Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የዋልያዎቹ  ጉዞ  እስከየት ድረስ?  ከዝምባቡዌው ድል በኋላ የቡድኑ ተጨዋቾች ይናገራሉ”ድላችን  ጣፋጭ  ነው፤  አሁን ላይ የሚያስፈራ  ቡድን  አለን”ታፈሰ ሰለሞን

 

ሊግ፡- በዓለም ዋንጫው የማጣሪያ ጨዋታ ዝምባቡዌን አሸንፋችኋል፤ ግጥሚያው ምን መልክ ነበረው? ደስታችሁን በተመለከተ ደግሞ ልዩ እንደነበርም ሰማን?

ታፈሰ፡-  መጀመሪያ ወደ ጨዋታው ሳመራ ከዝምባቡዌ አቻችን ጋር የነበረን የማክሰኞ ዕለቱ ፍልሚያ ለእኛ በጣም ጥሩ የነበረና ግጥሚያውንም እንደምናሸንፍ አስቀድመን ያወቅንበትም ነው፤ ይህ ጨዋታ ከመከናወኑም በፊት ከጋና ጋር አድርገነው የነበረውን ጨዋታ ጥሩ ተጫውተን መሸነፍ ሳይኖርብን ተሸንፈንበት ስለነበር በዛ የቁጭት ስሜት ውስጥ ነበርን፤ በቀጥታም ለቀጣዩ ጨዋታ ስንመጣም ይህን ግጥሚያ የግድ ማሸነፍ አለብን በሚል ከፍተኛ የሞራል ተነሳሽነት ወደ ሜዳ ስለገባንና አሰልጣኛችንም ውበቱ አባተ ደግሞ ስለተጋጣሚያችን ወደዚህ ጨዋታ የሚመጡት የመከላከል አጨዋወትን መርጠው መሆኑን ስለነገረን ከዛ በመነሳት ነው በጥሩ የኳስ ቅብብል ጫናን ፈጥረን ለመጫወት ስለቻልን ባገኘነው የፍፁም ቅጣት ምት ጎል ተጋጣሚያችንን ልናሸንፍ የቻልነው፤ ከጨዋታው በኋላ ደግሞ ይህን ግጥሚያ በድል ለማጠናቀቅ በመቻላችን የተሰማን ከፍተኛ የደስታ ስሜት በእኛ ቡድን ተጨዋቾች ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የቡድኑ አባላቶች ላይም ነው ሊፈጠር የቻለው፤ ከዛ ባሻገርም ውጤቱ መላው ህዝባችንንም ሊያስደስት የቻለበት አጋጣሚም ስለተፈጠረ ለእዚህ ላበቃን አምላክ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይግባ እላለው፡፡

ሊግ፡- በጋና ቆይታችሁ ሽንፈትን አስተናግዳችሁ ተመለሳችሁ፤ አሁን ደግሞ ዝምባብዌን አሸነፋችሁ፤ ይህን የድል ውጤት ያመጣችሁት በአጨዋወት ደረጃ በተለየ መልኩ ስለቀረባችሁ ነው?

ታፈሰ፡- እንደዛ እንኳን አይደለም፤ ግን ያሻሻልነው ነገር ነበር፤፤ ይህም የጋናው ጨዋታ ላይ ኳሱን እንቆጣጠርና  ወደ እነሱ ጎል ብዙ አንሄድም ነበር፤ ኳሷን ፖሰስ ብቻ ነበር የምናደርጋት፤ የአሁኑ ጨዋታ ላይ ግን ኳሱን ተቆጣጥረንና በተለይም ደግሞ የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተጭነን ስለተጫወትን ግጥሚያውን ለማሸነፍ ችለናል፡፡

ሊግ፡- ዋልያዎቹ ድል ባደረጉበት የማክሰኞ ዕለቱ ጨዋታ ዋንኛው የቡድኑ አስጨፋሪና አነቃቂ አንተ እንደነበርክ ሰማን?

ታፈሰ፡- የእውነት ነው፤ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ደስታችን ከልክ ያለፈ ስለነበርና ግቧን ያስቆጠርንበት ሰዓትም በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ የተገኘች ስለነበር የእኔም ስሜት ላቅ ያለ ሆኖ ነው ስለ ሀገራችን የሚገልፅን ጭፈራ በማውጣት ተጨዋቾቻችንን ሳስጨፍራቸው የነበርኩት፤ በዛ አስጨፋሪነቴም ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተም የ200 ብር ልሸለም ችያለው፤ በዚህ ዙሪያ ዋናው ስለተሸለምኩት ብር ሳይሆን በእያንዳንዳችን ተጨዋቾች ላይ የነበረው ስሜት በጣም ደስ እና ለየትም የሚል ነበርና የእዛን ዕለቱ ምሽት የማይረሳኝ ነው፡፡

ሊግ፡- ምን እያልክ ነበር ያስጨፈርካቸው?

ታፈሰ፡- “ና በለው! ኢትዮጵያ፤ ና በለው ኢትዮጵያ” እያልኩ ነው ሀገራችንን በሚያነቃቃ መልኩ ቡድናችንን እያወደስኩ ሳስጨፍር የነበርኩት፡፡

ሊግ፡- ዝምባብዌን ማሸነፍ መቻላችሁ ተገቢ ውጤት ነው?

ታፈሰ፡- አዎን፤ በጨዋታ እንቅስቃሴም ሆነ የግብ እድልን በመፍጠሩ በኩል  በልጠናቸው ስለተጫወትን ውጤቱ ይገባናል፡፡

ሊግ፡- የድል ግቡን ለማስቆጠር የመጨረሻ ደቂቃን ጠብቃችኋል፤ እስከዛ ሰዓት ድረስ ይሄዳል ብላችሁ ጠብቃችሁ ነበር?

ታፈሰ፡- በፍፁም፤ እኛ እንደውም በዕለቱ ከነበረን እንቅስቃሴና ካደረግነው ሙከራ አንፃር እስከ 3 የሚደርስ ጎልን ጠብቀን ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ኳስ ነውና እነዛን ሳናሳካ ቀረንና በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ ባገባናት ጎል ለማሸነፍ በቃን፡፡

ሊግ፡- ዋልያዎቹ ተሻሸለዋል ማለት ይቻላል?

ታፈሰ፡- አዎን፤ በተለይ ለአፍሪካ ዋንጫው ካለፍን በኋላ ለውጥ አለን፤ መሻሻሎችንም እያሳየን ነው፤ ብዙ ቡድኖችም ከእኛ ጋር ሲጫወቱ ሲቸገሩም እየተመለከትን ነው፤ ከዚህ በፊት በነበረው የኢትዮጵያ ቡድን ላይ ብዙ ጎል ይቆጠራል ተብሎ ነበር የሚታሰበው፤ አሁን ላይ ግን ያ በአህምሮአችን ውስጥ ፈፅሞ የለም፤ በስነ-ልቦናው ረገድም ተዘጋጅተን ወደ ሜዳ ስለምንመጣም ብዙ ነገሮችን እየቀየርንም ይገኛል፡፡

ሊግ፡- እየተሻሻልን መጥተናል ብለካልና የእዚሁ መሻሻል ዋንኛው ምክንያት ምንድን ነው?

ታፈሰ፡- የመሻሻላችን ሚስጥርና ምክንያት ነው ብዬ የማስበው ከዚህ ቀደም ኳስን የምንጫወተው በደመ-ነፍስ ነበር፤ ይሄ ነው የሚባል የጨዋታ ፍልስፍናም አልነበረንም በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጊዜና በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሀላፊነት ዘመን ላይ ግን እየተከተልን ያለው አጨዋወት ጥሩና ከኳስ ቁጥጥር ጋር የተዛመደና አሁን ደግሞ በውበቱ ጊዜ እንቅስቃሴያችን እያደገ በመምጣቱ ካለን የኳስ ስኪል አኳያ በቡድናችን ላይ መሻሻሎችን እየተመለከትን ነው፤ አሁን በያዝነው አጨዋወትም እኛን ንቆ ወደ ሜዳ የሚገባ ቡድን የለም፤ ከጨዋታ በፊትም የተቃራኒ ቡድን ብዙ አሰልጣኞች ጥሩነታችንን እየገለፁም ነው የሚገኘውና ይሄ ደግሞ ለእኛ ትልቅ የሞራል ብርታትም ነው የሚሆነን፡፡

ሊግ፡- በዓለም ዋንጫው ማጣሪያ ምን ውጤትን ለማምጣት ነው የሰነቃችሁት?

ታፈሰ፡- አሁን ላይ ምድቡን ደቡብ አፍሪካ እየመራች ነው፤ እኛና ጋናም እየተከተልን ነው፤ ገና አራት ጨዋታዎች አሉ፤ ከእዚህ በኋላ እኛ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ከመሪዋ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ጋር የደርሶ መልስ ግጥሚያን እናደርጋለንና እሱ ጨዋታ ላይ ነው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን በመመምጣት አስሩ ምርጥ ቡድኖች ወደሚገቡበት ጨዋታ ለማለፍ ጥረትን የምናደርገው፡፡

ሊግ፡- አሁን በምርጥ ብቃትህ ላይ ነው የምትገኘው?

ታፈሰ፡- በምርጥ ብቃቴ ሳይሆን ወደዛ ለመምጣት ነው ጥረትን እያደረግኩ የሚገኘው፤ የእውነት ለመናገር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎዬ ዘንድሮ ጥሩ ነበርኩ፤ ውድድሩ ካለቀ በኋላ ግን በክረምት ወራት ላይ በሳምንት ከምሰራው አንድ ልምምድ ውጪ ሌሎችን ተጨማሪና ብዙ ልምምዶችን ስለማልሰራ ኪሎ የመጨመር ነገር ገጥሞኝ ቀዝቀዝ ብዬ ነበር፤  አሁን ላይ ግን ያ የጨመረውን ሰውነቴን በኮቺንግ ስታፎቹና በዶክተራችን አማካኝነት በመመለስ ወደ ቀድሞ ብቃቴ እየተመለስኩ ነውና ይሄ መሆን መቻሉ አስደስቶኛል፡፡

ሊግ፡- በዝምባቡዌው ጨዋታ  ጉዳትን ያስተናገደው ሽመልስ በቀለን ቀይረህ ነበር ወደ ሜዳ የገባከው፤ በእዛ ዙሪያ ምን አልክ…የሽመልስ የጤንነት ሁኔታስ እንዴት ነው ?

ታፈሰ፡- ሽመልስ በቀለ ጥሩና ዋልያዎቹን በደንብ አድርጎ መጥቀም የሚችል ተጨዋች ነው፤ እሱ ሲጎዳም ነው እኔ ተቀይሬ የገባሁት፤ የዋልያዎቹ የአሁን ስብስብ ላይ እያንዳንዱ ተጨዋች ተቀያይሮና ተተካክቶ መግባት ይችላል፤ ብዙ ጥሩ ተጨዋቾች አሉን፤ ማንም ቢገባ የሚወጣውን ተጨዋች በደንብ ተክቶ መጫወት ይችላል፤ ለምሳሌ ግብ ጠባቂያችንን ተክለማሪያም ሻንቆን ብትወስድ በጋናው ጨዋታ ላይ በተፈጠረች ስህተት ጎል ተቆጥሮበት ለስነ-ልቦናው እንዲያርፍ ሲደረግ ወጣቱ ተጨዋች ፋሲል ገ/ሚካኤል  ተክቶት ጥሩ ተጫውቷልና ይሄ ለቡድኑ ግንባታ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ የሽመልስ ጤንነትን በሚመለከት አሁን ላይ መሻሻል አለው ለክፉ የሚሰጠውም አይደለም፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ?

ታፈሰ፡- ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለው፤ እንኳን አደረሳችሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P