Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የቁጭት ስሜት አለብን፤ ደጋፊውንና አመራሩን በውጤት ልንክሰው ይገባል”ሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ

/#በመሸሻ_ወልዴ


የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለተደጋጋሚ ዓመታት ያነሳው ቅ/ጊዮርጊስ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት ውጤት
ማጣቱን ተከትሎ የተቆጨ ሲሆን ይሄ ቡድን ዘንድሮ ወደ ቀድሞ ስኬታማነቱ ለመመለስ በሁሉም መልኩ ቆርጦ
መነሳቱን የቡድኑ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ሙሉዓለም መስፍን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል
የቅ/ጊዮርጊሱ አማካይ “ላለፉት ተከታታይ ዓመታት በተለይም ደግሞ ከሁለት ዓመት በፊት ላጣነው ዋንጫ በጣም
ተቆጭተናል፤ የዛን ዓመት ዋንጫን ያጣነው በዳኝነት በደል ነው፤ ስለሆነም ባለፉት ጊዜያቶች ቡድናችን ላላሳካቸው
አጠቃላይ ውጤቶች እኛ የቡድኑ ተጨዋቾች በጣም የተቆጨንበት ሁኔታዎች ስላሉ በዘንድሮ የውድድር ዘመን
ተሳትፎአችን እነዛን ቁጭቶች ወደ ኋላ በማስቀረት የቡድናችንን ደጋፊዎች እና አመራሮቻችንን በውጤት
ልንክሳቸው ይገባል” ሲልም ምላሹን ሰጥቷል፤ ከሙሉዓለም መስፍን ጋር ሊግ ስፖርት ያደረገችው አጠቃላይ
ቆይታም ይሄንን ይመስላል፡፡
ሊግ፡- የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችሁን ማክሰኞ ዕለት ጀምራችኋል፤ ልምምዳችሁ ምን ይመስላል? /ያነጋገርነው
ሐሙስ ጠዋት ነው/
ሙሉዓለም፡- ቅ/ጊዮርጊስ ቢሾፍቱ በሚገኘው የክቡር አቶ ይደነቃቸው ተሰማ የታዳጊ ወጣቶቹ አካዳሚው
እየሰራ ባለው የእስካሁኑ ያለፉት ሁለት ቀናት ልምምዱ እንዲህ ነበርን ለማለት ባልችልም ቀላል እና ከኳስ ጋር
የተያያዘ ዝግጅትን ግን እየሰራን ይገኛል፤ ከቀናቶች በኋላ ደግሞ ወደ ጠንካራ ልምምዶቻችን የምንገባባቸው
በቂ ስራዎች ስለሚኖሩን ያ ሙሉ ለሙሉ በጥሩ አቋም ላይ እንድንገኝ ያስችለናል፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ሲያስመጣ ቡድኑን የሊጉ ሻምፒዮና እንዲያደርግ፣ ለአፍሪካ
ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ እንዲያሳልፍ እና ካልሆነ ደግሞ ለኮንፌዴሬሽን ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲያበቃ
ከስምምነት ላይ ደርሷል፤ ይሄን የቡድኑ አሰልጣኝ የሚያሳካው ይመስልሃል?
ሙሉዓለም፡- ቅ/ጊዮርጊስ ወረቀት ላይ ባስቀመጠው መስፈርት አዲሱን የቡድኑን አሰልጣኝበሚፈልገው
መልኩ ውጤት እንዲያመጣለት ቢቀጥረውም በዘንድሮ የውድድር ዘመን እውነታውን ስታስቀምጥ ግን
የምንጫወተው ኳስ እስከሆነ ድረስ በአንዴ በእሱ ጥረት ብቻ የሚፈለገውን ድል እና ስኬት ለማስመዝገብ
ሁኔታዎች ቀላል ይሆኑለታል ብዬ ፈፅሞ አላስብም፤ ስለዚህም አሰልጣኙ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ የእኛ
ተጨዋቾች እገዛም በጣም ያስፈልገዋል፤ በተለይ ደግሞ አሰልጣኙ ለሚከተለው የጨዋታ ታክቲክ እኛ የቡድኑ

ተጨዋቾች በጣም ተገዥ ልንሆን እና ጠንክረንም ልንሰራ ይገባናል፤ ከዛ ውጪም ሌላ ውጤታማ
የሚያደርገንም ነገር ይኖራል፡፡
ሊግ፡- ውጤታማ የሚያደርጋችሁ ሌላው ነገር ምንድን ነው?
ሙሉዓለም፡-የሊግ ካምፓኒው የእዚህ ዓመት ውድድሩን ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የውድድሩን ፎርማት
ቀይሮት በተመረጡ 6 የክልል ስታድየሞች ላይ እንዲካሄድ ከውሳኔ ላይ በመድረሱና ጨዋታዎቹም
በዲ.ኤስ.ቲቪ የሚተላለፉ በመሆኑ ይሄ እኛን ውድድሩ እንዳይከብደን ስለሚያደርገን በእዚህ ተጠቃሚ
እንድንሆን ያደርገናል፡፡
ሊግ፡- በእዚህ መልኩ ጨዋታዎቹ መከናወናቸው ሌሎች ቡድኖችንስ አይጠቅማቸውም?
ሙሉዓለም፡-ይጠቅማቸዋል እንጂ ያም ሆኖ ግን የእኛን ቡድን ከሌሎቹ ቡድኖች አንፃር ጋር ስታመዛዝነው
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ላይ በተለይ ደግሞ ከሁለት ዓመት በፊት ተደርገው በነበሩት የተለያዩ ክልል ስታድየም
ጨዋታዎች ላይ ግጥሚያን እየተበደልን ለማሸነፍ የተቸገርንበት ሁኔታዎች ስለነበሩና ጠንካራም ቡድንን ይዘን
የምንቀርብም በመሆኑ የዘንድሮ ጨዋታዎች ከላይ በተገለፁት መልኩ መከናወናቸው እኛን ነው በጣም
ተጠቃሚ የሚያደርገን፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማጣት ከጀመረ ወደ ሶስተኛው ዓመት እያመራ ነው፤ ይሄ በጣም
አስቆጭቷችኋል?
ሙሉዓለም፡- እንዴት ነው የማያስቆጨን፤ በተለይ ደግሞ ከሁለት ዓመታት በፊት የነበረውን የሊግ ዋንጫ
ለማንሳት ተቃርበን ጅማ ከተማ ላይ ከጅማ አባጅፋር ቡድን ጋር ባደረግነው ጨዋታ በዳኝነት በደል መደበኛው
90 ደቂቃ አልቆ እስከ100 ደቂቃ ድረስ እና ተጨማሪም 4 ደቂቃ ታክሎበት እንድንጫወት በመደረጋችን
ያሸነፍነውን ግጥሚያ በተሰጠብን የፍፁም ቅጣት ምት አቻ እንድንወጣ ተደርገናል፤ ከዛ ውጪም አዳማ
ከተማም በጅማ በርካታ ግቦች እንዲቆጠርበት እና ጨዋታውን እንዲሸነፍ የተደረገበት ሁኔታም እኛን የሊጉን
ዋንጫ እንድናጣ አድርጎናልና ያ የሚያስቆጭ ሆኖብናል፤ ሌላው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ ማጣት ፈፅሞ
የለበትም፤ ይሄ ክለብ ድል የለመደ ነው፤ ውጤት በማምጣት እንጂ በማጣት አይታወቅምና ከነበረው አኩሪ
ታሪክ አንፃር በቅርብ ዓመታት ባጣናቸው አጠቃላይ ውጤቶች ስለተቆጨን በዘንድሮ የውድድር ዘመን
ደጋፊውንና አመራሮቹን ልንክሳቸው ነው የሚገባን፡፡
ሊግ፡- ለቅ/ጊዮርጊስ የቅርብ ጊዜ ውጤት ማጣት አሰልጣኞችን ቶሎ ቶሎ መቀያየሩንም በምክንያትነት የሚያነሱም
አሉ፤ በእዚህ ዙሪያስ የምትለው ነገር አለ?
ሙሉዓለም፡-አዎን፤ ወደ እኛ ቡድን ስትመጣ ከእዚህ ቀደም አሰልጣኝ ለረጅም ጊዜ የሚቆይበት ሁኔታ
አልነበረምና ይሄ የክለቡን ውጤት ከፍም ዝቅም የሚያደርግበት ሁኔታ ነበር፤ በተለይ ደግሞ ቆይታቸው አጭር
ስለሚሆንና ታክቲካቸውን ቶሎ ለመላመድም ስለሚቸግር ይህ ጎድቶንም ነበር፤ አሁን የመጣውን
ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ግን ቡድናችን ያስፈረመው ለሶስት ዓመት ጊዜ በመሆኑ ጥሩ እና ጠንካራ ቡድንን
ለመገንባት ያስችለዋል፤ እኛ ተጨዋቾችም የእሱን ታክቲክ በደንብ ለመላመድም ጊዜ ይኖረናልና ቡድናችን
አሁን እየተጓዘ ያለበት መንገድ በጣም ጥሩ ነው፡፡
ሊግ፡- በዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ በምን መልኩ ለመቅረብ ዝግጁ ነህ?
ሙሉዓለም፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኔ ሁሌም ቢሆን ራሴን ለጥሩ ተጨዋችነት ለማብቃት ከፍተኛ
ጥረትን አደርጋለውና የእዚህ ዓመት ላይም በግሌ የተሻለ ተጨዋች ሆኜ ክለቤን ለጥሩ ውጤት ለማብቃት
ጠንክሬ እየሰራሁኝ ነው፡፡
ሊግ፡- እንደ አንድ እግር ኳስ ተጨዋች ለብሔራዊ ቡድን ከመመረጥና ካለመመረጥ ጋር በተያያዘ የምትለው ነገር
አለ?

ሙሉዓለም፡-አዎን፤ ለብሔራዊ ቡድን ከመመረጡ ጋር በተያያዘእኔ በቀድሞው አሰልጣኝ ኢንስትራክተር
አብርሃም መብራቱ ጊዜ በስኳዱ ውስጥ ነበርኩበት፤ ከቆይታዎች በኋላ ግን ዳግም ለምን ልጠራ እንዳልቻልኩ
ፈፅሞ ላውቅ አልቻልኩም፤ በአሁኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጊዜም እኔ ካለኝ ጥሩ ችሎታ አንፃር ስለራሴ
ማውራት ቢከብደኝም ለብሔራዊ ቡድን ግን ለምን ለመመረጥ እንዳልቻልኩኝ አሁንም ፈፅሞ አላውቅም፤
ውበቱ የመረጣቸው ተጨዋቾች በቅርብ የሚያውቃቸውንና በአብዛኛውም ከእዚህ ቀደም በተለያዩ ቡድኖች
ውስጥ ያሰለጠናቸውን ተጨዋቾች ነው፤ አንድ አሰልጣኝ ተጨዋቾችን የሚመርጠው እሱ ለሚፈልገው
አጨዋወት እና ታክቲክ የሚሆኑትን እንደሆነ ባውቅም እኔ ካለኝ ወቅታዊ ብቃት አኳያ ለየትኛውም አይነት
አጨዋወት የሚሆን ጥሩ ብቃት አለኝና ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ ይገባኝ ነበር፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ለቀድሞው የቡድናቸው ታዋቂ ተጨዋች ሙሉጌታ ከበደ /ወለዬው/ ከአሜሪካን
መምጣቱን ተከትለው ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር አለ? ስለ ሙሉጌታ
ከበደስ ምን ትላለህ?
ሙሉዓለም፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅ/ጊዮርጊስ ሌጀንድ ተጨዋች ስለሆነው ሙሉጌታ ከበደ እኔ
በሚገባ ማወቅ የጀመርኩት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ገብቼ መጫወት በጀመርኩበት ወቅት ነው፤
ስለ እሱ ምርጥ ተጨዋችነት ብዙ ሲነገር ሰምቻለውና ይሄንን የሀገር እና የክለባችንን የቀድሞ ተጨዋች እነዚህ
ደጋፊዎች ባልተለመደ ሁኔታ ሲቀበሉት ስሰማ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ምክንያቱም እኛ ሀገር ላይ ብዙ ጊዜ
የሰራ እና የለፋ ሰው ሲገፋ ነው የሚታየው፤ ዋጋም አይሰጠውም፤ ለሀገር ብዙ ታሪክ የሰራ የጦር ጄኔራል
ምንም ነገር እንዳልሰራ መንገድ ላይ ወድቆ የሚታይበትን ሁኔታም የተመለከትንበት ሁኔታዎች ስላሉ
የቡድናችን ደጋፊዎች ይሄንን የኳስ ጀግና አክብረው ተጫውቶ ባሳለፈበት በአዲስ አበባ ስታድየም የሚያኮራ
እና የአሁኑ እንደዚሁም ደግሞ የመጪው ትውልድንም ደጋፊዎች የሚያስተምር ልዩ አቀባበልን
አድርገውለታልና ይሄ ይበል የሚያሰኝ ነው፤ ለሙሌ ይሄ ተደረገ ማለት ነገ ላይ ሌሎች ተጨዋቾችም በደጋፊው
ልብ ውስጥ ለመግባት እንዲችሉ በጣም ያግዛችኋልና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ላደረጉት ነገር ሊመሰገኑ
ይገባል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…?
ሙሉዓለም፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በየጊዜው ከተሰራ በኋላ ዳግም የሚፈርስበት ሁኔታ እንደዚሁም
ደግሞ አንድ ተጨዋች ሲመረጥም ሆነ ከስኳዱ ውጪ ሲደረግ በምን መስፈርት እንደተመረጠ እና ሊቀነስ
እንደቻለ የሚነገርበት ሁኔታ አለመኖሩ ብዙ ጊዜ ሀገርን ሲጎዳ እየታየ ይገኛል፤ ብሔራዊ ቡድን በርካታ ህዝብን
ወክለህ የምትሳተፍበት ውድድር ነው፤ እኛ ሀገር ላይ ያለው አሰራር አንዱ የሰራሁን በማፍረስ ሌላ ቡድን
ለመገንባት ጥረት የሚደረግበትና ሁሌም ደግሞ ስራችንን ከዜሮ ሆነን የምንሰራበት አሰራር ስላለን እንዲህ ላሉ
ነገሮች ሀይ የሚል አካል መጥቶ የእግር ኳሳችንን ጉዞ በትክክለኛ መስመር ልናስጉዘው ይገባናል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P