Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ከኮብልስቶን ሠራተኛነት እስከ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋችነት የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ተክለማርያም ሻንቆ




በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/


የኢትዮጵያ ቡናን በጥሩ ግብ ጠባቂነቱ እያገለገለ የሚገኘው ተክለማርያም ሻንቆ ካለፉት ዓመታት አንስቶ ለብሔራዊ ቡድንም ለመመረጥ የቻለ ተጨዋች ሲሆን ይህን ግብ ጠባቂ ስለኳስ ህይወቱ፤ ስለቤተሰቡ፤ ስለ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡናና ሌሎችን ተጨማሪ ጥያቄዎችን የሊግ ስፖርት ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አቅርቦለት ምላሾቹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቶናል፡፡


ሊግ፡- በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ በሊግ ስፖርት ጋዜጣ አንባቢዎቻችን ስም ከልብ እናመሰግንሃለን?
ተክለማርያም፡- እኔም የጋዜጣችሁ እንግዳ አድርጋችሁኝ ስላቀረባችሁኝ አመሰግናችኋለው፤ ለምትጠይቁኝም ጥያቄ መልሴን ለመስጠትም ተዘጋጅቻለው፡፡
ሊግ፡- ኮሮና ቫይረስ የዓለምም የአገራችንም መነጋገሪያ እና አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል፤ በሌሎች ሀገራት ትውልድን እያሳጣን ከመሆኑ ባሻገርም ወደ እኛው ሀገር ስንመጣም እስከ 9 የሚደርሱ ታማሚዎች በመገኘታቸው በሽታው እያሳሰበንም ይገኛል….በእዚህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር አለ?
ተክለማርያም፡- የኮሮና ቫይረስ በሽታን በተመለከተ የአሁን ሰዓት ላይ ወረርሽኙ ዓለም አቀፍ ከመሆኑ ባሻገር ብዙ ሰውንም እየነጠቀን ነው፤ ወደ እኛ ሀገር ስንመጣም እስካሁን ድረስ ሰው አይሙት እንጂ የቫይረሱ ተጠቂዎች በጥቂቱም ቢሆን እየተገኙ መጥተዋልና ለእዚህ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ልናደርግለት ይገባል፤ የኮሮና ቫይረስን በቀላሉ ልንመለከተው የሚገባን በሽታ አይደለም፤ ይሄ ህመም በፍጥነት መስፋፋት የሚችልም ነው፤ በተለይ ደግሞ እንደ እኛ ባሉት ሀገራት የአናናር እና የአዋዋል ዘይቤያችን እንደዚሁም ደግሞ በእጅ ከመጨባበጥ አኳያም የለመደነው የሰላምታ አሰጣጥም በይሉኝታ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ይህን ቫይረስ እንዳይስፋፋ ለማድረግ እና ቫይረሱን ለመከላከል ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚተላለፉትን መልዕክቶች ለምሳሌ፡- በርካታ ሰዎች ባሉበት ቦታ ላይ አለመሰባሰብ፤ እንደዚሁም ደግሞ በእጅ መጨባበጥ አያስፈልግም ስለተባለ ያንን ምንም ይሉኝታ ውስጥ መግባት ሳያስፈልግ በተግባር ሳይጨባበጡ በመቅረትና በሌላ መልኩ ሰላምታን በመለዋወጥ ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊነቴና እግር ኳስ ተጨዋችነቴ መልዕክቴን አስተላልፋለው፡፡
ሊግ፡- አሁን ደግሞ ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነትህ ህይወት እናምራ፤ የት ተወለድክ? የትስ አደግክ?
ተክለማርያም፡- የተወለድኩትና ያደግኩት ከአዲስ አበባ ከተማ 163 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዝዋይ ወይንም ደግሞ በቀድሞ አጠራሯ ባቱ ከተማ ላይ ነው፡፡
ሊግ፡- የአንተ የትውልድ ከተማ የሆነችው ዝዋይ በምኗ ትታወቃለች? በእግር ኳሱስ ከምርጡ ተጨዋች ብርሃኑ ቃሲም ውጪ እነማንንስ ለማፍራት ችላለች?
ተክለማርያም፡- ኢትዮጵያ ውስጥ የእኔና የመሰሎቼ የትውልድ ከተማ የሆነችው ዝዋይ ከሌሎች ተለይታ የምትታወቅበት ዋናው ነገር ቢኖር ሐይቋ ላይ ባሉት አምስቱ ገዳማቶችና በዓሳ ምርቶቿ ነው፤ ከእዛ ባለፈ ከሐይቋ ውጪም ትልቁ የአበባ ካምፓኒም እዛ ይገኛልና በዚህም ትታወቃለች፡፡ ሌላው ስለ ኳስ ተጨዋቾች ካነሳን ለእኛ ብዙ አርአያ የሆኑን ኳስ ተጨዋቾች የወጡባትም ከተማ ነችና ያም ይገልፃታል፤ ከኳስ ተጨዋቾቹ መካከልም በታዋቂነት ደረጃ ከላይ ስሙን ከገለፅከው ብርሃኑ ቃሲም ውጪ ሌላ ለብሔራዊ ቡድን እስከመጫወት ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው በዳሶ ሆራ እንደዚሁም ደግሞ ለሙገር ሲሚንቶ ይጫወት የነበረው ራህመቶ መሐመድና ግብ ጠባቂውን መሳፍንትን የመሳሰሉት ተጨዋቾችን ያፈራችም ሀገር ነበረችና እነሱን መጥቀስ እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- በልጅነት ዕድሜው የእግር ኳሱን መጫወት ስለጀመረበት መንገድና እስካሁን ድረስም የቤቱ ብቸኛው ስፖርተኛ እሱ ነው ስለመባሉ….?
ተክለማርያም፡- የሰማከው የእውነት ነው፤ ብቸኛው የቤቱ ስፖርተኛ እኔ ነበርኩ፤ አሁንም ድረስ ስፖርተኛው እኔ ነኝ፤ ሌሎቹን ካነሳን አንዱ ወንድሜና አምስቱ እህቶቼ በትምህርትና በሌላ የስራ ሙያ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ናቸው፤ ስለ እግር ኳሱ አጀማመሬ ከሄድን ደግሞ ኳስን መጫወት የጀመርኩት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጨዋቾች በሰፈር ደረጃ የጨርቅ ኳስን በማንከባለል ነው፤ ከዛም እዛ ስጫወት የተመለከተኝ የዝዋይ ከተማ አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ ለምን ወደ እኛ የፕሮጀክት ቡድን ውስጥ መጥተህ ሙከራ አታደርግም የሚል ጥያቄን አቀረበልኝና በእሱ አማካኝነት በግብ ጠባቂነት ሳይሆን በተጨዋችነት ለመሞከር ስሄድ አሁን ላይ ሁሉም የሚሞክረው በተጨዋችነት ነው ስለዚህም የተጨዋችነት ቦታው ስለሞላ በግብ ጠባቂነት ትሞክራለህ ሲለኝ አዎን አልኩትና በእዛው ሙከራን አድርጌ ተያዝኩ፤ በፕሮጀክቱም ለሶስት ዓመት ያህል ቆይታን አድርጌም እዛው ተጫወትኩ፤ ከዛ በኋላም የወረዳም ጨዋታ ነበርና ዝዋይ ከተማን በ17 ዓመት ዕድሜዬ ወክዬ ተጫወትኩ፤ ወዲያውኑም በኦሮሚያ አዘጋጅነት የሚካሄድ የዞን ውድድርም ነበርና ጅማ ላይ በተደረገው ውድድር ምስራቅ ሸዋን ወክዬ ስለተጫወትኩና ጥሩ ብቃትንም በግብ ጠባቂነቴ ስላሳየው የዝዋይ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የሙከራ እድሉን ሰጥቶኝ እነሱን ለመቀላቀል እንድችል ምርጫው ውስጥ ገባው፡፡ በጊዜው ግን ዝዋይ ከተማ በችሎታቸው በጣም ጥሩ የነበሩና ባላቸው ብቃትም አዉት ሻይን ያደረጉትን እነ ሞላ ክፍሉና ለኢትዮጵያ ቡና በኋላ ላይ ገብቶ የተጫወተው እነ ጌቱን የመሳሰሉ ግብ ጠባቂዎችን ይዞ ነበርና በክለቡ የመያዝ እድሉን ሳላገኝ ቀርቼ ከቡድኑ ልቀነስ ቻልኩ፤ የኳስ ህይወት አጀማመሬ እንግዲህ በተወሰነ መልኩ ይሄን ነው የሚመስለው፡፡
ሊግ፡- ከዝዋይ ከተማ የግብ ጠባቂነቱ ሙከራ በኋላ ሳይሳካልህ ሲቀር ወዲያው ኳሱን መጫወቱን አቆምክ… ወይንስ በዛው ቀጠልክበት?
ተክለማርያም፡- ኳሱንማ እንዴትና መቼ ተጫውቼነው የማቆመው፤ ያኔ እኮ ገና ወደ እግር ኳሱ ዓለም በክለብ ደረጃ ታቅፌ ለመጫወት ብቅ ያልኩበትና በእነሱም ለመያዝ ጥረት እያደረግኩ የነበርኩበት ጊዜ ነበር፤ የእግር ኳሱን ከመጫወቴ ጋር በተያያዘ ዝዋዬች እኔን በቡድናቸው ሳያካትቱኝ ሲቀር የቡድኑ አሰልጣኝ የነበረው አብዲ ቡሊ እኔን አስመልክቶ ያደረገው ነገር ቢኖር አሁን ላይ በቡድኑ ባትያዝም በቃ ችግር የለውም ልምምድህን እየሰራህ ቆይ እስከዛ ድረስ ግን አንድ ስራ አግኝቼልሃለው ሲለኝ እኔም በምላሼ ምንድን ነው የምሰራው? ብዬ ስመልስለት ይህቺን ዓመት ብቻ ታገስ እስከዛው ገንዘብ የምታገኝበት ስራ አለ እዛም ሄደ ትሰራለህ አለኝ፤ እኔም በድጋሚ ስራውን ንገረኝ ምንድን ነው የምሰራው ስለው ወደ አዳማ ከተማ ዝዋይን ወክለው ለኮብልስቶን ስልጠና የሚሄዱ ልጆች አሉ፤ ስልጠናው በኢትዮጵያ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥና የእዚህ ስልጠናም ስራ ብር የሚገኝበት ስለሆነ ወደዚያው ሂድ ሲለኝ አይኔን ሳላሽ የዝዋይ ከተማ ላይ ኳሱን የምጫወትበትን ነገር ለጊዜው ተውኩና ወደ አዳማ ለስልጠናውና እንደዚሁም ደግሞ ለስራውም ተጓዝኩ፤ በጊዜውምእዛም ስልጠናውንና ስራውን ሳይ ጥሩ ገንዘብ እንደሚያስገኝ አወቅኩና እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ድረስ አዳማ ላይ ኑሮዬን በማድረግና ስራዬንም ቀጥ አድርጌ በመስራት እስከ ቅዳሜ ከሰዓት ድረስ ስራዬን ሰርቼ ከጨረስኩ በኋላ ዝዋይ ከተማ ላይ የውስጥ ውድድር ተጀምሮ ስለነበር የእዛ ውድድር ተሳታፊ የነበረው የአባይ ሆቴል ባለቤት አንተ በእዚህ ውድድር ላይ ከአዳማ እየተመላለስክ እንድትጫወትልን እንፈልጋለን ስላለችኝ በእዚህ ደረጃ ቅዳሜና እሁድ ጨዋታዬንና ውሉዬን ዝዋይ አድርጌና ሰኞም በለሊት ወደ አዳማ እየተመለስኩ ኳሱን ሳላቆም ልጫወት ትቼያለው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ለመጀመሪያ ጊዜ በክለብ ደረጃ ለመጫወት የቻልከው ለማን ቡድን ነው?
ተክለማርያም፡- ለዝዋይ ከተማ ነዋ! በዚህ ቡድን ውስጥ ታቅፌ ለመጫወት የቻልኩትም በድጋሚ የመሞከር እድሉ ተሰጥቶኝ ነው፤ ከዚህ በፊት ለቡድኑ ሳልያዝ የቀረሁበትን ምክንያት ከላይ ገልጬዋለው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ለቡድኑ የተያዝኩበት ዋናው ምክንያት የኮብልስቶን ስራዬን አዳማ ላይ እየሰራውና በዝዋይ ደግሞ በውስጥ ውድድር ላይ ጥሩ በምጫወትበት ሰዓት ዋንጫ አግኝተንና እኔም ደግሞ የኮከብ ግብ ጠባቂነትን ሽልማት አግኝቼ ስለነበር ሰዎች አሁን ለዝዋይ ከተማ ቡድን መያዝ አለብህ ሲሉኝና ክለቡም በድጋሚ የሙከራ እድሉን ከሁለት ዓመት በኋላ በግማሽ ዓመት ላይ ሲሰጠኝ ለማለፍ በመቻሌ ነው፤ ያኔም ሙከራውን እንዳልፍኩ ክለቡ ለአንድ ዓመት ከግማሽ ወራትበቢጫ ትሴራ ሊያስፈርመኝ ችሏል፡፡
ሊግ፡- ለዝዋይ ከተማ የመሰለፍና የመጫወት እድሉን በወቅቱ ታገኝ ነበር?
ተክለማርያም፡- አዎን፤ ያኔ በቢጫው ትሴራ ባደግኩበት ዓመትም ላይ ነው የቡድናችን አሠልጣኝ የነበረው አብዲ ቡሊ በደንብ ይከታተለኝ ስለነበር እንደ ትላልቅ በረኞቹ ሁሉ እኩል የመጫወትእድሉን ይሰጠኝ የነበረው፡፡ የሁለተኛው ዓመት ላይ ደግሞ በክለባችን ውስጥ የነበሩት ዋና ግብ ጠባቂዎች አንደኛው በለጠ ተስፋዬ ይባላል ወደ ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ በመግባቱና ሁለተኛው በረኛም ሞላ በትልቅ ደረጃ የሚገኝ ግብ ጠባቂ ስለነበርና ወደ ባህርዳር ዩንቨርስቲም ሊገባ በመቻሉ ያን ዓመት ላይ እኔ በቋሚ ግብ ጠባቂነት ለመጫወት ቻልኩ፡፡
ሊግ፡- ከዝዋይ ከተማ በኋላስ ለየት ለየት ቡድኖች መጫወት ቻልክ? ቆይታዎችህስ ምን ይመስላሉ?
ተክለማርያም፡- በክለብ ደረጃ ዝዋይን እንደለቀቅኩ የተጫወትኩባቸው ክለቦች የመጀመሪያው ሼር ኢትዮጵያ ነው፤ እዛም እንደገባው በቅድሚያ የፊርማ 5 ሺ ብር ተሰጠኝ፤ ደመወዜም 500 ብር ነበር፤ ከዛ ውጪም በእዚህ ቡድን ባለሁበት ሰዓት ከፍተኛ ክፍያ ከሚሰጣቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ብሆንም በእዚህ ቡድን የሁለት ዓመት ቆይታዬ ጣቴን የመሰበር አጋጣሚን ከማስተናገዴ ባሻገር ለክለቡም ብዙ የመጫወት እድሉን ያላገኘሁበት ወቅት ስለነበር ጥሩ ጊዜን በቡድኑ አላሳለፍኩም፤ በኋላ ላይም ቡድኑን ያሰለጥን የነበረው አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃም ለእኔ ችሎታ ጥሩ እምነት ያለው ሆኖ ሳለ ለሶስተኛ ዓመት ጥሩ ክፍያ አሰጥቶኝ እንድቀጥል ቢፈልግም እኔ ግን ከገንዘብ ይልቅ ተሰልፌ መጫወትን ስለፈለግኩና ለአሰልጣኙም ከብሩ ይልቅ እንደምታጫውተኝ ማረጋገጫ ስጠኝ በሚለው ነገር ከተወያየን በኋላ ነው በመጨረሻ ሲሳይን አመስግኜው ቡድኑን ለመልቀቅ የቻልኩት፤ ከሼር በኋላ ደግሞ ሌላ የተጫወትኩባቸው ቡድኖች ለሀላባ ከነማ፣ ለአዲስ አበባ ከነማ እና ለሐዋሳ ከነማ ነው፤ ለሀላባ ስጫወት ከአሰልጣኙ ሚሊዮን አካሉ ጋር ተጣልቼ ስለነበር መልካም ያልሆኑ ጊዜያትን አሳልፌያለው፤ እሱ ክለቡን ሲለቅ ደግሞ ጥሩ ጊዜን አሳልፍያለው፤ ከእነዚህ ቡድን ቆይታዎቼ ደግሞ በተለይ ለአዲስ አበባ ከነማ ስጫወት ከወጣት ቡድን አንስቶ እስከ ብሔራዊ ቡድን ደረጃም ተመርጬ የተጫወትኩበት ጊዜ ስለነበር እነዛን ጊዜያቶች አልረሳቸውም፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ግብ ጠባቂነት ክሬዲት የለውም ይባላል? አባባሉን ትቀበለዋለህ?
ተክለማርያም፡- አዎን፤ የእውነትም ክሬዲት የለንም፤ ምክንያቱም አንድ አጥቂ 90 ደቂቃ ጎል ስቶ አንድ ጎል ሲያገባ ህዝቡ ያንን አጥቂ ያሞግሰዋል፤ በረኝነት ግን 90 ደቂቃ ሙሉ ጥሩ ሆነክና ብዙ ኳስ አድነህ አንድ ጎል ሲገባብህ ብዙ ሰው ነው የሚወቅስህና ለዛ ነው የበረኞች ልፋት ሳይቆጠርላቸው በመቅረቱ ክሬዲት የላቸውም የሚባለው፤ በረኞች በዛ ደረጃ በመታየታቸው ሁሌም በጣም ነው የማዝነው፡፡ በረኞች ማለት እኮ ለአንድ ቡድን ዋንኛ ምሰሶዎች እና ትልቅ ኃላፊነትንም የምትሸከምበት ቦታ ማለት ነው፤ ከዛ ውጪም የኃላፊነትም ጥግ ማለት ነውና በእዛ ደረጃ ነው ለግብ ጠባቂዎች ክሬዲት ሊሰጣቸው ይገባዋል የምለው፡፡
ሊግ፡- የግብ ጠባቂነት ሙያውን በጣም ወደከዋል?
ተክለማርያም፡- አዎን፤ ወደ ግብ ጠባቂነቱ ሙያ የመጣሁት በአንድ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ እኔ በተጫዋችነት ለመጫወት መጥቼ ሰው በመጉደሉ ሳቢያ ግብ ጠባቂ ሆኜ ነበር የተጫወትኩት፤ በኋላም በረኝነቱን ወደድኩትና በዛው ቀጠልኩበት፤ ወደ ፕሮፌሽኑም ዘልቄ ከገባው በኋላ በጨዋታ ሜዳ ላይ ቡድኔን ታድጌው ስወጣው ለእኔ የሚሰጠኝ እርካታ አለና ሙያውን ከእዚህ በመነሳትና ለእኔም ራሴን እንድችል በር የከፈተልኝም ስለሆነ በረኝነቱን በጣም ነው የምወደው፡፡
ሊግ፡- በእዚህ ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ቡና በመምጣት የክለቡ ግብ ጠባቂ ሆንሃል፤ ወደ ቡድኑ ገብቶ የመጫወት እልሙ ነበረህ?
ተክለማርያም፡- በጣም እንጂ፤ ጥሩ ጥያቄም ነው የጠየቅከኝ፤ ኢትዮጵያ ቡናን መውደድ የጀመርኩት ከልጅነቴ አንስቶም ነው፤ አንዴም ትንሽ ከፍ ካልኩ በኋላም አስታውሳለሁ 2003 ላይ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ሲያገኝ ከዝዋይ ግጥሚያውን ለመከታተል ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ነበር፡፡ በእዚያን ወቅት የመጨረሻው ቀን ጨዋታ ላይ ቡና የሚጫወተው ከሙገር ክለብ ጋር ነበርና በአጋጣሚ የዝዋይ ልጆች እነ ወንድወሰን በቡድኑ ውስጥ ነበሩና ጨዋታውን ለማየት ለምኜው ና ሲለኝ ከእነሱ ጋር ወደ ስታድየም በመግባት ቡናን እኔ ስደግፈው ነበርና በየትኛውም አጋጣሚ ነው ያኔ ለምቀርባቸው ልጆች ሁሉ የወደፊት አላማዬ ቡና ገብቶ መጫወት ነው፤ ወደ ቡድኑም ገብቼ ክለቡን ውጤታማ ማድረግም እፈልጋለሁ እላቸው ነበር፤ ከዛ ውጪም የአዲስ አበባ ከነማ ቡድን ውስጥ እያለሁ እንኳን ለቡድኑ በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ሁሉ እየተጫወትኩ የቡና ጨዋታ ብዙ ሳያመልጠኝ የምከታተልበትም ጊዜ ነበርና ያንን ፈፅሞ አልረሳውም፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና በቋሚ ተሰላፊነት እየተጫወትክ ይገኛል፤ ለቡድኑ መጫወት መቻል የተለየ ስሜት ይሰጣል?
ተክለማርያም፡- አዎን፤ ለቡና አይደለም ተጫውተህ ገና ለሟሟቅ ወደ ሜዳ ስትገባ የተለየ የደስታ ስሜት ነው የሚሰማህ፤ ከዛ ውጪም የደጋፊው ህብረ ዜማና አጨፋፈርም እምባ እንዲመጣብህም ያደርግሃል፤ ይሄን ደግሞ እኔ ገና የቡድኑ ደጋፊ ከነበርኩበት ጊዜ አንስቶ ክለቡን የተመለከትኩበት ሁኔታ ስላለና ለእዚህ ቡድንም የመጫወት እልሜንም ያሳካው ስለሆነ ለቡድኑ ለመጫወት መቻሌ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡፡
ሊግ፡-ለኢትዮጵያ ቡና በቋሚ ተሰላፊነት እንደምትጫወተው ሁሉ በረከትም ተሰልፎ የሚጫወትበት ወቅት አለ፤ አንተ ያኔ የሚኖርህ ስሜት ምንድን ነው?
ተክለማርያም፡- ለኢትዮጵያ ቡና በቋሚ ተሰላፊነት ስጫወትም ሆነ የተጠባባቂ ተጨዋች በምሆንበት ሰአት እኔ ሁሌም ያለኝ ስሜት አንድ አይነትና ተመሳሳይ ነው፤ በረከትም እንደዛው ነው፤ በእዚሁ ጉዳይ ላይም ሁለታችን የምንነጋገርበትና የምንግባባበትም ጉዳይ አለ፤ ከበረከት ጋር በቡና ቡድን ውስጥ ስንጫወት እሱ የቡድኔ አጋር ተጨዋች ብቻ ሳይሆን ከጠበቀ የጓደኝነት ግንኙነታችን ባሻገር ወንድሜም የሆነ ተጨዋች ነው፡፡ ወደ ሜዳ ለጨዋታ ስንገባ እሱ የተሰለፈ ቀን እኔ ነኝ ግምባሩን ስሜውና ውሃ ሰጥቼውም እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ይሁን ብዬው ወደ ሜዳ የማስገባው፤ እኔም በተቃራኒው ስገባ ሜዳ ያለውን ጥሩ ታያለህ፤ ይሄ ማንም ላይም አይታይም፡፡ ይሄ ማለት ምንድነው ሁለታችንም ፕሮፌሽኑን በስርአት የተረዳነው ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ተክለማርያም ዛሬ ትጫወታለህ ከተባልኩኝ የእኔ ስራ ሁሌ ዝግጁ ሆኜ ቡድኑን ማገልገል ብቻ ነው፤ በእዚህ ጨዋታ ላይ በረከት ወይንም ደግሞ ተክለማርያም ይጫወታል የሚለው ስልጣን የአሰልጣኙ ስለሆነ የእሱን ትዛዝ ነው የምናስከብርለትና ቡድኑንም ለመጥቀም የምንጫወተው እንጂ በረከት ስለገባ ብቻ በህይወቴ የእሱን ጥሩ አለመሆንና መጥፎ ነገርንም በፍፅም የማስብ አይደለም፤ እሱም እንደእኔው ነው የሚያስበው፤ በእዚሁም ነው እየተጓዝን ያለነው፡፡
ሊግ፡-የኢትዮጵያ ቡና የፕሪምየር ሊጉ ጉዞአችሁ ምን ይመስላል?
ተክለማርያም፡- በፕሪምየር ሊጉ ባለን የእስካሁኑ ጉዞ በግሌ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ይሄ ቡድን ገና በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ በአዲስ አሰልጣኝ፣ በአዲስ የጨዋታ ታክቲክና አሰልጣኙም ባማያውቃቸው አዳዲስ ተጨዋቾች ጭምር ለውድድር የቀረበም በመሆኑ ነው፤ ከዛ አኳያ አሁን ላይ በቡድኑ ውስጥ ያሉት ተጨዋቾች በእዚህ አጭር ጊዜ የእሱን ታክቲክ ለመተግበር በመሞከር ይህን የውጤት ጉዞ ማድረጋቸው መጥፎ የሚባል አይደለም፤ ልጆቹ አሁን ላይ ይሄን ከሰሩ በቀጣይነት ደግሞ ብዙ ነገር ሊሰሩ ስለሚችሉ ጉዞአችን ጥሩ ነው፡፡
ሊግ፡-ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ካደረጋቸው ጨዋታዎች አስቆጪው የቱ ነው?
ተክለማርያም፡- ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎቻችን መካከል ለእኛ በጣም ያስቆጨንና ያበሳጨን ግጥሚያ በ17ኛው ሳምንት ከጅማ አባጅፋር ጋር ያደረግነውና በመጨረሻ ሠአት ላይ የድል ግብ አስቆጥረን ወዲያውኑ ግብ ተቆጥሮብን አቻ የተለያየንበት ጨዋታ ነው፡፡ ያ ግጥሚያ በጣም ጥሩ የነበርንበትና የአሰልጣኙንም ታክቲክ የተገበርንበት ሆኖ ሳለ ባለቀ ሰዓት ግብ ተቆጥሮብን አቻ ስንለያይ በኳስ ህይወቴ እንደዛ ቀን ተበሳጭቼ አላውቅምም ነበርና ከመናደዴ ባሻገር ለሁለት ቀን ያህልም እንቅልፍ ያልተኛሁበት ነበር፡፡
ሊግ፡-በፕሪምየር ሊጉ በጣም የተፈተናችሁበት ጨዋታስ?
ተክለማርያም፡- ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረግነው ነው፤ ዘንድሮ ከዛ ጨዋታ ውጪ ኳስ ተቆጣጥሮ ያስቸገረው ቡድን ማንም የለም፡፡
ሊግ፡-ኢትዮጵያ ቡና ከመሪው ክለብ በ8 ነጥብ ተበልጦ ይገኛል፤ ቀጣይ የሊጉ ጉዞው ምን ይሆናል?
ተክለማርያም፡- ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ካደረጋቸው ጨዋታዎች ውስጥ በጣም ተቸግሮ ወይንም ደግሞ ተበልጦ የወጣበት ጨዋታ አንድ ብቻ በመሆኑና ክለቡም በየጊዜው ከጨዋታ ወደ ጨዋታም ሲያመራ እየተሻሻለ የመጣም ስለሆነ ሊጉ ሲያልቅ ክለባችንን በእርግጠኝነት የማገኘው ስፍራ በጥሩ ውጤት ላይ ሆኖ እንደሚያጠናቅቅ ነው፤ ውድድሩን ሲፈፅምም ከመሪው ጋር ከአሁን በሚያንስ የነጥብ ልዩነት እንጂ በእዚህ የነጥብ ልዩነት ሆኖ አይጨርስም፡፡
ሊግ፡-የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይም ሆነ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ በተለያዩ አሰልጣኞች ሰልጥነሃል ከእነዛ ጋር የአሁኑን አሰልጣኝህን ካሳዬ አራጌን ስትመዝነው…?
ተክለማርያም፡- አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን እንዴት እንደምገልፀው አላውቅም፤ አሁን አብሬው ስላለሁና እሱን ለማሞገስ ሳይሆን በሁሉምመልኩ እሱ በጣም የተለየ እና የሚገርም አይነት አሰልጣኝ ነው፤ ከዛ ውጪ ጥሩ ከማሰልጠኑ ባሻገር በተለይ ደግሞ ለተጨዋቾች ኃላፊነትን /ሪስክ/ የሚወስድበት ነገር ይለየዋልና ለእሱ ምስጋና አለኝ ፡፡
ሊግ፡- ወደ ግብ ጠባቂነቱ ስትመጣ የአንተ ተምሳሌት የነበረው ተጨዋች ማን ነበር?
ተክለማርያም፡- በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ለዓለም ብርሃኑ ነበር፤ ከውጪዎች ደግሞ ኢማኑኤል ኑዌር ነው፡፡

ሊግ፡- የቀጣይ ጊዜ የእግር ኳስ ህይወቱን የት ደረጃ ላይ ለማድረስ ጥረት እንደሚያደርግ…..?
ተክለማርያም፡- የእግር ኳስን በግብ ጠባቂነቱ ላይ አጥብቄው ስጀምር የመጀመሪያው ህልሜና ግቤ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ተመርጬ መጫወት ነበር፡፡ ሃገሬን ወክዬም መጫወትን እፈልጋለው፡፡ እኔም እስካሁን ባለኝ የስፖርት ህይወት ቆይታም ለብሄራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ተመርጪያለሁ፡፡ ለአንድ ጊዜም በዋናው ቡድን ደረጃ ተጫውቻለው፤ ወደፊት ግን ራሴን እያሻሻልኩ ስለምሄድ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር በበርካታ ጨዋታዎች ላይ ከመጫወት ባሻገር ፕሮፌሽናል ግብ ጠባቂ የመሆንም እልም አለኝ፡፡
ሊግ፡-ጎሜዝ ሲሉ ሰማን የአንተ ስም ነው ወይንስ የሌላ? ምን ማለትስ ነው…?
ተክለማርያም፡- ስሙ የእኔ ነው፤ ግን ቅፅል ስሜ እንጂ ዋናው ስሜ አይደለም፤ ይህን ስም ያወጣልኝም ለዝዋይ ከተማ የዋናው ቡድን ለመጫወት እንዳደግኩ ትንሽ ልጅ ነበርኩና አንድ የዋናው ቡድን የመሃል ሜዳ ተጨዋች ነው ደነቦ ባኩ ይባላል፡፡ ለተጨዋቾች ዝም ብሎ ቅፅል ስም ያወጣ ነበርና ቁጭ ብለን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን ስንከታተል ግብ ጠባቂው ጎሜዝ ያኔ የቶተንሃም በረኛና ብቃቱም በጥሩ ደረጃ ለይ ይገኝ ስለነበርና ፀጉሩንም ፍላት ይቆረጥ ስለነበር እኔን ይሄ ልጅ ጎሜዝን ነው የሚመስለው ብሎ ሲናገር ጎሜዝ የሚለው ስም ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀድቆልኝ ስሙን ልጠራበት ቻልኩ፡፡
ሊግ፡-የእግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮስ…?
ተክለማርያም፡- ወላጅ አባቴም ወንድሜም ሹፌሮች ነበሩና እንደእነሱ ነው ሹፌር እሆን የነበረው፡፡
ሊግ፡-ስለውሃ አጣጪ እና ስለትዳር ህይወትህ?
ተክለማርያም፡- የትዳር ህይወቴ በጣም ጥሩ ነው፤ ባለቤቴም ኤደን አድማሱም ትባላለች፤ ናታኒም የተባለ የአንድ ልጅም አባት ነኝ፡፡
ሊግ፡-ከባለቤቱ ጋር ስለተዋወቁበት መንገድ….?
ተክለማርያም፡- ከባለቤቴ ኤደን ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅንበት መንገድ በጣም የሚያስገርም ነው፤ ያኔ ለሃዋሳ ከተማ ክለብ ነበር የምጫወተው፤ ይሄን ጊዜ ታድያ ከቡድናችን ተጨዋቾች ዳዊት ፍቃዱ አቡቲ እና ሌላው ተጨዋች ፍቅረየሱስ ተወልደ ችምስ ጋር በመኪና እየሄድን ሳለ እሷ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበረችና መንገድ ላይ በምትጓዝበት ሰአት ሌቦች ሃብሏን ሲነጥቋት ተመለከትኩ ወዲያውኑም ያንን ተመልክቼ ነበርና ከመኪና ላይ ወርጄ ላስመልስላት ቻልኩ፡፡ በእዚያውም ተዋወቅኳትና እንዲህ እያልን ነው እየተግባባን በመምጣታችን ለእዚህ የፍቅር ህይወትና ለትዳርም ለመብቃት የቻልነው፡፡
ሊግ፡-ባለቤትህን ከአንተ ጀርባ ስትገልፃት….?
ተክለማርያም፡- ባለቤቴ ሄደን በኳሱ ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃ ብዙ ነገሮችን ያደረገችልኝ ስለሆነች ለእኔ ሁሉም ነገሬ ናት፤ ምክንያቱም እሷን ካገኘሁበት ሰአት ጀምሮ ነው በሁሉም ነገር ልለወጥ የቻልኩት፤ ከጥንካሬ ጀርባ እሷም በዋናነት አለችና በጣም ላመሰግናት እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….?
ተክለማርያም፡- በእግር ኳሱ ለዛሬ እዚህ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረሴ ያሰለጠኑኝን አሰልጣኞች ቤተሰቦቼን ባላቤቴን እና ከሁሉ በፊት ደግሞ ፈጣሪዬን አመሰግናለው፡፡

https://t.me/LEAGUESPORT

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P