Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የሸገር ደርቢውን ተጠባቂ ጨዋታ ማን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል? ተጋጣሚዎች፡-ኢትዮጵያ ቡና VS ቅ/ጊዮርጊስ


ቀን፡- እሁድ ሚያዝያ 27/2011
ሰዓት፡-10፡00
ቦታ፡- አዲስ አበባ ስታዲየም


“የሸገር ደርቢውን እንደሌሎች ጨዋታዎች እንመለከተዋለን፤ ቅ/ጊዮርጊስንም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን”
ሄኖክ ካሳሁን /ኢትዮጵያ ቡና/
“የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ስለማንሳት የሂሳብ ስሌት አንሰራም፤ በሸገር ደርቢው ቡናን በበላይነት እናሸንፈዋለን”
አስቻለው ታመነ /ቅ/ጊዮርጊስ/


የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ የሁለቱ ክለብ በርካታ ደጋፊዎች እና ብዙ የስፖርት አፍቃሪዎች በተገኘበት ነገ ከ10፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል፤ የሁለቱን ክለቦች ይኸውን ጨዋታ ለመመልከት በርካታ የስፖርት አፍቃሪ ወደ ሜዳ የሚተም ሲሆን የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ስታዲየሙ ሊይዝ የሚችለውን የትኬት መጠንን በማወቅ እና አሻሻጡንም በማሳመር እንደዚሁም ደግሞ የአዲስ አበባ ስታዲየም በሮችንም አስቀድሞ በሚከፈትበት ነገር ላይ ከወዲሁ ውሳኔ በመስጠት ጨዋታው በተሳካ ሁኔታ የሚካሄድበትን ነገር ሊፈጥር ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ ክለቦች እሁድ ዕለት የሚያደርጉት የሸገር ደርቢው ጨዋታ በሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች እና ተጨዋቾች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ሲሆን አንዳቸው አንዳቸውንም አሸንፈው ከሜዳ ለመውጣት በሚገባ መዘጋጀታቸውንም ለማወቅ ችለናል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ ክለቦች በሸገር ደርቢው የሚያደርጉት ጨዋታ እስከዛሬ ለበርካታ ጊዜያቶች የተገናኙ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ 19 ጊዜ በማሸነፍ 13 ጊዜ አቻ በመለያየት እና 7 ጊዜ በመሸነፍ ከተጋጣሚው ቡና የተሻለላፄጽ ማስመዝገብ ችሏል፤ ኢትዮጵያ ቡና ከቅ/ጊዮርጊስ የሚያደርጉት የሸገር ደርቢው ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ በደረጃው ሰንጠረዥ 3ኛ ስፍራ ላይ ሆኖ ኢትዮጵያ ቡናን የሚገጥም ሲሆን ቡና ደግሞ 8ኛ ላይ ሆኖ ቅ/ጊዮርጊስን የሚፋለምበት ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናና የቅ/ጊዮርጊስ ክለቦች ነገ እሁድ የሚያደርጉት ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ከመሪው ቡድን ራቅ ባለ ነጥብ የሚያካሂዱት ጨዋታ ሲሆን በእዚህ ደረጃ ላይ ሆነው ሲጫወቱም የመጀመሪያቸው ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስን የሸገር ደርቢ ጨዋታ አስመልክተን እንደዚሁም ደግሞ ስለ ቡድኖቻቸው ወቅታዊ አቋም እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ቡና አማካዩን ሄኖክ ካሳሁንን ከቅ/ጊዮርጊስ ደግሞ ተከላካዩን አስቻለው ታመነን አናግረናቸው ሁለቱም ተጨዋቾች የሚከተሉትን ምላሻቸውን ሊሰጡን ችለዋል፤ ተከታተሏቸው፡፡

ሄኖክ ካሳሁን /ኢትዮጵያ ቡና/
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን የሁለተኛው ዙር ላይ ተቀላቅለሃል፤ እስካሁን ያለህ ስሜት ምን ይመስላል?
ሄኖክ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው ዙር ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ያለኝ ስሜት ደስ የሚል እና ጥሩ ነው፡፡ የቡድኑን መለያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ተጨዋች ለብሶ መጫወት እና በእዛ ምርጥ ደጋፊም ፊት የራሱን ማንነት ማሳየት ስለሚፈልግ እና ከደጋፊውም አደናቆትን ማግኘት ስለሚፈልግ የቡድኑ ተጨዋች መሆኔ የተለየ የደስታ ስሜትም ነው የፈጠረብኝ፤ከእዛ ውጪም ጥሩ አቀባበል አድርገውልኝም ነበር የገባሁትና በእዚህ አሁንም ድረስ ልዩ ስሜት ይሰማኛል፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማህን ያኖርከው ቡድኑ ተደጋጋሚ ውጤቶችን ባጣበት ሰአት ላይ ነበር፤ እንደቡድኑ አዲስ ተጨዋችነትህ የውጤት እጦቱን በምን መልኩ ነው መግለፅ የምትፈልገው?
ሄኖክ፡- ኢትዮጵያ ቡናን ከሽረ እንደስላሴ መጥቼ ስቀላቀል ክለቡ አስቀድሞ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ በተደጋጋሚ ሽንፈቱ ጥሩ ያልሆነ ውጤት በሚያስመዘግብበት ጊዜ እና ከነበረበት የላይኛው ደረጃም በማሽቆልቆል ወደታች እየወረደ በነበረበት ወቅት የተመዘገበው ውጤት ቡናን የማይገልፀው እና በክለቡም ብዙ ያልተለመደ ስለነበር ለደጋፊው እና ለቡድኑ ተጨዋቾች ነገሮች ሁሉ አሳዛኝ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፤ ያም ሆኖ ግን እኔ ወደ ቡድኑ ከመጣሁበት ጊዜ አንስቶ ደግሞ የሁለተኛው ዘር ላይ በተደረጉት ጨዋታዎች ላይ የተመዘገቡት ውጤቶች በቂ እና ብዙም መጥፎ የሚባሉ ባይሆኑም እንደ ቡና ትልቅነት ግን በውጤታማነታችን ላይ ብዙ የሚቀረን ነገር አለ፡፡ ስለዚህም የቀሪዎቹ ስምንት ጨዋታዎቻችን ላይና በጥሎ ማለፉም ግጥሚያዎቻቸውን ላይ ለእዚህ ታላቅ ቡድን አንድ ነገርን ሰርተን ማለፍ የግድ ነው የሚለን፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና ባህር ዳር ከተማን በሰፊ ግብ ባሸነፈበት ሳምንት አንድ ለዜሮ ተሸንፏል፤ ጨዋታው ምን መልክ ነበረው? እንዴትስ ለሽንፈት በቃችሁ?
ሄኖክ፡- ከአዳማ ከተማ ያደረግነውን ጨዋታ ምንም እንኳን በሽንፈት ብናጠናቅቅም በእንቅስቃሴው በኩል እኛ የተሻልን ነበርን፤ ያም ሆኖ ግን ጎል የማስቆጠር ችግራችንእኛን ለሽንፈት ዳርጎናል፡፡ በተለይ የአጥቂው አቡበከር ናስር በቅጣት ለቡድናችን አለመጫወትመቻሉም ከፍተኛ ተፅዕኖን ፈጥሮብንም አልፏል፤ በሸገር ደርቢውም የአቡበከር አለመኖር ይጎዳናል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያን ትልቁ የሸገር ደርቢ ጨዋታ እሁድ በአስር ሰአት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ታደርጋላችሁ፤ስለ ጨዋታው ምን ትላለህ? የደርቢውን ግጥሚያስ ማን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል?
ሄኖክ፡- ኢትዮጵያ ቡናና ቅ/ጊዮርጊስ እሁድ የሚያደርጉት የሸገር ደርቢ ጨዋታ በሁለቱም ክለቦች ዘንድ ከወዲሁ በጉጉት የተጠበቀ ሲሆን ጨዋታውም ጥሩ ፉክክር የሚደረግበት ይሆናል፡፡
የእሁዱን የሸገር ደርቢ ጨዋታም ማን ያሸንፋል ለሚለው ጥያቄም በእግር ኳስ ላይ ማናቸውንም ግጥሚያዎች ለማድረግ ወደሜዳ የምትገባው ጨዋታውን አሸንፈህ 3 ነጥብ ይዘህ ለመውጣት ነውና አሁን ላይ ሆኜ ስለ ውጤቱ እንዲህ ነው ማለት ባልችልም የጨዋታው አሸናፊ ለመሆን ግን የምንችለውን ሁሉ ጥረትን እናደርጋለን፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ከእዚህ ቀደም በአብዛኛው ይካሄድ የነበረው ሁለቱም ቡድኖች በጥሩ ውጤት ላይ በሚገኙበት ሰአት እና የሊግ ዋንጫውንምለማንሳት የተመቻቸ እድል በነበረላቸው ሰአት እና አጓጊነቱም ተጠባቂ በነበረበት ሁኔታ ላይ ነበር፤ እሁድ የሚገናኙት ግን በእዛ ደረጃ ላይ ሆነው አይደለምና በእዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ?
ሄኖክ፡- ኢትዮጵያ ቡናና ቅ/ጊዮርጊስ ሁሌም ቢሆን ውጤት አጡም አገኙም እርስ በርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ለሁለቱም ክለብ ደጋፊዎችም ሆነ ለተጨዋቾቻቸው ልዩ ትርጉም ያለው ስለሆነ የእሁዱም የሸገር ደርቢ ጨዋታ ተጠባቂነቱ እና አጊጓነቱ አሁንም ተመሳሳይ እንደሆነ ነው እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው፤በሸገር ደርቢ ጨዋታውም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊም ሆነ ተጨዋቹ በቅ/ጊዮርጊስ ተሸንፎ መውጣትን አይፈልግም፤ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊም ተጨዋቹም በኢትዮጵያ ቡና ተሸንፎ መውጣትን ስለማይፈልግ የእሁዱ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ለሁለታችንም በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ያማረ ይሆንልናል ብዬም ነው እየጠበቅኩት ያለሁት፡፡
ሊግ፡- ከቅ/ጊዮርጊስ የሚኖራችሁ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ለአንተም የመጀመሪያህ ይሆንልሃል፤ በእዚህ የደርቢ ጨዋታ ላይ መሰለፍ መቻል ምን ስሜትን ይፈጥርልሃል?
ሄኖክ፡- ኢትዮጵያ ቡና ከቅ/ጊዮርጊስ በሚያደርገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ መጫወት መቻል የሚሰጠውን የደስታ ስሜት ከእዚህ በፊት የሌላ ክለብ ተጨዋች ሆኜ ከምሰማቸው ነገሮች እና ሁለቱ ቡድኖችም እርስ በርስ ሲጫወቱ የተመለከትኳቸው ሁኔታዎች ስላሉ የእሁዱ ጨዋታ ላይ እንደ አሰልጣኞቻችን የጨዋታ ፎርሜሽንበታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን የመጫወት እድል ባገኝ የሚፈጠርብኝ የደስታ ስሜት በጣም ከፍተኛምነው የሚሆነው እና እሁድን ጋጉቼም እጠብቀዋለሁ፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው ዙር ከመምጣትህ አኳያ ቡድኑን በሚገባ ጠቅሜዋለው ብለህ ታስባለህ?
ሄኖክ፡- በፍፁም፤ የኢትዮጵያ ቡናን ከመቀላቀሌ ለክለቡ የተጫወትኳቸው ጨዋታዎች ገና 3 እና 4 ከመሆናቸው አኳያአሁን ላይ ቡድኑን በሚገባ ጠቅሜዋለሁ በምልበት ደረጃ ላይ ገና አልደረስኩም፤ ቡናን መጥቀሜና አለመጥቀሜም የሚረጋገጠው እስከመጨረሻው ሳምንታት ድረስ በሚሰጠኝ የመሰለፍ እድል ላይ በማሳየው ብቃቴ ነውና አዲሱን ክለቤን በሚገባ ለመጥቀም እና ብሎም ደግሞ ጠንክሬ በመስራትም የቡድኑ ስኬታማ እና ውጤታማም ተጨዋች ለመባል እንደዚሁም ደግሞ ክለቡንም ለውጤት ለማብቃት የሚቻለኝን ነገር ሁሉ አደርጋለሁ፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና ቀጣዮቹን የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች የሚያደርገው ምን ውጤት ለማምጣት ነው?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን አሁን ላይ በርካታዎቹ ክለቦች በውጤት ደረጃ ከመቀራረባቸው አኳያ እከሌ የተባለው ቡድን ሻምፒዮና ይሆናል የምትልበት ጊዜ ላይ ባለመሆኑ ቡድናችን ቀሪዎቹን ጨዋታዎች የሚያደርገው ሁሉንም ግጥሚያዎች ለማሸነፍ ነው፤በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ ውጤት ለማምጣትም እንታገላለን፡፡ በኋላ ላይም የሚመጣውን ማናቸውንም ውጤት እንቀበላለን፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና የሊግ ዋንጫውን የማንሳት እድሉ ስለጠበበ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ጥሎ ማለፉ ጨዋታ አድርጓል ይባላል፤ እውነት ነው?
ሄኖክ፡- በፍፁም፤ እኛ አሁንም ትኩረት አድርገን እየሰራን ያለነው ሊጉ ገና ያልተጠናቀቀ እና ቀሪ ስምንት ጨዋታዎችም ስላሉት በእነዛ ግጥሚያዎችላይ ደግሞ አንድ ቡድን ሙሉ ጨዋታውን የሚያሸንፍ ከሆነም 24 ነጥብን የሚያገኝ በመሆኑ በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ ያለምንም ተስፋ መቁረጥ ስሜት እስከመጨረሻው ጨዋታዎቻችን ድረስ ሜዳ ገብተን በመጫወት የሚመጣውን ማናቸውንም ውጤት ልንቀበለው ነው የተዘጋጀነው፤ ስለ ጥሎ ማለፉ ጨዋታ ደግሞ ቀጥሎ በማሰብ እና ለግጥሚያውም ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ቡድናችንን ወደ ኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ ለመመለስ እንዘጋጃለን፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ ስትገባ ከሌሎች ቡድኖች አንፃር ምን የተለየ ነገርን አይተሃል? ለእዚህ ቡድን በሜዳ ውስጥ እንቅስቃሴስ ምን የተለየ ነገርን መስራትስ ትፈልጋለህ?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ስገባም ሆነ ከእዚያ በፊት በነበርኩባቸው የተጨዋችነት ዘመኔ ላይ ስለቡና በሚገባ የተረዳሁትና ያወቅኩት ክለቡ ኳስን ተቆጣጥሮ እና ፖሰስ አድርጎም የሚጫወት ስለመሆኑ ነው፤ ወደዚህ ቡድን ስትመጣ የቡድኑን አጨዋወት እንድትከተልም ይፈለጋልና አሁን ይሄንን እንቅስቃሴ የሌላ ቡድን ተጨዋች ሆኜም አንዳንድ አሰልጣኞች የጨዋታ ባህሪዬን ተመልክተው እንድጫወት ይፈልጉም ነበርና ይሄንን በቡና ቡድን ቆይታዬ ውጤታማ ግልጋሎት መስጠቱ ላይ ቀጣይ በሚኖሩን ጨዋታዎች ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት እንደምችል እና ከክለቡ አጋር ጓደኞቼም ጋር ስንቀናጅ ለቡድኑየድል ውጤት የሚያገኝበትን ነገር መስራት እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ የመጫወት እድሎችን ባገኘክባቸው ጥቂት ጨዋታዎች ላይ ምን ማሻሻልን ትፈልጋለህ?
ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ የገባሁት በቅርቡ ስለሆነ እስከአሁን ማሻሻል ስላለብኝ ነገሮች ብዙም ማየት አልተቻለኝም፤ ያም ሆኖ ግን ክፍተቶች ካሉብኝ እኔን የሚቀርቡኝ ሰዎች ስላሉ እነሱ ስለሚነግሩኝ ያለኝ ጥሩ ነገር ላይ የእነሱን ጨምሬ በኳሱቡድኔን በሚገባ መጥቀምና ጥሩም ደረጃ ላይ ማድረስ እፈልጋለሁ፤ የራሴንም የኳስ ብቃት በጣም አሳድገዋለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለአንተ ክስተቱ ቡድን ማን ነው?
ሄኖክ፡- መቐለ 70 እንደርታ፤ እነሱ ጠንካራ ቡድን አላቸው፤ ሲዳማ ቡናም ጥሩ ቡድን ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችን በአንድ ቃል ግለፅ?
ሄኖክ፡- “ፍቅር” ነው የሚባሉት፤ ሲደግፉም ያምራሉ፤ የስቴዲየሙም ድባብ ናቸው፡፡
ሊግ፡- የትንሳኤ በዓል እንዴት አለፈ?
ሄኖክ፡- የፋሲካ /የትንሳኤ/ በዓልን ዘንድሮ ያሳለፍኩት እንደ እግር ኳስ ተጨዋችነቴ ከቡድኔ አጋር ጓደኞቼና በቀናቶች ልዩነትም ከቤተሰቦቼም ጋር ቢሆንም በዓሉ በጥሩ እና በመልካም ሁኔታ ሊያልፍ ችሏል፤ በእዚህ አጋጣሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለቡና ደጋፊዎች እንደዚሁም ለቤተሰቦቼ አሁንም የዳግማዊ ትንሳኤ በዓል ስለሚከበር እንኳን አደረሳችሁ ልላችሁ እወዳለው”፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….
ሄኖክ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ስላለብን የእሁድ ተጠባቂ የሸገር ደርቢ ጨዋታ በሁለታችንም በኩል አንዱ በአንዱ ሽንፈት ሲገጥመው በደጋፊዎቻችንም ሆነ በተጨዋቾቻችን አካባቢ ንዴቶች ቢኖሩም የሚመዘገበው ውጤት በኳስ የሚያጋጥም ስለሆነ ያን በፀጋ ተቀብሎ መሄድ የሁለታችንንም ታላቅነት ያሳያል እና ይሄን እሁድ ዕለት ልንመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

አስቻለው ታመነ /ቅ/ጊዮርጊስ/
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ የሊግ መሪውን መቐለ 70 እንደርታን አሸንፎ የደረጃ መሻሻልን አሳይቷል፤ ጨዋታው ምን መልክ ነበረው?
አስቻለው፡- ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የነበረን የማክሰኞው ጨዋታ በሁለታችንም ክለቦች መካከል ጥሩ የመሸናነፍ ፉክክር የተደረገበት ግጥሚያ ሲሆን ከጨዋታው በፊት ስለ ተጋጣሚያችን ጥንካሬ ያለን ግምት ጥሩ ስለነበርና ለእነሱም ከፍተኛ ትኩረትን በመስጠትምየተጫወትነው ስለነበር በከፍተኛ የማሸነፍ ፍላጎት ወደ ሜዳ መግባታችን እናይህን ጨዋታ ማሸነፍ መቻል ደግሞ ከመሪው ክለብ ጋር ያለንን የነጥብ ልዩነትም የሚያጣብልን ስለነበርበማጥቃት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴን አድርገን ጨዋታውን አሸንፈን ልንወጣበት ችለናል፡፡
ሊግ፡- ተጋጣሚያችሁን መቐለ 70 እንደርታን እንዴት አገኘሃቸው?
አስቻለው፡- መቐለ 70 እንደርታ ጠንካራ እና ጥሩ ቡድን ነው፤ እነሱን ማሸነፍ መቻላችንምየእኛንም ጥንካሬ ያሳየ ነው፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታን ማሸነፍ መቻላችሁ ለእናንተ የሰጣችሁ የተለየ ትርጉም እና ጥቅም አለ?
አስቻለው፡- አዎን፤ መቐለ 70 እንደርታን ማሸነፍ መቻላችን ለእኛ የሰጠን ጥቅምም ትርጉምም ይህንን ግጥሚያ ማሸነፍ መቻል ቡድናችን የሊግ ዋንጫውን ለማግኘት የሚያስብ ከመሆኑ አንፃር ነጥቡን አጥብቦ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ወደ ላይ ለመምጣት ይፈልግ ነበርና ይሄ ነው ከመሪው ክለብ ጋር ጨዋታው ለእኛ ወሳኝ እና የተለየም ትርጉም የነበረው፡፡
ሊግ፡- የፕሪምየር ሊግ መሪውን መቐለ 70 እንደርታን ስታሸነፉ የድሉን ግብ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አካባቢ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረሃል፤ ያን ጊዜ የፍፁም ቅጣት ምቱን ልትመታ ስትሄድ እና መትተህ ግቧን ካስቆጠርክ በኋላ ምን ተሰማህ?
አስቻለው፡- ቅ/ጊዮርጊስ መቐለ 70 እንደርታን ድል ባደረገበት ጨዋታ የክለባችን የመጀመሪያ የፍፁም ቅጣት ምት መቺ እኔ ከመሆኔና ከእዚህ በፊትም በፍፁም ቅጣት ምት ግብ ያስቆጠርኩ ተጨዋች ስለሆንኩኝ የፍፁም ቅጣት ምትን ልመታ ስሄድ ያለምንም ስጋት ነው ወደ ስፍራው በማምራት ግቧን ለማስቆጠር የቻልኩት፤ የፍፁም ቅጣት ምቱን ልመታ ስሄድም የእኛ ቡድን ተጨዋች ሪቻርድ ኳሷን ይዟት ነበርና በእዚህ ጊዜ ላይ ነው በኃይሉ አሰፋ /ቱሳ/ የቡድኑ አንደኛ መቺ እኔ እንደሆንኩ ስለሚያውቅ ከሪቻርድ ላይ ተቀብሎትና ለእኔ ሰጥቶኝም በመምታት ነው የድሏን ግብ ላስቆጥር የበቃሁትና በወቅቱ ደጋፊዎቻችንም እንዲደሰቱ ስላደረግኩኝ የተሰማኝ የደስታ ስሜት በጣም ከፍተኛም ነበር፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስን የፍፁም ቅጣት ምት ጎል እና ስለተሰጠበት ምክንያት ምን ትላለህ?
አስቻለው፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ በመቐለ 70 እንደርታ ላይ ያገኘው የፍፁም ቅጣት ምት አሳማኝ እና የሚያሰጥም ነው፤ ይህ የፍፁም ቅጣት ምትም በእዚህ አመት ለመጀመሪያ ገዜ ያገኘነውና በእኔ አማካይነትም የተቆጠረች የድል እና መሪው ክለብንም ያሸነፍንበት የተለየች ግብ ስለሆነች ግቧን መቼም ቢሆን የምረሳት አይደለችም፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ነገ /እሁድ/ በ10 ሰአት ይከናወናል፤ ይሄ ደርቢ የሚደረገውም ብዙም ባልተለመደ መልኩ ሁለታችሁም ክለቦች ከመሪው ክለብ ጋር በነጥብ በራቃችሁበት ሁኔታ ላይ ከመሆኑ አንፃር በእናንተ በኩል ጨዋታው እንዴት ይጠበቃል? ማንስ የግጥሚያው አሸናፊ ይሆናል?
አስቻለው፡- የኢትዮጵያ ቡና እና የቅ/ጊዮርጊስ ክለቦች እሁድ የሚያደርጉት የደርቢ ጨዋታ እንደከዚህ ቀደሙ ሁለቱም ክለቦች ወደ ዋንጫው ባላቤትነት ለማምራት በቅርብ ሁኔታ ላይ በሚገኙበት ላይ ባይሆኑም ሁሌም ግን የሁለቱ ጨዋታ በጉጉት መጠበቁ አይቀሬ ነው፤ የእሁዱም ጨዋታ አንዱ በአንዱ መሸነፍን አጥብቆ የሚጠላበት ስለሆነም ጠንካራ የመሸናነፍ ፉክክርም ይታይበታል፡፡
የቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ይሄ የደርቢ ጨዋታም ከሌላው ጊዜ በተሻለም ጠንካራ ፉክክር ይደረግበታል ብዬ የማስበውም ይህን ጨዋታ ማሸነፍ መቻል ወደ ዋንጫው ፉክክር የምንጠጋበትን ሁኔታዎችን ስለሚፈጥርልን ጨዋታውን ለቡና የተለየ ዝግጅትን ሳናደርግ በከፍተኛ ጉጉት ነው እየጠበቅነው የምንገኘው፤ በጨዋታውም ቡናን በበላይነት አሸንፈን ከሜዳ እንወጣለን፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢ ጨዋታ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ብዙ ጊዜ የሚያምር አይደለም፤ ይሄ ያስማማሃል?
አስቻለው፡- አዎን፤ ጨዋታው የሚያምር እና ሳቢ ላይሆን የቻለው ሁለቱም ክለቦች ውጤትን ከመፈለግ እና ደጋፊዎቻቸውንም ለማስደሰት ከመጓጓታቸው አኳያ ነው፡፡
የአሁኑ የሸገር ደርቢ ግን ለውጦች የሚኖሩት ይመስለኛል ስለጨዋታው እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው የስፖርቱ አፍቃሪ ጥሩ ጨዋታን እንደሚመለከትም ነው፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት እድሉን ዛሬ ላይ ሆነህ እንዴት ታሰለዋለህ?
አስቻለው፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ የሊጉ ጨዋታዎች ሊጠናቀቁ የስምንት ሳምንታት በቀሩበት የአሁን ወቅት ላይ ከወዲሁ እያሰበ የሚገኘው ከፊቱ ያሉበትን ቀሪዎቹን ጨዋታዎች እያሸነፈ ስለመሄድ እንጂ የሊግ ዋንጫውን እናነሳለን፤ እናነሳም በሚሉት ጉዳዮች ላይ የሂሳብ ስሌት እያሰላን አይደለም፤ ከዛ ይልቅ የራሳችንን የቤት ስራ በምን መልኩ መወጣት እንዳለብን ሙሉ ትኩረታችንን ጨዋታዎቻችን ስለሰጠን እነዚያን ግጥሚያዎች አሸንፈን የሚመጣውን ማናቸውም ውጤቶች በፀጋ እንቀበላለን፡፡
ሊግ፡-በቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ አሁን ያለው ስሜት ምንድነው የሚመስለው?
አስቻለው፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ አሁን ላይ ጥሩ መነቃቃት አለ፤ ግጥሚያዎችንም የማሸነፍ ፍላጎታችን በጣም ጨምሯል፤ ይሄ ፍላጎትም እስከ መጨረሻው ድረስ ይቀጥላል፡፡
ሊግ፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በቀጣዩ ጨዋታዎቹ በጣም ሊቀርፈው የሚችለው ችግር ምንድነው?
አስቻለው፡-ወደ ተቃራኒ ቡድን የሜዳ ክልል እየገባን ጎል ያለማግባት ችግር አለብን፤ መቐለ 70 እንደርታን ስንፋለምም ይሄ ችግር ታይቶብናል፤ከቡና ጨዋታ ጀምሮ ግን ይህ ችግር ይቀረፋል፡፡
ሊግ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊን በአንድ ቃል ስትገልፀው?
አስቻለው፡- የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊን በሚመለከት በቃላት ተናግረክላቸው የምታበቃው አይደለም፤ ልዩ ደጋፊዎችም ናቸው፤ ውጤት ኖረም አልኖረም አሁን ላይ እያበረታቱንም ይገኛሉና እንደ 12ኛ ተጨዋቾቻችንየምንቆጥራቸውን ደጋፊዎቻችንን ላመሰግናቸው ነው የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- የትንሳኤ በዓል እንዴት አለፈ?
አስቻለው፡- የትንሳኤ በዓል ጥሩ እና መልካም ነበር፤ በዓሉን ያሳለፍነውም ከመቐለ 70 እንድርታ ጋር ወሳኝ ጨዋታ ስለነበረን በካምፕ እና የተወሰንነው ተጨዋቾች ደግሞ በጌታነህ ከበደ ቤት በመዋል የእሱን ዶሮም እየበላን ነውና በእዚህ አጋጣሚ ከጌታነህ ከበደም ጋር ለማሳለፍ በመቻሌም ደስተኛ ነበርኩ፤ በእዚህ አጋጣሚ ለመላው የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ለቤተሰቦቼ እንደዚሁም ለቅዱስ ጊዪርጊስ ደጋፊዎችም መጪው በዓልም የዳግማዊ ትንሳኤ የሚከበርበትም ስለሆነ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ……
አስቻለው፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች እሁድ እለት የሚያደርጉት ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ብዙ የስፖርት አፍቃሪ እና የሁለታችንም ደጋፊዎች በሜዳ ላይ በመገኘት የሚመለከቱት ስለሆነ የእዚያን ቀን በስታዲየም የሚታዩት አጠቃላይ ነገሮች አስተማሪ መሆን መቻል አለባቸው፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ አሁን ላይ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር በተያያዘ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለ በመሆኑ የእግር ኳስ ጨዋታ ደግሞ ከፖለቲካ፣ ከዘር እና ከኃይማኖት የፀዳም ስለሆነ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ካላቸው የረጅም ጊዜ ታሪክ እና የሀገሪቱም ታላላቅ ቡድኖች ስለሆኑ ደጋፊዎቹ በስቲዋርዶቻቸው አማካኝነት በመመራት ጨዋታው ምንም ውጤት ተመዘገበበት በፀጋ በመቀበል ግጥሚያው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ ምኞቴ ነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P