በነገው ዕትም ከሀገር ውስጥ ስደተኛውና ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ነገ 9 ሰዓት በአዳማ ይከሰታል…. ከሳምንታቶች በፊት ሊካሄድ ተብሎ ለሌላ ጊዜ እንዲራዘም የተወሰነና ነገ ሊካሄድ ሰአታት ስለቀረው የደርቢ ፍልሚያ ዙሪያ ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ቆይታ ያደረገው የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ “ኢትዮጵያ ቡናን ለማሸነፍና ክለባችንን ከፍ ለማድረግ ተዘጋጅተናል” ሲል የቡናማዎቹ አምበል በረከት አማረ በበኩሉ “ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሸነፍ ብዙ ነገሮችን ያስተካክላል ብዬ አምናለሁ” በማለት ለድል እንደተዘጋጁ ፎክረዋል…
.ቃለምልልሱን ይዘናል….
……በውጪ ዘገባ ደግሞ:…..
** 72 ሚሊዮን ፓውንድ የወጣበት የማን.ዩናይትዱ ራስመስ ሆይሉንድ የመጀመሪያ የሊግ ግቡን አስቶንቪላ ላይ አስቆጥሯል…ዴንማርካዊው እስካሁን ለምን ተቸገረ..? መረጃዎችን ይዘናል…..
** ለተከላካይ ክፍሉ ቅድሚያ ሰጠ ስለተባለው የአርሰናል የዝውውር እቅድ የምንላችሁ አለ….
** ቸልሲ ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚገባ ተረጋግጧል የአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖሺቲኖ እቅድ ዙሪያ መረጃዎችን አካተናል….
** የ2023/24 የውድድር አመት አጋማሽ ኮከቦች እነማን ናቸው ..? ሐረጃዎችን ይዘናል….
** ሰር ጂም ራትክሊፍ 25 በመቶውን የማን.ዩናይትድ ድርሻ በእጃቸው አስገብተዋል…ውሉ ለዚህ ታሪካዊ ክለብ ያለው ፋይዳ ዙሪያ የምንላችሁ አለ….
** የጋሬዝ ቤል የማይረሱ አጋጣሚዎችና የጥበበኛው አጥቂ ንዋንኩ ካኑን ለአርሰናል የተቆጠሩ አስገራሚ ግቦችን በተመለከተ መረጃ ይዘናል
….. እናም ሌሎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አካተናል …
ነገ ጠዋት ቡናዎን ሲፈልጉ ማኪያቶዎን ወይም ያሻዎት ሌላ ከሆነ ልብዎ የፈለገውን እየተጎነጩ ሊግን በእጅዎ ያስገቡ…
….ቅዳሜና እሁድዎ የሚደሰቱበት ቀኖችዎ ይሁኑ….