Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

5G በኢትዮጵያ እውን ሆኗል “ኢትዮጵያን በአለም የቴክኖሎጂ መድረክ ጥግ እስክናደርስ እንቅልፍ አንተኛም” ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ

 

በአለምሰገድ ሰይፉ

ለታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴክኖጂን ከማስተዋወቅም ባሻገር የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዋነኛ የጀርባ አጥንት የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ፍጥነቱ የአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴና ቀነኒሳ በቀለ አይነት መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው፡፡ በቴክኖሎጂ እድገታቸው ጣራ የነኩ ሀገሮች የኔትዎርክ ቴክኖጂያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየፈጠነ ቢሆንም ሁሌም ይሄን ቴክኖሎጂ ወደሀገር ቤት ለማስገባት እንቅልፍ የማይተኛው ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ ታሪክ ሰርቷል፡፡

ከ250 ከሚልቁ የአለም ሀገራት 70ዎቹ ብቻ ያጣጣሙትን አዲሱን 5G ቴክኖሎጂን በመቀላቀል ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት 6ተኛዋ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ በመሆን ለሕዝቡ አዲስ የምስራች ጀባ ብለዋል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ሀገራዊ ተደራሽነቱን በማስፋትና የሕዝቡን የመግዛት አቅም ከግምት በማስገባት በአገልግሎት ክፍያው ላይ ከፍተኛ ቅናሽ እያደረገ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ደግሞ አለም በከፍተኛ ደረጃ የተደመመበትን የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የሆነውን 5G በማስተዋወቅ ስራ የጀመረ ሲሆን ለጊዜው በአዲስ አበባ በተመረጡ 6 ቦታዎች የ5G ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መሆን የጀመረ ሲሆን በቀጣይነትም በሌሎች የአዲስ አበባ ቦታዎችና አጎራባች ክልሎች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገራችን በቴሌኮም ዘርፍ ቀዳሚና ፋና ወጊ የሆነ ትልቅ ኩባንያ ሲሆን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ዘመኑ የወለዳቸውን ቴክኖጂዎች በማስተዋወቅና እግረ መንገዱን በሀገሪቱ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሕይወትን በከፍተኛ ደረጃ በመደገፍ ላይ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም ነው፡፡

የቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመንና የማሻሻል አንዱ አካል የሆነው የ5G የሞባልይ ቴክኖሎጂ የሙከራ አገልግሎቱን በአዲስ አበባ በስድስት ጣቢያዎች ማስጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ የ5G የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት እስከ 10 GBS የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ሲኖረው ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን /Ultra low latency/ እጅግ በላቀ ሁኔታ በመቀነስ ወደ 1 ሚሊ ሰከንድ የሚያደርሰ ሲሆን በተጨማሪም በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ውስጥ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ በርካታ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን እርስ በርሳቸው ለማገናኘት የሚያስችል አለማችን የደረሰበት የመጨረሻው የገመድ አልባ ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን የ5G ኔትዎርክ የቀድመ ገበያ የሙከራ አገልግሎት በዋና መዲናዋ አዲስ አበባ ያስጀመረ ሲሆን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እስከ 150 የ5G ጣቢያዎችን በመትከል በአዲስ አበባና በሌሎች የክልል ከተሞች ተጨማሪ ማስፋፊያ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በአሁን ሰዓት ያስጀመረው የ5G አገልግሎት የስነ ምህዳሩን ዝግጁነት ለመፈተሽ የሚያስችለውን የቅድመ ገበያ የሙከራ አገልግሎት ሲሆን የበለጠ ተደራሽነቱን ለማስፋትና የደንበኞቹን 5G የመጠቀም ፍላጎት ማደግ፣ 5G መጠቀሚያ መሳሪያዎችንና የ5G መጠቀሚያ ቀፎዎች በስፋትና አቅምን ባገናዘበ መልኩ ገበያ ላይ መኖር እንዲሁም በሀገራችን ያሉ የ5G አገልግሎት የመጠቀም ዝግጁነቱ ሲረጋገጥ ኢትዮ ቴሌኮም ስነ ምህዳሩን የማስፋት አላማ እንዳለውም ተገልጿል፡፡ ይህን የ5G ቴክኖሎጂ በአዲስ አበባ በቅድመ ሙከራ ደረጃ ለማስጀመር ይቻል ዘንድ የኢትዮጵያ ኮምዩኒኬሽንስ ባለስልጣን ጊዜያዊ የስፔክትሪም ፈቃድ በመስጠት የተባበረ ሲሆን ኔትዎርኩን የዘረጋው ደግሞ የረጅም ጊዜ የኢትዮ ቴሌኮም አጋር የሆነው ህዋዌ ቴክኖሎጂስ ነው፡፡

በዚህ የ5G እውን መሆን በተበሰረበት የሸራተኑ ዝግጅት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደተናሩት በአፍሪካ ደረጃ በምስረታ ግንባር ቀደም የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣይነትም ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ታላቋን ሀገር የዘመናዊ ቴክኖጂ ባለቤት ለማድረግ ጠንክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አበክረው እንደተናገሩት “ኢትዮጵያን በአለም የቴክኖሎጂ መድረክ ጥግ እስክናደርስ ድረስ ፈፅሞ እንቅልፍ አንተኛም” በማለት የኢትዮ ቴሌኮምን ቀጣይ የስራ አፈፃፀም በከፍተኛ ደረጃ የማሳደግ ሕልም እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P