Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ፋሲል ቅ/ጊዮርጊስን በማሸነፉ ብቻ ለእኛ ስጋት አይሆንብንም”
አበበ ጥላሁን /ኢትዮጵያ ቡና/


ኢትዮጵያ ቡናን በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከመከላከያ ክለብ በመምጣት የተቀላቀለው አበበ ጥላሁን በዘንድሮው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ቡድናቸው ለሻምፒዮናነት እንደሚጫወት አስተያየቱን ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር ባደረገው ቆይታ ሰጥቷል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና የአሁኑን ስያሜ ቤትኪንግን ከመያዙ በፊት የእግር ኳስን ለሲዳማ ቡናና ለመከላከያ ቡድኖች በመጫወት ያሳለፈው ጠንካራው የተከላካይ ስፍራው ተጨዋች አበበ ጥላሁን በቡና ቆይታው ከቡድኑ ጋር የሊግ ዋንጫውን ከማንሳት ባሻገር የቡድኑ ስመ ጥር ተጨዋች ለመሆን ከወዲሁ እያለመም ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ጋር ባደረገው እና 2-2 በተለያየበት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ለቡድኑ የመጀመሪያ ግጥሚያውን ለማድረግ የቻለው አበበ ጥላሁን ብዙዎቹ ሊጫወቱለት ለሚጓጉት እና ለሚመኙት ቡድን መለያውን አጥልቆ በመጫወቱም በጣሙን እንደተደሰተም ገልጿል፡፡


ሊግ ስፖርት ከእዚሁ ተጨዋች ጋር ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ጋር ስላደረገው የቤትኪንግ የመጀመሪያ ጨዋታ፣ ስለተመዘገበው ውጤት፣ ስለ ቡድናቸው፣ ኢትዮጵያ ቡና በእዚህ ዓመት ሊያሳካው ስላሰበው ውጤት፣ ስለ ራሱ እና ከፋሲል ከነማ ጋር ዛሬ ስለሚያደርጉት ጨዋታ ጠይቀነው ምላሹን ሰጥቶናል፤ መልካም ንባብ፡፡


ሊግ፡- ወልቂጤ ከተማን በተፋለማችሁበት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ነጥብ ተጋርታችሁ ወጥታችኋል፤ ጨዋታው እና ውጤቱ እንዴት ይገለፃል?
አበበ፡- ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረግነው ጨዋታ እንደ መጀመሪያ ግጥሚያችን ሲታይ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳየንበት እና የአሰልጣኛችንንም ታክቲክ በአብዛኛው የተገበርንበት ነበር፤ በዕለቱ ጨዋታውን 2-0 ስንመራ ነበር፤ በመጨረሻ ግን ይዘነው የነበረውን እንቅስቃሴያችንን ልናስቀጥል ስላልቻልን ማሸነፍ የሚገባንን ግጥሚያ ሁለት ግብ ተቆጥሮብን በአቻ ውጤት ልናጠናቅቅ ችለናል፡፡
ሊግ፡- ውጤቱ አበሳጭቷችኋል፤ አስቆጭቷችኋል?
አበበ፡- አዎን፤ ምክንያቱም በጨዋታው የእኛ ቡድን ነበር ከእነሱ በተሻለ መልኩ የግብ እድሎችን ፈጥሮ የነበረው፤ ከዛም ውጪ 2-0 መምራት መቻልም የማይገኝ ውጤት ነበር፤ ግን ውጤቱን ልናስቀጥል ስላልቻልን ነጥብ ተጋርተን ልንወጣ ችለናል፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና ነጥብ መጣል የቱን ነው በምክንያትነት የምታነሳው?
አበበ፡- የመጀመሪያው የያዝነውን የመሪነት ውጤት አስጠብቀን እንዳንወጣ መጨረሻ ላይ የትኩረት ማነስ ድክመት ነበረብን፤ ይሄ እግር ኳስ ላይ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም አይነት ነውና የቀጣይ ጨዋታችን ላይ በእርግጠኝነት የሚሻሻል ነገር ይኖራል፤ ሌላው ሊጠቀስ የሚችለው ደግሞ ቡድናችን እንደ ህብረት በመጫወት የግብ እድሎችን በመፍጠሩ በኩል ጥሩ ሆኖ ሳለ ተጨማሪ ግቦችን አለማስቆጠሩም ለነጥብ መጣላችን በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚ ወልቂጤ ከተማን በጨዋታው እንዴት እና በምን መልኩ አገኘሃቸው?
አበበ፡- በአብዛኛው አዲስ ቡድንን ነው እየገነቡ ያሉት፤ ጠንካራም ናቸው፤ በከፍተኛ ፍላጎትም ነው ኳስን የሚጫወቱት፤ ከአምናው ተቀይረውም መጥተዋል፤ በሁለተኛው አጋማሽ ላይም በእኛ ከተመሩ በኋላና እኛም ያገኘናቸውን የግብ እድሎች ባልተጠቀምንበት ጨዋታ ሁለት ግቦችን አስቆጥረውብን በሚፈልጉት መልኩ አቻ መውጣትን ፈልገው ዋጋ ሊያስከፍሉን ችለዋል፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ጨዋታህን ነው ያደረግከው፤ ለቡና መጫወት የተለየ ስሜት አለው?
አበበ፡- በጣም እንጂ፤ ይሄን የመጀመሪያ ጨዋታዬን ብዙዎች ሊያጠልቁት በሚመኙት እና ሊጫወቱለትም በሚፈልጉት በቡና ማልያ ሆኜ ሳደርግ ከፍተኛ ደስታ ነበር የተሰማኝ፡፡
ሊግ፡- በበርካታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ሳትታጀብ ነበር ጨዋታውን ያደረግከው፤ ከእዚህ አንፃርስ?
አበበ፡- ለኮቪድ ወረርሽኝ በወጣው መመሪያ የተነሳ በብዛት እነሱ በስታድየም ባይታደሙም ዋናው ነገር የተወዳጁን እና የዝነኛውን ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን ማሊያ ለብሼ መጫወቴ ብቻ ለእኔ በቂ ነው፤ ደግሞም እኮ ጥቂቶቹ ደጋፊዎች እንደ ብዙ ሆነው ባሉበት ሁኔታም ነበር የተጫውትኩት፤ ሌላው ደጋፊዎቻችን በዲ.ኤስ.ቲቪ እኛን የተመለከቱበት ሁኔታም ነበርና በእዚህ መልኩም የቡናን የመጀመሪያ ጨዋታዬን ማድረግ መቻሌ በጣም ነው ሊያስደስተኝ የቻለው፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና በመግባትህ እና በመጫወትህ አንተ እድለኛ ነህ ወይንስ እነሱ?
አበበ፡- በጣም እድለኛውማ እኔ ነኝ! ምክንያቱም ኢትዮጵያ ቡና እኮ ብዙ ታሪክ የሰሩ ተጨዋቾች ተጫውተው ያለፉበት እና በብዙ ምርጥ ደጋፊዎችም ለዘመናት የተደገፈም ቡድን ነውና፤ ይሄ ሲታይ የእዚህ ቡድን አንዱ አካል ተጨዋች ስለሆንኩ ራሴን እንደ እድለኛ ቆጥሬ ፈጣሪዬን በጣም ነው የማመሰግነው፡፡
ሊግ፡- ብዙ ተጨዋቾች ወደ ኢትዮጵያ ቡና ይመጣሉ፤ በኋላ ላይም የቡና ተጨዋቾች ነበሩ ይባላሉ፤ እንደዛ መባል ብቻ በቂ ነው? አንተስ ራስህን እንደዛ ነው የምትመለከተው?
አበበ፡- የኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ስትሆን የክለቡን ማሊያ ማጥለቅ ብቻ ለእኔ በቂ ነው ብዬ አላስብም፤ ማሊያንማ ማንኛውም ተጨዋች በቡድኑ እስከተፈለገበት ጊዜ ድረስ አጥልቆ ሊጫወት ይችላል፤ ለእኔ ግን የቡና ተጨዋች ነበር ለማለት በክለቡ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ሁሌም ስሙን ሊያስጠራው እና ሊያስሞግሰው የሚችል ነገርን ሊሰራ ይገባል፤ ያኔም ነው የቡና ተጨዋችም ሊባል የሚገባው፤ አሁን ላይ እኔም ክለቡን በተቀላቀልኩበት ወቅት ራሴን የቡና ተጨዋች ነኝ ለማለት በሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን ላደርግ ይገባል፤ የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋች መሆንንም ስለምፈልግ ለእዚህ እንደ ትልቅ እየተገነባ ላለው ቡድን እንደ ግልም እንደ ቡድንም የሚጠበቅብኝን ስራ ለመስራት ተዘጋጅቻለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና እየተከተለ ያለውን አጨዋወት እንዴት ተመለከትከው፤ ለአንተስ ከበደህ?
አበበ፡- ቡድናችን ጥሩ አጨዋወትን ነው እየተከተለ ያለው፤ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በሚከተለው የጨዋታ ታክቲክ ኳስ ያለ አግባብ እንዲባክን አይፈለግም፤ እሱ በእንቅስቃሴው ያለ ድካም እንድትጫወትም ነው የሚያደርግህ እና የቡድናችንን አጨዋወት በጣም ወድጄዋው፤ እንቅስቃሴው ከበደህ ወይ ላልከኝ፤ አሁን ላይ ከቡድኑ ጋር በጣም ስለተዋሃድኩ በፍፁም አልከበደኝም፤ እንዳይከብደኝ ያደረገኝም ወደ ቡድኑ ከመምጣቴ በፊት የያዝኩት የጨዋታ እንቅስቃሴ ከክለቡ ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ ነው፤ ቡናም በአሰልጣኙ ካሳዬ አራጌ እይታ እኔን ወደ ቡድኑ ያመጣኝም ለዛ እንቅስቃሴ ትሆናለህ ብሎም ነውና ሳይከብደኝ ነው የመጀመሪያ ጨዋታዬን ለማድረግም የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን ከወዲሁ እንደ መቀላቀልህና መጫወትም እንደመጀመርህ ቡድኑ ተመቸህ?
አበበ፡- በሁሉም ነገር ነዋ! ከኮች ስታፉ ጀምሮ እስከ ተጨዋቾቹ ድረስ ጥሩ ምቾት ተሰምቶኝ ነው በመጫወት ላይ የምገኘው፤ ከክለቡ የጎደለብኝ ነገርም ምንም የለም፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና የተጨዋቾች ስብስብ በአንተ እይታ በምን መልኩ ይገለፃል?
አበበ፡- በአብዛኛው ማለት ይቻላል በወጣት እና ኳስን በጣም በሚችሉ ተጨዋቾች ነው ስብስባችን /ስኳዳችን/ እየተገነባ ያለው፤ ቡድኑ ጠንካራ እና አይበገሬ ክለብን ለመስራት የረጅም ጊዜን ግብም አስቀምጧልና ይሄ ሊበረታታ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስን ያሸነፈውን ፋሲል ከነማን ነው ዛሬ የምትፋለሙት፤ ከእዚህ አንፃር ስለጨዋታው እና ስለ ውጤቱ ምን የምትለው ነገር አለ?
አበበ፡- ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ጥሩ ፉክክር ይታይበታል ብዬ እጠብቃለው፤ በዕለቱ እኛ የምንገጥመው ቡድን ምንም እንኳን ጠንካራውን ቅ/ጊዮርጊስ አሸንፎ የሚጠብቀን ቢሆንም ክለባችን በአሁን ሰዓት ላይ ካለው ጥሩ አቋም አንፃር የሚፈጥርብን ምንም አይነት ተፅህኖ አይኖርም፤ የድል ውጤቱን ይዘን እንደምንወጣም አልጠራጠርም፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና የእዚህ ዓመት ግብ እና እልም ምን ውጤትን ማሳካት ነው?
አበበ፡- ምን ጥርጥር አለው፤ መቼስ ለቡና እየተጫወትክ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ እንሆናለን ብቻ ብል ማንም አይሰማኝም፤ ለቡና ስትጫወት ሁሌም የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ነው የምታልመው፤ ሁሉም ቡድኖች የየራሳቸው ግብ ቢኖራቸውም አሁን አሁን ላይ ግን አይደለም ኢትዮጵያ ቡና ሌሎቹም እኮ ዋንጫን ለማግኘት እንደሚጫወቱ ነው እየተናገሩ ያሉትና ቡና እየተመለከተ ያለውን የዘንድሮው ጠንካራ የሊግ ውድድርን የያዘውን የጨዋታ እንቅስቃሴ ማስቀጠል ከቻለ ሻምፒዮና የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡
ሊግ፡- ቤትኪንግ ሊጋችን በዲ.ኤስ.ቲቪ መተላለፍ ጀምሯል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር አለ?
አበበ፡- ይሄ መሆን መቻሉ ለእግር ኳሳችን ብዙ ነገሮችን ነው ይዞልን የመጣው፤ የአገራችንን እግር ኳስ አንድ ደረጃ ከፍ እንዲልም ያደርገዋል፤ ከእነዛም ከሚገኙት እድሎች መካከልም ግጥሚያዎቹ በመላው ዓለም የሚታዩበት ሁኔታም ስላለ ጥሩ ብቃትን የሚያሳዩ ተጨዋቾቻችን በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ደረጃ ወደ ውጪ ወጥተው የሚጫወቱበትን እድልም ይፈጥርላችኋልና ለዛ ሁላችንም ጠንክረን ልንሰራ ይገባል፡፡
ሊግ፡- አንድ ነገር በልና እናጠቃል?
አበበ፡- በፈጣሪ እርዳታ 2013 የውድድር ዘመን በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ምኞት ነው ያለኝ፤ ራሳችንን የምናይበት፤ አገራችንንም የምንጠብቅበት እንደዚሁም ደግሞ ከቡናም ጋር ጥሩ የውድድር እና የስኬት ጊዜን የምናሳልፍበት ዓመትም እንዲሆንልን እመኛለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P