Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ጉረኛ አይደለሁም፤ በሜዳ ላይም ከሜዳ ውጭም ራሴን ዝቅ አድርጌ የምኖር ተጨዋች ነኝ”ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)

“ጉረኛ አይደለሁም፤ በሜዳ ላይም ከሜዳ ውጭም ራሴን ዝቅ አድርጌ የምኖር ተጨዋች ነኝ”

“አቡበከር ልዩና ምርጥ ተጨዋች ነው፤ ሁሌም ከአጠገቤ ሆኖ እንዲጫወትም ተመኝቼዋለሁ”

ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ረቡዕ ከማዳጋስካር አቻው ጋር ላለበት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው እንዲረዳው ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአቋም መለኪያ ግጥሚያውን ረቡዕ ዕለት ያደረገ ሲሆን 4-0ም አሸንፏል፤ የዋልያዎቹን የድል ግብም መስሑድ መሐመድ፣ ጌታነህ ከበደ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና አቡበከር ናስርም ሊያስቆጥሩ ችለዋል፤ ብሔራዊ ቡድናችን ይህን ጨዋታ ሲያሸንፍ በኳስ ቁጥጥሩና የጎል ዕድሎችን በመፍጠር በኩል ከተጋጣሚው የተሻለ የነበረ ሲሆን ጎሎችን ያስቆጠረበት መንገድም የቡድን ስራ የታየበት ስለሆነም እንቅስቃሴው በጥሩነቱ የሚጠቀስም ሆኗል፤ በብሔራዊ ቡድናችን በዚህ ጨዋታ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን ካደረጉት እና ግብም ካስቆጠሩት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነውን ሱራፌል ዳኛቸውን ከእዚህ ጨዋታ ጋር በተያያዘ እንደዚሁም ደግሞ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ አስቀድሞ ከነበረው አቋም አሁን ላይ መሻሻሎችን ስለማሳየቱ እና ከእራሱ ባህሪያት ጋር በተያያዘ እና ከማዳጋስካር ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ጥያቄዎችን አቅርቦለት ምላሾቹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- በፋሲል ከነማ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታህ የ2011ዱ የሀገሪቱ ምርጥ ተጨዋች ተብለህ በኮከብ ተጨዋችነት ተሸልመሃል፤ ብዙዎች ሱራፌል ያንን ብቃቱን ዳግም እያሳየን አይደለም ይሉሃል…ይሄ ያስማማሃል?

ሱራፌል፡-የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የተጀመረበት ሰሞን ጨዋታዎች ላይ የእውነትም እኔ በምፈልገው እና ብዙዎችም በሚጠብቁኝ የአቋም ደረጃ ላይ እግር ኳሱን በቂ በሆነ መልኩ ተጫውቼው ነበር ለማለት ፈፅሞ አልችልም፤ ይሄ ደግሞ የእግር ኳሱ ባህሪይ ይመስለኛል፤ እግር ኳስን ስትጫወት አንዴ ጥሩ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥሩ ላትሆን ትችላለህ፤ ከፍ እና ዝቅ ማለትም ያለ ነው፤ ጥሩ ሳትሆን ደግሞ አንተን የሚተችህም ይበዛል፤ ይሄ ደግሞ እኔንም አጋጥሞኛል፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ያ አስቀድሞ ጥሩ ብቃቱን ያሳይ የነበረው ተጨዋች ወደነበረበት ምርጥ ችሎታው ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ከፍተኛ ዝግጅትን እያደረገ ይገኛል፤ አሁን ላይም በችሎታው ላይ መሻሻሎችን እያሳየም ይገኛል፡፡

ሊግ፡- ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በተጀመረበት ሰሞን በአንተ ዙሪያ እንደዛ ሊባል የቻለው ያንን ያህል ከአቋምህ ወርዶ ስለነበር ነው ማለት ይቻላል?

ሱራፌል፡- በፍፁም፤ በጣም በተጋነነ እና ለየት ባለ መልኩ በችሎታዬ ላይ ጥሩ አለመሆን እኔን በሚባለው መልኩ አላጋጠመኝም፤ ከዛ ይልቅ ብዙ ነገሮች ከእኔ ስለሚጠበቁም ነበር በእኔ ዙሪያ ላይ ብዙ ነገሮችም ሊባሉ የቻሉትና እነዛ ናቸው ከባድ የሆኑብኝ፤ በፋሲል ከነማ ቆይታዬ እኔ ጎሎች እንዳስቆጥር፤ ጣጣቸውን የጨረሱም ኳሶችን ለጓደኞቼ እንዳቀብል እና እንዳዘጋጅ ሁሌም ይፈለጋል፤ የዘንድሮ የውድድር ጅማሬ ላይ ግን ሁሉም ተጨዋች ከሰባት ወራቶች የኮቪድ ወረርሽኝ ርቀት በኋላ ወደ እግር ኳሱ በመምጣት የተጫወትንበት ጊዜ ስለነበርና በእዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ወደምትፈልግበት ብቃትህ ላይ ለመምጣት ብዙ መስራትም ስለሚያስፈልግ በዛ በምታወቅበት ደረጃ ላይም ነው እንዳልገኝ ያደረገኝ እና አንድአንዴ እንዲህ ያሉ ነገሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፤ ከኳሱ በዚህ መልኩ ተለይተህ ስትመጣ የማይሳኩ ነገሮችና በአንተ ላይም ጫና የሚፈጥሩብህ ነገሮችም አሉና እንዲህ ያሉ ነገሮች ናቸው ሊያጋጥሙን የቻሉት፡፡

ሊግ፡- ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ላይ በነበረህ አቋም ለብሔራዊ ቡድን ሳትመረጥ ቀርተህ ነበር፤ አሁን ደግሞ ተመርጠህ በአቋም መለኪያ ጨዋታው ላይ እስከመሳተፍ ጥሩ እስከመጫወት እና ብሎም ደግሞ ጎል እስከማስቆጠር ደረጃም ላይ ደርሰህ ነበር፤ በዚህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር ይኖርሃል?

ሱራፌል፡- ቀደም ሲል በነበረው የብሔራዊ ቡድን ምርጫ ላይ የእኔ በስኳዱ አለመካተት እና ለቡድኑም አለመመረጥ የጠቀመኝ ነገር ቢኖር የራሴን ችሎታ እና ወቅታዊ አቋሜን እንድመለከት ነው ያደረገኝ፤ በዛን ወቅት የሚቀረኝ ነገር እንደነበር እና የራሴንም ችሎታ በደንብ አድርጌም አስተካክዬ መምጣት እንዳለብኝ ስለተረዳው ከዛም ውጪ ደግሞ በስነ-ልቦናው ደረጃም ጠንካራ መሆን እንዳለብኝ ስላውቅኩኝም ነው አሁን ላይ ለውጦችንና መሻሻሎችን በማሳየቴ ዳግም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጠርቼ ልጫወት የቻልኩት፡፡

ሊግ፡- ወደ ጥሩ አቋሜ እየተመለስኩ ነው ብለሃል፤ ምርጡን ሱራፌልንስ መች የምናየው ይሆናል?

ሱራፌል፡- የእግር ኳስ ተጨዋቾች አቋም ከፍና ዝቅ እንደሚል የታወቀ ነው፤ እኔንም ያንን ያህል በተጋነነ መልኩ ባይሆንም ከላይ በገለፅኳቸው ሁኔታዎች አጋጥመውኝ ነበር፤ ወደ ጅማ ካመራንበት የቤት ኪንጉ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ጀምሮ ግን ወደምፈልገው አቋም እና ደረጃ ላይ ለመምጣት በመቻሌ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ከዚህ በኋላም ሌላ የምጠብቀው ነገር አለ፤ ይሄም ምርጡን ተጨዋች ማለትም ከዚህ ቀደም በ2011 ኮከብ ተጨዋች ተብሎ ከተሸለመው ሱራፌል ዳኛቸው የሚሻለውን ራሴን በሜዳ ላይ ማሳየት ነው የምፈልገውና ይሄም የሚሳካ ነው የሚመስለኝ፡፡

ሊግ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ማላዊን በወዳጅነት ጨዋታ ገጥሞ 4-0 አሸንፏል፤ ግቦቹን ካስቆጠሩት ተጨዋቾች መካከልም አንዱ አንተ ሆነሃል፤ በጨዋታው እና ጎልን በማስቆጠርህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?

ሱራፌል፡- ከማላዊ አቻችን ጋር ያደረግነው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ምንም እንኳን ግጥሚያው በእኛ ቡድን የበላይነት እና አሸናፊነት የተጠናቀቀ ቢሆንም እነሱም መጥፎ የሚባሉ አልነበሩም፤ ማላዊዎች ኳስን ይችላሉ፤ ጠንካሮች ናቸው፤ በፊዚካል እና በፍጥነት ደረጃ ደግሞ ከእኛ ይሻሉም ነበር፤ ከዛ ውጪም እኛን በእግር ኳሱ ደረጃ የሚበልጡን ናቸው፤ በእዛን ዕለት ጨዋታ ግን በተወሰነ መልኩ ኳስን ተቆጣጥረው ለመጫወት ቢሞክሩም በዛ ደረጃ እኛ ከእነሱ እንሻል ስለነበርንና ተደጋጋሚ የግብ እድሎችን በመፍጠሩ በኩል ጥሩ ስለነበርን ሌላው ደግሞ ከያዝነው አጨዋወት አኳያም የእነሱ ጡንቻ በጣም ትላልቅ በመሆኑና ያለ ኳስም ብዙ ሮጠው ሊደክሙ ስለቻሉም እነሱን ልናሸንፋቸው ችለናል፤ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብዙ ጊዜ ረጅም ኳስን የሚጫወትና ኳስን የሚጠልዝ ቡድን በጣም ነው የሚቀለው፤ ከማላዊዎች ጋር ግን ስንጫወት ብዙ ጎሎችን አስቆጠርንባቸው እንጂ ቀሎን አይደለም የተጫወትነው፤ በአጨዋወት ከእነሱ ስለተሻልን ብቻም ነው ያሸነፍናቸው፤ ለዋልያዎች ጎልን በማስቆጠሬ ዙሪያ የምለው ነገር ቢኖር መጀመሪያ ላይ በተጠባባቂ ስፍራ ላይ ሆኜ ጨዋታውን እየተመለከትኩ ነበር፤ ወደሜዳ ስገባ ኳሱን መያዝ እንዳለብኝ ተነገረኝ፤ ቡድናችን ደግሞ ኳስን ይዞ የሚጫወት ስለነበር በልምምድ ሜዳ ላይ ግብ ለማስቆጠር የምንሰራውን የታክቲክ ግብን ነው ላስቆጥር የቻልኩትና በግቧና ጨዋታውን በማሸነፋችን በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡

ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻችን ጋር በወዳጅነቱ ግጥሚያ ላይ ስትጫወት ግቡን ያስቆጠርከው አቡበከር ናስር አቀብሎህ ነበር፤ አንተም ደግሞ ለእሱ አቀብለኸው ግብን አስቆጥሯል፤ በእዚህ ዙሪያ ማለት የምትፈልገው ነገር አለ?

ሱራፌል፡- አዎን፤ እኔና አቡበከር በዛን ዕለት ጨዋታ ተቀይረን ነበር የገባነው እና በጣም ነው ልንጣጣም የቻልነው፤ ለሁለታችን መጣጣም የቡድኑ ኳስ የመያዝ አጨዋወትም ሊጠቅመን ችሏልና ለእዛ ነው እኔ ያቀበልኩትን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ በእነሱ ተከላካዮች መሃል ሆኖ በማምለጥ ግብ ሊያስቆጠር የቻለውና እሱም የእኔን የአቋቋም ሁኔታ በመመልከት ግብ እንዳስቆጠር ፈልጎ ሰጥቶኝ ኳሷን ከመረብ ላይ ልዶላት የቻልኩት፡፡

ሊግ፡- ይህን ስትመለከት እንደ መሀል ሜዳ ተጨዋችነትህ ከአጥቂው አቡበከር ናስር ጋር ተጣምሮ መጫወት አስመኘህ ማለት ነው?

ሱራፌል፡- ከእሱ ጋር አንድ ላይ ሆኖ መጫወት በጣም ነው እንጂ ያስመኘኝ፤ ልጁ ገና ወጣት፣ ብልጥ እና ጎበዝ የሆነም ተጨዋች ነው፡፡ ጎል ለማስቆጠር ያለው የቦታ አጠባበቅ /ፖዚሽኑ/ ይገርማል፤ ኳስን ደጋግመህ እንድትሰጠው አቋቋሙም ያስገድድሃል፤ ከዛ ውጪ የተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾች እሱ ላይ ኦፍ ለመስራት ሲቸገሩም እያየን ነው፤ ሌላው ራሱን እንዴት አድርጎ ከኦፍሳይት ፖዚሽን ነፃ ማድረግ እንዳለበትም ጠንቅቆ የሚያውቅ ልጅም ነውና ይህን ስመለከት ሁሌም በየትኛውም የውድድር ደረጃ ከእሱ ጋር በአንድ ቡድን ውስጥ ሁሌም አብሬው በመሆን እንድጫወት ያስመኘኝም ተጨዋች ነው፤ ስለ አቡኪ ይሄን አልኩ እንጂ ስለሌላም አንድ ተጨዋች አንድ ነገርን ማለትም እፈልጋለሁ….

ሊግ፡- ስለ ማን..?

ሱራፌል፡- ስለ ሙጂብ ቃሲም?

ሊግ፡- ቀጥል…?

ሱራፌል፡- ከላይ ስለ አቡኪ ሳወራ ሙጂብንም እያሰብኩት ነበር፤ ሙጂብንም ከአቡኪ ቀጥሎ ሁሌም በየትኛው የውድድር ደረጃ አብሮኝ እንዲጫወት የምፈልገው ተጨዋች ነው፤ በእርግጥ ከእሱ ጋር በፋሲል ከነማ ቡድን ውስጥ አብረን እየተጫወትን ነው፤ ከአቡኪ ጋር ግን የምንገናኘው ብሔራዊ ቡድን ሲመጣ ብቻ ነው፤ ለዛም ነው ከአቡኪ ጋር ሁሌም አብሬው ተጣምሬው መጫወት ብችል እያልኩ እና እየተመኘሁም ያለሁት፤ ሙጂብን በተመለከተ እሱም ጥሩ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ነው፤ ሊጉ ላይ ልምድ ያለውም ተጨዋች ነው፤ በችሎታው ላይ ብዙ ለውጦች አሉት፤ ጎሎችን እያስቆጠረ ያለው አህምሮውን ተጠቅሞ ነው፤ ይሄ ተጨዋች ከዚህ ቀደም በነበረው የኳስ ህይወት ተከላካይ ነበር፤ ከዛ ስፍራ መጥቶ በሊጉ ውድድር ላይ በርካታ ግቦችን ለማስቆጠር መቻሉን ልናደንቅለት ይገባል፤ ሙጂብ በጣም የተሻሻለና ልምዱን በመጠቀምም እየበሰለ ያለ አጥቂ ነው፤ ለዛም ነው እንደ አቡኪ ሁሉ ከእሱም ጋር አብሬው ተጣምሮ መጫወቱን የፈለግኩት፡፡

ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ረቡዕ ማዳጋስካርን ባህርዳር ላይ ትፋለማላችሁ፤ ለእዚህ ጨዋታ ያላችሁ ዝግጁነት ምን ይመስላል? ምን ውጤትስ ይመዘገባል….?

ሱራፌል፡- ከእነሱ ጋር የምናደርገው የረቡዕ ጨዋታ ለእኛ ማሸነፍ እና ማሸነፍ ብቻ የሚለውን መርህ ይዘን ወደ ሜዳ ስለምንገባ ለጨዋታው በጥሩ መልኩ ተዘጋጅቷል፤ ይሄ ፍልሚያ ከማዳጋስካሮች የበለጠ ለእኛ ነው ወሳኝነቱ ምክንያቱም ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ እኛ ሁለቱንም ግጥሚያዎች ማሸነፍ አለብንና እነሱ ግን ይሄን ጨዋታ ቢሸነፉ እንኳን የመጨረሻ ጨዋታቸውን ብዙም ጠንካራ ካልነበረችው ኒጀር ጋር ስለሚያደርጉ ሌላ የሚጠብቁት ዕድል አላቸው ስለዚህም፤ የእኛ የመጀመሪያው ሙሉ ትኩረት ጨዋታችን የረቡዕ ነው ስለዚህም የፈጣሪ እገዛ ይታከልበትና ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአቋም መለኪያ ደረጃ ስንጫወት ያሳየነውን የጨዋታ እንቅስቃሴ በማሳየት ግጥሚያውን ለማሸነፍ ዝግጁ ነን፡፡

ሊግ፡- የዘንድሮ አቋምህን ተከትሎ ሊጉ በተጀመረባቸው ጨዋታዎች አካባቢ ስላንተ በተለያዩ የማህበራዊ ድረ-ገፆችም ሆነ ሚዲያዎች ላይ ብዙ ነገሮች ሲባሉ ነበሩ፤ ከእነዛ ውስጥ ደግሞ በተለይ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ችሎታው ወርዷል፤ ጉረኛ እና ሌላም ሌላም ነገሮችን እየተባልክ ስለ አንተ ብዙ ነገሮች ይባሉ ነበር፤ እነዛን ስትሰማህ ምን አልክ?

ሱራፌል፡- በተፈጥሮዬ ብዙ ጊዜ ሚዲያዎችን የመከታተል ባህሪው የለኝም፤ ማህበራዊ ድረ-ገፆችንም ቢሆን ወደ ፌስ ቡክ ውስጥ ስገባ ቪዲዮዎችንና ኢ.ቲ.ዩብ የሆኑ ነገሮችንም ነው ብዙ ጊዜ የማየው፤ የሚፃፉ ኮመንቶችንም ብዙ አላይም፤ እኔን ሊጠቅሙኝ የሚችሉ እና ራሴን ሊያሳድጉ የሚችሉ ነገሮችንም ነው ብዙ ጊዜ የምከታተለው፤ ከዛ በተረፈ በእኔ ላይ ይነገሩ ስለነበሩም ሆነ አሁንም ደግሞ ካሉ እነዛን የምቀበላቸው እንደራሴ እንጂ እንደየሰው አመለካከት አይደለም፤ ሰው ሁሌም የሚያስበውን ነገር ነው የሚናገረውም የሚፅፈውም፤ እኔ ደግሞ እንደራሴ ነው ነገሮችን የምቀበለው፤ ለምሳሌ እኔን አስመልክቶ ሰዉ ጉረኛ ነው፤ ጢባራ ነው፤ እንዲህ ነው የሚሉትን ነገሮች አልፎ አልፎ የምሰማበት ጊዜ ያለ ቢሆንም የእኔ ምላሽ ግን በዛ ደረጃ ላይ የምገለፅ ተጨዋች አይደለሁም፤ እኔን የሚያውቀኝ ሰው ያውቀኛል፤ ጉረኛ ነው የሚሉኝ ሰዎች እኔን በቅርብ ርቀት የማያውቁኝ ናቸው፤ አንድ አንዴ ምናለ የማያውቁኝ ሰዎች ቀርበው ቢያዩኝም እላለው፤ አንድአንዶች እኔን ቀርበውና ተረድተውኝ ይቅርታ ያሉኝ ሰዎች አሉ፤ ለእንዲህ ያሉ ሰዎችም የይቅርታ ምላሽን የሰጠዋቸውም አሉ፤ ይህን ካልኩ አሁንም ደግሜ ደጋግሜ መናገር እፈልጋለውኝ በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ እኔ በሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጪ ባለኝ ባህሪዬ ጉረኛ የምባል ተጨዋች አይደለሁም፤ ከዛ ይልቅ በተሰማራሁበት በዚህ ሙያዬም ላይ ሆነ በሌሎች ስራዎቼ ራሴን ዝቅ አድርጌ የምኖርም ተጨዋች ነኝ፤ ለእኔ በሁሉም ነገሬም የሚያውቀኝ ሰው ከተረዳኝም በቂዬም ነው፡፡

ሊግ፡- ምንአልባት አንተን በዛ ደረጃ ላይ እንድትታይ ያደረገ ነገር በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ጅማሬ ጨዋታዎች ላይ ቅጣት ምቶች ሲሰጡ አብዛኛዎቹን ምቶች ራስህ ብቻ ስለምትመታ እና በሜዳ ላይ የጨዋታ እንቅስቃሴዎች ውስጥም በሆነውም ባልሆነውም ድርጊቶች ውስጥ ጎልተህ ስለምትታይ እና ብዙዎችም እንደሚሉት ራስህን የተለየ አይነት ተጨዋች አድርገህ ስለምትቆጥር ይሆን…?

ሱራፌል፡- በመጀመሪያ የፋሲል ከነማ የተጨዋችነት ቆይታዬ ላይ ከቅጣት ምቶች ጋር በተያያዘ ከቡድኑ ተጨዋቾች ውስጥ አብዛኛውን ምቶች የምመታው እኔ ስለሆንኩኝ ነው በዛ ስፍራና አካባቢ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ የምታየው እና ምቶቹንም የምመታው፤ የሊጉ የያኔ የጨዋታ ጅማሬዎች ላይም እኔ የምመታቸው ኳሶች ወደ ግብነት ሳይቀየሩ ሲቀሩና አቅጣጫቸውንም ቀይረው ሲሄዱ ብዙ ነገሮች በእኔ ላይ ይባሉ እንደነበሩም አውቃለው፤ በዛን ወቅት እኔ ቡድኔ የጨዋታዎቹ አሸናፊ እንዲሆን ከመፈለግ አንፃርም ነበር በእኔ ላይ በምመታቸው ምቶችም ሆነ ግጥሚያን ለማሸነፍ በሚታዩብኝ ስሜታዊ የመሆን ነገሮችም ላይ ሰዎች ሳይረዱኝ የተለያዩ ነገሮችን ሊሉ የቻሉት፤ ስለ ቅጣት ምቶቹ የእውነት ነው የምልህ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ያዘጋጃቸው ኳሶች በጣም ስስ እና ጥንካሬ የሌላቸው ስለነበሩም ነው በቆሙም ሆኑ ባልቆሙ ኳሶች ላይ በጠንካራ ምቶቼ የምታወቅ ተጨዋች ስለሆንኩኝ እና ኳሶቹም ከእኔ እግር ጋር አብረው ስላልሄዱም የምመታቸው ምቶቼ ዒላማቸውን እንዳይጠብቁልኝ አድርገውብኝ የነበሩትና ይሄን ነው ልል የቻልኩት፤ ከኮትዲቭዋር ጋር ስንጫወት የነበረው ኳስ በጣም ጠንካራ ነበር፤ ያ ተስማምቶኝም ጎልን ላስቆጥር ችያለው፤ እኔ የምፈልገው እንደዛ አይነት ኳሶችን ነው፤ ሌላው ልናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር በኳስ ጨዋታ ዘመኔ ራሴን የተለየው አይነት ተጨዋች አድርጌ ለአንድም ቀን አስቤ አለማወቄ ነውና ሰዉ በዚህ ደረጃም ቢረዳኝ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡፡

ሊግ፡- ከዛ ውጪ ዘንድሮ በተደጋጋሚ ጊዜ ባልተለመደ ሁኔታ ብዙ ካርዶችንም እያየህ ነው…በእዚህ ዙሪያስ ማለት የምትፈልገው ነገር አለ?

ሱራፌል፡- አዎን፤ በእዚህ ዓመት ሊጉ ገና በርካታ ጨዋታዎች እየቀሩት ብዙ ቢጫ ካርዶችን እየተመለከትኩኝ ነው የምገኘው፤ ይሄን ሳይ በእኔ ላይ ብዙም ያልተለመደ ነገር ነው፤ አብዛኛዎቹን ካርዶች የማየውም ከመጥፎ ነገሮች ተነስቼ አይደለም፤ አልሸነፍ ባይና እለኸኛ ተጨዋችም ስለሆንኩኝ እና ስሜታዊ ከመሆን አኳያ አንድአንዴ የቆሙና የማይነኩ ኳሶችን በመምታት እና የዳኛን ውሳኔዎችንም በመቃወም ምላሽን ስለምሰጥም ነው ካርዶችን የምመለከተው እና እነዚህን ነገሮች ማስተካከልና ማሻሻል እፈልጋለሁ፤ ደግሞም ይሄን ማስተካከል ለእኔ ቀላል ነገር ነው፤ ምክንያቱም ችሎታዬ ላይ የነበረውን ከባዱን ነገር ለማስተካከል ችያለውና፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተከታዩን ኢትዮጵያ ቡናን በ8 ነጥብ እና ሌሎቹን ደግሞ ከዛ በላይ በሆነ ነጥብ ከመምራቱ አኳያ የዘንድሮውን የሊጉን ዋንጫ ወደ ቤቱ ያስገባል እየተባለ ነው፤ በዚህ ዙሪያ አንተ ምን እያልክ ነው?

ሱራፌል፡- እንደ ቡድኑ ተጨዋችነቴ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት አሁንም ከእኛ ውጪ ዕድሉ ያላቸው ቡድኖች ስላሉና ጠንክረውም እየሰሩ እንደሆኑም ስለማውቅ የእኛን ቡድን በተመለከተ ዋንጫውን የሚያነሳበት ጊዜው አሁን አይደለም፤ የሊጉ ሁለተኛው ዙር ገና መጀመሩ ነው፤ ከዚህ በመነሳት ተከታዮቻችንን በ8 ነጥብ ስለበለጥን ብቻ ዋንጫውን ወደ ቤታችን እናስገባለን ማለት አይደለም፤ ስለዚህም እኛ ፋሲሎች በቀጣዮቹ የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎቻችን ላይ ብዙ የቤት ስራ ስላለብን ብዙ ቡድኖችም እኛ የሊጉ መሪ ከመሆናችን አኳያ ጠንክረው እንደሚመጡብንም በደንብ አድርገን ስለምናውቅም በእነዛ ግጥሚያዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን በመምጣት እና ጨዋታዎቹንም በማሸነፍ የእዚህ ዓመትን ድል ለመቀዳጀት በሚገባ እንዘጋጃለን፡፡

ሊግ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የእዚህ ዓመት ተሳትፎአችሁ የየቱ ክልል ቆይታችሁን ነው በምርጥነት የምትገልፀው…የተቆጨህበትስ አለህ?

ሱራፌል፡- የሊጉ ምርጡ ቆይታችን ጅማ ላይ የነበረን ነው፤ ወደዛ ስንጓዝም አምስቱን ጨዋታዎቻችንንም ነበር ለማሸነፍ የቻልነው፤ በመቀጠል ደግሞ ባህርዳር ላይ የነበረን ቆይታም ከአንድ ጨዋታ በስተቀር ይኸውም ከሰበታ ከተማ ጋር ካደረግነው አቻ ከተለያየንበት ግጥሚያ አኳያ ሁሉንም በድል ያጠናቀቅንበት ስለሆነ እሱን በተከታይነት የምጠቅሰው ነው፤ ያስቆጨኝ ጨዋታዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ በነበረን ቆይታ ከኢትዮጵያ ቡናም ከባህርዳር ከተማም ጋር ስንጫወት ከእነሱ ተጨዋቾች በቀይ ካርድ ወጥተው እና እኛ በትርፍ ሰው ተጫውተን የተሸነፍንበት እና አቻ የተለያየንበት ጨዋታ ሁሌም የሚያስቆጨኝ ነው፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ በእዚህ ጥያቄዬን ላጠቃል፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማላዊ አቻውን በአቋም መለኪያ የገጠመበት ዕለት ሰኞ ዕለት በሰው እጅ ተገድሎ ህይወቱን ላጣው የኢትዮጵያ ቡናው ደጋፊ ቴዎድሮስ አበባው /ቴዲ ቡናማው/ የአንድ ደቂቃ የዕሊና ፀሎት ተደርጎለት ነበር፤ የልጁን እልፈት ስትሰማ ምን አልክ…በቅርብስ ታውቀው ነበር ?

ሱራፌል፡- የቴዲ ቡናማውን ህልፈት ለመጀመሪያ ጊዜ ልሰማ የቻልኩት በብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ላይ ስለሆንን እዛ ሆኜ ነው፤ ስለ አሟሟቱ የተፈጠረውን ነገር ስሰማም በጣምም ነው ያዘንኩት፤ እዛ ያለነው የብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችና ሌሎችም ተጨዋቾች እንደዚሁም ደግሞ መላው የእግር ኳሱ አፍቃሪና የሀገራችን ህዝብም ነው በድርጊቱ ሊያዝን የቻለው፤ ይሄን ስንሰማ ሀገራችን ላይ የህግ ከለላ የሌለም ይመስላል፤ ስለ ቴዲ በቅርብ ባላውቀውም ስለ እሱ እና ስለሚሰራቸው ስራዎች ግን ከምሰማቸው ነገሮች ብዙ ነገሮችን ላውቅ ችያለሁ፤ በጣም ትሁት ልጅ እንደሆነም ሰምቻለው፤ አሟሟቱ ልብን ይነካል፤ ከዚህ በላይ ብዙ ነገርን ማለት አልችልም፤ ፈጣሪ ነፍሱን በአፀደ ገነቱ ያኑረው፤ ለቤተሰቦቹ እና ለቡና ደጋፊዎች እንደዚሁም ደግሞ ለመላው የስፖርቱ አፍቃሪ መፅናናቱን እመኛለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P