርጫ?

አማኑሄል፦ አልመርጥም፤ ያገኘሁትን እበላለው።

ሊግ፦ ከመጠጥ?

አማኑሄል፦ ውሃ።

ሊግ፦ ከሙዚቃ?

አማኑሄል፦ የአፍሮቢት ዘፈኖችን እወዳለው። ቴዲ አፍሮና ዊትኒን ደግሞ አደንቃለው።

ሊግ፦ ከተመለከትካቸው ፊልሞች የወደድከው?

አማኑሄል፦ ኩዊን ኤንድ ስሊምንና ረቡኒን።

ሊግ፦ እናጠቃል?

አማኑሄል፦ በእግር ኳስ ተጨዋችነቱ እዚህ ደረጃ ላይ ለመጣሁበት መንገድ በቅድሚያ ፈጣሪዬንና ቤተሰቦቼን ማመስገን እፈልጋለው። ከዛም የሰፈሬን ላፍቶ  ጓደኞቼን፣ የፕሮጀክት አሰልጣኜን ከዛ በተጨማሪ ደግሞ እስካሁን ድረስ በምክሩም ጭምር ከጎኔ ሆኖ እያበረታታኝ ያለውና በቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ ያሰለጠነኝ ደረጄ ተስፋዬን በጣም ላመሰግናቸውና ወደፊት ደግሞ ጥሩ ደረጃ ደርሼ ላኮራቸው እፈልጋለው።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P