Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የእግር ኳስን በመጫወቴ ምክንያት ከአጎቴም ከእናቴም ተጣልቼ ለብቻዬ እየኖርኩ ነው” “ለኢትዮጵያ ቡና ለረጅም ዓመት መጫወት ብቻ ሳይሆን የኳስ ጫማዬንም በቡድኑ ብሰቅልም ደስ ይለኛል” ገዛኸኝ ደሳለኝ /ኢትዮጵያ ቡና/

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ለተለያዩ ክለቦች እና  በኋላ ላይ ደግሞ እስከ ብሄራዊ ቡድን ደረጃ  ተጨዋቾችን  እንዲፈሩ በማድረግ ትልቁን ሚና ከሚጫወቱት ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የአስኮ ፕሮጀክት ነው። ይህ ፕሮጀክት  ብዙ ተጨዋቾችን በማውጣትም   ይታወቃል። አሁን ላይም ለኢትዮጵያ  ቡና በተከላካይ ስፍራ ላይ  በጥሩ ሁኔታ የሚጫወተውን ገዛኸኝ ደሳለኝንም አፍርቷል።

ደሳለኝ  70 ኪሎ ግራም  ሲመዝን 1 ሜትር ከ72 ይረዝማል።   ይህ ተጨዋች ከኳስ ውጪ የሙያ ትምህርቱን  በዊንጌት ሲማር የቆየ ቢሆንም የኳሱ ሁኔታ ነገሮችን ስላላመቻቸለት  ትምህርቱን ሊያቆም ችሏል።  ተጨዋቹ  በርቀትም ቢሆን  ወደፊት ትምህርቱን መቀጠል እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ለኢትዮጵያ  ቡና ከተተኪው ቡድን አንስቶ አሁን ላይ ለዋናው ቡድን የሚጫወተውን ይኸውን ተጨዋች የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ በኳስ ህይወቱ እና በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነዋል። ተጨዋቹም ይህን ምላሽ ሰጥቶናል።

 

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፍቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግናለን?

ገዘኸኝ፦ እኔም በጣም አመሰግናለሁ።

ሊግ፦ ይህቺን ምድር የተቀላቀልከው የት ተወልደህ በማደግ ነው?

ገዘኸኝ፦ የተወለድኩት በአስኮ አዲስ ሰፈር ነው፤ እዛም ነው ኳስን በመጫወትም ያደግኩት።

ሊግ፦ በአስኮ ፕሮጀክት ውስጥ ሰልጥነህ አልፈሃል?

ገዘኸኝ፦ አዎ፤ እዛ ሰልጥኜ  በማለፍም ነው ለዛሬ እውቅና እየበቃው ያለሁት።

ሊግ፦  በልጅነት ዕድሜህ  የእግር ኳስ ተጨዋች የመሆን ፍላጎት ነበረህ?

ገዘኸኝ፦ አዎ።

ሊግ፦ የእግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ኖሮስ ምን ትሆን ነበር?

ገዘኸኝ፦ ወይ የመኪና ሹፌር አለያም በሌላ ሙያ ላይ እሰማራ ነበር።

ሊግ፦ የልጅነት ዕድሜህ ላይ  አድንቀህ ያደግከው ተምሳሌትህ /ሞዴልህ/ የነበረው ተጨዋች ማን ነው?

ገዘኸኝ፦ ከሀገር ውስጥ  ዑመድ ኡኩሪ  ነበር የሚመቸኝ። በጣምም ነበር የምወደው።  የእሱ አድናቂውም ነበርኩ።  በተለይም ደግሞ የሚመታቸው  ሹቶች  ደስ ይለኝም ነበር። ከባህር ማዶ ተጨዋቾች ደግሞ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂውም ነኝና እነዚህ ተጨዋቾች ናቸው የእኔ ተምሳሌቶች።

ሊግ፦ ከባህር ማዶ ክለቦች የማን ደጋፊ ነህ?

ገዘኸኝ፦ የማንቸስተር  ዩናይትድ።

ሊግ፦ ለቤተሰባችሁ ስንተኛ ልጅ ነህ? ስንት ወንድም እና እህትስ አለ?

ገዘኸኝ፦ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ፤ አንድ ወንድምም አለኝ።

ሊግ፦ ስፖርተኛውስ አንተ ብቻ ነህ?

ገዘኸኝ፦ አዎ፤ ወንድሜ ደግሞ  ተማሪ ነው።

ሊግ፦ በአብዛኛው ቤተሰብ  ዘንድ  የእግር ኳስን ልጅ  ሆነህ  ስትጫወት  ይከለከላል፤  ትምህርትህን ተማርም ነው የምትባለው፤ በእዚህ ዙሪያ ከአንተ ጋር በተያያዘ  ምን  የምትለው ነገር  ይኖራል?

ገዘኸኝ፦  በጣም የሚገርምህ  እኔን በተመለከተ ኳስ በመጫወቴ ብቻ  ያኔ  ከቤተሰቤ ጋር ተጣልቼ ወጥቻለሁ፤  በወቅቱ የምኖረው አጎቴ  ጋር ነበር። ፀባዬ በወቅቱ  እንደ አሁኑም አልነበረም። ኳስን ስጫወት በሜዳ ላይ ተጣላው። አሰልጣኜም አጎቶቼ  ቤት ሄዶ ተናገረብኝ።  ጥሩ  ኳስ  የመጫወት ችሎታ እና አቅሙ  እያለሁ  ፀባዩ  ብዙ  አይደለም ሲላቸውና ከእነሱም ጋር በቃላት ስመላለስ   በኋላ  ላይ ሌላ ባል ወዳገባችው ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ፤  እዛም ሄጄ በኳሱ ምክንያት ከእናቴ ጋርም  ስላልተስማማው በአሁን ሰዓት ለብቻዬ ነው  እየኖርኩ ያለሁትና በኳስ ተጨዋችነቴ ብዙ ፈተናዎችን  አልፌም ነው እዚህ ደረጃ ላይ የተገኘሁት።

ሊግ፦  በፕሮጀክት ተጨዋችነት  ለምን ያህል ጊዜ ቆየህ? እንዴትስ ወደ ክለብ ተጨዋችነት  አመራህ?

ገዘኸኝ፦ ለአምስት ዓመታት ነው  በፕሮጀክት ላይ የቆየሁት፤ እነ አብይ እና  ደስታም ናቸው ያሰለጠኑን። ከዛም ለኢትዮጵያ  ቡና የታዳጊዎች ቡድን በሽያጭ ተሰጠን።  ወደ ክለቡ  ገባው፤ ጥሩ ጊዜንም አሳለፍኩ።

ሊግ፦ ኢትዮጵያ  ቡናን በዋናው ቡድን ደረጃ እንዴት ተቀላቀልክ?

ገዘኸኝ፦ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ  በአንድ ጨዋታ ላይ አይቶኝ ነው  ለዋናው ቡድን ዝግጅት ከጠራኝ በኋላ እና በሲቲ ካፑም ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን ለማሳየት ስለቻልኩ  የዋና  ቡድኑን የተቀላቀልኩት።   ያኔ ያደግነውም  እኔና ከወጣት ቡድኑ  ሱራፌልም ነበርን።

ሊግ፦ በልጅነት ዕድሜህ  በሀገር ውስጥ ደረጃ  አንድ ቡድንን ልትደግፍ ትችላለህ፤  አንተ ማንን ደግፈህ ነው ያደግከው?

ገዘኸኝ፦ ኢትዮጵያ  ቡናን።

ሊግ፦  ቡናን የደገፍከው  አሁን የቡድኑ ተጨዋች ስለሆንክ ነው?

ገዘኸኝ፦ አይደለም።

ሊግ፦ የደገፍክበት ምክንያት  ምን ነበር?

ገዛኸኝ፦  አጨዋወታቸውን ወድጄ ነው የደገፍኳቸው። ያኔ  የእነሱን ኳስ  በብዛት  የሰፈር ልጆች ስለነበሩም በፋይፍ ኤል ሞልተን ነበር ወደ ስታዲየም ልንደግፋቸው የምንሄደው።  ቡናን በጣምም ነው የምወደው። አሁን የቡድኑ  ተጨዋች ስለሆንኩ ደግሞ በጣም ደስ ብሎኛል።

ሊግ፦ የኢትዮጵያ  ቡና  ተጨዋች  መሆንህን ሲያውቁህ  ያኔ  አብረኸቸው ስታዲየም  ይገቡ የነበሩት ጓደኞችህ ምን አሉ?

ገዛኸኝ፦ በጣም ነው ደስ ያላቸው።  የሰፈሬ ልጆች  ይኮሩብኛልም።  ሲያገኙኝ አይዞህ በርታም ይሉኛል። በእኔ ደስተኛም ሆነዋል።

ሊግ፦ በኢትዮጵያ  ቡና  የተተኪ ቡድን ውስጥ ረዘም ያለ ጊዜ ቆየህ?

ገዛኸኝ፦ ብዙም አይደለም፤  በወጣት እና  በተስፋ ቡድን ውስጥ ለአራት ዓመት  ያህል ነው የቆየሁት።

ሊግ፦  ብዙ ጊዜ  ስለ  ዋናው ቡድን አሰልጣኞች እንጂ ስለ  ተተኪ ቡድን  አሰልጣኞች ተጨዋቾች ሲያወሩ አይደመጡም፤  በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ይኖርሃል?

ገዛኸኝ፦ እኔን እታች በጥሩ ሁኔታ ያሰለጠነኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ነው። ብዙ ነገርንም አድርጎልኛል።  በባህርዬ ከሰዎች ጋር ስለምጋጭ ተጣልቼ በድጋሚም ነው ለቡድኑ በመጥራት ያጫወተኝ እና ለእዚህ ደረጃ ለመብቃቴ አንዱ ተጠቃሽ እሱ ነውና ሊመሰገን ይገባል።

ሊግ፦ በባህሪህ  ደረጃ  አስቸጋሪ  እንደነበርክ ራስህ ጠቅሰካል፤ ይህ አሁንም አብሮክ አለ?

ገዛኸኝ፦ በፍፁም፤  በጣም ተሻሽያለሁ።

ሊግ፦ አሁን  በተከላካይ ስፍራ  ላይ  እንመልከትህ እንጂ  አጥቂም ነበርክ፤   በእዚህ ዙሪያ ምን ማለት  ትችላለህ? የተሳካ ጊዜንስ እያሳለፍክ ነው?

ገዛኸኝ፦  አዎ፤ ማለት ይቻላል።  አጥቂ  እያለሁ  አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ነው ወደ ተከላካይ ስፍራ ወስዶ ያጫወተኝ።  በእዛ ስፍራ ላይም አበረታች ብቃቴን እያሳየው እገኛለሁ።

ሊግ፦ ኢትዮጵያ  ቡናን  አጠር ባለ  ቃላት ግለፀው ብትባል?

ገዛኸኝ፦ በመጀመሪያ  ቡድኑ ለእኔ ፍቅር ነው። ስለ ቡድኑ በውስጤ ብዙ ነገር ስላለና ከልጅነቴ አንስቶም ስለደገፍኩት  ስለ ክለቡ  በቃላት መግለፅ ለእኔ  ከባድ ይመስለኛል።  ቃላቶችም ያጥሩኛል።

ሊግ፦  በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ  ኢትዮጵያ  ቡና  እያደረገ ያለው የውድድር ተሳትፎ ምን ይመስላል?

ገዛኸኝ፦  የአሁኑ ዓመት ላይ  ቡድናችን  እያደረገ ያለው  የውድድር   ተሳትፎ  እኛንም ደጋፊዎቻችንንም  ብዙም አላስደሰተም።  የተከፋውን ደጋፊም  በመጪው ዓመት ላይ  ልናስደስተው የግድ ይለናል።

ሊግ፦ እንደ  ኢትዮጵያ  ቡና ተጨዋችነትህ  በሜዳ ላይ ምን  ነገሮችን ማሻሻል ይኖርብኛል ብለህ ታስባለህ?

ገዛኸኝ፦  ከሁሉም በላይ አሰልጣኞች እና  እኔን በቅርብ የሚያውቁኝ  የስፖርት አፍቃሪዎች  ናቸው እንቅስቃሴዬን ተመልክተው እንዲህ ብታደርግ

ሲሉኝ ከእዛ በመነሳት ነው ምክራቸውን  ሰምቼ ችሎታዬን የማሻሽለው። በእኔ በኩል ደግሞ ይዤ የመጣሁት  የቁጠኝነት  ባህሪህ  ነበርና  ያን እያሻሻልኩት  ነው።

ሊግ፦  ላለፉት በርካታ ዓመታት  ብዙ  የእግር ኳስ ተጨዋቾች  ወይ  ለኢትዮጵያ  ቡና ወይ ለቅ/ጊዮርጊስ ገብተው ስለመጫወት ያልሙ ነበር።  የአንተ ግብህ የሆነው ይሄ  ብቻ  ነው?

ገዛኸኝ፦ አይደለም፤ እኔ ከሀገር ውጪ ወጥቶ ስለመጫወትም ነው የማስበው። ለሀገሬ ብሄራዊ ቡድን መጫወትም ሌላው  እልሜ ነው። ለእነዚህም የወደፊት ግቦቼ ፈጣሪ ይርዳኝ።

ሊግ፦ ብዙ ጊዜ ግራኝ እግር ኳስ ተጨዋቾች ቀኝ እግራቸው መቆሚያ  ነው ብቻ  ሲባል ይሰማል፤ የአንተም ነው?

ገዛኸኝ፦  /እንደ መሳቅ ካለ  በኋላ/   ኸረ   እኔ እስካሁን ድረስ  እጫወትበታለው።  ከውጪ  ለሚታየው ሰው  አይታወቅም። ለእኔ ፓስ ማድረግ አይከብደኝም። ጥሩም ነኝ። እንደ ሌሎች ግራኝ ተጨዋቾችም ራሴን አላስብም።

ሊግ፦  በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ  ለአንተ  ምርጡ ቡድን ማን ነው?

ገዛኸኝ፦ ለራሳችሁ አደላክ ካላልከኝ እና  ከያዝነውም ጥልቅ ያልሆነ የተጨዋቾች ስብስብ አኳያ እንደ አምናው ባንሆንም  አሁንም የእኛን  ቡድን  ቡናን ነው በሜዳ ላይ  እንቅስቃሴው ምርጥ የምለው። ከእኛ ሌላ ፋሲል ከነማዎችም ጥሩ ናቸው።

ሊግ፦  በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ እና ደካማው ጎናችሁ ምንድን ነው?

ገዛኸኝ፦ ጠንካራው ጎናችን ኳስ ይዘን መጫወታችን ነው።  ደካማው ጎናችን ደግሞ አልፎ አልፎ   የምንሰራቸው ስህተቶች አሉ  እነዛን  አርመን  እንመጣለን።

ሊግ፦ ለኢትዮጵያ  ቡና  ረጅም ዓመታት ትጫወታለህ?

ገዛኸኝ፦ አዎ፤ እጫወታለሁ  ብዬ አስባለው። ከመጫወት ውጪም ጫማዬን ብሰቅልም ደስ ይለኛል።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር  ሊጉ  ዘንድሮ በጣም ያስደሰተክ  እና ያስቆጨ ጨዋታ የቱ ነው?

ገዛኸኝ፦  በጣም  ያስቆጨኝ  ጨዋታ  በባህርዳር ስታዲየም ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረግነውን  ነው።  ጨዋታውን 1-0 ተሸንፈንበታል።  ይህ ጨዋታ ያናደደኝም እነሱ አብዛኛውን የጨዋታ ሰዓት ሜዳ ላይ እየወደቁ ሰዓት ይገሉ ስለነበርና ከእዛም ውጪ  በመጨረሻው ሰዓት ላይ  በፔናሊቲ ግብ  ስላስቆጠሩብንም  ጨምር  ነው። በጣም ያስደሰተኝ ጨዋታ ደግሞ  ከወልቂጤ ከተማ ጋር ተጫውተን 4-3 ያሸነፍንበት ጨዋታ ነው።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዘንድሮ ለአንተ  ጎልቶ የወጣብህ  ተጨዋች ማነው ?

ገዛኸኝ፦   አቡበከር ናስር እንዳለ ሆኖ የፋሲል ከነማው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሱራፌል ዳኛቸው ሌላው  ጥሩ ሆኖ ያገኘሁት ተጨዋች ነው።

ሊግ፦  የኢትዮጵያ  ቡናን የተጨዋቾች  ስብስብ በተመለከተ ምን ትላለህ?

ገዛኸኝ፦  የዘንድሮ  የተጨዋች  ስብስባችን ያን ያህል  ምርጥ የሚባል አይደለም።  ለዛም ነው በምንፈልገው ደረጃ ውጤትን  ልናመጣ ያልቻልነው። በተሰጠን ልክም ነው ውጤት እያመጣን የምንገኘው።

ሊግ፦  የኢትዮጵያ  ቡና የካምፕ ጓደኛህ ማነው?

ገዛኸኝ፦ ብዙ ናቸው።

ሊግ፦ ከእግር ኳሱ ውጪ የእረፍት ጊዜህን በምን ታሳልፋለህ?

ገዛኸኝ፦ በካፌ ውስጥ  ከጓደኞቼ ጋር በመሆንና በመጨዋወት ነው የማሳልፈው።

ሊግ፦  ለኢትዮጵያ  ብሄራዊ ቡድን ተመርጦ የመጫወት ፍላጎትህ የቱን ያህል ነው?

ገዛኸኝ፦  በጣም ከፍተኛ ነው። ለሀገር  ከመጫወት ውጪ ምን የሚያስደስት ነገር አለ።

ሊግ፦ በህይወት ዘመንህ አስደሳች እና  አሳዛኝ ገጠመኝህ ምንድን ነው?

ገዛኸኝ፦  በጣም  አስደሳቹ  ገጠመኜ  ለኢትዮጵያ  ቡና አድጌ ስፈርም ሲሆን  ያዘንኩበት ሁኔታና ገጠመኜ ደግሞ በተስፋ ቡድን ውስጥ ሳለሁ  የኳስ ፍቅሬ ከፍተኛ ቢሆንም ከቡድኑ ስባረር   በቃ ኳስ ላቆም ነው በሚል ላዝን ችያለሁ፤  ያ ካለፈ በኋላ ግን የእግዚአብሔር  ፈቃድ  ሆኖ  ወደ ተጨዋችነቱ ተመልሻለሁ።

ሊግ፦ የኢትዮጵያ  ቡና ደጋፊዎች በተለየ መልኩ የሚገለፁ ናቸው?

ገዛኸኝ፦ አዎ፤ እነሱ ማለት እኮ ዝናቡ፣ ብርዱ፣ ፀሀዩ ሳይበግራቸው ቡድናቸውን የትም ክልል ሳይቀሩ የሚደግፉ ናቸው።  በእዛ ላይ ህብረ ዝማሬያቸው ደስ ይላል።  ስለ እነሱ ለማውራት ቃላቶችም ያንሱኛል።

ሊግ፦  የእንግሊዝ  ፕሪምየር  ሊግ እና  የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፤ ማንቸስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ድሉ ይገባቸዋል?

ገዛኸኝ፦  ማን. ሲቲ ይገባዋል ብዬ ነው የማምነው። ሪያል ማድሪድን  ግን በተቃራኒው። ሊቨርፑል ቢበላው ደስ ይለኝ ነበር።

ሊግ፦ ፋሽን ተከታይ ነህ?

ገዛኸኝ፦ ብዙም  አይደለሁም። እንደ ወጣት መልበስ ብፈልግም  ለአለባበሴ  አልጨነቅም።

ሊግ፦ በእግር ኳሱ እዚህ ደረጃ ላይ ደረስክ፤ እነማን ይመስገኑልህ /ይወደሱልህ/?

ገዛኸኝ፦ የማመሰግናቸው  በመጀመሪያ ደረጃ  በአስኮ ፕሮጀክት  ያሰለጠኑኝን እነ አብይ እና ደስታን ከዛ  በመቀጠል ደግሞ በትጥቅ ያግዙን የኘበሩትን የአስኮ ጤና ቡድንን  እና አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬንና ካሳዬ አራጌን እንደዚሁም የኢትዮጵያ  ቡና ደጋፊዎችን ለማመስገን እፈልጋለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P