Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ኢትዮጵያ ቡናን ተቃራኒ ሆነህ ስትገጥመው ለክለቡ እንድትጫወት ያስመኝሃል” አበበ ጥላሁን (ኢት.ቡና)

ኢትዮጵያ ቡና ለፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎው በዝውውር መስኮቱ ካስፈረማቸው ተጨዋቾች መካከል አንዱ ለመከላከያ ክለብ በተከላካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው አበበ ጥላሁን ይገኝበታል፤ ይሄ ወጣት ተጨዋች በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ለአርባምንጭ ከተማ፣ ለሲዳማ ቡናና ለመከላከያ ቡድኖች ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በአንድ ወቅትም ኬንያ ላይ ተደርጎ በነበረው እና አገራችን ተካፋይ በነበረችበት የሴካፋ ሻምፒዮና ውድድር ላይም በሩዋንዳ በተሸነፍንበት ጨዋታ ላይ ተቀይሮ በመግባት እና ከኡጋንዳም ጋር አቻ በተለያየንበት ጨዋታም በቋሚ ተሰላፊነት ለዋልያዎቹ መጫወቱም ይታወሳል፤ ኢትዮጵያ ቡናዎች ይህን ተጨዋች የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቻቸው ፈቱዲን ጀማል ከክለባቸው መልቀቁን ተከትሎ ያስፈረሙት ሲሆን ሊግ ስፖርት ይህን ተጨዋች በጋዜጠኛዋ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አማካኝነት ወደ ቡና ስላደረገው ዝውውር፣ ተጨዋቹ ስላሳለፈው የእግር ኳስ ህይወት እንደዚሁም ደግሞ ስለ ቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቱ፣ ስለቤተሰቦቹና ሌሎች ከእሱ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታን አድርጋ ምላሽ ተሰጥቷቷል፤ ሊግን ተከታተሏት፡፡
ስለ ትውልድ ስፍራው እና ስለ እግር ኳስ ጨዋታ ጅማሬው
“የተወለድኩትና ያደግኩት በአርባምንጭ ከተማ ሲቄላ ወይንም ደግሞ ሚካሄል መንደር በሚባለው ስፍራ ነው፤ የእግር ኳስ ጨዋታ ጅማሬዬም በትምህርት ቤት ደረጃ በመጫወት ነው፤ የተጫወትኩበት ትምህርት ቤትም……….ይባላል”፡፡
የልጅነት ዕድሜው ላይ ስለነበረው ባህሪይ እና ኳስን ከመጫወቱ ጋር ቤተሰቡ ጋር ስለነበረው አመለካከት
“አስተዳደጌንና ባህሪዬን በተመለከተ የተረጋጋው አይነት ልጅ ሆኜ ነው ያደግኩት፤ ኳስን ከመጫወቴ ጋር በተያያዘም ቤተሰቦቼ በተለይ ደግሞ አባቴ ሁሌም እንድጫወት ይደግፈኝ እና ይገፋፋኝ ነበር፤ የቤተሰቦቼ እገዛም ነው ለዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ ለመገኘቴ ምክንያት የሆነኝ”፡፡
በቤተሰቡ ከሚገኙት ልጆች ውስጥ ብቸኛው ስፖርተኛና ወንድ ልጅም እሱ ስለመሆኑ
“አዎን፤ አልተሳሳትክም፤ የቤቱ ብቸኛው ወንድ ልጅ እና ስፖርተኛው እኔ ነኝ፡፡ ለቤቱም ሶስተኛው ልጅ ነኝ፤ አምስት እህቶችም አሉኝ፤ እነዚህ እህቶቼም የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ናቸው፤ ተማሪ እህትም አለኝ”፡፡
የእግር ኳስን እንደ ቡድን በመሰባሰብ ስለተጫወተበት የመጀመሪያ ሁኔታ
“የእግር ኳስ ጨዋታ ጅማሬዬን ከጓደኞቼ ጋር ተሰባስቤ በቡድን ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወትኩት አርባምንጭ ላይ በግለሰቦች ደረጃ ተቋቁሞ በነበረው የፕሮጀክት ቡድን ውስጥ ነው፤ ከዛም ቆይታዬ በኋላ ወደ አርባምንጭ ወጣት ቡድን /ቢ ቡድን/ ውስጥ ሙከራን አድርጌ ልገባ ቻልኩ፤ ይህ ነው በቡድን ደረጃ የእኔ የኳስ ጨዋታ ጅማሬዬ የነበረው”፡፡
የእግር ኳስን መጫወት ሲጀምር ተምሳሌቱ /ሞዴሉ/ አድርጎት ስለነበረው ተጨዋች
“የእግር ኳስ ጨዋታው ላይ ባለው ጥሩ ችሎታውም ሆነ ስነ-ምግባሩ ተመልክቼው በማድነቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ለራሴ አርአያዬ ወይንም ደግሞ ሞዴሌ ያደረግኩት ተጨዋች በአርባምንጭ ከተማ እና በሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ አብሬው የመጫወት ዕድሉን ያገኘሁት አንተነህ ተስፋዬን ነው፤ እሱ እንደ እኔው ሁሉ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ነው፤ አሁንም ድረስ በጣም ነው የማደንቀው”፡፡
የእግር ኳስን በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ሲጫወት ምርጥ እና ጣፋጭ የሚባለውን ጊዜ ስላሳለፈበት ክለብ
“የእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ ላይ በክለብ ደረጃ ለአርባምንጭ ከተማ፣ ለሲዳማ ቡና እና ለመከላከያ ቡድኖች ለመጫወት ችያለሁ፤ በእነዚህ ቡድኖች የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬም ጥሩ የሚባል ጊዜን ለማሳለፍ በቅቻለሁ፤ ከሁሉም ግን ምርጡን እና ጣፋጩን የኳስ ህይወቴን ያሳለፍኩበት ቡድን ሲዳማ ቡና ነው”፡፡
በሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ የነበረውን የተጨዋችነት ዘመን ቆይታውን ከሌሎች ቡድኖች አንፃር በምን መልኩ ሊያስበልጥ እንደቻለ
“ሲዳማ ቡና በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ ባለኝ ችሎታ ራሴን በደንብ የገለፅኩበት እና ብቃቴንም በሚገባ ያሳየሁበት ክለቤ ነው፤ ከዛ ውጪም ቡድኑ ውስጥ በነበርኩበት ሰዓትም የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ የሚፎካከር ትልቅ እና የተደራጀም ቡድን ስለሆነ ሌላው ደግሞ የክለቡ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎቹም አስገራሚ እና ለእኔም ሆነ ለሌሎች ተጨዋቾችም ጥሩ ስለነበሩም እነዚህ መሰል እና በእዚህ ቡድን በነበረኝ ቆይታዬም በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ አማካኝነትም ለቡድኔ ባሳየሁት ጥሩ ብቃት ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን ከመመረጥ አንስቶ እስከመጫወት ደረጃ ላይም የደረስኩበት ጊዜ ስለነበር ክለቡን ለዛ ነው በቀዳሚነት አስቀምጬ እና የመጀመሪያዬም ምርጫዬ አድርጌ ምርጡን እና ጣፋጩን ጊዜያት በክለቡ እንዳሳለፍኩኝ ልጠቅሰው የፈለግኩት”፡፡
በፕሪምየር ሊግ ደረጃ የተጫወትክባቸው የአርባምንጭ ከተማ እና የመከላከያ ክለቦች በከፍተኛው /ሱፐር ሊግ/ ደረጃ በተለያዩ ወቅቶች ወርደው መጫወታቸውን ስትመለከት
“አርባምንጭ ከተማ ከስር ጀምሮ እኔን በማሳደግ ለእውቅና እንድበቃ ያደረገኝ ቡድን ነው፤ መከላከያም ቢሆን በእግር ኳሱ የተጫወትኩበት የሀገሪቱ ትልቅ ቡድን ነው፤ ከእዚህ ቡድን ጋርም የሀገሪቱን ትላልቅ የሚባሉ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫንና የአሸናፊዎች አሸናፊን ዋንጫም ለማግኘትም ችያለሁ፤ እነዚህ ሁለት ቡድኖች ለአገራችን እግር ኳስ በርካታ ተጨዋቾችን ከማፍራት በተጨማሪ ለብሔራዊ ቡድናችንም ተጫውተው ያለፉ ልጆችንም ከእዚህ ቀደም እና አሁን በቅርቡ ከማስገኘታቸው አኳያ አሁን ላይ በታችኛው ሊግ ደረጃ ሲጫወቱ ማየት በጣም ያሳዝናል፤ ያማልም፤ ቡድኖቹ ከነበራቸው አቅምና ብቃት አንፃርም ሲመዘኑም በእዛ ደረጃ መጫወትም አይመጥናቸውም ነበርና እግር ኳስ ስለሆነ ግን ያ እውን ሊሆን ችሏል”፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ከእዚህ ቀደም ሲመረጥ ስለተፈጠረበት ስሜት እና አሁንም ዳግም ይኸውን ቡድን ስለመቀላቀል
“ለዋልያዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የመመረጥ ዕድሉን ያገኘሁት የሲዳማ ቡና ተጨዋች በነበርኩበት ሰዓት ላይ ነው፤ ያኔ ይኸው ጥሪ ሲደርሰኝም ሀገሬን የማገልገል ከፍተኛ ፍላጎቱ ስለነበረኝ ደስታዬን መቆጣጠር አቅቶኝም ነበር፤ ለብሔራዊ ቡድን እንደተመረጥኩም ብዙ ነገሮችን ላደረገችልኝ እናቴም ነበር ስልክ ደውዬም ልነግራት የቻልኩት፤ እሷም መመረጤን ከእኔ አንደበት ስትሰማም እንደ እኔውም ነበር በጣም ለመደሰት የቻለችው፤ ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ እና መጫወት መቻል ትልቅ ክብርን የሚያስገኝ ነገር ነው፤ አሁን ላይ የእዚህ ቡድን አባል ባልሆንም የሁሉም ተጨዋቾች ዋና እልም የሆነውን ይህን ብሔራዊ ቡድን በድጋሚ በመቀላቀል ጠንክሬ እሰራለው፤ ጠንክሬ ሰርቼም አቅሜን ማሳየትም እፈልጋለው”፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ተመርጦ ስላደረጋቸው ጨዋታዎች
“ለዋልያዎቹ በመመረጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረግኩት ጨዋታ ኬንያ ላይ ተደርጎ በነበረው የሴካፋ ውድድር ላይ ከብሩንዲ ጋር ስንጫወት ነው፤ ያኔ ሽንፈትን ባስተናገድንበት ጨዋታም ላይ ተቀይሬ ነበር የገባሁት፤ ከእዚህ ጨዋታ በኋላ ደግሞ ከኡጋንዳ ጋር በነበረን ጨዋታ በቋሚ ተሰላፊነት ጥሩ ለመጫወት ብችልም ቡድናችንም ጥሩ ቢንቀሳቀስም ግጥሚያውን ማሸነፍ የሚገባን ቢሆንም ጨዋታውን አቻ ለመውጣት በመቻላችን ወደ ቀጣዩ ዙር እንዳናልፍ አድርጎን ነበርና በጊዜው በጣም ተቆጭቼ ነበር”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት አሁን ላይ የደረስክበት ደረጃ ፈጣን ወይንስ አዝጋሚ
“በእግር ኳሱ ከመጣሁበት ጊዜ አንፃር ከሆነ ለእኔ በጣም ፈጥኗል፤ ምክንያቱም ኳስን በፕሪምየር ሊግ ደረጃ መጫወት የጀመርኩት ከ2006 ዓ/ም አንስቶ ነው፤ በእዚህ ጊዜ ውስጥ ለአርባምንጭ ከተማ እስከ 2008 ድረስ ተጫወትኩ፤ ከ2009 እስከ 2010 ደግሞ ለሁለት ዓመት ለሲዳማ ቡና ተጫወትኩ፤ ከዛም በፕሪምየር ሊጉ በ2011 እና አምና ደግሞ በከፍተኛው ሊግ በነበርንበት ሰዓት ለመከላከያ ቡድን ተጫወትኩ፤ በመሀልም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በሚያስመርጠኝ ደረጃም ላይ ሆኜ ለሀገሬም ልጫወት ቻልኩ፤ ይህ ሁሉ ሲታይ በአጠቃላይ በእዚህ የሰባት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አሁን ላይ አዲሱን ክለቤን ኢትዮጵያ ቡናን እስከተቀላቀልኩበት ጊዜ ድረስ ያለውን የኳስ ጉዞዬን ስመለከተው በጣም የፈጠነ ነው”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና ተፈልገህ ለክለቡ ፊርማህን አኑረሃል፤ ወደ ቡና ከመግባትህ አኳያ አሁን ላይ ራስህን በትልቅ ተጨዋችነት ደረጃ ላይ ነው የምታስቀምጠው
“በፍፁም፤ የእግር ኳስን ስጫወት ሁሌም ቢሆን ሰዎች ስለራሴ ይናገሩ እንጂ እኔው ራሴ እንደዚህ አይነት ተጨዋች ነኝ፤ ምርጥም ተከላካይ ነኝ ብዬ አላውቅም፤ ከዛ ይልቅ የማስበው በምጫወትባቸው ክለቦች ውስጥ ለቦታዬ የሚሰጡኝን የግልም ሆነ የቡድን ልምምዶችን በብቃት በመወጣት ቡድኔን ስለማገልገል ነውና ይሄ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለው”፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከማምራትህ በፊት የመከላከያ ተጨዋች ነበርክ፤ ክለቡ ከአመት በፊት ከፕሪምየር ሊጉ ሲወርድ ምክንያቱ ምን ነበር? ለመውረዱስ ራሳችሁን ተጠያቂ አድርጋችኋል?
“አዎን፤ ለመከላከያ ከፕሪምየር ሊጉ መውረድ ሁላችንም የቡድኑ አካላቶች ተጠያቂዎች ነን፤ ይሄ ቡድን ያን ዓመት ላይ በነበረው ጥሩ ብቃቱ ከሊጉ ይወርዳል ብለንም ፈፅሞ አልጠበቅንም ነበር፤ በዛ የውድድር ዓመት ክለባችን በጥሎ ማለፉ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡናን በግማሽ ፍፃሜው ቅዱስ ጊዮርጊስን ደግሞ በፍፃሜው ጨዋታ እንደዚሁም ደግሞ ጅማ አባጅፋርን በአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ አሸንፎ ሻምፒዮና ሲሆን የፕሪምየር ሊጉንም ዋንጫ እስከማንሳት ይፎካከራል ብለን ብንጠብቅም ሊጉ ሲጀመር ግን በተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ነጥቦችን ልንጥል በመቻላችንና በክለባችን ውስጥም ተጨዋቾችና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ያልተግባቡበትም ብዙ ነገሮች ስለነበሩ በእዚህ የተነሳ ውጤት እያጣን ስለሄድን ልንወርድ ቻልን፤ ለክለቡ መውረድ ሁሉም የየራሱ ድርሻም ነበረው”፡፡
በፕሪምየር ሊጉ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው 4 ቁጥር መለያን በተደጋጋሚ ስለማድረግ ሚስጥሩ
“ምንም ሚስጥር የለውም፤ ለአርባምንጭ ከተማ በምጫወትበት ሰዓት መጀመሪያ ላይ 21 ቁጥር ማልያን ነበር የምለብሰው፤ ከጎኔ ደግሞ በችሎታው በጣም የማደንቀው አንተነህ ተስፋዬ 4 ቁጥር ማልያን አጥልቆ ይጫወት ነበር፤ አንትዬ ልክ ክለባችንን ሲለቅ እኔ ለእሱ ካለኝ አድናቆት የተነሳ 4 ቁጥርን መልበስ ቻልኩ፤ ወደ ሲዳማ ቡናም ሳመራ ይኼውን 4 ቁጥር መለያን ለማድረግ የቻልኩት አሁንም አንተነህ ከክለቡ በለቀቀበት ሰዓት ላይ ነውና ከእዛን ጊዜ አንስቶ ነው ይኸውን ቁጥር በመውደድ እስካሁን እየለበስኩት ያለሁት”፡፡
በዘንድሮው የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡናን ስለተቀላቀለበት መንገድ
“ኢትዮጵያ ቡናን በትክክለኛው የዝውውር መስኮት ከመቀላቀሌ በፊት አስቀድሜ ወደ ፌዴሬሽን ሳላመራ ለሀድያ ሆሳህና ነበር ፊርማዬን ያኖርኩት፤ ያም ሆኖ ግን ወደዚህ ቡድን በተጓዝኩበት ሰዓት እነሱ ቃል በገቡልኝ መልኩ የምፈልገውን ጥቅም ሊፈፅሙልኝ እና ሊሰጡኝ ስላልቻሉ እኔን ወደፈለገኝ እና ጥሩ ጥቅምን ወደሰጠኝ ሌላው ቡድን ኢትዮጵያ ቡና ላመራ እና ያለምንም ማንገራገርም ለክለቡ ፊርማዬን ለማኖር ችያለሁ”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና ተፈልገህ ፊርማህን አኖርክ፤ ወደ ቡድኑ ስትገባ ምርጫዬ ትክክለኛ ነው ብለህ አሰብክ?
“አዎን፤ ለቡና መጫወትን እፈልግ ነበር፤ ለእኔ አጨዋወትም ቡድኑ ትክክለኛ ምርጫዬም ነበር፤ ከዛ ውጪም ቡና የምወደው ቡድንም ነው፤ ለዛም ነው እነሱ በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ አማካኝነት ጥሪውን አቅርበውልኝ ወደ ቡድኑ ና ሲሉኝ ልፈርም የቻልኩት”፡፡
ኢትዮጵያ ቡናን በተለያየ ወቅት ተቃራኒ ተጨዋች ሆነህ ገጥመሃል፤ ያለውን ስሜት ስትገልፀው
“ኢትዮጵያ ቡና በአገራችን እግር ኳስ ትልቅ ቡድን ከመሆኑና በብዙ ደጋፊዎችም ታጅቦ የሚደገፍ ከመሆኑ አኳያ እነሱን የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ሆነህ ስትገጥም ያለው ስሜት በጣም ደስ የሚል ነው፤ የትም የማይቀሩ እና ክለባቸውንም እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ የሚደግፉ አስደናቂ ደጋፊም ያላቸው ስለሆኑ ከእነሱ ቡድን ጋር ስትጫወት ጥሩ የፉክክር መንፈስን በሜዳ ላይ ይዘህ እንድትጫወት ያደርጉሃል፤ ከዛ ውጪም ኢትዮጵያ ቡናን ተቃራኒ ሆነህ ስትገጥመውም ካለው ድባብ እና ቡድኑ ከሚከተለው አጨዋወት ተነስተህም ለክለቡ እንድትጫወትም ያስመኝሃልና ስሜቱ በእዚህ ደረጃ ላይ ጭምር የሚገለፅም ነው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ግጥሚያውን ለማድረግ ከወዲሁ ስላደረበት ጉጉት እና ከክለቡ ጋር በእዚህ ዓመት ለማስመዝገብ ስላሰበው ውጤት
“የኢትዮጵያ ቡና መለያን አጥልቄ የመጀመሪያዬን ጨዋታ ማድረግ በጣም ናፍቆኛል፤ ይሄ ናፍቆቴም አንደኛው ለእዚህ ቡድን መጫወትን አጥብቄ እፈልገው የነበረ በመሆኑና ከዛ ውጪ ደግሞ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ከእግር ኳሱ ለብዙ ወራቶች ርቀን ስለነበር ያንን ናፍቆቴን ለመወጣትም ጭምር ነው፤ ከቡና ጋር በእዚህ ዓመት ለማሳካት የማስበው ውጤት ደግሞ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ እስካሁን ይሄን ዋንጫ ከየትኛውም ቡድን ጋር አላነሳውም ስለዚህም ከቡና ጋር ይህን ስኬት መቀዳጀት እፈልጋለውኝ፤ ወደ ቡድኑ መጥቼ ለአራት ዓመት ፊርማዬን ለማኖር የቻልኩትም ከቡድን አጋር ጓደኞቼ ጋር ሆኜ እንዲህ ያሉ እና ተፈላጊ የሆኑ የሻምፒዮናነት ድልን ማግኘት ነው፤ ቡና ደግሞ በየዓመቱ ወደ ውድድር የሚገባው የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እንጂ ዝም ብሎ ለመፎካከር ስላልሆነም ይህን ድል ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን በተከታታይ ዓመትም ለማምጣት ከወዲሁ በርትተን እንሰራለን”፡፡
በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያ ቡናን ዘንድሮ ያለ ደጋፊው ሲጫወት ማየት
“ኢትዮጵያ ቡናን በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ያለ ደጋፊው ሲጫወት ማየት ያልተለመደ ነው፤ ያለ ደጋፊው በሜዳው ላይም ሆነ ከሜዳው ውጪ ሲጫወትም የሚኖረውን የፉክክር ስሜትም ከወዲሁ ሳስበው ትንሽ ከበድም የሚል ነው፤ ስለዚህም ይሄ ወቅቱ ያመጣብንን ክፉ ወረርሽኝ ፈጣሪ አጥፍቶልን ክለባችን በደጋፊዎቹ ፊት የሚጫወትበት ጊዜ ሩቅ አይሆንምና ያን ጊዜ በተስፋ እንጠባበቀው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና እና ለቅ/ጊዮርጊስ መጫወትን ብዙ ተጨዋቾች የመጨረሻ እልማቸው ሲያደርጉ ይሰሙ ነበር…..አንተስ?
“እኔ በእዛ ደረጃ የማስብ አይነት ተጨዋች አይደለውም፤ አሁን ላይ ሌላ ተጨዋቾችም ቢሆኑ ወደ ውጪ ወጥቶ መጫወት የሚያስገኘውን ጥቅም እየተረዱ ስለመጡ ከእንደዚህ አይነት ነገሮች ሳይወጡ የቀሩ አይመስለኝምና ያንን የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እድልን ለማግኘት ነው እቅዴና እልሜ አድርጌ የምገኘው፤ እስከዛው ግን ያን እድል እስካገኝ ድረስ ለእዚህ ታላቅ ለሆነው ክለብ ኢትዮጵያ ቡና አቅሜን ሳልሰስት እጫወታለው፤ ቡድኑን ለውጤት ለማብቃትም ከፍተኛ ጥረትን አደርጋለው”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና በቋሚ ተሰላፊነት ለመጫወት ስለሚኖረው ፉክክር እና ቡናዎች አንተን የቡድናቸው አካል ለማድረግ ስላወቁበት ሁኔታ
“ኢትዮጵያ ቡናዎች ወደ ቡድናቸው እኔን ሲያመጡኝ ዝም ብለው በግምት አይደለም፤ በሲዳማ ቡና በነበረኝ የተጨዋችነት ቆይታዬ ስለ እኔ መረጃ ነበራቸው፤ ከዛ ውጪም አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ እና ኮቺንግ ስታፉም በእኔ ላይ እምነት ስላላቸው እና ለክለቡ የጨዋታ እንቅስቃሴም እንደምሆን ተረድተውም ነው ያመጡኝና በእዚህ ታላቁን ክለብ በመቀላቀሌ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ቡድኑ ውስጥ በቋሚነት ለመሰለፍ ስለሚኖረው ፉክክር ደግሞ ቡና ዝም ብለህ ገብተህ የምትጫወትበት ቡድን አይደለም፤ የበርካታ ደጋፊዎቹን አደራ ተሸክመህ የምትጫወትበት ክለብ ነው፤ ከዛ ውጪም ቡድኑ በአዲስ መልክ እየተገነባ ያለ ቡድን ስለሆነም በእዚህ ክለብ ውስጥ በቋሚ ተሰላፊነት ገብቶ ለመጫወት ከባድ ፉክክር እና ቻሌንጆችም ስለሚጠብቀኝ ከወዲሁ ራሴን በአካልም በስነ-ልቦናም በሚገባ እያዘጋጀሁት ነው የምገኘው”፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማህን ልታኖር የተቃረብክባቸው የመጨረሻ ሰዓታቶች ምን ይመስሉ እንደነበር
“ለኢትዮጵያ ቡና ገብቶ መጫወት የማይፈልግ ተጨዋች ማንም የለም፤ እኔም ከተፈለግኩ ወደ ቡና ገብቼ መጫወትን አስቀድሜም እልሜ ስለነበር ለቡድኑ ልፈርም በተቃረብኩበት ሰዓት በጣም ነበር ደስ ያለኝ፤ ለቡድኑ እንደፈረምኩም ለውዷ ባለቤቴም ነው ደስታዬን ላበስራት የቻልኩትና እሷም ወደ ቡና በመግባቴ በመደሰት እንኳን ደስ አለህ በማለትም ምላሿን ልትሰጠኝ ችላለች”፡፡
ስለ ትዳር ህይወቱና ባለቤቱ ከኳሱ ጀርባ ስለምታደርግለት እገዛ
“የትዳር ህይወቴን ጣፋጭ በሆነና በጥሩ መልኩ ነው ከባለቤቴ ጋር እያሳለፍኩ ያለሁት፤ ባለቤቴ እስከዳር አድማሱ ትባላለች፤ የአንድ ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሁለት መንትያ ልጆችን ልናፈራ ችለናል፤ ወንዱ ልጃችን አሜንአብ አበበ ሲባል ሴቷ ደግሞ ሀሴት አበበ ትባላለች፤ ውዷ ባለቤቴ ከኳሱ ጀርባ ስለምታደርግልኝ እገዛ በትንሽ ቃላት ብቻ የምገልፀው አይደለም፤ ፈጣሪ ጥሩ ሚስት ሰጥቶኛል፤ በኳሱ ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃም እንደ ቤተሰቦቼ ሁሉ ትልቁን አስተዋፅኦም ያደረገችልኝ ነችና እሷን በጣም ነው የማመሰግናት”፡፡
ባለቤትህ እግር ኳስን ትወድ እንደሆነ እና በምን ሙያ ላይ እንደተሰማራች
“እሷ ለእግር ኳሱ ቅርብ ናት፤ ለአርባምንጭ ከተማ በምጫወትበት ሰዓትም ሜዳ በመግባት ጨዋታም ታይ ነበር፤ የቡድኑም ደጋፊ ናት፤ ሲዳማ ቡና በነበርኩበት ሰዓትም አንድ አንዴ ጨዋታን ታይ ነበርና ኳስን እንደምትወድ ከእዚሁ ማረጋገጥ ይቻላል፤ ከዛ ውጪ ባለቤቴ በአሁን ሰዓት የተሰማራችበት ሙያ በንግዱ ዓለም ላይ ነው”፡፡
ከባህር ማዶ ስለሚደግፈው ቡድን እና ስለሚያደንቀው ተጨዋች
“የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ፤ የማደንቀው ተጨዋች ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ነው”፡፡
ስለቀጣይ ጊዜው የእግር ኳስ ተጨዋችነት እልሙ
“አሁን ላይ በቅድሚያ ለአራት ዓመታት በደስታ ፊርማዬን ላኖርኩበት ኢትዮጵያ ቡና ጥሩ ግልጋሎትን ሰጥቼ ቡድኑን ለውጤት ስለማብቃትና ስለመጥቀም እንደዚሁም ደግሞ የቡድኑን ደጋፊዎች፣ አሰልጣኞች እና ተጨዋቾቻችንን ጭምር በችሎታዬ ለማስደሰት ነው እያሰብኩ ያለሁት፤ ከዛ በኋላ ደግሞ የኳስ ጨዋታ ዘመኔን ወደ ባህር ማዶ በመጓዝም እስከመጫወት ድረስም ነው የምመኘውና ይሄን ለማሳካት የሚያግዙኝን ነገሮች በመፈለግ ከፍተኛ ጥረቴን እያደረግኩኝ ነው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ ምርጡ ጥምረቴ የሚለው
“ምርጡ ጥምረቴ በአርባምንጭ ከተማ ክለብ ውስጥ በነበርኩበት ሰዓት ከአንተነህ ተስፋዬ ጋር የነበረኝን ነው የማስቀድመው፤ ከእሱ ውጪ ልጠቅሰው የምፈልገው ደግሞ በሲዳማ ቡና ከኬንያዊው ሰንደይ ሙቱክ ጋር የነበረኝንና በመከላከያ ደግሞ ከአዲስ ግደይ ጋር የነበረኝን ነው”፡፡
ስለ ቡና ደጋፊዎች
“የቡናን ደጋፊዎች የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ሆኜ ተመልክቼያቸዋለው፤ ክለባቸውን ከልብ ይወዳሉ፤ ያለ ማቋረጥ 90 ደቂቃም ይደግፋሉ እና በእነዚህ ደጋፊዎች ፊት ወደፊት ለመጫወት የምችል ተጨዋች በመሆኔ ራሴን እንደ እድለኛ እቆጥረዋለሁኝ”፡፡
በመጨረሻ….
“ቤተሰቦቼ በኳሱ ዛሬ ላይ እዚህ ለደረስኩበት ደረጃ ትልቅ አስተዋፅኦን አበርክተውልኛልና ከፈጣሪ ቀጥሎ አመሰግናቸዋለው፤ ሌላው ደግሞ ውዷ ባለቤቴ እንደዚሁም ከልጅነቴ ጀምሮ ያሰለጠኑኝ አሰልጣኞች፤ እንደዚሁም ደግሞ በክለብ ደረጃ ለእኔ እዚህ ስፍራ ላይ መገኘት በማሰልጠን ለጥሩ ስፍራ ያደረሱኝን አሰልጣኝ አለማየው አባይነህ /አሌኮን/ እንደዚሁም ደግሞ ጥሩ መስመር ያስያዘኝን አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ከልብ ለማመስገን እፈልጋለውኝ”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P