Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ቅ/ጊዮርጊስ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል “እኛ ፍትህ ፍለጋ እንጂ የትኛው በሚያስቀና ስራቸው ነው የእነርሱን ስልጣን የምንሻው?” አቶ አብነት ገ/መስቀል

በአለም ሰገድ ሰይፉ


በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነው ታላቁ የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ በቀጣዮ የውድድር ዓመት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ደጋፊዎቹን ለመካስ ይቻለው ዘንድ ዘንድሮ ወገቡን ጠበቅ አድርጎ ተነስቷል፡፡ ለዚህም ስኬት ይረዳው ዘንድ ጥሩ ክህሎት ያላቸውን ተጨዋቾች ከማስፈረምም ባሻገር በአፍሪካ ደረጃ ጥሩ ልምድ ያለውና የሚቾ ምትክ ሊሆን የሚችል አሰልጣኝን አስሶ ከሰርቢያ አሰመጥቷል፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ጥሩ ተፎካካሪ ቡድን መሆኑ ብቻ ሳይሆን የተለመደውን የዋንጫ ክብር ለመመለስ ይችል ዘንድ ሌት ተቀን እየሰሩ ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ ደግሞ በክለቡ ሕልውና ፈፅሞ ድርድር የማያውቁት የክለቡ የቦርድ አመራር አባላት ይሄን ፍላጎት ከጫፍ ለማድረስ እየተጉ ናቸው፡፡
የቅ/ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በ2012 ዓ.ም የውድድር ዘመን የክለቡን ኃያልነት ዳግም የሚመልስና ባለፈው ሁለት ተከታታይ ዓመታት በዋንጫ ርሃብ የተጎዳውን ደጋፊ ለመካስ ይችል ዘንድ የቡድኑን ዋና አለቃ ለማግኘት ከሀገር ውስጥና ከውጭ የተለያዩ ሙያተኞችን ያሰሰ ሲሆን በስተመጨረሻም ቅ/ጊዮርጊስን ሊመጥን ይችላል የሚሉትን ሰርቢያዊ አሰልጣኝ ሰርጂዮን ማስፈረማቸውን ፈረሰኞቹ ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም በቀጣዮ ሁለት ዓመታት ቅ/ጊዮርጊሶች ከሰርቢያዊው አሰልጣኝ ጋር አብረው የሚዘልቁ ይሆናል፡፡ ይኸው አዲሱ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ በማጥቃት ላይ ያተኮረ ቡድን የመገንባት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀው በቀጣይነትም የእርሳቸውን የጨዋታ ፊሎዞፊ ለመናገር መጀመሪያ የቡድኑን ተሰላፊዎች አቅምና ችሎታ ማየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ የፊርማ ስነ ስርዓት በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ለክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ ቀርበው ፕሬዝዳንቱ አጥጋቢ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ እንደአቶ አብነት ገለፃ ቅ/ጊዮርጊስ ታላቅ ክለብ ከመሆኑ አንፃር ማናቸውም አይነት የተጨዋቾችና የአሰልጣኞች ምርጫ የሚካሄደው በጥንቃቄና ስርዓት በተከተለ መንገድ መሆኑን ገልፀው ቅ/ጊዮርጊስም በ2012 የውድድር ዘመን ክለቡን በኃላፊነት ይዞ ወደ ሜዳ የሚገባውን ሙያተኛ አፈላልጎ ለማግኘት ደክሟል በማለት ተናግረዋል፡፡
በመቀጠልም ከጋዜጠኞች ከተነሱት አንኳር ጥያቄዎች መካከል ቅ/ጊዮርጊስ በ2012 የውድድር ዘመን በየትኛው ሊግ ይወዳደራል? የሚለው ነው፡፡ እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ ከሆነ መንግስት በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ሁሉም በየክልሉ እንዲጫወት ማድረግ ያለበት ለቅ/ጊዮርጊስ አሊያም ለኢትዮጵያ ቡና ብሎ ሳይሆን ለራሱ ሲል ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ ፕሪምየር ሊጉ ይቀጥል ቢባል ያን ያክል ሚሊዮን ብር ወጥቶባቸው የተገነቡ ስታዲየሞች ሰላማዊ የውድድር መድረክ ሳይሆን የደም ገንዳ ባይሆኑ አብነት ምንም አያውቅም ብላችሁ ውቀሱኝ፡፡ በመሆኑም አሁን ያለው ሁኔታ እስኪረጋጋ ድረስ ሁላችንም በየክልላችን ብንጫወት የተሻለ ይሆናል ብለን እናስባለን፡፡
በተረፈ በተደጋጋሚ ሲነገር እንደምሰማው ቅ/ጊዮርጊስ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ፎርፌ ስለሰጠ ወደታችኛው ዲቪዚዮን ይወርዳል ይባላል፡፡ ሲጀመር ይህ ታላቅ ክለብ ፎርፌ ሰጥቶ አያውቅም፡፡ እኛ መብታችንን ጠየቅን፤ እነርሱ መልስ መስጠት ስለተሳናቸው ጨዋታውን አላደረጉም፡፡ ቅ/ጊዮርጊስ ሁሌም የሚሟገተው ለአንድ ለክለባችን ብቻ ሳይሆን ለሀገር ስፖርት እድገት በማሰብ ነው፡፡ እንደዛ ባይሆን ኖሮ ምንም ትርፍና ፋይዳ ለሌለው ፉትቦል ይሄን ያክል ሚሊዮን ብሮችን አያፈስም ነበር፡፡
የፌዴሬሽኑ አመራሮች ግን የተንጋደደውና ከሕግ ውጪ የሆነ አሰራር ሲከተሉ እንዲያርሙ ስትነግራቸው የእነርሱን ስልጣን ለመንጠቅ የፈለግክ ይመስላቸዋል፡፡ እኔን ግን ሁሌም የሚገርመኝ የትኛው በሚያስቀና ስራቸው ተቀንቶ ነው የእነርሱን ስልጣን ለመጋፋት ትግል የምንገጥመው? በእንደዚህ አይነቱ የተዝረከረከ ስራ ይሄን ኃላፊነት ለመሻማት ማንም የሚጓጓ የለም በማለት ተናግረዋል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P