Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ፋሲል ከነማ፣ መቐለ 70 እንደርታና ሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ሲጫወቱ ደደቢትን በመከተል ደ/ፖሊስ እና መከላከያ ከሊጉ ወረዱ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ማን በበላይነት ያጠናቅቅ ይሆን? ከእሁዱ የፕሪምየር ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ በፊት ሶስቱ ተጨዋቾች ይህንን አስተያየት ለሊግ ጋዜጣ ሰጥተው ነበር፡፡

በመሸሻ ወልዴ [GBOYS]

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ ሻምፒዮና የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቶች ተከስተውበት፣ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ጋርም በተያያዘ የውድድር መቆራረጦች አጋጥመውት እንደዚሁም ፈፅሞ ሁለት የማይገናኙ ነገሮችን ስፖርቱን የፖለቲካው እና የዘር መጠቀሚያ በማድረግ ጭምር እና የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ደግሞ በፕሪምየር ሊግ አስቀድሞ የወጣልኝን ጨዋታ ሳላከናውን ቀጣይ ጨዋታዬን አላደርግም በማለት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ውሳኔ ተቃውሞ በፍርፌ ተሸናፊ የሆነበትና አሁንም ቢሆን ጥያቄዬ ካልተመለሰም ሌላውን ጨዋታ አላደርግም፤ ራሴን ከውድድሩ አገላለው በማለት ውድድሩ ብዙ ውዝግቦችን አስተናግዶ በነገው ዕለት ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዘንድሮ ባካሄደው አብዛኛው የፕሪምየር ሊግ ውድድሩም ሻምፒዮናውን በአግባቡ አልመራም፤ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች በቂና አጥጋቢ ምላሾችም አልተሰጠንም በማለትም ከክለቦች ተቋውሞም ቀርቦበታል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በብዙ ችግሮች ተተብትቦ ሊካሄድ ቢችልም ዓመቱን ሙሉ የተደረጉት ውድድሮች ግን በነገ ዕለት ይጠናቀቃሉ፤ በዚህ የሻምፒዮና ውድድርም ዋንጫውን ለማንሳት ፋሱል ከነማ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡና ዕድሉ ስላላቸው ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በወሳኝነታቸው አቻ የማይገኝላቸውም ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፍፃሜውን በሚያደርግበት ቀን ከዚህ ቀደም ሶስት ቡድኖች ዋንጫውን ለማንሳት ዕድሉ ሲኖራቸው የታየው በ1990 ዓ.ም ሊጉ ሲጀመር ሲሆን ያኔም ኢትዮ-ኤሌክትሪክ፣ ኢትዮጵያ ቡናና፣ ኢትዮጵያ መድን ነበሩ፤ በመጨረሻው ቀን በተደረገው ጨዋታም ኢትዮ- ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አቻ በመለያየቱ የውድድሩ ሻምፒዮና ሊሆን ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ሶስት ክለቦች በመጨረሻው ቀን ሲጫወቱ ከ21 ዓመታት በኋላ ልንመለከት በተዘጋጀንበት የአሁኑ ወቅት ለእዚህ ፍልሚያ የቀረቡት ቡድኖች ፋሲል ከነማ፣ መቐለ 70 እንደርታና ሲዳማ ቡና እንደሆኑ የጠቀስን ሲሆን ፋሲል ከነማ ነገ ግጥሚያውን የሚያደርገው ወደ ሽረ በመጓዝ ከስሁል ሽረ እንደስላሴ ጋር ሲሆን የውድድሩ ባለድል ለመሆን ተጋጣሚውን ማሸነፍ ብቻ በቂ ይሆንለታል፤ ፋሲል ይህን ጨዋታ ካሸነፈ ሌሎቹ ቢያሸንፉ እንኳን ካለው የግብ ክፍያ አንፃር መቐለን በግብ ክፍያ ሲዳማን በነጥብ በመብለጥ ሻምፒዮና ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለመቐለ 70 እንደርታ ማንሳትን በተመለከተ ደግሞ ቡድኑ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ካሸነፈ እና ፋሲል ከነማ ከተሸነፈለት ሻምፒዮና ሲሆን ለሲዳማ ቡና ደግሞ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ካሸነፈ እና ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ አቻ ከወጡለት ሻምፒዮና ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ዋንጫን ስለሚያነሱ ቡድኖች ይሄን ካልን ከሊጉ መውረድን በተመለከተ ደግሞ ደደቢት አስቀድሞ መውረዱን ያረጋገጠ ሲሆን መከላከያ ደግሞ በመቐለ 70 እንደርታ የተሸነፈበት ጨዋታ እንዲወርድ አድርጎታል፤ ደቡብ ፖሊስም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አቻ ከተለያየ በኋላ ከሊጉ ሊወርድ ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮከብ ግብ አግቢነትን በተመለከተ የመቐለ 70 እንደርታው አማኑኤል ገብረ ሚካኤል በ17 ግብ ሲመራ የሲዳማ ቡናው አዲስ ግደይ እና የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም በ15 ግብ ተከታዩን ስፍራ ይዘዋል፤ የውድድር ዘመኑ ኮከብ ግብ አግቢና ሻምፒዮናው ክለብ ማን ይሆናል፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ነገ መጠናቀቁን አስመልክቶ የዋንጫውን እድል ለማንሳት ዕድሉ ካላቸው የሶስቱ ክለቦች ተጨዋቾች መካከል የፋሲል ከነማውን አምሳሉ ጥላሁን /ሳኛ/ የመቐለ 70 እንደርታውን ዮናስ ገረመው /ሀላባ/ እና የሲዳማ ቡናውን ዳዊት ተፈራን /ኦዚል/ አናግረናቸው ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

“የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የማንከፍለው መስዋትነት የለም፤ ሻምፒዮና እንሆናለን”
አምሳሉ ጥላሁን (ሳኛ)
/ፋሲል ከነማ/


ሊግ፡- የፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታችሁን ነገ እሁድ ከስሁል ሽረ ጋር ከሜዳችሁ ውጪ ታደርጋላችሁ፤ ይሄን ጨዋታ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የምትጫወቱ ከመሆኑ አንፃር ግጥሚያውን እንዴት እየጠበቃችሁት ነው?
አምሳሉ፡- ከስሁል ሽረ ጋር የምናደርገው የነገው ጨዋታ ግጥሚያው ለእኛ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት የምንጫወትበት ከመሆኑ አኳያ ሲታይ ጨዋታው የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ነው፤ ይሄንን አስቀድመን ስለምናውቅም ያለንን አቅም ሁሉ አሟጠን እስከመጨረሻው ሰአት ደረስ ለመጫወት እና ተጋጣሚያችንንም አሸንፈን ለመውጣት በሚገባ ነው የተዘጋጀነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ከፍ አድርጎ ለማንሳት አሁን ከያዛችሁት ነጥብ እና የጎል ክፍያ በመነሳት ከእናንተ ከመቐለ 70 እንደርታ እና ከሲዳማ ቡና ማን የተሻለ እድል ይኖረዋል?
አምሳሉ፡- እኛ ነና! ምክንያቱም በእሁዱ ጨዋታ ያለን ልዩ እና አንድ አማራጭ ግጥሚያውን ከሜዳችን ውጪ የምናደርግ ስለሆነ ማሸነፍ ብቻ ነው፤ ይሄን ጨዋታ አሸነፍን ማለት ደግሞ ካለን የጎል ክፍያ ብልጫ አኳያ ምንም ነገርን ሳንጠብቅ እና በራሳችን እድል ብቻ በመወሰን ሁሉም ነገር አበቃለትም ማለት ነውና ይሄንን ነው ጨዋታው ላይ በተግባር የምናውለው፡፡
ሊግ፡- ለፋሲል ከነማ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከሜዳው ውጭ እንደመጫወቱ ነገ አስቸጋሪ ይሆንበታል የሚሉ አሉ፤ ይሄንን እንዴት ነው የምትመለከተው?
አምሳሉ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ማንሳቱ ላይ በእርግጥ የነገውን ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ከሚያደርገው ግጥሚያ አንፃር እና እኛ ደግሞ ከሜዳችን በመውጣት ከመጫወታችን አኳያ ስንመለከተው በሁሉም ነገር ከባድ የሚሆንብን ለእኛ ቢሆንም ቡድናችን ግን ካለው ወቅታዊ የሆነ ጥሩ አቋሙና ሁሉም ተጨዋች ደግሞ የአሁን ሰዓት ላይ በመልካም ጤንነት እና በጥሩ ሁኔታም ላይ ከመገኘታቸው አኳያ ቡድናችን የነገው ጨዋታ አሸናፊ ሆኖ በእርግጠኝነት ዋንጫውን ያነሳል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ዘንድሮ የሚገባው ግን ለማን ነው?
አምሳሉ፡- ለፋሲል ከነማ ነዋ! ምክንያቱም ዓመቱን ሙሉ ከሁሉም ቡድኖች በተሻለ መልኩ በጣም ለፍተናል፡፡ ይሄ ዋንጫም የልፋታችንም መገለጫ ስለሆነም ነገ እሁድ ክለባችንን የውድድር ዘመኑ ሻምፒዮና ለማድረግ የማንከፍለው አይነት መስዋዕትነት የለም፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረውን ጨዋታ በፎርፌ አሸንፎ ነው የነገውን የፍፃሜ ቀን ጨዋታ እየተጠባበቀ የሚገኘው፤ ሳይጫወቱ ነጥብ ማግኘት እና ተጫውቶ ነጥብ ማግኘትን እንዴት ነው የምትመለከተው?
አምሳሉ፡- እንደ ፋሲል ከነማ ክለብ ተጨዋችነቴ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረንን ጨዋታ ተጫውተን ግጥሚያውንም አሸንፈን 3 ነጥብን ይዘን ብንወጣ ኖሮ በጣም ነበር ደስ የሚለኝ፤ ጨዋታ ሳትጫወት ነጥብ ይዞ መውጣት ብዙም ስሜት አይሰጥም፤ ያም ሆኖ ግን የሆነው ሆኗልና በዚህ ዙሪያ ብዙም የምለው ነገር ባይኖረኝም በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ እኛ በፎርፎ አሸናፊ ሆነን የእሁዱን የመጨረሻ ቀን ጨዋታ እንድንጠባበቅ ተደርገናል፡፡
ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊ ከስሁል ሽረ ጋር ላላችሁ የነገው ጨዋታ በተለየ መልኩ ይቀርባል?
አምሳሉ፡- አዎን፤ ጎንደር ላይ የሚቀር ደጋፊ ያለ አይመስለኝም፤ ይሄ ጨዋታ የሞትና ሽረት ጉዳይ ነው፤ በደጋፊዎቻችን ምርጥ ድጋፍ ታጅበን በመጫወት ነው ዋንጫውን ወደክልላችን ይዘን የምንመለሰው፡፡
ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊ ለየት የሚል ነው?
አምሳሉ፡- አዎን፤ ክለባቸውን ከልብ ነው የሚወዱት፤ ለዛሬ የውጤት ማማራችንም ቡድኑን እዚህ ደረጃ ያደረሱትም እነሱ ናቸው፤ በተደጋጋሚ ጊዜ አንድ እና ሁለት ጎል ስናስቆጥርም፤ ጨዋታን ስናሸነፍም የእነሱ የጩኸት ድምፅ እና ድጋፍም እገዛ አበርክቶልናልና ሊመሰገኑ ነው የሚገባው፡፡
ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ ተሳትፎአችሁ ላይ ቡድናችሁ እንዴት በውጤታማነት ማማው ላይ ሊቀመጥ ቻለ?
አምሳሉ፡- ፋሲል ከነማን የእዚህ አመት ተሳትፎው ላይ ውጤታማ ያደረገው ነገር ቢኖር ከውድድር አመቱ መጀመሪያ አንስቶ እስከአሁን ድረስ ያለው የእርስ በርስ ፍቅሩና መከባበሩ ነው፤ ከዛ ውጪ ጥሩ አሰልጣኝ አለን፤ የቡድናችንም የተጨዋቾች ስብስብ እግር ኳስን በጥሩ መልኩ በሚጫወቱ ልጆች የተገነባ ስለሆነ ይሄ ነው በዋናነት ውጤታማ ያደረገን፡፡
ሊግ፡- በፋሰል ከነማ ክለብ ውስጥ ዘንድሮ ያሳለፍከውን ጊዜ እንዴት ነው የምትመለከተው? እሁድስ ለክለባችሁ የመጨረሻው ጨዋታ በመሆኑ ከአንተ ምንድነው የሚጠበቀው?
አምሳሉ፡- በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ እስካሁን ያሳለፍኩት ቆይታ በጣም ጥሩ የሚባል ሲሆን ለቡድናችንም ውጤት ማማር ከቡድን አጋር ጋደኞቼ ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረትንም ሳደርግ ነው የነበርኩት፤ የነገው የእሁድ ጨዋታችንም ላይ ግጥሚያው ለእኛ ምን ማለት እንደሆነ ጠንቀቄ ስለማውቅ ለቡድኔ ኳሳዊ የሆነ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ልከፍልለት ተዘጋጅቻለሁ፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ የሊጉን ዋንጫ ቢያነሳ ማስታወሻ ልታደርግለት ያሰብከው ሰው አለ?
አምሳሉ፡- አዎን፤ ዋንጫውን እንዳነሳን ማስታወሻነቱን የማደርግላቸው በዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎአችን ላይ እኛን ለመደገፍ ተከትለው በመምጣት የሞት አደጋ ለደረሰባቸው ደጋፊዎቻችን ነው፤ ለእነሱ ሌላ ብዙ የማስታወሻ ነገር ቢደረግላቸው በራሱ የበለጠ ጥሩም ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- ስለቤተሰብህ እስኪ ጥቂት በለን……?
አምሳሉ፡- ቤተሰቦቼን በሚመለከት ከፍቅረኛዬ ራሄል ተስፋዬ ጋር ትዳር መስርቼ 3 ልጆች ልናፈራ ችለናል፤ የመጀመሪያ ልጄ የ3 አመት እድሜ ያላት አሚን አምሳሉ ስትባል ሁለቱ ደግሞ ልክ የዛሬ ስድስት ወር የተወለዱ መንታ ልጆች ናቸው፤ ፍቅር እና ማኪቫም ይባላሉ፡፡
ባለቤቴ ለእኔ የእግር ኳስ ህይወት የዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ትልቁን አስተዋፅኦ አበርክታልኛለችና በጣሙን ልትመሰገን ይገባታል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ……..?
አምሳሉ፡- በድጋሚ አንድ ነገርን ማለት እፈልጋለው፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ዘንድሮ የሚገባው ለእኛ ፋሲሎች ነው፤ ከፈጣሪ እርዳታም ጋር ይሄን ውድድር በሻምፒዮናነት እንደምናጠናቅቅ በጣም እርግጠኛ ነኝ፡፡

“የሊጉን ዋንጫ የማንሳት ዕድላችን በፋሲል ጨዋታ ላይ ቢመሰርትም ሻምፒዮና የምንሆን ይመስለኛል”
ዮናስ ገረመው (ሀላባ) /መቐለ 70 እንደርታ/


የመከላከያ እግር ኳስ ክለብን በማሸነፍ አሁንም የዋንጫው ፉክክር ውስጥ ስለመገኘታቸው
“መቐለ 70 እንደርታ ከመከላከያ ጋር የነበረውን ጨዋታ በማሸነፍ ነገ እሁድ በሚጠናቀቀው የዋንጫው ፉክክር ውስጥ ለመገኘት መቻሉ ቡድኑ በሜዳ ላይ ካለው አቅምና ብቃት አንፃር ያመጣው ውጤት የሚገባው ሆኖ ነው ያገኘሁት፤ ከእነሱ ጋር የነበረንን ጨዋታ በእዛ ጭቃ ሜዳ ላይ ተጫውተን እና መስዋትነትንም ከፍለን ግጥሚያውን በድል ልንወጣ መቻላችንም ሊያስደንቀን ነው የሚገባው”፡፡
የመከላከያን እና የእናንተን አጠቃላይ የ90 ደቂቃ የጨዋታ እንቅስቃሴ ግለፀው?
“መቐለ 70 እንደርታ እና መከላከያ ረቡዕ እለት ያደረጉት ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች ውጤቱ በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ አንፃር ይኸውም እኛ ከዋንጫው ፉክክር ላለመውጣት እነሱ ደግሞ ወደታችኛው ሊግ ላለመውረድ ያደረግነው ስለነበር የግጥሚያው ሜዳ ጭቃ ከመሆኑ ጋር ተደማምሮ ጨዋታው በጣም ከባድ እና ጥሩም ፉክክር የተደረገበት ነበር፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ መከላከያዎች ጥሩ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቢችሉም የጎል አጋጣሚዎችን አግኝቶ በመጠቀም በኩል ደግሞ የእኛ ቡድን የተሻለ ስለነበር ሁለት የመሪነት ጎሎችን በማስቆጠር እና ግብ በማግባት ስለቀደምናቸው ለእኛ ነገሮች ሁሉ ጥሩ ሊሆኑልን ችለው ለእረፍት ወደ መልበሻ ክፍል ልናመራ ችለናል፡፡ የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ የቡድናችን ተጨዋች የሆነው ስዩም ተስፋዬ በቀይ ካርድ ወጥቶብን ስለነበርና በእንቅስቃሴም በኩል ጎዶሎ ሆኖ መጫወታችን እንድንቸገር ስላደረገን ያለን አማራጭ ውጤታችንን አስጠብቀን ለመውጣት መጫወት ነበርና በዛ መልኩ አንድ ጎል ቢቆጠርብንም ያሰብነውን የማሸነፍ ውጤት አሳክተን ግጥሚያውን በድል ልናጠናቅቅ ችለናል”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታቸውን ነገ እሁድ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ስለማድረጋቸው እና የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ስለሚኖራቸው እድል
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት በጣም አስፈላጊ ከነበሩት ግጥሚያዎች መካከል አንዱ የነበረውን የመከላከያ ክለብን በረቡዕ ዕለት ጨዋታ ማሸነፍ መቻላችን በቡድናችን ውስጥ አሁን ላይ ከፍተኛ መነቃቃትን ሊፈጥርልን ችሏል፡፡ ሌላው ዋንጫ ሊያስገኝልን ከሚችሉ ግጥሚያዎች መካከል አንዱ የሆነውን ጨዋታ ደግሞ እሁድ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በሜዳችን እና በደጋፊዎቻችን ፊት የምናደርግ ስለሆነ ይሄን ጨዋታ በእርግጠኝነት እናሸንፋለን፤ የሊጉን ዋንጫ የምናነሳበት እድልን በተመለከተ ይሄ የሚወሰነው እኛ የራሳችንን የቤት ስራ እሁድ በሚደረገው ጨዋታ ከተወጣን በኋላ የፋሲል ከነማ እና የስሁል ሽረ ጨዋታ ውጤትን በመስማት የምናውቀው ይሆናል፤ ያንን እንጠብቃለን፤ ፋሲል ካሸነፈ በጎል ክፍያ ስለሚበልጠን እነሱ ሻምፒዮና ይሆናሉ፤ ከተሸነፉ እና አቻ ከተለያየ ደግሞ እኛ ሻምፒዮና እንሆናለን፡፡ ስለዚህም ለሁሉም ነገር ፈጣሪ ያውቃል ብለን ነው የእሁዱን ግጥሚያ እየተጠባበቅን ነው የምንገኘው”፡፡
የፋሲል ከነማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ጎንደር ላይ አለመከናወኑ እና ፋሲል ከነማ በፎርፌ የጨዋታው አሸናፊ ስለመሆኑ
“ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረበትን ጨዋታ ሳያከናውን በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ የፎርፌ አሸናፊ መሆን መቻሉ እኛን ጎድቶናል፤ ያም ሆኖ ግን እንደ አሰራር ይሄን በመቃወም የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የራሱን መንገድ ለመጓዝ ችሏል፤ እኛ የማናውቀው አንድ ነገር ሊኖር ስለሚችልም እንደ ተጨዋችነቴ በዚህ ላይ ብዙ ነገር ባልናገር በጣም ነው ደስ የሚለኝ”፡፡
የመቐለ 70 እንደርታ የፕሪምየር ሊጉ ጉዞ እና የውጤታማነቱ ምስጢር
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአችንን በተመለከተ ዘንድሮ እኛ የተጓዝነው ጉዞ ብዙ ጫናዎችን በመቋቋም ጭምር ያሳለፍንበት ስለነበር አጠቃላይ ውድድሩ በጣም ከባድ የሆነብን ነበር፡፡ ውድድሩን በሰፊ የነጥብ ልዩነት እስከመምራትም ደረጃ ደርሰን ነበር፤ አሁን ላይ ከፋሲል ከነማ ጋር በእኩል ነጥብ ላይ ሆነን ሊጉን ለመምራት መቻላችንም የእኛን ጥንካሬ ነው የሚያሳየው”፡፡
መቐለ 70 እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ነገ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች አንዳቸውን የሊጉ ሻምፒዮና ያደርጋቸዋል፤ ማን ይሆን የዋንጫው ባለድል?
“የፈጣሪ እርዳታ ይሁንና ክለባችን መቐለ 70 እንደርታ ዋንጫውን የሚያነሳ ይመስለኛል”
መቐለ 70 እንደርታ ክለብ ውስጥ ስለነበረው የዘንድሮ ቆይታ
“በዘንድሮው የውድድር ዘመን ተሳትፎዬ ጥሩ ጊዜን ነው ያሳለፍኩት፤ ለዛም ያመጣነው ውጤት ያሳውቃል”፡፡
የኢትዮጵያ ፐሪምየር ሊግ አጠቃላይ ፉክክሩን በተመለከተ
“የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የፉክክር ስሜት 3 እና 4 ክለቦችን ለዋንጫ ሲያፎካክር የቆየ ከመሆኑ አንፃር ጥሩ ሆኖ ነው ያገኘሁት፤ ውድድሩ በጣም አጓጊም ነበር፤ አሁን ላይ ደግሞ እንደአምናው አይነት ምንአልባት አሸናፊው ቡድን በጎል ክፍያ ልዩነት አልያም ደግሞ ያ ካልተሳካ በጣም ጠባብ በሆነ የነጥብ ልዩነት የሊጉን ባለድል ክለብ ሊያሳውቀን የተዘጋጀው የፍፃሜ ቀሪ ጨዋታን እየተጠባበቅን ነውና ሁሉም የስፖርት አፍቃሪ እና የየቡድኖቹ ደጋፊዎች እንዲህ ያሉ ፉክክሮችን ለመመልከት የሚፈልጉ ከመሆናቸው አኳያ ጥሩ ነገርን ተመልክተናል ብዬ ነው የማስበው”፡፡
መከላከያ እናንተ ካሸነፋችሁት በኋላ ከፕሪምየር ሊጉ ወርዷል፤ የቡድኑ ተጨዋች ባትሆንም ምን ተሰማህ?
“የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ የአገራችን ትልቁ እና በሜዳ ላይ በሚያሳየው የጨዋታ እንቅስቃሴም ብዙ ተጨዋቾች ሊጫወቱበት የሚመኙት ቡድን ስለነበር ከሊጉ መውረዱ በጣም ያሳዝናል፤ ሙሉ ለሙሉ መውረዱን ያረጋገጠውም ከእኛ ጋር ባደረገው ጨዋታ ሸንፈትን ሊጎነጭ በመቻሉ ነው፡፡
ከመከላከያ ጋር የነበረን ጨዋታ የውጤቱ አስፈላጊነት ለሁለታችንም ነበር፤ ያን ጨዋታ እኛ በማሸነፋችን በዋንጫው ፉክክር ውስጥ እንድንቆይ ስላደረገን ስንደሰትበት እነሱን ደግሞ ሊያወርዳቸው ስለቻለ ሊያሳዝናቸውና ሊያስከፋቸው ችሏል፡፡
የመከላከያ ክለብ መውረድ ከክለቡ ትልቅነት አንፃር እና እኔም በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጨዋች በነበርኩበት ጊዜ ያጋጠመኝ አይነት ስለሆነ በጣም ነው ያሳዘነኝ፤ የቡድኑ መውረድ በተለይ ደግሞ በክለቡ ውስጥ ላሉት ተጨዋቾች በጣም አሳዛኝ እና የበለጠም የእግር እሳት ጭምር ነው የሚሆንባቸው”፡፡
የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎችን በተመለከተ
“የመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ደጋፊ እስካሁን ድረስ ከቡድናችን ጎን በቆም አስፈላጊ የሚባለውን ድጋፍ ሁሉ ሲሰጡን ነበር፤ አይዟችሁ በርቱ እያሉም ስለሚያበረታቱን ነው ይሄን የመሰለ ውጤት ልናመጣም የቻልነውና ይሄ ድጋፋቸው ተጨማሪ ኃይል ሊሆንልንም ችሏል”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በሰፊ ነጥብ መርታችሁ ነው በኋላ ላይ በነጥብ ልትበለጡ እና አሁን ላይ ደግሞ በነጥብ የተጋራችሁት፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ማለፋችሁን በተመለከተ
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ስትመለከት እና ከመሪው ስር ስትከተል ያለው ውጥረት እና ጫና ከፍተኛ እና ልዩነትም ያለው ነው፡፡ የሊጉ መሪ ስትሆን የአንተ ነጥብ መጣል ብዙዎች ይፈልጉታል፡፡ ያኔም ጫናዎች እየደረሱብክ መሪነቱን አስጠብቆ መጓዙ ላይ እንድትቸገር ያደርጋልና ዘንድሮ ውድድሩን ያሳለፍነው በዚህ መልኩ ነው”፡፡
በመጨረሻ…..
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን ፈጣሪ በሰላም አስጨርሶን ማየት ከፍተኛ ምኞቴ ነውና የሁሉም ክለብ ደጋፊዎች በስፖርታዊ ጨዋነት የውድድር አመቱን የመጨረሻ ቀን እንዲመለከቱ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ”፡፡

“የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ብናነሳም ባናነሳም ምርጥ የውድድር ዘመንን አሳልፈናል”
ዳዊት ተፈራ (ኦዚል) /ሲዳማ ቡና/


ስለ ሲዳማ ቡና የዘንድሮ የውጤታማነት ጉዞ
“በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎአችን ላይ ክለባችን እያደረገ ያለው የውጤታማነት ጉዞው በክለቡ ታሪክ አዲስ እና ታይቶም የማይታወቅ ሲሆን በተለይ ደግሞ በሜዳው ላይ ያለመሸነፍ ሪከርድን ያስመዘገበ እና ከዚሀ ቀደምም ለአንድም ጊዜ አሸንፈነው የማናውቀውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም ዘንድሮ ድል ያደረግንበት የውድድር ዘመን ስለነበር እነዚህ ስኬቶች ቡድናችንን ውጤታማ አድርጎት እስከነገው የፍፃሜው የዋንጫ ፉክክር ቀናት ድረስ እንዲጓዝም አስችሎታል”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳት ስለሚኖራቸው እድል
“ለሲዳማ ቡና የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ የማንሳት እድሉ ነገ በሚጠናቀቀው የፍፃሜ ቀን ጨዋታ የሚወሰንለት በእኛ ግጥሚያችንን ማሸነፍ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሳይሆን ሊጉን በቅርብ ተፎካካሪነት ማለትም የእኛን ቡድን በአንድ ነጥብ ልዩነት የሚመሩት ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ ቡድኖች መሸነፍና ወይንም ደግሞ አቻ መውጣት ላይም የተመረኮዘ ስለሆነ ሻምፒዮና ስለመሆን እድላችን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ከባድ ነው፤ ያም ሆኖ ግን እኛ ሲዳማ ቡናዎች የነገውን ጨዋታ በማሸነፍ የሚመጣውን ማናቸውንም ውጤት የምንጠባበቅ ነው የሚሆነው፤ ሲዳማ ቡና በእዚህ የውድድር ዘመን የሊጉ አሸናፊ ባይሆን እንኳን እስካሁን የተጋዘበት መንገድ በአብዛኛው ጎኑ ጥሩ የሚባል እና የሚያበረታታው ነው የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ብናነሳም ባናነሳም ምርጥ የውድድር ዘመንንም አሳልፈናል
በዚህ በኩል ለክለባችን አድናቆት ሊሰጠውም ይገባል”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአችሁ ላይ ከዋንጫው ፉክክር ወጣችሁ በተባላችሁበት ሰአት ነው ተመልሳችሁ ወደ ፉክክሩ የገባችሁት፤ ስለዚህ የለውጥ ምስጢር
“ልክ ነህ፤ ሲዳማ ቡና በመጀመሪያው ዙር የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው በፉክክሩ ላይ ከቆየ በኋላ ነው የሁለተኛው ዙር ውድድር ሲጀመር በተደጋጋሚ ነጥብ በመጣሉ ምክንያት ከዋንጫው ፉክክር ወደ መውጣት አምርቶ የነበረው፤ ይሄ ውጤትም በቡድናችን ውስጥ ፈፅሞ ይገጥመናል ብለንም አላሰብንም ነበር፡፡ ያም ሆኖ ግን ኳስ ነውና ያ ችግር አጋጠመን፤ በኋላ ላይ ግን ያሉብንን ክፍተቶች በማረም እና በቡድናችን ዙሪያም በመነጋገር ተመልሰን ወደ ውጤታማነታችን ስለመጣን ከእኛ በላይ የነበረው እና በ9 እና በ11 ነጥብ ይበልጠን የነበረው መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜ ጨዋታዎች ላይ ውጤት ስላጣ እኛም ስለ ደረስንበት ተመልሰን ወደ ዋንጫው ፉክክር ውስጥ ልንገባ ችለናል”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአችሁ ላይ በመሪው ክለብ በሰፊ ነጥብ በምትመሩበት ጊዜ የእናንተ ሀሳብ የነበረው ምንድነው?
“ሲዳማ ቡና የሊጉን የሁለተኛው ዙር ውድድር ሲጀምር የክለቡ ዋነኛ ህልምና ፍላጎት የነበረው ለዋንጫው ከመጫወታችን አንፃር በተለይ በሜዳችን ስንጫወት በአንድም ግጥሚያ ላይ አቻ ላለመውጣት እና የሜዳችን ውጪ ጨዋታዎቻችን ላይ ደግሞ ውጤቶችን ይዞ መውጣት ነበር፡፡ ሆኖም ግን የአቻ ውጤቶች አጋጠመን፤ ያኔም ነው ከላይ ያለው መቐለ 70 እንደርታ በነጥብ ርቆን ሊሄድ ችሎ የነበረው፤ በጊዜውም በሰፊ የነጥብ ልዩነት በተመራንበት ሰአትም በቡድናችን ውስጥ የነበረው ስሜት መሪው ላይ እንደምንደርስ እና ከዋንጫው ፉክክርም እንደማንወጣም ነበር ያሰብነውና አሁን ላይ ያለንበትን ውጤት እና ደረጃ ስመለከት ቡድናችን ምን ያህል ጠንካራ እንደነበር ነው ለመገንዘብ የቻልኩት”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መሪነትን ደቡብ ፖሊስን ባሸነፋችሁበት ወቅት በእኩል ነጥብ ከፋሲል ከነማ እና ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በጋራ የያዛችሁበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር፤ በመከላከያ በሰፊ ግብ በተሸነፋችሁበት ጊዜ ደግሞ መሪዎቹን ለመከተል ቻላችሁ፤ ስለነዛ ስሜቶች ምን ትላለህ?
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታችንን ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በፊት ከደ/ፖሊስ ጋር አድርገንና ግጥሚያውንም በማሸነፍ የሊጉ የመሪ ደረጃ ላይ በእኩል ነጥብ ስንቀመጥ የተሰማኝ የደስታ ስሜት በጣም ከፍ ያለ ነበር፤ ያ ጨዋታ ለእኛ ሁለት አይነት መልክ የነበረው ነው፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ የእኛ ቡድን ለዋንጫ ከመጫወቱ አንፃር ግጥሚያውን በእርግጠኝነት እናሸንፋለን በሚል ከፍተኛ የኦቨር ኮንፊደንስ ስሜት መጥቶብን ስለነበርና በእንቅስቃሴም ላይ ችኩል ስለነበርን ያ ቡድናችንን በሜዳ ላይ ጥሩ እንዳይጫወት አድርጎታል፤ ደ/ፖሊስም በዛ ጨዋታ እንደ እኛ ሁሉ ጥሩ አልነበረም፡፡ የሁለተኛው አጋማሸ ላይ ግን ቡድናችን ያሉበትን ችግሮች አርሞ በመምጣቱ ከ2-1 መመራት አንሰራርቶ 4-2 ሊያሸንፍ ችሏል፤ ከመከላከያ ጋር የነበረን ጨዋታ ደግሞ ቡድናችንን ፈፅሞ ባልጠበቅነው መልኩ ጥሩ ሳይሆን ቀርቶ እና የመጫወቻ ሜዳውም ለምንፈልገው እንቅስቃሴ አስቸግሮን በእነሱ በሰፊ ግብ ተሸንፈን ልንወጣ እና በነጥብም በጥቂት ልዩነትም ከመሪዎቹ እንድናንስም አድርጎናልና ያ ግጥሚያ ለክለባችን ሻምፒዮና መሆን ወሳኝ ከመሆኑ አኳያ ከፍተኛ የቁጭት ስሜትን ፈጥሮብናል”፡፡
በደ/ፖሊስ ተመርታችሁ ያሸነፋችሁበት እና በረብሻ የተቋረጠው እና በድጋሚ የተጀመረው ጨዋታ ለእናንተ ማሸነፍ እንደጠቀማችሁ ይነገራል
“በፍፁም፤ ደ/ፖሊስን ለማሸነፍ የጨዋታው መቋረጥ እኛን አልረዳንም፤ በጨዋታው አሸናፊ ያደረገን በእለቱ የነበረን እንቅስቃሴያችን ነው”፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው ፉክክርን በተመለከተ
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮ ውድድር ከየቱም ጊዜ ይለያል፤ እስካሁን በተደረጉት ጨዋታዎችም በርከት ያሉ ቡድኖች ለዋንጫው ሲፎካከሩ ቆይተው ነገ ለሚጠናቀቀው የመጨረሻ ቀን ውድድርም ሶስት ክለቦች ዋንጫውን ለማንሳት ከፍተኛ ትግል የሚያደርጉበትም ይሆናል፤ ሻምፒዮናው ሁሌም በእዚሁ መልኩ ቢጓዝ የሀገሪቱም እግር ኳስ ላይ ብዙ ለውጦችም ይኖራሉና በዚህ በኩል በጣም ደስ ይላል፤ የእዚህ ዘመን ውድድርም እስከመጨረሻው ሰአት ድረስ በእዚሁ መልኩ መሄዱም ለእግር ኳስ ማህበረሰቡም አጓጊነቱን ይጨምራልና ይሄ ይበል የሚያሰኝ ነው”፡፡
ሲዳማ ቡናን ከሌላው ጊዜ ይለየዋል የምትለው ነገር
“ሲዳማ ቡናን ዘንድሮ በያዘው ቡድን ከሌላ ጊዜ ይለየዋል የምለው ነገር ቢኖር ቡድኑ በአብዛኛው የተገነባው በወጣት ተጨዋቾች መሆኑና በርካታ የሊጉንም ግጥሚያዎችም በማሸነፉ ነው፤ ከዛ ውጪም በሜዳው ላይ ያለውን ቀሪ ጨዋታም አሸንፎ የሜዳ ላይ ሪከርዱንም ለመስበር የተዘጋጀ ስለሆነና እያንዳንዱም የቡድኑ ተጨዋቾች ያላቸው የአሸናፊነት መንፈስም ከፍ ያለ መሆኑ ይሄ ክለቡን ከሌላው ጊዜ ይለየዋል”፡፡
የሲዳማ ቡና አሰልጣኝን በሚመለከት
“አሰልጣኝ ዘርኃይ ሙሉ ምንም እንኳን ገና ወጣት እና ወደሙያው ከመጣም በኋላ ብዙ አመታት ያላስቆጠረ አሰልጣኝ ቢሆንም ይሄን ቡድን እዚህ ደረጃ ላይ ለማድረስ እየሰራ ያለው ስራ ሊደነቅለት ይገባል፡፡ አሰልጣኝ ዘርአይም በክለቡ ቆይታ ተጨዋቾችን የሚረዳበት ነገር ቡድኑን ስኬታማ እያደረገለት ይገኛል፡፡ የእግር ኳስን በፈለግክበት መልኩ እንድትጫወትም ነፃነትን ይሰጥሃል፡፡ ይሄ የተለየ ብቃቱ ነው”፡፡
የሲዳማ ቡና ክለብ ውስጥ ስላለው ቆይታ
“የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብን የተቀላቀልኩት ዘንድሮ ቢሆንም በቡድኑ ያለኝ ቆይታ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ወደዚህ ቡድን ካመራሁበት ጊዜ አንስቶም የቡድኑ ደጋፊዎች በሜዳ ላይ በማሳየው እንቅስቃሴ አድናቆትን እየሰጡኝ በመምጣት ለእኔ ያላቸው ጥሩ ነገርን ልመለከት ችያለሁና በቀሪው የክለቡ ግጥሚያም ከእኔ የሚጠበቀውን መልካም ነገር በማድረግ ቡድኔን ለውጤት ማብቃትና ደጋፊዎቻችንንም ማስደስት እፈልጋለሁ”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P