Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ጥሩ የውድድር ዓመትን አላሳለፍኩም፤ ለዋልያዎቹ አለመመረጤም ተገቢነው”አብዱልከሪም መሐመድ (ቅ.ጊዮርጊስ)


የቅ/ጊዮርጊሱ የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች አብዱልከሪም መሐመድ /ተርምኔተር/ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ጥሩ ብቃቱን ለክለቡ አለማሳየቱን ጠቅሶ ለብሔራዊ ቡድንም
ለመመረጥ አለመቻሉም ተገቢ እንደሆነም ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ላይ ለሲዳማ ቡና፣ ለሐዋሳ ከተማ፣ ለኢትዮጵያ ቡናና ለአሁኑ ክለቡ ቅ/ጊዮርጊስ በጥሩ መልኩ ለመጫወት የቻለውና
በቅ/ጊዮርጊስ ተጨዋችነቱም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮከብ ተጨዋችነትን ክብር ለአንድ ጊዜ ያገኘውን ይኸውን ተጨዋች ሊግ ስፖርት ስለ ዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ የውድድር
ዘመን፣ ስለ ክለቡ፣ ከኳስ ለወራቶች ስለመራቁ፤ ከብሔራዊ ቡድን ምርጫ ጋር እና ከራሱ አቋም ጋር በተያያዘ ጥያቄዎችን አቅርበንለት ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ ለረጅም ጊዜ ነው ከኳሱ የራቅከው ስሜቱን እንዴት አገኘኸው?
አብዱልከሪም፡- በጣም ከባድ ነው፤ ምክንያቱም ከኳስ አይደለም ለወራት ለአንድ ቀን እንኳን መለየት ጥሩ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማህ ያደርግሃልና፤ ይሄ ደግሞ ለእኔ ብቻ ሳይሆን
ለሁሉም እግር ኳስ ተጨዋቾችም ጭምር ነው፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ የተነሳ ያለፉትን ወራቶች በምን መልኩ ነበር ያሳለፍካቸው?
አብዱልከሪም፡- ብዙውን ጊዜ በቤቴ እና በአካባቢዬ ነበር የተለያዩ የስፖርት መስሪያ መሳሪያዎች /ማቴሪያሎች/ ስለነበሩኝ በእነዛ ስፖርትን በመስራት ያሳለፍኩት፤ ከዛ በኋላ
ደግሞ ወጣ ብሎ ስፖርት ለመስራት መፈቀድ ሲጀመር ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር የሰው ቁጥር አሳንሰንና ተራርቀን ከኳስ ጋር የተያያዘ እንደ መሀል ባልገባ አይነት ቀለል ያሉ ልምምዶችንና
በጂምናዝየም ደረጃም ጭምር ነው እየተመላለስኩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችንም ሳከናውን የነበርኩት፡፡
ሊግ፡- እንደ አንድ እግር ኳስ ተጨዋች በ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ምን ያቀድከው ነገር አለ?
አብዱልከሪም፡- የእኔ እቅዶች የመጀመሪያው ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ጥሩ እና በውጤታማነት የታጀበ ስኬታማ የውድድር ዓመትን ማሳለፍ ነው፤ ከዛ በመቀጠል ደግሞ ዓምና
ያጣሁትን የቀድሞ ብቃቴን መልሼ ማግኘት፣ በሜዳ ላይ ቡድኔን መጥቀም እና እንደዚሁም ደግሞ ደጋፊዎቻችንንም በውጤት ማስደሰት መቻል ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የአምናው ውድድር ለአንተ በምን መልኩ ነበር ያለፈው?
አብዱልከሪም፡- በግሌ ጥሩ የውድድር ዓመትን አላሳለፍኩም፤ ለእዛም በምክንያትነት የማነሳው ቡድናችን በየጊዜው አሰልጣኞችን ስለሚቀያይር እና አሰልጣኞቹም ከሚከተሉት
አዳዲስ የሆነ አጨዋወት ጋርም በአንዴ እና በፍጥነት ለመላመድ ልቸገርም ስለቻልኩኝ ነው፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስን የዘንድሮ የተጨዋቾች ስብስብ በምን መልኩ ትገልፀዋለህ? ቡድኑን ስለተቀላቀሉት አዳዲስ ተጨዋቾችስ ምን ትላለህ?
አብዱልከሪም፡- አዲሱ የቡድናችን የተጨዋቾች ስብስብ በጣም ጥሩ ነው፤ ክለባችንን የተቀላቀሉትም አዲስ ግደይ እና ከነዓን ማርክነህም ቡድኑን በጣም ሊጠቅሙ እና ሊያግዙም
የሚችሉ ልጆች ናቸውና ውጤት እንድናመጣ ከተፈለገ እነዚህን ተጨዋቾች እኛ ነባሮቹ ነን ከጎናቸው ሆነን ልናግዛቸው የሚገባን፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ካስፈረማቸው ተጨዋቾች አኳያ ዘንድሮ ለቡድኑ በቋሚነት ለመሰለፍ የሚኖረው ፉክክር ምን ይሆናል ብለህ ታስባለህ?
አብዱልከሪም፡- የእኛ ቡድን በእዚህ ዓመት ያስፈረማቸው ተጨዋቾችም ሆነ በክለቡ ውስጥ አሁን ያለነው ነባር ተጨዋቾች በተመጣጣኝ ችሎታ ላይ የምንገኝ ነንና በሜዳ ላይ
ለቡድኑ በቋሚነት ለመሰለፍ የሚኖረው ፉክክር በጣም ነው ከባድ የሚሆነው፤ ይሄ ፉክክር መኖሩም ለእያንዳንዱ ተጨዋችም ሆነ ለቡድናችን ከፍተኛ ጥቅምም ነው የሚሰጠው፤
ለተጨዋቹ ችሎታውን አሳድጎ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሲያደርገው ለቡድናችን ደግሞ ሁሉም የአቅሙን አውጥቶ ስለሚጫወት ውጤት እንድናመጣም ነው የሚያደርገን፡፡
ሊግ፡- የፕሪምየር ሊጉ ያለተመልካች ሊጀመር ከውሳኔ ላይ ተደርሷል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን አልክ?
አብዱልከሪም፡- እኛ ኢትዮጵያኖች የእግር ኳስን ያለተመልካች ከእዚህ በፊት ተጫውተን አናውቅም፤ አሁን ላይ በዛ ደረጃ እንድንጫወት መወሰኑ በጣም ነው የሚከብደው፤
ምክንያቱም ኳስ ጨዋታ ያለ ደጋፊ ብዙ ጣህም የለውምና፤ ግን ምን ታደርገዋለህ ነባራዊ ሁኔታው ስለሚያስገድደን ተመልካች በሌለበት መጫወታችን የግድ ነው የሆነውና አሁን
ላይ የጨዋታውን የመጀመሪያ ቀናቶች በጉጉት እየተጠባበቅን ነው የምንገኘው፡፡
ሊግ፡- እግር ኳሱን የምንጀምርበት ቀናት ናፍቆሃል?
አብዱልከሪም፡- በጣም፤ በተለይ ደጋፊዎች ቢኖሩ ደግሞ የበለጠ ነበር ናፍቆቱ የሚጨምርብኝ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ዘንድሮ ማን ያነሳል?
አብዱልከሪም፡- እኛ ነና! ይህን ድል ለማሳካትም ነው ዘንድሮ ቆርጠን የምንነሳው፤ በእዚህ የውድድር ዓመት ላይም በተለይ የሊጉ ውድድር ሲጀመርና ወደ ጨዋታዎቹ ላይም ስንገባ
እያንዳንዱን ግጥሚያዎችም በደጋፊዎቻችን ፊት እንደምንጫወት በመቁጠርም ጭምር ነው የአሸናፊነቱንም ክብር የምንጎናፀፈው፡፡
ሊግ፡- የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን ካጣችሁ ሁለት ዓመታቶች አለፉ፤ ይሄ ከቡድናችሁ ይጠበቃል?
አብዱልከሪም፡- በፍፁም፤ ምክንያቱም ቅ/ጊዮርጊስ ድል የለመደ ክለብ ነው፤ ሁሌም ደግሞ ለአሸናፊነትና ለሻምፒዮናነትም የሚጫወት ነው፤ እንዲህ ሆና ሳለ ግን ባለፉት
ዓመታቶች የሊጉን ዋንጫ ሲያጣ ለማንም ነው ሊያስገርም የቻለውና ይሄ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ፈፅሞ አይደገምም፤ ያለብንን ጥቃቅን ችግሮች ቀርፈን፤ የእዚህ ዓመትን
ዋንጫም አንስተን በውጤት የተከፉትን ደጋፊዎቻችንን አመራሮቻችንን እና ራሳችንንም የምናስደስትም ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- ከእዚህ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ነበርክ፤ አሁን አሁን ግን በስኳዱ ውስጥ የተካተትክ እና ለቡድኑም የተመረጥክ ተጨዋች አይደለህም፤ መኖር ነበረብኝ
ብለህ ታስባለህ?
አብዱልከሪም፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አለመጠራት መቻል ጥሩ ችሎታ ላለው ማንኛውም ተጨዋች ሊያስቆጭ ይችላል፤ ይሄ ሆኖ ሳለ ግን በእኔ በኩል በአቋም ደረጃ አምና
ካሳለፍኩት ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን አኳያ ለብሔራዊ ቡድን አለመመረጤ ተገቢ ነው፤ ስለዚህም የነበረኝን አቅም የማውቅ አይነት ተጨዋች ስለነበርኩ ለዋልያዎቹ
አልተመረጥኩም ብዬም የምቆጭ አይነት ተጨዋች አይደለሁም፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተመረጡት ተጨዋቾች መመረጥ ያለባቸው እና ብቁም ችሎታ የነበራቸው ናቸው ብለህ ታስባለህ?
አብዱልከሪም፡- አዎን፤ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ባሳለፍነው ዓመት ሊጉ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳዩትን ተጨዋቾች ነው ለመመረጥ የቻለው፤ እሱ ጥሩ ቡድንም ይገነባል ብዬም
እጠብቃለው፡፡
ሊግ፡- ወደ ብሔራዊ ቡድን ዳግም ስለመመለስ ምን እያሰብክ ነው?
አብዱልከሪም፡- የዋልያዎቹ ተመራጭ ተጨዋች ሆኜ ቡድኑን ለመቀላቀል ዘንድሮ ብዙ ነገሮችን መስራት ይኖርብኛል፤ አምና ጥሩ የውድድር ዓመትን አላሳለፍኩም ስለዚህም
ጠንክሬ እየሰራው በመምጣት ቡድኔን መጥቀምና ወደ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋችነትም መመለስን ዳግም እያሰብኩኝ ነው ያለሁት፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…..?
አብዱልከሪም፡- የኮቪድ ወረርሽኝን ፈጣሪዬ ዓላ ከምድረ ገፅ እንዲያጠፋልን ከፍተኛ ምኞቴ ነው፤ ይህን ካልኩ የምንወደው ኳሳችንም በፍጥነት ተጀምሮልን የ2013ትን የፕሪምየር
ሊግ ዋንጫን ቡድናችን ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲያነሳ እና ደጋፊዎቻችንም እንዲደሰቱም ከቡድናችን ተጨዋቾች ጋር በጋራ በመሆን ከፍተኛ መስዋትነትን እንደምንከፍልም ለመናገር
እወዳለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P