Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በቤትኪንጉ በጠንካራ ተፎካካሪነት ተጠብቀናል፤ በተጠበቅነው ልክም እንጓዛለን” ፍፁም ዓለሙ /መቻል/

በቤትኪንጉ በጠንካራ ተፎካካሪነት ተጠብቀናል፤ በተጠበቅነው ልክም እንጓዛለን

ፍፁም ዓለሙ /መቻል/

በኢትዮጵያ  ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለቀድሞ ክለቦቹ  ፋሲል ከነማ እና  ባህርዳር ከተማ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴን  አሳይቷል፤ በሜዳ ላይ የነበረውም ብቃት  በተመልካች እይታ ውስጥ እንዲገባና ከፍተኛ አድናቆትም እንዲሰጠው አድርጎታል።

የእግር ኳስን ለጥቁር አባይ ክለብ በመጫወት ጥሩ ጅማሬን ያሳየው እና ባለፉት ተከታታይ ዓመታቶች ላይም በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጎልተው ከወጡት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ፍፁም ዓለሙ በዘንድሮው የክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ለመቻል /ለመከላከያ/ ክለብ መጨረሻ ላይ ፊርማውን ያኖረ ተጨዋች ሲሆን ከእዚሁ አዲስ ፈራሚ ተጨዋች ጋር የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አጠር  ያለ ቃለ-ምልልስን አድርጎ ምላሽ ተሰጥቶታል፤ ተከታተሉት።

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግንሃለን?

ፍፁም፦ እኔም እንግዳችሁ አድርጋችሁ ስለጋበዛችሁኝ አመሰግናችኋለሁ።

ሊግ፦ በዝውውር መስኮቱ አዲስ ክለብህን መቻል ለመቀላቀል ችለሃል፤ ወደ ቡድኑ እንዴት ልታመራ ቻልክ?

ፍፁም፦ ወደ መቻል ያመራሁት እና ፊርማዬን  ያኖርኩት በመጨረሻዎቹ ሰዓታቶች አካባቢ ነው። ለቡድኑ ልፈርም የቻልኩትም ቡድኑ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾችን እያስፈረመ ስለነበርና ጓደኞቼም ደግሞ ይህን ሁኔታ አጠናክረውልኝ ጠንካራ ቡድንን ለመገንባት መታሰቡንም ስላበሰሩልኝ ወደ አዲሱ ቡድኔ ምንም ነገርን  ሳላቅማማ ልፈርም ችያለሁ፤ ከክለቡም ጋር የፕሪ-ሲዝን ዝግጅቴንም ልጀምር በቅቻለሁ።

ሊግ፦ መከላከያ በአዲሱ የውድድር  ሲዝን በቀድሞ መጠሪያ ስሙ መቻል በሚል ይጠራል፤ ስለዚህ ቡድን የቀድሞ ስምና ዝና የምታውቀው ነገር አለ?

ፍፁም፦ እኔ እንኳን ብዙ የማውቀው ነገር አልነበረኝም፤ ያም ሆኖ ግን አሁን ክለቡን ከተቀላቀልኩ በኋላ አብረውኝ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ስለ ቡድኑ የቀድሞ ታሪክ እነሱም የሰሙትና የሚያውቁትም ነገር  አለና በደንብ አድርገው እያሳወቁኝ ነው። እኔም ከክለቡ ጋር በደንብ ስዛለቅ ደግሞ ብዙ ነገሮችን ስለ ክለቡ ማወቄም የማይቀር ነው።

ሊግ፦ የመቻል /የመከላከያ/ ስብስቡን እንዴት ተመለከትከው? ምን ውጤትንስ ከእዚህ ቡድን ጋር ማግኘት ትፈልጋለህ?

ፍፁም፦ ጠንካራ የተጨዋቾች ስብስብን ነው የያዝነው፤ በእዚህ ቡድን ቆይታዬም ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ዋንጫን ማንሳት ስለማልምም  ጠንካራ ለሚሆነው የሊጉ ውድድር ጠንክረን ሰርተን  እንመጣለን ብዬም ነው የማስበው።

ሊግ፦ ቤትኪንጉ የመጪው ዓመት ላይ  ለየት ያለ ውድድር ይኖረዋል?

ፍፁም፦ አዎን፤ ብዙ ቡድኖችን ከሚያስ ፈርሙት ተጨዋቾች አኳያ ስመለከታቸው ውድድሩ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ጠንካራና ለየት ያለ ነው የሚሆነው። ከእነዛ ጠንካራ ተሳታፊ  ቡድኖች መካከልም ደግሞ  መቻል ስሙ የሚጠቀስም ነውና  ይኸውን ቡድን ለስኬት ለማብቃት ጥረትን እናደርጋለን።

ሊግ፦ በእግር ኳስ ያለፉት የጨዋታ ዘመን ቆይታህ ለተለያዩ ቡድኖች መጫወት ችለሃል፤ እነዛ ጊዜያቶች አስደሳቾች ናቸው?

ፍፁም፦ በጣም፤ ደስተኛ ሆኜም ነው ኳሱን የተጫወትኩት።

ሊግ፦ በኳስ መከፋት እና ማዘንም እኮ ያጋጥማል?

ፍፁም፦ ተከፍቼ አላውቅም ብዬ አልዋሽህም፤ ለፋሲል ከነማ በተጫወትኩበት ዓመት ላይ  መቀለ 70 አንደርታ ሻምፒዮና ሲሆን የሊጉን ዋንጫ አጥተን ነበርና ያኔ ከፍቶኛል። ያን ያዘንበትን ታሪክ የሚረሳ ተጨዋችም አይኖርም።

ሊግ፦  የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ አልናፈቀህም?

ፍፁም፦ ናፍቆኛል፤ አንዳንዴ በኳስ እነዚህን ስኬቶች ታስብና ላታሳካ ትችላለህ፤ ቢሆንም ግን ይህን ድል አንድ ቀን ማሳካቴ የማይቀር ነው።

ሊግ፦  በሜዳ ላይ ባለህ የኳስ ብቃት የብዙዎቹን ተመልካቾች እና ደጋፊዎቻችሁን ቀልብ ለመሳብ ብትችልም ቁጡነት እና ስሜታዊነት ግን ይታይብሃል፤ ያ ባህሪህ  አንዳንዴም ለካርድ ሰለባነትም ሲዳርግህ ተመልክተናል?

ፍፁም፦ ልክ ነህ፤ ያን የማደርገው ሌላ ነገር አስቤ ሳይሆን ኳስ ጨዋታው በራሱ ስሜታዊ ስለሚያደርግ ነው። የተለየ የሚባል መጥፎ ባህሪም የለብኝም።

ሊግ፦  ወደ መቻል /መከላከያ/ ክለብ ስታመራ እነሱ አንተን የተቀበሉበት የአቀባበል ሁኔታ ምን መልክ ነበረው?

ፍፁም፦ እነሱ በቅርብ እንደሚያውቁኝ ያህል ነው ጥሩ አቀባበልን ያደረጉልኝ። ለእኔ ክብር እንዳላቸውም ጭምር ስለነገሩኝ  እኔም  አክብሬያቸው ለቡድኑ ልፈርም ችያለሁ። ፈጣሪ ያክብራቸውም ነው የምለው።

ሊግ፦ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ባለፉት ሁለት ዓመታት እንዴት ተመለከ ትከው?

ፍፁም፦ በእነዚህ ጊዜያቶች ውድድሩ የዲ ኤስ ቲቪ ሽፋንን አግኝቶ ነበርና ሁሉም ነገር በግልፅ ስለሚታይ  ከሌላው ጊዜ አኳያ  ጨዋታዎቹን ለየት እንዲሉ እና ዉብ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋልና ይህን የውድድር ሲስተም ወደ እዚህ እንዲመጣ ላደረጉ አካላቶች ከፍተኛ አድናቆት አለኝ።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊጉ የዘንድሮ ተሳትፎአችሁ  ቡድናችሁ የውድ ድር ዘመኑን ያጠናቀቀበትን ሁኔታ እንዴት አድርገህ ትገልፀዋለህ ?

ፍፁም፦ በእግር ኳስ አንዳንዴ በሚጠበቅብህ መልክ ላትጓዝ ትችላለህ፤ የውድድር ዘመኑን ስንጀምር  ጠንካራ ቡድን ስለነበረን ሁሌም ለማሸነፍ ነበር ወደ ሜዳ የምንገባው። ያም ሆኖ ግን በኳስ ላይ በሚፈጠሩት ነገሮች ውጤትን አጣን።  በተሰጠን ግምትም አይደለም ሊጉን ልናጠናቅቅ የቻልነውም።

ሊግ፦ መቻል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማርሽ ባንድ ታጅቦ ነው እየተደገፈ ያለው። ያንን የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ሆነህ ተመልክተሃል። አሁን ደግሞ የቡድኑ ተጨዋች ስለሆንክ በእዛ መልኩ የምትደገፉበት ሁኔታ ተቃርቧል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን አልክ?

ፍፁም፦ ይሄ ድጋፍ ወጣ ያለ እና አሪፍ  ነው፤ በማርሽ ባንድ መሆኑም ይበልጥ ያነቃቃሃል። ደጋፊዎቹ በእዛ መልኩ እኛን እንዲህ ከደገፉን ደግሞ እኛም ለእነሱ የሚፈልጉትን ውጤት ከጓደኞቼ ጋር በመሆን እናስገኝላችኋለን።

ሊግ፦ በመከላከያ ቆይታህ የተሳካ የኳስ ጊዜያትን ታሳልፋለህ?

ፍፁም፦ አሁን ላይ ሆኜ እንደዚህ አልልህም፤ ሁሉን የሚያውቀውና የሚፈቅደው እግዚአብሔር ነው። በእርሱ ፈቃድ ለክለቤ ያለኝን ነገር ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ፤ እሱ ደግሞ ምላሹን ነው የሚሰጠኝ።

ሊግ፦ ቤትኪንጉ አቡበከር ናስርን ጎልቶ አውጥቶ ወደ ደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እንዲያመራ እና ጥሩ እንዲጫወት እንደዚሁም ደግሞ ከጅማሬው ጎል እንዲያገባም አድርጎታል፤ ስለ እሱ ምን ቴላለህ? ይሄን ስትመለከትስ እኔስ የሚል ስሜት በውስጥህ አላጫረብህም?

ፍፁም፦ አቡኪ የተለየ ተጨዋች ነው፤ ምንም ነገርን ቢያደርግም ለእሱ ይገባዋል። ሁሉም ነገር ቢያንስበት እንጂ የሚበዛበትም አይደለም። ከኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ሙሉ የተሟላ አቅም ያለው ተጨዋችም እሱ ነው ብዬም ነው የማስበው። ከእዚህ በላይ ሆኖ እንደማየውም እርግጠኛ ነኝ። አጨዋወቱን ስመለከተውም ለሌሎች ተጨዋቾችም በርን የሚከፍት ነው። በትክክለኛ ቦታ ላይ የሚገኝ ተጨዋች ስለሆነም ፈጣሪ በፈቀደው መልኩ እኔም ጠንክሬ በመስራት ያን ዕድል ለማግኘት እሞክራለሁ።

ሊግ፦ የፕሪ-ሲዝን ዝግጅትን ጀምራችኋል፤ ምን ይመስላል?

ፍፁም፦ ዝግጅቱን የጀመርንበት መንገድ አሪፍ እና ጥሩ ነው። ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ  አለን፤  ይህ ስብስብም በትጋት ልምምዱን እየሰራም ነው የሚገኘው። ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋርም እኔም  ከእዚህ ቀደም ባህርዳር ከተማ እያለሁ አብረን ልምምድ የሰራን በመሆኑም ነገሮችን ቀላል አድርጎልኛልም።

ሊግ፦ ስናጠቃልል?

ፍፁም፦ መቻል ጠንካራ  የተጨዋቾች ስብስብን/ ስኮድን /ነው የያዘው። በውድድር ዘመኑ ጠንካራ ቡድንንም ይዞ ይቀርባል። ብዙዎች ከወዲሁ እኛን እየጠበቁን ይገኛልና በተጠበቅነው ልክ እንሆናለን ብዬ አስባለሁ። ከእዛ ውጪ ማስተላለፍ የፈለግኩት መልዕክት በኳስ ህይወት ቆይታዬ የዛሬ ደረጃ ላይ እንድደርስ ከእዚህ በፊት የነበርኩባቸው ክለቦች ደጋፊዎች ለእኔ ለነበራቸው ክብር፣ ለሰጡኝ አድናቆት አመሰግናችኋለሁ፤ ፈጣሪ ያክብርልኝም ነው የምለው።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P