Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የእግር ኳስ ተጨዋች ስትሆን ሁሌም ጠንክረህ መስራት እንጂ በስምና ዝና ብቻ መሸወድ የለብህም” ሀብታሙ ታደሰ (ኢት.ቡና)

በመሸሻ ወልዴ


ኢትዮጵያ ቡናን ዘንድሮ ተቀላቅሎ ውድድሩ በኮቪድ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ ለክለቡ ስኬታማ እንቅስቃሴን እያሳየ ይገኛል፤ ተጨዋቹ ሀብታሙ ታደሰ ይባላል፤ ጥሩ ችሎታና አቅም እንዳለውም በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ላይ ለማሳየት ችሏል፤ ይሄ ወጣት ተጨዋቾች በኳሱ ጥሩ ደረጃ ለመድረስ ካለው ፍላጎት በተጨማሪ የእግር ኳስ ተጨዋቾችንም ለታላቅ ደረጃ ለመብቃት እንዲችሉ ስምና ዝና አይሸውዳቸውም ብሎ ይናገራል፤ ከተጨዋቹ ጋር ያደረግነው ቆይታ ይሄን ይመስላል፡፡


ሊግ፡- በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግንሃለን?
ሀብታሙ፡- እኔም አክብራችሁ እንግዳችሁ ስላደረጋችሁኝ በጣም አመሰግናችኋለሁ፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ 19 እግር ኳሳችን ከቆመ አሁን ላይ አራት ወራት አስቆጥሯል፤ ያለ ኳስ ለእዚህን ያህል ጊዜ መቆየት መቻል ምን ስሜትን ፈጥሮብሃል?
ሀብታሙ፡- ብዙ ነገሮችናቸውበውስጤ የተፈጠረብኝ፤በእዚህ ወረርሽኝ ኳሱ በመቆሙ ምክንያት ከእኛ በላይ ብዙ የተጎዱ ሰዎች ሞልተዋል፤ ያጡም አሉ፤ ከዛ በተጨማሪ ደግሞ መጀመሪያ ወደ እግር ኳሱ ስትመጣም ኳስ ሁላችንንም አንድ ያደርገናል፤ ብዙ ነገሮችንም ያስተካክልልናል፤ ቤተሰብ እና ፍቅር እንዲኖረንም ያደርገናልና ከእዚህ ከምትወደው ከምታከብረው ስራለወራቶች ያህል ስትገለል ከፍተኛ ጫና ይፈጠርብሃል፤ ያም ሆኖ ግን ነገ የተሻለ ቀን ስለሚመጣ የእግር ኳሳችንን መጀመራችን አይቀሬ ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- በኳስ ለእንደዚህን ያህል ጊዜ ርቀህ ታውቃለህ?
ሀብታሙ፡- በፍፁም ርቄ አላውቅም፤ በተለይ ለእዚህን ያህል ጊዜ ከኳሱ ለመራቅ መቻል ለተጨዋቾች ኳሱ እንጀራችን ስለሆነና ጫናም ስላለው በጣም ይከብዳል፤ ሁኔታውንም እንዲህ ብሎ መግለፅም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- የኳሱን መቆም ተንተርሰው ደመወዝ የሚከፍሉ እና የማይከፍሉ ክለቦች አሉ፤ በዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ?
ሀብታሙ፡- በደመወዝ ክፍያው ዙሪያ እኔ ስለማውቀው ክለቤ ነው ለመናገር የምፈልገው፤ ቡናበተስማማነው መሰረት ደመወዛችንን እየከፈለን ይገኛል፤ ቡድንህ ደመወዝ ሲከፈልህም ከጫና ነፃ ትሆናለህ፤ አህምሮህንም እንድታረጋጋና እንድታሳርፈውም ያደርግልሃል፤ ከእዚህ ጋር በተያያዘ ጨዋታ በነበረ ጊዜ ደመወዝ የማይከፍሉ ክለቦች እንደነበሩም እናውቃለን፤ ያም ሆኖ ግን የእግር ኳስ ተጨዋች ስትሆን አልተከፈለኝም ዝም ብለህ መቀመጥ የለብህምና ለመጪው ጊዜ በተሻለ አቅምና ብቃት ላይ ለመቅረብ ከበፊት በላይ የአካል ብቃትና የትንፋሽ ስራዎችን እየሰራው ነው የሚገኘው፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ 19 የሊጉ ውድድር እንዲሰረዝ ከተደረገ በኋላ አንተን በዋናነት የናፈቀህ ነገር ምንድን ነው?
ሀብታሙ፡- የናፈቀኝ ወደ እግር ኳስ ጨዋታው በመመለስ ከቡድን ጓደኞቼ ጋር በመገናኘት ልምምድን መስራት፤ ከዛም ባሻገር በድጋፍ ድባባቸው በሚያምሩት የቡና ደጋፊዎች ታጅቤም ኳሱን መጫወት፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ለመሆን መቻልህ የተለየ ስሜትን ፈጥሮብሃል? ልጅ እያለህስ ለእዚህ ቡድን እጫወታለሁ የሚል ምኞት ነበረህ?
ሀብታሙ፡- ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት ከልጅነቴ ጀምሮ የነበረ እልሜ ነው፤ በዛ ደረጃም ደርሼ ለእዚህ የሀገራችን ትልቅ ክለብ ለመጫወት እንድችልም የመጫወት አቅሙ ስላለኝ ብዙ ልፋቶችንም አድርጌያለውና በኋላ ላይ ጥሬና ጠንክሬም ሰርቼ በመምጣቴ ለክለቡ ለመጫወት ችያለው፤ ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት መቻል ስለሚሰጠው ስሜት ደግሞ መናገር የምፈልገው፤ ቡና ከስሙ በፊት የሀገሩን መጠሪያ ያስቀደመ ድንቅ ቡድን ነው፤ ከብሔራዊ ቡድን ቀጥሎም /ወደፊት ከእግዚአብሄር እርዳታ ጋር መጫወቴ ስለማይቀር/ ለቡና በመጫወቴም በጣሙን ነው ደስ የሚለኝ፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወትን መቼ የምታሳካው ይመስልሃል?
ሀብታሙ፡- አሁን በያዝኩት አቋሜ ከቀጠልኩኝና ከእዚህም የተሻለ ነገርን ለመስራት ከቻልኩኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን ተመርጬ እንደምጫወት እርግጠኛ ነኝ፤ ያኔም ተመርጬ ስጫወት ደስተኛም ነው የምሆነው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳሱ ካለህ ብቃት በመነሳት አሁን በደረስክበት ደረጃ ዘግይቻለሁ ወይንስ ፈጥኛለሁ ብለህ ታስባለህ?
ሀብታሙ፡- ፈጥኛለሁ ነው የምለው፤ ምክንያቱም እኔ የተወለድኩበት የቡሌ ኦራ አካባቢ ከአዲስ አበባ ከተማ ሩቅ በመሆኗ እና ከዛም ተነስቼ እዚህ በትልቅ ቡድን ውስጥ በመጫወት እየታወቅኩ ያለሁበት ሁኔታ ስላለ ለዛ ነው የኳሱ እድገቴን ፈጣሪ ጭምር ስለረዳኝ ፈጣን ነው ለማለት የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት በጀመርክበት ሰዓት የቱን ተጨዋች ነው አርአያ ያደረግከው?
ሀብታሙ፡- አስተዳደጌ ከስፖርተኛ ቤተሰብ ነው፤ ወንድሞቼም በተለይ ደግሞ ዳግም ታደሰ ለሙገር ክለብ ይጫወት ስለነበርና ሌሎችም የማውቃቸው ለደቡብ ፖሊስ ይጫወት የነበረው ቀነኒ አብደላ እና ሌላው እግር ኳስ ተጨዋች ዮሴፍ ወልደአገኘውም ኳስን ይጫወቱ ነበርና እነሱን አርአያ አድርጌ በማደጌ ነው በኳሱ የተሳብኩት፤ በኋላም ላይ ፈጣሪ በሰጠኝ ብርታት ተነስቼም ነው ወደ ኳስ ተጨዋችነቱም ሙሉ ለሙሉም ዘልቄ የገባሁት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ጨዋታ እንጀራዬ እና መተዳደሪያዬ ይሆናል ብለህ ያሰብክበት ጊዜ መች ነበር?
ሀብታሙ፡- የ10ኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ሰዓት ነው፤ ያኔ ጥሩ ችሎታው ነበረኝና ወደ ቡሌ ኦራ ክለብ ውስጥ በቢጫ ትሴራ በመግባት ለመጫወት ቻልኩ፤ በእዛን ወቅት እኔ በነበርኩበት ሰዓትም ከአዲስ አበባ እና ከሐዋሳም እየመጡ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ስለነበሩና ራሴንም ከእነሱ ጋር በማነፃፀር የምመለከትበት ሁኔታዎች ስለነበርና ያኔ አሰልጣኜ የነበረው በቀለ እልሁም ጥሩ ደረጃ ላይ እንደምደርስ ስለነገረኝና እሱ ባለኝ መሰረትም አቅም እንዳለኝም ስላውቅ በኳሱ ጠንክሬ ከሰራው ትልቅ ደረጃ ላይ እንደምደርስ በማመኔ ኳሱን ሙሉ ለሙሉ እንጀራዬ አደረግኩ፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከማምራትህ በፊት የወልቂጤ ከተማ ተጨዋች ነበርክ፤ በእዛ የነበረህ ቆይታ ምንድን ነበር የሚመስለው?
ሀብታሙ፡- በወልቂጤ የነበረኝ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ለሁለት ዓመት የዘለቀ ሲሆን ቡድኑ ለእኔም ትልቅ ትምህርት ቤቴ ነበር፤ ብዙ ነገሮችን ማለትም በስራህ ምን ያህል የላብህ ዋጋ እንደሚከፈልህም ያየሁበት ቡድኔ ነውና ለእኔ ክለቡን እንደቤቴ ነው የማየው፡፡
ሊግ፡- በሁለት ዓመቱ የክለቡ ቆይታህ ለአንተ ምርጡ ጊዜ የነበረው የቱ ነበር?
ሀብታሙ፡- የሁለተኛው ዓመት ማለትም የዓምናው፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው ዓመት ላይ ብዙም የመጫወት እድሉን አላገኝም ነበር፤ ከዛ ግን ቡድኑ እኔ ላይ ተስፋን አይቶ እንድቀጥል ባደረገኝ የቀጣዩ ዓመት ላይ የጨዋታ ልምድን በሚገባ ስላገኘውና በተደጋጋሚ ጨዋታዎች ላይ ጎሎችን በማስቆጠር እና ለኮከብ ግብ አግቢነቱም በከፍተኛው ሊግ ላይ ስለተፎካከርኩ እንደዚሁም ደግሞ ለጓደኞቼም በርካታ ኳሶችንም ለማቀበል የቻልኩበት ዓመት ስለሆነ ያኔ ጥሩ ጊዜው ለእኔ እሱ ነበር፡፡
ሊግ፡- በወልቂጤ ከተማ ቆይታህ 13 ግቦችን ለማስቆጠር ችለሃል፤ በአንድ ጨዋታ ደግሞ በናሽናል ሲሚንት ቡድን ላይ 6 ግቦችን ልታገባም በቅተሃል፤ ይሄ ብዙም ያልተለመደ ነው፤ ምን ትላለህ?
ሀብታሙ፡- 13ቱን ግቦች ያስቆጠርኩት በ9 ጨዋታዎች ነበር፤ በእነዚህ ጥቂት ጨዋታዎች ይህን በማሳካቴም በጊዜው በጣም ነው ደስተኛ የሆንኩት፤ ሆኖም ግን በአንድ ጨዋታ 6 ግቦችን ማስቆጠሬን ተንተርሶ ለመናገር የምፈልገው ወደፊት ብዙ ነገሮችን እንደምሰራም ነው የተረዳሁት፤ 6 ግብ በአንድ ጨዋታ በማስቆጠሬ ብዙ ሰው ሊገረም ይችላል፤ የሰው መገረም ሳይሆን እኔ ገና ምንም እንዳልሰራው ስለማውቅና ነገም የተሻለ ነገር እንደምሰራ ስለማውቅ ነው ለቀጣዮቹ ጊዜያት ስኬታማነቶቼ ስል እነዛ ግቦች በደንብ እንድዘጋጅባቸው የሚያደርገኝ፡፡


ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋቾች ጥቂት ስምና ዝናን ሲያገኙ ስለሚሆኑት ነገር አስተውለህ ታውቃለህ?
ሀብታሙ፡- አዎ፤ ያ ሞራልና እውቅና ማግኘትም ሸውዷቸውም ተመልክቻለው፤ እኔም እንደዛ ብሆን እነዛን ያህል ግቦች ሳስቆጠር እሸወድ ነበር፤ ምክንያቱም ከፌዴሬሽን በጊዜው በአንድ ጨዋታ ያን ያህል ግብ ሳስቆጥር የተሰጠኝ ምንም አይነት ሰርተፊኬት አልነበረም፤ ቢሰጠኝ ሞራል ይሆነኝ ነበር፤ ግን እኔ በትልቁ ሊግ ላይ የምሰራቸው በርካታ ስኬቶች ስለሚኖሩ እነዛን እየጠበቅኩ ነው የምገኘው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ እግር ኳስ በጥቂት ስምና በዝና ለሚያምኑ ተጨዋቾች የምትላቸው ነገር ይኖራል?
ሀብታሙ፡- በሚገባ! አሁንም ደግሜ መናገር እፈልጋለው ዝናና እውቅና በተለይ ስፖርተኛውን በአንዴ ይሸውዳል፤ ስራህን ሳትሰራ ረስተህ እንድትሄድም ያደርግሃል፤ ከዛ ቀጥሎ ደግሞ እግር ኳስ ብዙ መልፋትንና ላብንም ይፈልጋልና ያን ጠንክረህ በመስራትና በቂ እረፍትንም በማድረግ ነው ልትጓዝ የሚገባህ፤ ስራህን ካላከበርክና ካለፋህ ደግሞ ኮንዲሽን የሚባል ነገር ስላለ የትም መድረስ አትችልም፤ አንድ አንዱ ተጨዋች ደግሞ ስሜ ብቻ ይበቃል ብሎ የሚቀመጥም አለና ይሄ ጥሩ ነገር አይደለም፤ ያን ሲያደርግ ለቡድኑም ለራሱም ስንፍናን እንጂ እውቅናን አይጨምርለትም፡፡ ከዛ ውጪም ዛሬ ያጨበጨበልህ ሰው ነገ መሳደቡ አይቀርምና ሁሌም ለማስጨብጨብ መልፋት አለብህ፡፡
ሊግ፡- ኳስን በግምባር ገጭቶ የማስቆጠር ከፍተኛ ብቃት አለህ፤ ይሄ ከልምድ የመጣ ነው?
ሀብታሙ፡- በወልቂጤ ከተማ ውስጥ በነበረኝ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ በጭንቅላቴ በመግጨት ጎል ያስቆጠርኩባቸው ጊዜያቶች በተለያዩ ግጥሚያዎች 6 ናቸው፤ ወደ ቡና ከመጣው በኋላ ደግሞ አንድ ጎልን በተሰለፍኩባቸው ጥቂት ጨዋታ ላገባ ችያለውና እነዛን ላሳካ የቻልኩት ሙሉ ተጨዋች መሆን አለብኝ በሚል ሁሉም ላይ ጠንክሬ ስለሰራው ነው፤ በቡና ቆይታዬ ግን ከመስመር እየተነሳው ስለምጫወት ነው እንደበፊቱ ወልቂጤ እንደነበርኩት ያህል ተደጋጋሚ ግቦችን ሳላስቆጥር የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- በችሎታህ አሁን ላይ ምን ይጎድልሃል?
ሀብታሙ፡- በእግር ኳሱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ የሚቀሩኝ ነገሮች አሉ፤ በተለይ ደግሞ ብዙ ልምድ የለኝምና አቅሜን ቆጥቤ መጫወት አልቻልኩም፤ አሰልጣኛችን ካሳዬም ይሄን ነገር በሚገባ ነግሮኛልና በቀጣይ ጊዜ ከጨዋታ ወደ ጨዋታ በምጓዝበት ሰዓት እነዛን የሚጎድሉኝን ነገሮች አሻሽላቸዋለው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና ቆይታህ አዲሱን አሰልጣኝ እንዴት አገኘኸው? ስለ ቡድናችሁ የውድድር ዘመን ቆይታስ ምን የምትለው ነገር ይኖርሃል?
ሀብታሙ፡- ቡና በሁሉም ነገር ማለት ይቻላል ዘንድሮ በአዲስ መልክ የተዋቀረ ክለብ ነበር፤ አዲስ የጨዋታ ታክቲክንም ይዞ ነበር የመጣው፤ ከጨዋታ ወደ ጨዋታም ተግባብተንና ተሻሽለንም ነበር፤ እንደ ግል ሳይሆን እንደ ቡድንም ሲጫወት ቆይቷልና የነበረን የውድድር ዘመን ቆይታ ጥሩ የሚባል ነው፤ አሰልጣኙን በተመለከተም ሁላችንንም ኳሱን በእውቀት እንድንጫወት ያደረገን ስለሆነ ከእሱ ጋር ተመቻችተንም ነው የነበርነው፡፡
ሊግ፡- ከእግር ኳስ ውጪ የተለየ አዋዋል ነው የነበረህ?
ሀብታሙ፡- አዎን፤ በድግሪ ደረጃ በሰርቬይንግ ሙያ ትምህርትን መማር ጀምሬ ነበር፤ ከኳስ ውጪ በዛ ነበር ጊዜዬን አሳልፍ የነበረው፡፡ ይሄን አስመልክቶም አንድ ነገር መናገር የምፈልገው የእግር ኳስ ተጨዋቾች ነገ የሚገጥማቸው ነገር ስለማይታወቅ ጎን ለጎን ትምህርት ቢማሩ ጥሩ ነው፡፡
ሊግ፡- በዓለም አቀፍ እግር ኳስ የማን ክለብ ደጋፊ ነህ? የምታደንቀውስ ተጨዋች?
ሀብታሙ፡- የአርሰናል ደጋፊ ነኝ፤ የሮናልዲኒኦም አድናቂ ነኝ፤ ሮናልዲኒኦ ግን ስምና ዝና አታሎት ካለው ችሎታ በላይ ባለመጓዙ የሚያናድደኝ ነገር አለ፤ ለዛም ነው ተጨዋቾች በስምና ዝና አይታለሉ የምለው፡፡
ሊግ፡-በሙዚቃው ዓለም የማን አድናቂ ነህ?
ሀብታሙ፡- ከውጪዎቹ የዳይመንድ ከእኛ ሀገር ደግሞ አስጌ ደስ ይለኛል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችን በምን መልኩ ትገልፃቸዋለው?
ሀብታሙ፡- ደጋፊው ከቤተሰብ በላይ ነው፤ በማህበራዊ ህይወትም አብረውክ ነው ያሉት፤ በሜዳ ላይ መደገፍ ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገር ላይ ስለሚሳተፉም ደስ ይሉኛል፤ ለእኛ ለሚያደርጉት ነገር ሁሉም ሊመሰገኑም ይገባል፡፡
ሊግ፡- ከማን ጋር ተጣምረህ መጫወትን ትመኛለህ?
ሀብታሙ፡- ከቡድናችን አጥቂ አቡበከር ናስር ጋር፤ ከእሱ ውጪም ሚኪያስም አለ ታፈሰም አለ፤ ብዙዎቹም የፈጠራ አቅም ስላላቸው ከእነሱ ጋር በመጫወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ስለማንሳት ምን ትላለህ?
ሀብታሙ፡- ይሄን ዋንጫ በተመለከተ ዘንድሮ በውጤት ደረጃ ከመሪዎቹ ጋር ብዙም በነጥብ የተራራቅንበት ሁኔታ ስላልነበር የሚመጣው ነገር አይታወቅም ነበር፤ ዋንጫውን ለማንሳትም ነበር ዘንድሮ ስንጫወት የነበረው፤ ይሄን የሊግ ዋንጫ ስለማንሳት በተመለከተ አንድ ቀን እልሜን ማሳካቴ አይቀርም፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…?
ሀብታሙ፡- በእግር ኳሱ ጥሩ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ ነገር ይጠብቀኛል፤ ለዛም ጠንክሬ እሰራለው፤ እስካሁን ግን እዚህ ለመድረሴ የረዱኝን ቤተሰቦቼን የልጅነት አሰልጣኜን ተከተል ወሰንን፤ ወደ ወልቂጤ ያስገባኝን አዲሴ ካሳንና በቀለ እልሁን አመሰግናቸዋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P