Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የሸገር ደርቢ ታላቅና ተጠባቂ ጨዋታ | ሳምሶን ጥላሁን /ኢትዮጵያ ቡና/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የሸገር ደርቢ ታላቅና ተጠባቂ ጨዋታ
ቅ/ጊዮርጊስ vs ኢትዮጵያ ቡና

ነገ 10፡00 ሰዓት
የቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ደጋፊዎች፣ እንደዚሁም ደግሞ የሁለቱም ቡድን ተጨዋቾችና የስፖርቱ ተመልካቾች በጉጉት የሚጠብቁት የሸገር ደርቢ ጨዋታ ነገ እሁድ ከ10 ሰአት ጀምሮ በርካታ የእግር ኳሱ አፍቃሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በሚያከናውኑት የነገው የሸገር ደርቢ ጨዋታም ከሌላው ጊዜ በበለጠ በርካታ የእግር ኳሱ አፍቃሪዎች ግጥሚያውን ይከታተሉታል ተብሎ በመጠበቅ ላይ ሲሆን የጨዋታው ባለሜዳም ቅ/ጊዮርጊስ መሆኑም ታውቋል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች በፕሪምየር ሊጉ የውድድር ታሪክ ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ በደርቢው ፍልሚያ የሁለት ዙር ጨዋታዎችን በማከናወን ሲገናኙ በእስከዛሬው የእርስ በርስ ግንኙነታቸው አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች በማሸነፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ የበላይነቱን የወሰደ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ ስንመለከት የአቻ ውጤት የተመዘገበበት ውጤት ቁጥሩ ከሌላው ጊዜ ግንኙነታቸው አኳያ ከፍ ያለ ሆኖም ተመዝግቧል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች ከእዚህ ቀደም የፊንፊኔ ደርቢ የሚል ስያሜን በኋላ ላይ ደግሞ የሸገር ደርቢ የሚል መጠሪያ የያዘውን ጨዋታዎቻቸውን ከማከናወናቸው በፊት በሁለቱም ቡድን ደጋፊዎችም ሆነ ተጨዋቾች በኩል ለግጥሚያው የሚሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር አንዳቸው አንዳቸውን አሸንፈው ለመውጣት እና ከጨዋታው በኋላም ቀኑን በፌሽታ እና በደስታ አጣጥመው ለመዋል ከፍተኛ ዝግጅትን የሚያደርጉበት ሁኔታን የተመለከትን ሲሆን የደርቢው ጨዋታ ከቅርብ ዓመታቶች ወዲህ በሜዳ ላይ ሲደረግ ግን የሁለቱም ቡድን ተጨዋቾች በደጋፊዎቻቸው እንደሚሰጣቸው የአማረ እና ድንቅ ድጋፍ የተመልካቹን የኳስ ስሜት የሚያረካ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ባለመሆኑ ደርቢው በሜዳ ላይ ከሚታየው እንቅስቃሴ አንፃር አጓጊነቱ ያን ያህል የሚያስነግርለት አይደለምና በዚህ በኩል መሻሻል እንዳለበትም በሁሉም ዘንድ እየተነገረም ይገኛል፡፡
የቅ/ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች የነገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ላይስ በግጥሚያው ምን ያሳዩን ይሆናል? በደርቢው ጨዋታ ዙሪያና ተያያዥ የሆኑ ጥያቄዎችን ከሁለቱ ቡድን ተጨዋቾች መካከል ከቅ/ጊዮርጊስ ተከላካዩን አስቻለው ታመነን እና አጥቂውን አቤል ያለውን ከኢትዮጵያ ቡና ወገን ደግሞ አማካዮቹን አማኑኤል ዩሃንስንና ሳምሶን ጥላሁንን አናግረናቸው ምላሻቸውን ሰጥተውናል፤ እንደሚከተለውም ይቀርባል፡፡
“ቅ/ጊዮርጊስን በሸገር ደርቢው አሸንፈን እኛን ወደፊት በማስጓዝ እነሱን ወደ ኋላ ማስቀረት እንፈልጋለን”
ሳምሶን ጥላሁን /ኢትዮጵያ ቡና/
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና 1 ወልዋሎ አዲግሪት ዩኒቨርሲቲ 0 የሚል ውጤት ከሸገር ደርቢው ጨዋታ በፊት ተመዝግቧል፤ ግጥሚያውን እንዴት አገኘኸው? በስቴድየሙ ውስጥ የነበረውስ ድባብ ምን ይመስላል?
ሳምሶን፡- ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ጋር የነበረን የረቡዕ ተስተካካይ ጨዋታ ከእረፍት በፊት ቡድናችን ከእነሱ በተሻለ ጥሩ የተንቀሳቀሰበት እና የጎል አጋጣሚያዎችንም አግኝቶ ያልተጠቀመበት ሲሆን፤ የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደግሞ የመሪነቱን ጎል ካስቆጠርን ወዲህ ከዚህ በፊት ጎል የሚገቡብን ሁኔታዎች በመጥፎ እና በአጉል ሰዓቶች ላይ ስለነበር ያን ችግር ለመቅረፍ ብለን በማሰብ ከ20 ደቂቃ በኋላ ወደ ራሳችን ሜዳ ኋላ ሸሽተን የተጫወትንበት ሁኔታ አለና እንደ አጠቃላዩ ጨዋታ የድል ውጤቱን አሳክተን በመውጣታችን በጣም ደስ ብሎናል፤ የጨዋታው እለት ስለነበረው ድባብ መናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር ደግሞ ስታዲየሙ ላይ ይታይ የነበረው የአደጋገፍ ስታይል በጣም ደስ የሚል ነበር፤ የቡድናችን ደጋፊዎች ከጎናችን ሆነውም እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ሲያበረታቱን ነበርና በእዚሁ አጋጣሚም ለተገኘው ድል እንኳን ደስ ያላችሁም ልላችሁ እወዳለሁ”፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና ያለፉት ሁለት ተከታታይ የሊግ ግጥሚያውን በፍፁም ቅጣት ምት ጎል አሸንፏል፤ በጨዋታው ላይ በሚገኝ ኳስ ጎል አለማስቆጠራችሁን እንዴት ተመለከትከው?
ሳምሶን፡- የወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲንም ሆነ የአዳማ ከነማ ክለቦችን በተፋለምንባቸው የሊጉ ጨዋታዎች ግጥሚያዎቹን አሸንፈን የወጣነው በፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች ቢሆንም ከወልዋሎ ጋር ስንጫወት የአጨራረስ ችግር ጎዳን እንጂ ጨዋታውን ያለፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች በሁለት እና ሶስት ጎሎች ልዩነት ማሸነፍ እንችል ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ያገኘናቸውን ጎል የማስቆጠር እድሎች መጠቀም አልቻልንም፡፡ በእለቱ በጨዋታ ጎል ባናስቆጥርም የፍፁም ቅጣት ምትም የጨዋታው አንዱ አካል ስለሆነ በእዚያ ተጠቅመን ባለድል ሆነናል፤ የቀጣይ ጨዋታዎቻችን ላይ ደግሞ ያሉብንን የአጨራረስ ችግሮች አስተካክለን በግጥሚያ ላይ በሚገኝ እንቅስቃሴ ወደ ተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል ጋር በተደጋጋሚ የምንቃረብበት ብቃቱ ስላለን ብዙ ጎሎችን የምናስቆጥርበት ሁኔታ በቅርቡ ይኖረናል”፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢ ጨዋታ ነገ ይከናወናል፤ አንተ ደግሞ ከዚህ የሁለቱንም ክለቦች ማሊያ ለብሰህ ደርቢውን አከናውነሃልና ስለሸገር ደርቢው ጨዋታ ምን ትላለህ? የቡናን መለያ በማድረግ የቀድሞው ቡድንህን የምትፋለምበት የነገው የደርቢ ጨዋታስ በምን ውጤት የሚጠናቀቅ ይመስልሃል?
ሳምሶን፡- በአገራችን የእግር ኳስ ታሪክ በከፍተኛ ጉጉት በሚጠበቀው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ከዚህ ቀደም ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኜ ቡናን ገጥሜያለሁ፤ በተቃራኒውም ቡና ሆኜም ቅዱስ ጊዮርጊስን ተፋልሜያለሁ የሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ሲገናኙ ሁሌም በተለይ ደግሞ በስቴድየሙ ውስጥ የሚኖረው የድጋፍ ድባብ ደስ የሚል ሆኖ ባገኘውም ሁለቱ ክለቦች ካላቸው ተቃርኖ እና አንዱ በአንዱ መሸነፍን አጥብቆ ካለመፈለግ አንፃር ግን በሜዳ ላይ የሚታየው የጨዋታ ፉክክር የተመልካቹን የኳስ ስሜት የሚስብ አለመሆኑ ይሄን ሁሌም እንደድክመት ነው የምቆጥረው፤ የዘንድሮው ደርቢ ግን ነገ ሲከናወን ካለፉት አመታቶች አንፃር ጥሩና የተሻለ የሜዳ ላይ ፉክክርን የምናሳይ ይመስለኛል፤ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር የሚኖረንንም ይህንን ጨዋታ በአሸናፊነት መንፈስ ስሜት ውስጥ ስላለን እኛ አሸንፈን ደጋፊዎቻችንን ይበልጥ የምናስደስታቸው ያህል የእርግጠኝነት ስሜት ይሰማኛል”፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ የአሁን ሰዓት ላይ ካለው ወቅታዊ አቋም ተነስተህ ለእናንተ የሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ስጋትን ይፈጥርባችኋል?
ሳምሶን፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብን ተደጋጋሚ ጨዋታዎች ዘንድሮ ስንመለከት ያለው አጀማመር እንደበፊቱ አይደለም፤ ትንሽም ደከም ብለዋል፤ ያም ሆኖ ግን ከኛ ጋር የደርቢው ጨዋታ ላይ ሲጫወቱ ጠንክረው የሚመጡበት ሁኔታ ስላለ አሁን ላይ እኛ እያሰብን ያለነው እነሱ ስጋትን ይፈጥሩብናል ብለን ከማሰብ ይልቅ ከእነሱ የተሻለ አቋምን የጨዋታው ዕለት ይዘን ቀርበንና በጨዋታም በልጠን ግጥሚያውን ስለማሸነፍ ነው እየተዘጋጀን የምንገኘው”፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡናና የቅ/ጊዮርጊስ የነገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከስፖርታዊ ጨዋነት አንፃር ምን ቢደረግ ጥሩ ነው ትላለህ?
ሳምሶን፡- የሁለታችን የሸገር ደርቢው ጨዋታ ነገ ከመከናወኑ በፊት ግጥሚያው በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የስፖርታዊ ጨዋነቱ ላይ ሁለቱም ክለቦች በጋራ ተገናኛተው በደንብ ሊነጋገሩበት የሚገባ ጉዳይ አለ፤ ፀጥታን ከማስከበር አኳያም አሁን እየሰማነው ያለውም ነገር ጥሩ ነው፤ የደርቢው ጨዋታ ነገ ሲከናወንም ከእኛም ሆነ ከእነሱ ተጨዋቾችም የሚጠበቅ ነገር ሊኖር ይገባል፤ ከእኛ የሚጠበቀው የሚደግፉንን ደጋፊዎች ኳስና ኳሱን ብቻ መሰረት አድርገን በመጫወት እነሱን በጨዋታ ልናስደስት ይገባል፤ ደጋፊን የሚያነሳሱ ነገሮችን በፍፁም ልናደርግም አይገባምና ጨዋታው በሰላም የሚጠናቀቅ ይመስለኛል”፡፡
ሊግ፡- ለፕሪምየር ሊጉ የዋንጫ ፉክክር ለምታደርጉት ጉዞ ከቅ/ጊዮርጊስ የሚኖራችሁ የነገው የሸገር ደርቢው ፍልሚያ ለእናንተ በጣም ወሳኝ ነው….?
ሳምሶን፡- ከቅ/ጊዮርጊስ የምናደርገው የነገው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ለእኛ በይበልጥ ወሳኝ ነው፤ ጨዋታውን ካሸነፍን ከተቃናቃኛችን በነጥብ የምንርቅበት ሁኔታ ስለሚፈጠርና ወደ ዋንጫው ፉክክርም ለመጓዝ የሚኖረንን እድል ስለሚያለመልምልን ጨዋታውን ለማሸነፍ በሙሉ ኃይላችን ተዘጋጅተናል”፡፡
ሊግ፡- እንደ ቡና ተጨዋችነትህ የሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ከአንተ ምን ይጠበቅ?
ሳምሶን፡- የደርቢ ጨዋታዎች ብዙ ጊዜ የአንተን ማንነት የምታሳይበት ጨዋታ ነው፤ ግጥሚያዎቹም በዓመት ውስጥ ለሁለት ጊዜያት የምታደርጋቸው ናቸውና የነገው ጨዋታ ላይም ለወሳኙ ፍልሚያ ራሴን በደንብ አዘጋጅቼ ሜዳ ላይ በመቅረብ ክለቤን ውጤታማ አደርጋለው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P