Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“እስከመጨረሻው ጠንክሮ የሚጓዘው ቡድን ዋንጫውን ያነሳል፤እሱም ቅ/ጊዮርጊስ ነው”
ጋዲሳ መብራቴ /ቅ/ጊዮርጊስ/

“በኢትዮጵያ ቡና የደረሰብን አስቆጪው ሽንፈት በጣም አንቅቶናል”

“እስከመጨረሻው ጠንክሮ የሚጓዘው ቡድን ዋንጫውን ያነሳል፤እሱም ቅ/ጊዮርጊስ ነው”
ጋዲሳ መብራቴ /ቅ/ጊዮርጊስ/

በመሸሻ_ወልዴ

ቅ/ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ ቡና የ3-2 ሽንፈትን ካስተናገደ በኋላ ከጅማ አባጅፋር እና ከወላይታ ዲቻ ጋር ያደረጋቸውን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎቹን በድል ተወጥቶ ወደ አሸናፊነቱ የተመለሰ ሲሆን በቤት ኪንጉ የዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው የእዚህ ቡድን ስኬታማ ተጨዋችነቱን በማሳየት ላይ ያለው ጋዲሳ መብራቴ ክለባቸው ወላይታ ዲቻን በሳላህዲን ሰይድ የ86ኛ ደቂቃ ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፎ ከወጣ በኋላ በተገኘው ድል መደሰቱን ገልፆ ቡድናቸው እየተሻሻለ ስለመምጣቱና በተለይ ደግሞ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ሲጫወቱ የደረሰባቸው አስቆጪው ሽንፈት በጣም እንዳነቃቸው እና በቀጣይነትም ለሚያደርጓቸው ጨዋታዎችም ትምህርት ሆኗቸው ከእዚህ በኋላ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከፈለጉም በእያንዳንዱ ጨዋታዎች ላይ ምንም አይነት ነጥቦችን መጣል እንደሌለባቸውም አስተያየቱን ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ሰጥቷል፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ወላይታ ዲቻን ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 15 ያሳደገ ሲሆን በደረጃው ሰንጠረዡም እንደ ኢትዮጵያ ቡና ሁሉከመሪው ቡድን ፋሲል ከነማ ጋር የሚያስተካክለው አንድ ጨዋታ እየቀረው ከፋሲል ከነማ ጋር በ4 ነጥብ ከቡና ጋር ደግሞ በአንድ ነጥብ በማነስ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ቅ/ጊዮርጊስ የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን የ9ኛ ሳምንት ጨዋታውንም ከባህር ዳር ከተማ ጋር በዛሬው ዕለት በ9 ሰዓት ያደርጋል፡፡
ከቅ/ጊዮርጊሱ ተጨዋች ጋዲሳ መባራቴ ጋር በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ያደረግነው ቆይታም ይህንን ይመስላል፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ ወላይታ ዲቻን ጨምሮ ያለፉትን ሁለት ግጥሚያዎች ድል በማድረግ ወደ አሸናፊነት ስለመምጣቱ
“በቅድሚያ በእነዚህ ሁለት ጨዋታዎቻችን ላይ ድልን ስለተጎናፀፍንና ወደምንታወቅበትም የአሸናፊነት መንፈሳችን ስለተመለስን በጣም ደስ እንዳለኝ ለመናገር እፈልጋለው፤ ቅ/ጊዮርጊስ ሁልጊዜም ቢሆን ከስህተቱ ተምሮ የሚመጣ ቡድን እንጂ ችግሮቹን ሌሎች አካላቶች ላይ ለጥፎ የሚያልፍ ክለብ ስላልሆነ እኛም በተለይ ደግሞ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን ጨዋታ ላይ ቡድናችን አስቆጪ የሚባለው ሽንፈት ባጋጠመው ወቅት በጨዋታው ዙሪያ ችግሮቻችን ምንድን እንደነበሩ በሚገባ ስለተነጋገርንበት እና በጨዋታዎቹ ላይም ነቃ ብለንም ስለቀረብንበት እና ተሻሽለንም ስለመጣን ፍልሚያዎቻችንን በድል ልናጠናቀቅ ችለናል”፡፡
ወላይታ ድቻን ለማሸነፍ እና የድሉን ግብ ለማስቆጠር ረጅም ደቂቃ አስፈልጓችሁ ነበር፤ በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?
“ወላይታዎች ላይ የድሉን ጎል አስቆጥረን በአሸናፊነት ከሜዳ ለመውጣት ረጅም ሰዓት የወሰደብን ዋንኛው ምክንያት በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እነሱ በውጤት ቀውስ ውስጥ ስላሉና ተጋጣሚያቸው ደግሞ እኛም ስለሆንን በመከላከል ላይ ያተኮረን የጨዋታ እንቅስቃሴ ሊከተሉ በመቻላቸው ነው፤ ቅ/ጊዮርጊስ በእዚህ ጨዋታ ውጤታማ ለመሆን ብዙ ልፋትና ጥረት አድርጎ ነው መጨረሻም ላይ ሳላህዲን ባስቆጠረው ግብ አሸናፊ ልንሆን የቻልነው እና ይህ ድል የሚገባን ሆኖም ነው ያገኘነው”፡፡
የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን አጠቃላይ ተሳትፎአችሁን በተመለከተ
“ውድድሩ ሲጀመር በሽንፈት ነበር የጀመርነው፤ ከዛም እየተሻሻልን መጣንና ወደ ውጤታማነት መጣን፤ ከዛም አስቆጪውን ሽንፈት በቡና ካስተናገድን በኋላ ያ ጨዋታ እኛን ብዙ አንቅቶን አሁን ደግሞ መልሰን ወደ ስኬታማነቱና ወደ አሸናፊነቱ ተመልሰናል፤ ይሄ የአሸናፊነት ጉዞአችንም ወደፊት ይቀጥላል”፡፡
በኢትዮጵያ ቡና የደረሰባቸው ሽንፈት ደጋፊዎቻቸውን ስለማስቆጨቱ
“የእውነት ነው ባይቆጩም ነው በጣም የሚገርመው፤ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊ በቡና መሸነፍን በፍፁም አይፈልግም፤ ቁጭቱ ግን የእነሱ ብቻ ሳይሆን የእኛም ጭምር ነው፤ የመጀመሪያው ተቆጪዎቹም ተናዳጆችም እኛ ነበርን፤ በእግር ኳስ ግን አንድ አንዴ እንዲህ ያሉ ሽንፈቶች የሚያጋጥሙ ስለሆነ ከአንተ የሚጠበቀው ከዛ ሽንፈት ስህተት መማር መቻል ነው፤ እኛም ከአስቆጪው የቡና ሽንፈት ብዙ ስለተማርንና ያ ጨዋታም በጣም እንድንነቃም ስላደረገን ነው ባለፉት ሁለት ግጥሚያዎቻችን ላይ ወደ አሸናፊነት መንፈሱ ልንመለስ የቻልነው”፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ምርጥ የተጨዋቾች ስብስብ እንጂ ምርጥ አሰልጣኝ የለውም ስለመባሉ
“ይሄን የሚሉት የቡድናችንን ልምምድ ያልተመለከቱ ወይንም ደግሞ በአንድ ሁለት ጨዋታዎቻችን ላይ ሽንፈትን በማስተናገዳችን ሊሆን ይችላል፤ ውጤት ከጠፋ ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት አባባሎችም ይነሳሉ፤ እኛ ግን አሰልጣኛችንን በቅርብ ርቀት እንደተመለከትነውና እንደተረዳነው አሰልጣኙ ጥሩ እና ጎበዝ የሆነ ባለሙያ ነው፤ በየልምምዳችን የተለያዩ አይነት የጨዋታ ታክቲኮችንም ነው እያሰራን ያለው ስለዚህም ቅ/ጊዮርጊስ ምርጥ የተጨዋቾች ስብስብ ብቻ ያለው ሳይሆን ጥሩም አሰልጣኝ ያለው ክለብ ነው”፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ በመከላከሉ ላይ ጥንካሬውን አጥቷል፤ በተለይ ደግሞ ቀደም ሲል በነበሩት ጨዋታዎች ላይ የአስቻለው አቋም ዋዥቋል ስለመባሉ
“የቅ/ጊዮርጊሱን የኋላ ማገር እና ጠንካራውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አስቻለው ታመነን በተመለከተ ስለ እሱ ብቃት እና አቋም ተጨዋቹ ከጉዳት በመምጣት እየተጫወተ ከመሆኑ አኳያ ምንም ቢባል ለተጨዋቹ እንከን የምታወጣለት አይደለም፤ አስቻለው ለቡድኑ መጫወት የጀመረው ከጉዳት መልስ በመምጣት ነው፤ ቀደም ሲሉ በነበሩት አንድ አንድ ጨዋታዎች ላይም በሙሉ ጤንነቱ ስላልተጫወተም ነበር ክፍተቱ የነበረው፤ ክፍተቱ ደግሞ የእሱ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ነበር፤ ቅ/ጊዮርጊስ በመከላከሉም ላይ ጥንካሬውን አጥቶ የነበረውም እንደ ቡድን እንጂ በተከላካይ ስፍራ ተጨዋቾቹ ላይም አልነበረምና አሁን ላይ ብዙ ነገራችን ተሸሻሏል፤ አስቻለውም ወደ መልካም ጤንነቱም መመለሱን ከወላይታ ድቻ ጋር ባደረግነውና አሸናፊ በሆንበት ጨዋታም ላይ አሳይቷልና እሱ አስገራሚ እና ምርጥ ተከላካይ መሆኑን ከእዚህ በኋላም ዳግም የሚያስመለክተን ይሆናል”፡፡
በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ በተለየ ብቃት ምርጥ ሆኖ ስላገኘው ተጨዋች
“ከፋሲል ከነማ ሙጂብ ቃሲምን ከኢትዮጵያ ቡና አቡበከር ናስርን እንደዚሁም ደግሞ የእኛዎቹም አቤል ያለው እና ጌታነህ ከበደን በጥሩ ብቃት ላይ ሆነው ነው እየተመለከትኳቸው ያለው ጥሩ የውድድር ጊዜንም እያሳለፉ ነው”፡፡
ለቅ/ጊዮርጊስ ጌታነህ ከበደ ተደጋጋሚ ጎሎችን ከማስቆጠሩ ጋር በተያያዘ ቡድኑ የእሱ ጥገኛ ነው የሚል ሀሳብ ስለመነሳቱ
“በፍፁም፤ /ሳቅ እንደ ማለት ብሎ/ ቅ/ጊዮርጊስ በታሪኩ የማንም ተጨዋች ጥገኛ ሆኖ አያውቅም፤ ቡድኑ ጎሎችን የሚያስቆጥረው በጋራ እንደ ቡድን ስለሚጫወት ነው፤ ጌታነህም ጎልን የሚያስቆጥረው ከቡድኑ ጋር በጋራም ስለሚንቀሳቀስ ነው”፡፡
የቅ/ጊዮርጊስ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ቀድሞ ወደሚታወቅበት የኮከብ ግብ አግቢ ፉክክር ውስጥ ስለመግባቱና ለቡድናቸው እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት
“የእግር ኳስን ከደቡብ ፖሊስ ክለብ ተጨዋችነቱ አንስቶ አሁንም ድረስ እስከሚጫወትበት ክለቡ ቅ/ጊዮርጊስ የዘለቀው ጌታነህ በሙሉ ጤንነት ላይ ይሁን እንጂ ሜዳ ከገባ ጎል ከማስቆጠር ወደ ኋላ የማይልና በጣም የማደንቀው ተጨዋች ነው፤ አሁንም ቀድሞ ወደሚታወቅበት ጎል አግቢነቱ በመመለስ ቡድናችንን በጥሩ ሁኔታ እያገለገለ ይገኛል፤ ይሄ ጉዞው ዳግምም ይቀጥላል”፡፡
በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው ለቅ/ጊዮርጊስ የሚያሰጋው ቡድን ማን እንደሆነና የውድድሩ ሻምፒዮና ማን እንደሚሆን
“ለእኛ የሚያሰጋንም ሆነ የሚያስፈራን ቡድን ማንም የለም፤ የውድድሩ ሻምፒዮና የሚሆነው ቡድን ደግሞ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በጥንካሬው የሚጓዘው ቡድን ሲሆን ያ ክለብም ቅ/ጊዮርጊስ ነው”፡፡
በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ ብዙ ጎሎች ስለመቆጠራቸው እና ሊጉ ለየት ብሎ ቀርቦበት እንደሆነ
“ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከሌላው ጊዜ የሊግ ተሳትፎ አንፃር በዋናነት ለየት ብሎብኛል የምለው ጨዋታዎቹ በዲ.ኤስ.ቲቪ በመተላለፋቸውና ዓለምም የእኛን ተጨዋቾች የሚከታተልበት ሁኔታ ሊፈጠር በመቻሉ ነው፤ ይሄ መሆኑም ብዙ ቡድኖችን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው እንዲመጡም አድርጓቸዋል፤ ከዛ ውጪም ተጨዋቾቻችን የራሳቸውን ችሎታ ለማሳየት እና ወደ ውጪም በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ለመጫወት እና ራሳቸውንም ለመሸጥ እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረትን የሚያደርጉበትን ሁኔታም እየተመለከትን ይገኛል፤ ይሄ ሊበረታታ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከእዚህ ቀደም የሊጉ ጨዋታዎቻችን በተሻለ መልኩ በርካታ ግቦች ለመቆጠራቸው ምክንያት ነው ብዬ የማስበው ይሄ ውድድር ለእያንዳንዱ ተጨዋች በዲ.ኤስ.ቲቪ መተላለፉ የሚያስገኘው ጥቅም ስላለው እና እያንዳንዱም ተጨዋች በጥሩ ሁኔታም ተዘጋጅቶ ስለሚመጣና ጨዋታዎቹም እየፈጠኑም በመምጣታቸው ነው”፡፡
በመጨረሻ….
“ለቅ/ጊዮርጊስ በዘንድሮው የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎዬ ላይ እያሳየሁት ያለው አቋም በጣም የሚያበረታታ እና በለውጥ ላይም እንዳለው ያሳየኝ ነው፤ ለእዚህ ቡድን በቀጣዮቹ ጨዋታዎቻችንም ላይ አቅሜ በሚችለው መልኩ ሁሉ ጥሩ ግልጋሎቴን በመስጠት ክለቡን ለውጤት ለማብቃትም ዝግጁ ነኝ”፡፡

https://t.me/Leaguesport

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P