Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከሊጉ ላለመውረድ የምንጫወትበት ጊዜ አብቅቷል” ቸርነት ጉግሳ (ወላይታ ድቻ)

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን  ከሚያሳዩት ተጨዋቾች መካከል የወላይታ ድቻው የመስመር ላይ አጥቂ ቸርነት ጉግሳ ስሙ በጉልህ ይጠቀሳል። ቸርነት ጉግሳ በዚህ የውድድር ዘመን  ተሳትፎው ውስጥም የጎላ እንቅስቃሴን እያደረገ  ባለበት የአሁን ሰዓት ላይ ክለቡን ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በጥሩ ደረጃ ላይ እንዲያጠናቅቅ ለማድረግ ተግቶ እንደሚሰራም ይናገራል።

የወላይታ ድቻው የመስመር ላይ አጥቂ ቸርነት ጉግሳ ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ ጋር ክለባቸው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በሐዋሳ ከተማ ላይ ከመጫወቱ በፊት በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እያደረጉት ስላለው የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎ፣ ስለ ራሱ፣  ስለ ቀጣይ ጨዋታዎቻቸውና ስለሊጉ ተፅህኖ ፈጣሪው ተጨዋች ማን እንደሆነ ይናገራል፤ ተከታተሉት።

ስለ እግር ኳስ ጨዋታ ጅማሬው እና ስለመጀመሪያ ክለቡ

“የእግር ኳስን መጫወት የጀመርኩት የልጅነት ዕድሜዬ ላይ ሆኜ ተወልጄ ባደግኩበት በወላይታ ሊጋባ ጀርባ ቀበሌያችን 03 አካባቢ ነው። በሰፈር እና በፕሮጀክት ደረጃም ነው ኳሱን ተጫውቼም ያደግኩት። ትንሽ ከፍ ካልኩ  በኋላ ደግሞ አሁንም ድረስ የእኔ የመጀመሪያዬ ክለብ ለሆነው ወላይታ ድቻ  ከተተኪው አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ደረጃ ኳስን እየተጫወትኩኝ ነው”።

 በልጅነት ዕድሜው የእግር ኳስን ሲጫወት በቤተሰቡ አካባቢ ተፅህኖ ተፈጥሮበት እንደሆነ

“ያኔም ሆነ  ካደግኩኝ በኋላ በፍፁም ተፅህኖው አልነበረብኝም፤ ያለ ምንም ጫናም ነው ኳስን በመጫወትም  ያደግኩት። እነሱ እንደውም የታላቅ ወንድማችንን ሽመክት ጉግሳን ስኬት ያዩም ስለነበር ለእኔ እንደውም ብዙ ነገርን በማድረግ ሲያበረታቱኝም ነበር”።

በእግር ኳስ ተምሳሌቱ ስለነበረው ተጨዋች

“ለእኔ ታላቅ ወንድሜ ሽመክት ጉግሳ ነበር ተምሳሌቴ፤ እሱን ሲጫወት በማየትም ነው ያደግኩት በጣም ስለማደንቀው አርአያዬም አደረግኩት፤ ሌላ የማደንቀው ተጨዋች ደግሞ ጌታነህ ከበደን ነው”።

ከባህር ማዶ  ክለቦች ውስጥ የማን ደጋፊ እና የየትኛው ተጨዋች አድናቂ  እንደሆነ

“በክለብ ደረጃ የምደግፈው ማንቸስተር ዩናይትድን ነው። የማደንቀው ተጨዋች ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልዶን”።

በልጅነት ዕድሜው የእግር ኳስ ተጨዋች እሆናለሁ ብሎ አስቦ እንደሆነና ኳስ ተጨዋች ባይሆን ኖሮ ምን ይሆን እንደነበር

“በዛ ጊዜ ኳስን ለስሜት ከመጫወት ውጪ ሌላ ያሰብኩት ነገር ፈፅሞ አልነበረም። ኳስ ተጨዋች ስለመሆን ማለምም የጀመርኩት ዕድሜዬ ከፍ እያለ ሲሄድም ነበር። ምንአልባት እንደ አሁኑ ኳስ ተጨዋች ባልሆን ቢሆን ኖሮ ደግሞ ልሆን የምችለው ነጋዴ መሆን ነበር”።

በቤተሰቡ ውስጥ እሱን ጨምሮ ሁለቱ ወንድሞቹ ኳስ ተጨዋች ስለመሆናቸው

“ይሄ መታደል ነው። ልክ እንደ ቡናው አቡበከር ናስር ቤተሰቦችም ነው ከኛም ቤት ውስጥ ሶስት ወንድማማቾች በኳሱ ልንወጣ የቻልነውና እንደዚህ አይነት ግጥምጥሞሽ ከዚህ በኋላ የሚኖርም አይመስለኝም። በእኛ ቤተሰብ ውስጥ የመጨረሻዋ እህታችን ተማሪ ከመሆኗ ባሻገር የሶስታችን ኳስ ተጨዋች ሆነን መውጣታችንንም ሳይ ልዩ ደስታም ሊሰማኝም ችሏል”።

በወላይታ ድቻ ስላለው የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው

“አሁን አራተኛ ዓመቴን ይዣለሁ። ከተተኪው ቡድን  አንስቶም ነው በዓመት በዓመት በማደግ በጥሩ መልኩ እየተጫወትኩኝ የምገኘው”።

ለወላይታ ድቻ ስላደረገው የመጀመሪያ ጨዋታው

“ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በተደረገ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ነበር ተቀይሬ በመግባት የተጫወትኩት። በጨዋታው ብንሸነፍም ጥሩ ልንቀሳቀስ ችያለሁ”።

በእግር ኳሱ ተጫውቶ ስላሳለፈባቸው ቦታዎች

“መጀመሪያ የመሀል  ተጨዋች ነበርኩ፤ ከዛም  የመስመር ላይ  አጥቂ  ሆንኩኝ። አሁንም በዚህ ስፍራ ላይ  ሆኜ  ነው  በኳሱ እየተጫወትኩ ያለሁት”።

ከወንድሙ ሽመክት ጉግሳ ጋር በተቃራኒነት ሲጫወቱ ስላጋጠመው ሁኔታ

“በወላይታ ድቻ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ከእሱ ጋር እስካሁን ለስምንት ጊዜያት ያህል በተቃራኒ ቡድን ሆነን ኳስን ልጫወት ችያለሁ። በዚህ ጊዜ ውስጥም እኔን ያጋጠመኝ ነገር ቢኖር  ሁለታችንም ወደ ሜዳ ከገባን በኋላ ፈፅሞ ወንድማማቾች የማንመስል እና የማንነጋገርም መሆናችን ነው። ከዛ ውጪ ለምንጫወትበት ቡድንም ግጥሚያው እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስም አቅማችንን ሳንሰስት የምንፋለም መሆናችንም ነው”።

ከቤታቸው ውስጥ ቀልደኛው ማን እንደሆነ

“በእኛ ቤተሰብ ውስጥ ቀልደኛው እና የሚያዝናናን ሰው ቢኖር አሁን ላይ ለወላይታ ድቻ እየተጫወተ የሚገኘው አንተነህ ጉግሳ ነው። እሱ ቀልድና ጨዋታን በደንብም ተክኖበታል”።

ከሊጉ ላለመውረድ ይጫወት የነበረው ቡድናቸው ዘንድሮስ

“ወላይታ ድቻ የእውነት ነው ከዚህ በፊት ከሊጉ ላለመውረድ ነበር ሲጫወት የነበረው። ይሄ ሊገጥመን የቻለውም ወደ ሜዳ ከገባን በኋላ ነገሮችን ቀለል አድርጎ የመመልከትና በእንቅስቃሴ ደረጃም ቶሎ የመርካት ሁኔታዎች ስለነበሩ እንደዚሁም  ሜዳ ላይ ብዙ ስለማንነጋገርና አሰልጣኞቻችን የሚሰጡንን ታክቲክ ስለማንተገብርም ነበርና ውጤትን ባጣንበት ጊዜ ነገሮች ሁሉ ደስ አይሉም ነበር። አሁን ላይ ግን ብዙ ነገሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቡድናችን ላይ ስለተቀየሩና አበረታች ውጤትንም እያስመዘገብን በመሆኑም እንደ ከዚህ ቀደሙ ላለመውረድ የምንጫወትበት ጊዜ ያበቃ እና  በደረጃ ተፎካካሪነትም የውድድር ዘመኑን የምንጨርስ ይመስለኛል”።

በቤትኪንጉ ተፅህኖ ፈጣሪ ስለሆነው ተጨዋች “አቡበከር ናስር ነዋ! በዚህ ደረጃ ከቡናው የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ውጪ የምጠቅሰው ሌላ የለኝም”።

በአሁን ሰዓት በኳሱ ስለሚገኝበት ደረጃና ስለ ወደፊት እልሙ

“በእግር ኳሱ አሁን ላይ ገና ነኝ። ብዙ የሰራሁትም ነገር የለም። ከዚህ በኋላ በሚኖረኝ ቆይታ ግን ብቃቴን በጣም አሻሽዬና በተለይም ደግሞ በርካታ ጎሎችን ለክለቤ ማስቆጠሩ ላይ በደንብ ሰርቼ በመምጣት ለሀገሬ ብሄራዊ ቡድን እስከመጫወት እና ወደ ውጪም ወጥቶ በፕሮፌሽናል ደረጃም እስከመጫወት ድረስም እያለምኩ ነው የምገኘው”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ ስለተደሰተበትና ስለተከፋበት አጋጣሚዎች

“በጣም የተደሰትኩት ቅ/ጊዮርጊስን ባሸነፍንበት ጊዜ ነው። እነሱን ስናሸንፍ ጥልቅ የሆነ የደስታ ስሜትም ነው ሊሰማኝ የቻለው። በውድድር ዘመኑ ልከፋ እና በጣም ደግሞ ላዝን የቻልኩት አዲስ አበባ ላይ በነበረን ጨዋታ ፈፅሞ ባልጠበቅነው ሁኔታ በሐዋሳ ከተማ ክለብ 4-1 በሆነ  ሰፊ  ውጤት በተሸነፍን ጊዜ ነው”።

በቤትኪንጉ ከየትኛው ቡድን ጋር ሲጫወቱ የቅድሚያ ምርጫው እና ፍላጎቱ እንደሆነ

“እኔ ቡድኖችን አበላልጬ አላውቅም። ከሁሉም ጋር ስጫወት ስሜቴ ተመሳሳይ እና አንድ አይነት ነው”።

ከእግር ኳስ ወጪ ጊዜውን የት እንደሚያሳልፍ

“ሁሌም ከቤተሰቦቼ ጋር ነው የማሳልፈው። ከእነሱ ጋር ስሆንም በጣም ነው ደስ የሚለኝ”።

ወደ ትዳር ህይወት ገብቶ እንደሆነ

“እንደ መሳቅ ካለ በኋላ  በዛ ደረጃ ገና ነኝ። ወደፊት ግን ፈጣሪ ሲፈቅድ መመስረቴ አይቀርም”።

ከሙዚቃና ከምግብ ቀዳሚው  ምርጫ ማን እንደሆነ

“በሙዚቃው የመጀመሪያ ምርጫዬ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ ነው። እሱን በጣምም ነው የማደንቀው ከምግብ ደግሞ የመጀመሪያ ምርጫዬ ጥሬ ስጋ ነው። ቁርጥን በጣም ስለምወድ ብዙ ጊዜ እሱንም ነው የምመገበው”።

የትንሳኤ በዓልን በምን መልኩ እንዳሳለፈ

“በሐዋሳ ከተማ ላይ ነው ከቡድናችን ተጨዋቾች ጋር በዓሉን በጥሩ መልኩና ሁኔታ ላይ ያሳለፍኩት”።

አዝናኙና ቀልደኛው የቡድናቸው ተጨዋች ማን እንደሆነ

“የእኛ ክለብ ውስጥ ቀልደኛ ሆኖ እኛን የሚያዝናናን ተጨዋች ግብ ጠባቂያችን መክብብ ነው። እሱ ካለ ሳቅ አለ”።

በመጨረሻ

“በእግር ኳስ ተጨዋችነት አሁን ለመጣሁበት  መንገድ  እና ለደረስኩበት ደረጃ ቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ። ከእሱ በመቀጠል ደግሞ ቤተሶቦቼንና በተለይም ደግሞ ወንድሞቼን ከእነሱ ውጪም እኔን ያሰለጠኑኝ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋልና መልዕክቴን አድርሱልኝ”።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P