Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ዳዊት ተፈራ /ኦዚል/ “በራስህ ችሎታ እምነቱ ካለህ ቅ/ጊዮርጊስ ገብቶ መጫወት አያስፈራም” “ቅ/ጊዮርጊስ ገብቶ መጫወትን አስብ ነበር፤ ጥሩ አቅሙ ስላለኝ የተሳካ ጊዜያትን አሳልፋለሁ”

 

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ለሲዳማ ቡና በመጫወት ጥሩ ጊዜያትን አሳልፏል፤ ከቁመቱ አጠር ያለውና ቀጠን ብሎም በሜዳ ላይ ኳስን እንደፈለገ አሽሞንሙኖ የሚጫወታት ዳዊት ተፈራ /ኦዚል/ በክረምቱ ወራት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ሻምፒዮኖቹን ቅ/ጊዮርጊሶች በመቀላቀል ወደ ክለቡ አምርቷል። በአሁን ሰዓትም ከታንዛኒያው ሲምባ ቡድን ጋር በአቋም መለኪያ ለሚጫወተው አዲሱ ቡድኑም ልምምዱን እየሰራ ይገኛል።

የቅ/ጊዮርጊሱ አዲሱ ፈራሚ ዳዊት ተፈራ /ኦዚል/ ከጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ስላለፉት ዘመኖቹ የእግር ኳስ ጉዞው፣ ስለ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎአቸው እና ስለ አዲሱ ቡድኑ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበንለት የሰጠንን ምላሽ በሚከተለው መልኩ አቅርበንሎታል።

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ ውድድር እንዴት አለፈ?

“የሊጉን ውድድር ስንጀምር ዋንጫ ለማንሳት ነበር። ያም ሆኖ ግን ይሄ ጉዞአችን  ለእኛ በፈለግነው መልኩ ባይሄድልንም የሶስተኛ ደረጃን ይዘን ማጠናቀቃችን በራሱ  መጥፎ የሚባል ውጤት አይደለም”።

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሲጀመር የተጠባባቂ ተጨዋች ስለመሆኑና በኋላ ላይ ደግሞ የመሰለፍ ዕድልን ስለማግኘቱ

“በእዛን ሰዓት ለመቀመጤ ምክንያት ሆኖኝ የነበረው አስቀድሞ  ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ለሆነው ብሄራዊ ቡድን በተመረጥኩበት ሰዓት ትንሽ ድካም ስለነበረብኝና በመሀልም ጉዳት አጋጥሞኝ ስለነበር በቅድሚያ ሙሉ ሲቲ ካፑን ሳልጫወት ቀረው፤ በኋላም ላይ ከጉዳቴ እስካገግም ድረስም የተጠባባቂ ተጨዋች በመሆን ተቀይሬ  እየገባሁ ልጫወትም ቻልኩና በቂ ዝግጅትን ስላልሰራው እና ትንፋሼ እስኪመለስም ነበር ተጠባባቂ የነበርኩት።  ከእዛን በኋላ ግን በቋሚነት የተጫወትኩባቸውም ግጥሚያዎች ነበሩ”።

ባሳለፈው የእግር ኳስ ህይወት ደስተኛ ስለመሆኑ

“አዎን በጣም ደስተኛ ነኝ፤ በሲዳማ ቡና ቤት አራት ዓመታት ቆይታን አድርጌያለሁ፤ በእነዚህ ጊዜያቶች ውስጥም ክለቡ ከፍተኛ ያስመዘገበው  ውጤት አራተኛ ደረጃ ነበር። በኋላ ላይ ግን ሁለተኛም  ሶስተኛም  ሆነን ሊጉን ለማጠናቀቅ ችለናል። ሌላው ደግሞ ይሄ ክለብ በታሪኩ ቅ/ጊዮርጊሶችን አሸንፎ አያውቅም ነበር። እኔ ከመጣው በኋላ  ግን ልናሸንፈው ችለናልና በነበርኩባቸው ዓመታቶች ጥሩ ጊዜን ላሳልፍ ችያለው”።

የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ለአንተ ከፍተኛ አድናቆት አላቸው፤ ከእዚህ ቀደም ለጅማ ስትጫወት አንድ ደጋፊ እኔን ከማድነቁ የተነሳ የውስጥ እግሬን ሊስም ችሏል ብለህ ነበር። በሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ በተመሳሳይ ወይንም በሌላ የአድናቆት አገላለፅ ያጋጠመ ነገር አለ?

“በሲዳማ ቡና ቆይታዬ እኔን ያጋጠመኝ ደጋፊዎቹ ለእኔ ካላቸው ትልቅ ቦታ አንፃር አቅፈውኝ ሲስሙኝ የተመለከትኩበትን ነው። ከቡድኑ እንድወጣባቸውም አይፈልጉም። ሊጉ ከተጠናቀቀ በኋላ እንኳን ከክለቡ እንዳልወጣባቸው ባህርዳር ድረስ በመምጣት ሲለምኑኝም ነበርና እነዚህ ሁኔታዎች በጣሙን ገርመውኛል”።

ከሲዳማ ቡና በመልቀቅህ እነሱ ጋር ስላለው የተለየ ስሜት

“በአንድ በኩል ደስተኛ የሆኑበትን ሁኔታም ልመለከት ችያለሁ። ምክንያቱም በቡድኑ ቆይታዬ በጥሩ መልኩ አገልግዬአቸዋለውምና”።

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በዲ. ኤስ. ቲ ቪ ስለመተላለፉ

“የዲ. ኤስ. ቲቪ መምጣትና በቀጥታ ስርጭትም የጨዋታዎቻችን መተላለፍ በተለይ ለእኛ  ሀገር። ኳስ ተጨዋቾች በጣም አሪፍ ነው። ምክንያቱም ከእዚህ ቀደም ጥሩ ብቃት ኖሮ ለብሄራዊ ቡድን አትመረጥም ነበር። አሁን ግን ጥሩ ችሎታ ካለህ ጨዋታዎቹ በደንብ ስለሚታዩ ትጠራለህ በብቃትህ ከአንድ ቡድን ወደ ሌላኛው ቡድን እንድታመራም ያደርግሃል። ከእዛ ውጪ ወደ ባህርማዶ ሄደህ የሙከራ ዕድልን እንድታገኝም ሁኔታዎችን ያመቻችልሃልና  ጥቅሙ በጣም የጎላም ነው”።

ለብሄራዊ ቡድን ተመርጦ በመጫወቱ ዙሪያ ከወዲሁ  ምን ነገሮችን ታስባለህ?

“በሲዳማ ቡና ቤት ጥሩ ጊዜን አሳልፌያለሁ። ብሄራዊ ቡድን ግን አንተ ስለፈለግክ ብቻ የሚሆን ነገር አይደለም። እኔ ለራሴ ሁልጊዜ ጥሩ ነኝ ብዬ አስባለሁ። ጥሩ ስለሆንኩ ብቻ እመርጣለሁ አልልም። አሰልጣኝ ሁሌም የራሱ የሆነ ስትራቴጂ አለው ዛሬ ባልመረጥ ነገ ተራው የእኔ ይሆናል ብዬ ስለማስብ እና አንድ ቀን ደግሞ እንደ ሌሎቹ ተጨዋቾች ሀገሬን የማገልገል ፍላጎት ስላለኝ ያን አጋጣሚ ማሳካቴ የማይቀር ነው”።

ቀጠን ስላለው  የአካል ብቃቱ እና በሜዳ ላይ ኳስን ሲጫወት  በአህምሮ ፈጣን ስለመሆኑ

“ብዙ ጊዜ ሊጉን ተዟዙረን ስንጫወት ከድካም የተነሳ  ትንሽ ያስቸግረኝ  ነበር። ከእዛ ውጪም ኳስ ችለህ ከሰውነትህ ደቀቅ ካልክ የማትፈርምበትም ሁኔታ አለ። አሁን ላይ ግን የፈለገ የሰውነት ብቃት ይኑርህ ጨዋታዎቹ በዲ ኤስ ቲ ቪ ስለሚተላለፉ በአካል ብቃቱ በኩል ለእኔ ያስቸገረኝ ሁኔታ ምንም የለም። እንደውም አካል ብቃቴን በጣምም እየወደድኩት ነው። ምክንያቱም ፍሌክሴብል ሆኜም እየተጫወትኩ ነው። በአህምሮዬም የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ኳሶችን በመመልከትም ቀድሞ ምን ማድረግ አለብኝ ብዬም በማሰብና ከራሴም ጋር በመማከር  እየተጫወትኩም ነውና  በእነዚህ  ሁኔታዎች ነው በመጓዝ ላይ ያለሁት”።

ወደ ትልቅ ቡድን ውስጥ እገባለሁ የሚል የበፊት እቅድ እና ራዕይ ነበረህ?

“አዎን፤ እኔ  ሁልጊዜ የተሻልኩ  ተጨዋች ነኝ ብዬ ነው የማስበው። ካለኝ ጥሩ አቅምና ችሎታ አንፃርም የተሻለ ቡድን ይገባኛል ብዬም ነው ለራሴ የምነግረው። ይህን ወደ ትልቅ ቡድን ውስጥ ገብቶ መጫወትን ደግሞ ዛሬ ሳይሆን ጅማ በነበርኩበት ሰዓት ነው ያሰብኩት። ቅ/ጊዮርጊስ ገብቶ መጫወትም እልሜ ነበርና አሁን ላይ ወደ ቡድኑ ስላመራሁኝ በጣም ነው ደስ ያለኝ”።

ስለ ቅ/ጊዮርጊስ ምን ምን ነገሮችን ታውቅ ነበር? ወደ ቡድኑ በመምጣትህ የተለየ የሆነብህ ነገርስ ካለ

“የሊጉን ውድድር በፊት ሳይ ቅ/ጊዮርጊስ ስለነበረው ሀያልነት እና አቅሙ በደንብ አውቅ ነበር። ትላልቅ ተጨዋቾችም ነበሩት። ከእነዛ ልጆች መካከልም እነ ሳላህዲንን በደምብ አውቃቸውና አደንቃቸውም ነበር። በእዚሁ አጋጣሚ ከሳላህዲን ሰይድ ጋር በሲዳማ ቡና ቤት ውስጥ አግኝቼው ስለተጫወትኩም በጣም ዕድለኛ ነኝ። ከእዛ ውጪ በቅ/ጊዮርጊስ ቡድን ውስጥ ሌሎችን ተጨዋቾችም የማየት ዕድሉን ያገኘሁበት አጋጣሚ ስላለና እነሱ የደረሱበት ደረጃም መድረስን ስለምፈልግ ለእዛ ለመብቃት ጠንክሬ እሰራለሁ”።

ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ስታመራና ፊርማህን ስታኖር ስለነበረው አቀባበል

“አሁን ላይ የታንዛኒያውን ሲምባ ለምንገጥምበት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ልምምድን ጀምረናል። ወደ እዛ ሳመራም የተደረገልኝ አቀባበል በጣም ጥሩ እና የወደድኩትም ነበር። ሁላችንም ከእረፍትም  ነበር ለመምጣት የቻልነውና ለተደረገልኝ ጥሩ አቀባበል ክለቡንና ተጨዋቾቹን አመሰግናለሁ”።

በቅ/ጊዮርጊስ የተሳካ  ወይንስ ፈታኝ ጊዜያትን ታሳልፋለህ?

“ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ብዙ ጊዜ ተቃራኒ ሆኜ ተጫውቻለሁ። ያኔ ስጫወትም እንደማንኛውም ተጨዋች ወደዚህ ቡድን ውስጥ ገብቶ የመጫወት እልሜ ከፍተኛ   ነበርና የተሳካ ጊዜያትን እንደማሳልፍ እርግጠኛ ነኝ።  ወደዚህ ቡድን ስታመራም  የተሳካ የኳስ ጊዜያትን ለማሳለፍ በራስህ ልትተማመን ይገባል። ከእዛ ውጪ  ለእዚህ ቡድን የምታደርገው እያንዳንዱ ጨዋታም  የዋንጫም ስለሆነ ጥሩ ጊዜን ነው ከክለቡ ጋር የማሳልፈው”።

ወደ አዲሱ ቡድኑ ማምራትህን ተከትሎ ከክለቡ ሀላፊዎች የተነገረ የተለየ ነገር አለ?

“አዎን፤ ወደዚህ ቡድን ስትመጣ ሁሌም ውጤት ይፈለጋልና ይሄ ተነግሮኛል። እኔም አውቅ ነበር። ጫናም ይኖራል። ይሄን ደግሞ ልትቋቋምም ይገባል። ስለዚህ ቡድን የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ሆኜ ያወቅኳቸው እና ከእነሱም ጋር ስንጫወት በምን መልኩ መጫወት እንዳለብን የተረዳዋቸው  ብዙ ነገሮች ስለነበሩም እነዛን ሁሉ በአዲሱ ክለብ ተጨዋችነቴም የክለቡ ሀላፊዎች የነገሩኝ ነገርም ስላለ ልቋቋማቸው  ዝግጁ ነኝ”።

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ቅ/ጊዮርጊስ ነበር ያነሳው፤ ድሉ ይገባዋል?

“እኔ እንደውም ዋንጫው ይገባቸው ነበር ያልኩት እኛን አዳማ ላይ ባሸነፉን ቀን ነበር። በመሀል ግን ወደ ባህርዳር ካመሩ በኋላ ሊዳከሙ በመቻላቸው ነው የዋንጫ ባለቤትነታቸውን በመጨረሻው ቀን ላይ ሊያረጋግጡ የቻሉትና ድሉ ለቅ/ጊዮርጊሶች ይገባቸዋል”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ ምርጡ ተጨዋች ለአንተ ማን ነው?

“ጥሩ ተጨዋች ያልኳቸው ብዙ ቢሆኑም የሲዳማ ቡናው ይገዙ ቦጋለ እና የቅ/ጊዮርጊሱ ጋቶች ፓኖም ብቃት ግን በጣም አስገርሞኛል። ሁለቱም የተሳካ የውድድር ጊዜያቶችንም ነው ያሳለፉት”።

በሁለተኛው ዙር ተከፍቶ በነበረው የዝውውር መስኮት የሳላህዲን  ሰይድ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ የውድድር ዘመኑን ስለመጨረሱ

“የእሱ መምጣት በጣም አስደስቶኝ ነበር፤ ክለባችንንም በውጤት ደረጃ ጎል እያገባም  ጠቅሟል። በቆይታው ልምዱን ያካፍለን ነበር። ይመክረንም ነበር፤ በእዚህ አጋጣሚ  በጣም ጥሩ ሰው እንደሆነም መናገር እፈልጋለሁ”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ናፍቆሃል?

“አዎን፤ ምንጊዜም ተጨዋች ስትሆን ለታሪክም ለምንም ነገር ስኬታማ ለመሆን ዋንጫ ያስፈልግሃልና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ያመራሁበት አንዱ ምክንያትም ይህን ፈልጌ ነውና ይሳካልኛል ብዬም አስባለሁ”።

ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ስታመራ ስንት ቁጥር መለያ ተሰጠህ?

“እኔ 10 ቁጥርን ብፈልግም ይሄ በቡድኑ ነባር ተጨዋች ስለተያዘ  በክለቡ ውስጥ የቀረው  የ16 ቁጥር  መለያ ነው የተሰጠኝ”።

ቅ/ጊዮርጊስ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮናነቱን ተከትሎ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ ይሳተፋል። ከእዚህ ጋር በማያያዝ የምትለው ነገር ካለ?

“አሁን ላይ ልምምዳችንን ጀምረናል። የአቋም መለኪያ ጨዋታም  ልናደርግ  እየተዘጋጀን ይገኛል። አሰልጣኛችን ጥሩ ልምምድም እያሰራን ይገኛል። ሰውን የሚረዳ አሰልጣኝ ነው ያለን። ለብሄራዊ ቡድን ተመርጠው የነበሩት ተጨዋቾች ደግሞ  ቡድኑን ሲቀላቀሉ ጠንካራውና አስፈሪው ቡድን በአፍሪካ የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎው ላይ ከእዚህ ቀደም ካስመዘገበው  የተሻለ የሚባል ውጤት ይኖረዋል”።

ወደማጠቃለሉ እናምራ

“በእግር ኳስ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረሴ ያሰለጠኑኝን አሰልጣኞች በሲዳማ ቡና ስጫወት የቡድኑን ደጋፊዎችና አመራሮች እንደዚሁም ደግሞ የእኔ አድናቂዎች የሆኑትን ሰዎች እና ቤተሰቦቼን እንዲሁም ጓደኞቼን ማመስገን እፈልጋለሁ”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P