Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“አሰልጣኝ ውበቱ ጥሩ ኳስን እንድንጫወት ቅርፅ አስይዞናል፤ የእሱ መልቀቅ አይጎዳንም” ሱራፌል ዳኛቸው /ፋሲል ከነማ/

በመሸሻ ወልዴ

በአፍሪካ ክለቦች የኮንፌዴሬሽን ካፕ
ጨዋታ አገራችንን በመወከል የተሳተፈው
ፋሲል ከነማ የታንዛኒያውን አዛም ባህር
ዳር ስታዲየም ላይ ገጥሞ በዛብህ መላዮ
ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፏል፤
ፋሲል ከነማ በክለቡ ምስረታ ታሪክም
ሆነ በክልሉ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን
ኢንተርናሽናል ግጥሚያ አከናውኖ ድል
ያደረገበት የእሁዱ ጨዋታ በሜዳው ግብ
ካለማስተናገዱ ጋር በተያያዘ በውጤትም
ሆነ በጨዋታው እንቅስቃሴ በአበረታችነት
መልኩ እየተገለፀለት ሲሆን ክለቡ
በመጪው ሳምንት ወደ ታንዛኒያ በመጓዝ
የሚያደርገውን ጨዋታም በስኬታማነት
በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፍበት
እድል እንደሚኖረውም የቡድኑ ተጨዋቾች
አስተያየታቸውን እየሰጡበት ይገኛል፡፡
የፋሲል ከነማ ክለብ የታንዛኒያውን
አዛም ካሸነፈ በኋላ ቡድኑ ስላገኘው ድል፣ ስለ
መልሱ ጨዋታ እንደዚሁም ደግሞ ሌሎችን
ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለስኬታማው የክለቡ
የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሱራፌል ዳኛቸው
አንስተንለት ተጨዋቹ ምላሹን በሚከተለው
መልኩ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በሜዳውና በደጋፊው
ፊት የታንዛኒያን አዛም 1ለ0 አሸንፏል፤
ጨዋታው ምን ይመስል ነበር? ውጤቱንስ
እንዴት አገኘኸው?
ሱራፌል፡- የታንዛኒያውን አዛም 1ለ0
ያሸነፍንበት ጨዋታ በጣም ጥሩ እና
በተለይ ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ ኳስን
ይዘንና መስርተን የተጫወትንበት ነው፤
ከተጋጣሚያችንም በእንቅስቃሴ ተሽለንም
የተገኘንበት ነበር፤ ከዛ ውጪ ቡድናችን
ባገኘው ውጤትም እኛ ተጨዋቾች እና
ምርጦቹ ደጋፊዎቻችን በጋራ የተደሰትንበት
ነውና የተገኘውን ጣፋጭ ድል በልዩ መልኩ
ነው መግለፅ የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- በፋሲል ከነማ እና በአዛም መካከል
የነበረው ልዩነት ምን ነበር?
ሱራፌል፡- የፋሲል ከነማና የአዛም
ክለቦች ባደረጉት የእሁድ እለቱ ጨዋታ
በሜዳ ላይ የነበረው ልዩነት የእኛ ቡድን ኳስን
ተቆጣጥሮ የሚጫወት መሆኑና እነሱ ደግሞ
በረጅም ኳስ ላይ በማተኮር በመልሶ ማጥቃት
አጨዋወት የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው ነበር፤
በእሁዱ ጨዋታ ይሄ ልዩነት በሁለታችን
ቡድኖች መካከል የነበረ ቢሆንም የሁለተኛው
አጋማሽ ላይ ግን የእኛም ቡድን የእኔን
መዳከም ተከትሎ ይኸውም ዘንድሮ ያለምንም
እረፍት ለክለቤ ከመጫወቴ አንፃር የድካም
ስሜት ተፈጥሮብኝ ስለነበር አጨዋወታችን
ወደ እነሱ አይነት እንቅስቃሴ አምርቶ በእዚሁ
ሁለታችንም የረጅም ኳስን እንቅስቃሴ
የተጠቀምንበትም ሁኔታ ነበር፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ አዛምን ያሸነፈበት
የ1ለ0 ውጤት ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ
በቂው ነው?
ሱራፌል፡- ውጤቱን ከፈጣሪ እርዳታ
ጋር አዎ! በቂ ነው ብለን ተቀብለናል፤ ወደ
ተከታዩም ዙር ለማለፍ ጠንክረን ሰርተን
ለጨዋታው እንቀርባለን፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ አዛምን ከመፋለሙ
በፊት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተጋጣሚያችሁን
ለማሸነፍ ከፈለጋችሁ በእዚህ መልኩ
ተጫወቱ፤ ተጫውታችሁም ከፈለገ 40 ጎል
ይገባባችሁ ብሎ ወደ ሜዳ እንዳስገባችሁ
ተነግሯል፤ በእዚህ ሀሳቡ ተጠቃሚ ሆናችሁ?
ሱራፌል፡- ከታንዛኒያው አዛም ጋር
በነበረን የእሁድ እለቱ ጨዋታ አሰልጣኝ
ውበቱ አባተ ከተጋጣሚያችን የጨዋታ
ታክቲክ በመነሳት እናንተ በኳስ ቁጥጥር ላይ
ያመዘነ እንቅስቃሴን መከተል ከቻላችሁ፤
እኔም የማሰራችሁን የጨዋታ ታክቲክ
በሜዳ ላይ መተግበር ከቻላችሁ እነሱን
ከማስደንገጥ አልፎ የራስ መተማመን
ስሜታቸውን ማጥፋት ስለምትችሉ በእዚህ
አሸናፊ ትሆናላችሁ ብሎን ነበርና ይሄንን
ተጠቅመን ነው በመጀመሪያው አጋማሽ
ባስቆጠርነው ብቸኛ ግብ ተጋጣሚያችንን
ልናሸንፍ የቻልነውና የአሰልጣኙን ታክቲክ
መተግበራችን ተጠቃሚ አድርጎናል፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ያለ ውበቱ አባተ
በአዲሱ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የመልሱን
ጨዋታ ያደርጋል፤ ይሄ በቡድኑ ውጤት
ማምጣት ላይ ተፅህኖን ይፈጥርባችኋል?
ሱራፌል፡- በፍፁም፤ አሰልጣኝ ውበቱ
አባተ ከቡድኑ ጋር ከቤተሰብ ጉዳይ ጋር
በተያያዘ የተለያየው እኮ ቡድኑን ሰርቶትና
ቅርፅ አስይዞት ነው፤ ወደ ቡድናችን የመጣው
አዲሱ አሰልጣኝ ስዩም ከበደም ከውበቱ አባተ
ጋር የሚመሳሰል አይነት የጨዋታ ታክቲክን
የሚከተል ባለሙያ ስለሆነ አሁን ላይ የውበቱ
አባተ አለመኖር እኛን አይጎዳንም፤ እንደውም
የስዩም በእዚህ ሰዓት ወደ ቡድናችን መምጣት
ጥሩ አጋጣሚም ነው የሆነልን፡፡
ሊግ፡- አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ፋሲል
ከነማን ተረክቧል፤ ስራውንም ጀምሯል፤
እንዴት ተመለከትከው?
ሱራፌል፡- የክለባችን አዲሱ አሰልጣኝ
ስዩም ከበደ ወደ እኛ መጥቶ ልምምድ
ማሰራት ከጀመረ አሁን ገና ሁለት ቀኑ
ነው /ተጨዋቹን ያነጋገርነው ሐሙስ ዕለት
ነው/፤ ልምምዱን እንደተመለከትኩት ብዙ
ስራው ከውበቱ አባተ ጋር የሚመሳሰል
እና ጉልበትንም የማይጨርስ ስልጠናን
ነው እየሰጠን የሚገኘው፤ ጉልበት የሚፈጅ
የሩጫ ልምምድን ከመስራት ይልቅ ከኳስ
ጋር የተያያዘና ኳስ ላይም መሰረትን ያደረገ
ጥሩ ስራን እያሰራን ስለሆነም ከወዲሁ
አሰለጣጠኑን እየወደድነው ነው የምንገኘው፤
በእዚሁ ስልጠናም የክለባችንን የስኬታማነትና
የጥሩ አጨዋወታችንን ጉዞ እናስቀጥላለንም
ብዬ አስባለው፡፡
ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊን እሁድ
እለት እንዴት ተመለከትካቸው?
ሱራፌል፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊን ባህር
ዳር ላይ እሁድ እለት ስንጫወት ለተመለከተ
እነሱ የእግር ኳሱ በጣም አድማቂና መሳጭ
ሆነውም ነው ያገኘዋቸው፤ የፋሲል ከነማ
ደጋፊ ለክለቡ ያለው ስሜትና ክብር ሁሌም
ደስ ይላል፤ ለቡድናችን ተጨዋቾች ያላቸው
ፍቅርም በልዩ መልኩ እንድትመለከታቸውም
ያደርግሃልና ኳሱን ለቡድኑ ሁሌም
የምትጫወተው ጥሩ ስሜት ኖሮህም ነው፤
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እኛን የሚያበረታቱ፤
ቡድናቸውም ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሶ ማየትን
የሚያልሙ ናቸውና ሁሌም ለሚሰጡን
ድጋፍና አክብሮት እኛም እንደተጨዋችነታችን
ልናመሰግናቸው እንፈልጋለን፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች
ከአሁን በኋላ የሚከፈላቸው ወርሃዊ
ደመወዝ ከ50 ሺህ ብር እንዳይበልጥ በሚል
ተወስኗል፤ ይሄን እንደሰማህ ምን አልክ?
ሱራፌል፡- ውሳኔውን ስሰማ እኔም
እንደሌሎች ተጨዋቾች ቅሬታ ነው የተሰማኝ፤
በእዚህ በኩል ደስተኛ አልሆንኩም፤
ምክንያቱም እግር ኳስ ተጨዋቾች በየክለቡ
ውስጥ ገብተን ኳስን የምንጫወተው
ለምንጫወትበት ክለብ ጥሩ ስራ ሰርተን
የተሻለ ነገርን ለማግኘት ነው፤ ይሄ በሆነበት
ሂደት ላይ ለእኛ ሀገር ተጨዋቾች አሁን
የሚከፈለው ገንዘብ ከኳሱ እድገት ጋር
የሚመጣጠን አይደለም በሚል ምክንያት
ተጨዋቾችን ሳያነጋገሩና እነሱን ባላማከለ
ሁኔታ ከእዚህ በፊት ይከፈልህ የነበረው
ደመወዝህ ተቀንሶ ከአሁን በኋላ በእዚህ
በተወሰነልህ ብር ነው የምትጫወተው ስትባል
ማንም ደስተኛ አይሆንምና ብሩ ላይ ብቻ
አተኩረን ከምንነጋገር ለእግር ኳሱ መፍትሄ
በሚሆነው ነገር ላይ ሃሳቦችን እያቀረብን
ብንወያይ መልካም ነው የሚመስለኝ፤
የኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት ዝቅ ማለቱ
የእውነት ነው፤ የተሻለ ተጨዋችና
አሰልጣኝ ማፍራቱ ላይ መስራት እንዳለብንም
አምናለውኝ፤ ተጨዋቹም አሰልጣኙም
ለተቀጠረበት ክለብም ተገቢውን ግልጋሎት
መስጠት እንዳለበትም ሀገሩንም በሚገባ
መጥቀመም ይኖርበታልና ይሄንን ግዴታውን
እንዲወጣ ማድረግ እንጂ የተጨዋቾችን
ደመወዝ መቀነስ ኳሱን ያሳድገዋል ብሎ
ማሰብ በጣም ከባድ ነገር ነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P