Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

አቶ ዘውገ ቃኘው በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሕዝብ ግንኙነት በአለም ሰገድ ሰይፉ

አቶ ዘውገ ቃኘው በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ፌሬሽን ሕዝብ ግንኙነት

በአለም ሰገድ ሰይፉ

ይሄን ዓመት ያክል ያለአንዳች ክፍያ በበጎ ፈቃደኝነት ስፖርቱን ማገልገል ትንሽ ሊከብድ ይችላል፡፡ አቶ ዘውገ ቃኘው ግን አድርገውታል፡፡  የአንድ ጎልማሳ ዕድሜ በሚቆጠረው የዓመት ልኬት በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ህዝብ ግንኙነት በመሆን አሁን ድረስ እያገለገሉ  ናቸው፡፡

እስከ ሕይወቴ ፍፃሜ ድረስ ገና እሰራለሁ በማለት አሁንም የጋለ ሞራል ያላቸው እኚህ ግለሰብ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አለም ሰገድ ሰይፉ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

ሊግ፡– በሰሜን አሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ ለምን ዓመት ያክል ቆዮ?

አቶ ዘውገ፡- ፌዴሬሽኑ የተቋቋመው እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ1984 ዓ.ም ነው፡፡ እኔ ደግሞ በዳላስ ከተማ ነዋሪነቴ በ1983 ዓ/ም ነበር ከፌዴሬሽኑ ምስረታ ጀምሮ ከኢትዮ ዳላስ ቡድን ጋር በመሆን ግልጋሎቴን ጀምሬያለሁ፡፡

ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በፌዴሬሽኑ ውስጥ በተለያየ የአመራርነት ቦታ ላይ ሰርቻለሁ፡፡ በዛን ወቅት የኢትዮ ዳላስ ተጨዋች በመሆንም አገልግያለሁ፡፡

ሊግ፡– እንደነገሩኝ  ከሆነ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት  ነው እያገለገሉ የሚገኙት፡፡ ይሄን ያክል ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት መስራት ትንሽ አይከብድም?

አቶ ዘውገ፡- ፌዴሬሽናችን ስራውን እንደጀመረ ለ8 ዓመታት ያክል ስታዲየም ለሚታደመው ተመልካች ንግግር የምናደርግበት ማይክ አልነበረም፡፡ ዳላስ ላይ ውድድሩ አንድ ተብሎ ሲጀመር “ዘውገ ለምን የዚህ ፕሮግራም አስተዋዋቂ አትሆንም” በማለት የዳላስ ቡድን መሪ መረጠኝ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አሁን ውድድሩ በኮቪድ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ለ34 ዓመታት የስታዲየሙ የሬዲዮ ተናጋሪ በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ፤ ከዚያም ባሻገር የኢትዮ-ዳላስ የቡድን መሪ በመሆን ቦርዱን ተቀላቅዬ የሰራሁበትም አጋጣሚ አለ፡፡

አንተ ቀደም ብለህ ወደአነሳሀው ጥያቄ ሳመራ አንድ አንዴ ገንዘብ ተከፍሎ ከምትሰራው ስራ በተሻለ ሁኔታ በነፃ የምታገለግለው ነገር የሚመረጥበት አጋጣሚ ይፈጠራል፤ ከዚህ አንፃር በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምሰጠው አገልግሎት በነፃ ቢሆንም በብዙ ሺ ዶላር እንደሚከፈለው ሰው ከፍተኛ ደስታ የማገኝበትና በአገልግሎቴ የምኮራበት ስራ ነው፤ እኔ አሁን አሁን ትዝ የሚለኝ በነፃ ስለማገልገሌ ሳይሆን ዓመታዊ ውድድሩ ደርሶ ከእነ ማይኬ ስታዲየም መገኘት ነው የሚናፍቀኝ፡፡

ሊግ፡- በየዘመናቱ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሲቀያየሩ አንተ ግን አሁን ድረስ ከሀላፊነትህ ያለቀቅክበት ሚስጥር ምንድን ነው?

አቶ ዘውገ፡- በአንድ ወቅት ከሀላፊነቴ ለቅቄ ነበር፤ ነገር ግን በየውድድር አመቱ ሁሌም ስለምታይ ከሀላፊነት የለቀቅኩ አይመስላቸውም፤ እናም ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ ህይወቴን በሙሉ  በህዝብ ግንኙነት ክፍልና በአስተዋዋቂነት ስለምታይ ሰዎች ሁሌም እንደፌዴሬሽን ባለስልጣን ሊያየኝ ይችላል፡፡

እንደሚታወቀው ፌዴሬሽናችን በተለያየ ጊዜ ምርጫ ያካሂዳል፤ ምርጫ ስልህ ደግሞ ዝም ብሎ የይስሙላ ምርጫ ሳይሆን እጅግ ዲሞክራሲያዊ አካሄድን የተከተለ ምርጫ ነው የሚደረገው፤ እዛ ፌዴሬሽን ውስጥ አንዱ ሰው ስለፈለገ ብቻ ዕድሜ ልክ እዛ ቦታ ላይ አይቀመጥም፡፡

ሊግ፡- ፌዴሬሽናችሁ አሁን ያለበት ቁመና ምን ይመስላል?

አቶ ዘውገ፡- የፌዴሬሽናችን ቁመና ሁሌም እንዳማረ ነው፤ ሁሌም እንዳማረበት የመቆየቱ ሚስጥር ደግሞ የህዝብ ድርጅት በመሆኑ ነው፤ በአንድ ወቅት ችግር ውስጥ በነበረበት ጊዜ ይህን ታላቅ ፌዴሬሽን ከችግር ውስጥ ያወጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፤ ለ38 ዓመታት ያለ አንዳች መንገታገት በየዓመቱ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰብ መቻል ቀላል ነገር አይደለም፤፤ ወደፊትም ይሄ ፌዴሬሽን ምንም አይሆንም፤ ምክንያቱም የህዝብ ጥበቃ፣ ድጋፍና እገዛ ስለማይለየው አሁን ደግሞ የበለጠ እያደገና እየጎለበት ነው፤ በርካታ የውስጥና የውጪ ፕላኖችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ ከዚህም ባሻገር ከሚያገኘው ገቢ ቆጥቦ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ተለይቶ የሚታወቅ ተቋም ነው፤ በቅርቡ እንኳን ለትምህርት ቤትና ሆስፒታሎች ማስገንቢያ 350 ሺ ዶላር ሰጥተናል፤ ይህ እንዲቀርብ ምሳሌ ያነሳሁት እንጂ አንተ ራስህ የምታውቀው ፌዴሬሽናችን ያደረጋቸው በርካታ እገዛዎች አሉ፡፡

ሊግ፡- ዘንድሮ ውድድሩ ይካሄዳል?

አቶ ዘውገ፡- ምን ጥያቄ አለው፤ እስካሁንም ውድድሩ እንዳይካሄድ  አለም አቀፍ ጉልበተኛ የነበረው የኮሮና ቫይረስ ነበር፤ ሆኖም በ2022 በምንም ምክንያት ውድድሩ መቋረጥ የለበትም የሚል የጋራ መግባባት ላይ በመደረሱ አመታዊ ቶርናመንቱ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የዘንድሮ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያኖች አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ከጁላይ ሶስት እስከ ጁላይ ዘጠኝ በሜሪላንድ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ሊግ፡- ዘንድሮ ውድድሩ የሚካሄድበትን ቦታ ለመግለፅ የዘገያችሁበት ምክንያት ምንድን ነው?

አቶ ዘውገ፡- አንድን ውድድር ለሚያዘጋጀው ከተማ መርጦ ለመስጠት በየዓመቱ የሚወጡትን መስፈርትና መመዘኛዎቹን ሟሟላት ያስፈልጋል፤ በቂ ሜዳ፤ ጥራቱን የጠበቀ ሆቴልና ለውድድሩ ግብአት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በብቃት ማቅረብ ለአንድ አስተናጋጅ ከተማ የሚቀርቡ ክራይቴሪያዎች ናቸው፤ እናም ውድድሩ የሚካሄድበትን ቦታ ዘንድሮ ለማሳወቅ ትንሽ የዘገየንበት ምክንያት ከላይ የጠቀስኳቸው መስፈርቶች በአጥጋቢ ሁኔታ መመለሳቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ነበር፡፡

ሊግ፡- በህይወት ዘመንህ ምን ማየት ይናፍቅሃል?

አቶ ዘውገ፡- በህይወቴ የሚናፍቀኝ እኔ የማውቀው አይነት የእግር ኳስ ጥራትና የጨዋታ ክህሎት ሀገራችን ላይ ተፈጥሮ ህዝባችን ከአውሮፓ ሀገር የኳስ ሱስ በመላቀቅ የሀገሩን እግር ኳስ የሚናፍቅና የሚወድ ዜጋ እንዲሆን እመኛለሁ፡፡ ወደ ፌዴሬሽን ስንመለስ ደግሞ ይሄን ያክል ብዙ አመታት ከማገልገሌ አንፃር በየዓመቱ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚደረገው አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል አንድ ቀን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በህዝባችን ፊት ይህ ታላቅ ውድድር ሲካሄድ ማየት የዘወትር ምኞቴ ነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P