Google search engine

ኤርትራዊው የባህርዳር ከተማው ተጨዋች ዓሊ ሱሌይማን ጉዳትን አስተናገደ- በ23 ቀን ውስጥ ወደ ሜዳ ሊመለስ ይችላል

 

በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ባህርዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረጉት የአበበ ቢቂላው የምድብ ሁለት ጨዋታ ኤርትራዊው የባህርዳር ከተማው የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ዓሊ ሱሌይማን በትከሻው አካባቢ ጉዳትን አስተናግዶ ከሜዳ መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ተጨዋቹ ወደ ሆስፒታል ካመራም በኋላ የቀዶ ጥገና /ሰርጀሪ/ እንዲደረግለት ቢነገረውም ወደ ሆስፒታሉ ድንገት እንዲመጣ በተደወለለት የኢትዮጵያ ቡናውና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድናችን ፊዚዮትራፒስት ይስሃቅ ሽፈራው ጉዳቱ ከታየ በኋላ እኔ ጋር ተጨዋቹ ይምጣ እጁን ከትከሻው ጋር በማያያዝና እንዲገጥምለትም በማድረግ በ23 ቀናት ጊዜ ውስጥ ወደ ሜዳ እንዲመለስ ጥረት እንደሚያደርግ  መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡

የባህርዳር ከተማው ዓሊ ሱሌይማን አገራችን አስተናግዳው በነበረው የሴካፋ ውድድር ላይ ለሀገሩ የኤርትራ ቡድን ጥሩ እንቅስቃሴን ለማሳየት የቻለ ሲሆን ጎሎችንም ለማግባት ችሏል፤ በሴካፋ ያሳየው ብቃትም በባህርዳሮች እንዲፈለግ አድርጎት ፊርማውን አኑሯል፤ በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የመጀመሪው ቀን ጨዋታም ላይ አዳማ ከተማን ሲያሸንፉ ጎል ከማግባት ባሻገር ያሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴው ለዕለቱ የጨዋታው ኮከብነት ሽልማት አብቅቶትም የዋንጫና የ12 ሺብር ሽልማትም እንዲያገኝም አድርጎታል፡፡

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this: