Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከአምናው የተሻለ ቡድን አለን፤ የፕሪምየር ሊጉንም ዋንጫ ዳግም እናነሳለን”ያሬድ ከበደ /መቐለ 70 እንደርታ/

በመሸሻ ወልዴ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑ መቐለ 70 እንደርታ ዘንድሮ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ይህን ዋንጫ ለማንሳት እንደሚፎካከርና ክብሩንም ዳግም ሊጎናፀፍ እንደሚችል የቡድኑ ስኬታማ ተጨዋች ያሬድ ከበደ አዳማ ከተማን በሜዳቸው እና በደጋፊያቸው ፊት ካሸነፉበት ግጥሚያ በኋላ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፤ መቐለ 70 እንደርታ በሊጉ ለሚያስመዘግባቸው ውጤቶች ለቡድኑ ጥሩ ከመንቀሳቀስ ውጪ እንደ ቡድንም በመጫወት በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘውን ይኸውን ተጨዋች አዳማ ከተማን ስላሸነፉበት ጨዋታ፣ በሌሎች ግጥሚያዎች ዙሪያ፣ ስለራሱና በዘንድሮ የሊግ ውድድርም ምን ውጤት ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ለተጨዋቹ ጥያቄዎችን አቅርቦለት ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታ በአዳማ ከተማ ላይ ያስመዘገበውን ድል እንዴት ትገልፀዋለህ? የሁለታችሁ ጨዋታስ ምን መልክ ነበረው?
ያሬድ፡- አዳማ ከተማን በሜዳችንና በደጋፊዎቻችን ፊት ታጅበን የተፋለምንበት የረቡዕ ጨዋታ በሁለታችንም መካከል ጥሩ ፉክክር የተደረገበት ሲሆን፤በጨዋታው የእኛ ቡድን በርካታ የግብ አጋጣሚዎችን አግኝቶ ያልተጠቀመበት እናበአዳማዎች በኩል ደግሞ በመከላከሉ ላይ በጣም ጠንካራ የነበሩበትን ሁኔታ ተመልክተናል፤ በመጨረሻ ላይ ግን የኋላ መስመሩን ሊከፍቱልን የቻሉበትን አጋጣሚ ስላገኘንና ተጭነናቸውም ስለተጫወትን ግቦችን አስቆጥረን ጨዋታውን ልናሸንፍ ችለናል፡፡ በእዚህም ጠንካራ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታም ሆነ ባገኘነው ውጤት በጣም ተደስተናል፡፡
ሊግ፡- የሁለታችሁን ጨዋታ ጥሩ ፉክክር የተደረገበት ብለሃል፤ ያን እንድትል ያስቻለህ ሁኔታ ምን ነበር?
ያሬድ፡- የመቐለ 70 እንደርታና የአዳማ ከተማን የረቡዕ ጨዋታ ጥሩ ፉክክር ተደርጎበታል ለማለት የቻልኩት ያለምንም ምክንያት አይደለም፤ በእለቱ በሁለታችንም መካከል ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት ከመሞከር ባሻገር ተደጋጋሚም ጎል የማስቆጠር ሙከራ ተደርጎበታልና ይሄ ነው ጨዋታውን ጥሩ እና ጠንካራ ፉክክርም እንዲኖረው ያደረገው፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታ አዳማን ለማሸነፍ እንዲችል የረዳው ጠንካራ ጎኑ ምን ነበር? የቡድኑ ክፍተትስ? በጨዋታው አዳማዎችንስ በምን መልኩ አገኘኸቸው?
ያሬድ፡- መቐለ 70 እንደርታ በጨዋታው የነበረው ጠንካራ ጎን ካለፈው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ግጥሚያ አንፃር በማጥቃትም ሆነ በመከላከሉ በኩል በጣም ተሽሎና ጥሩ ሆኖ የቀረበ መሆኑ ነው፡፡ ክፍተት ጎናችን ደግሞ ፈፅሞ አልታየኝም፡፡ የአዳማ ከተማን ክለብ በተመለከተ በጨዋታው እነሱ የመሃል ሜዳቸው ላይ የሰው ቁጥርን አብዝተው የተጫወቱ ስለነበሩ እነሱን ፔኔትሬት አድርጎ ለመጫወት ከብዶን ነበር፤ በኋላ ላይ ግን በረጅም ኳስ ጭምር ለመጫወት ስለሞከርን በመጨረሻ ላይ በከፈቱልን በር ተጠቅመን ጨዋታውን ለማሸነፍ ችለናል፡፡
ሊግ፡- ባለፈው እሁድ የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና በቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፏል፤ የሽንፈቱ ምክንያት ምንድን ነበር?
ያሬድ፡- ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነበረን ያለፈው ሳምንት ጨዋታ ለቡድናችን ሽንፈት ምክንያት ነው ብዬ የምጠቅሰው ከእረፍት በኋላ የትኩረት ማነስ ችግር አጋጥሞን ነበር፤ ያም ነው የጎዳን ፡፡ ሌላ ችግር ፈፅሞ አልነበረም፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ ኳስን ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረን ነበር፡፡ ከእረፍት መልስ ስንገባ ግን በራሳችን ጥቃቅን ችግርም ነው በራችንን ልንከፍትላቸው ስለቻልን ጎል አስቆጥረው ሊያሸንፉን የቻሉት፡፡
ሊግ፡- የመቐለ 70 እንደርታ የአሁኑ ቡድንና የአምናው ቡድን በአንተ አንደበት ሲነፃፀር?
ያሬድ፡- የዘንድሮው ይሻላል፤ ከአምናው ቡድናችን የዘንድሮው በመከላከልም ሆነ በማጥቃቱ በኩል በጣም የተጠናከረና የተሻለም ቡድን ነው፡፡
ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ ከባድ በሆነው ከሜዳ ውጪ ማሸነፍ እናንተ ሲዳማ ቡናን ረትታችኋል?
ያሬድ፡- ሲዳማ ቡናን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ልናሸንፈው የቻልነው ባለን ህብረት እና አንድነት ነው፤ ከእነሱ ጨዋታ በፊት ከቡና ጋር በነበረን ግጥሚያ ነጥብ ጥለን ቁጭት ነበረን፤ የግድ ይሄን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን በሚል ነው ወደ ሜዳ ተነጋግረን በመግባት የጨዋታው ባለድል ልንሆን የቻልነው፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ዳግም ያነሳል?
ያሬድ፡- አዎን፤ እርግጠኛ ነኝ፤ መቶ ፐርሰንት ዋንጫውን ከደጋፊያችን ጋር እናነሰዋለን፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታ በቀጣይ ጊዜ ስለሚያከናውናቸው ጨዋታዎች ምን የምትለው ነገር አለ?
ያሬድ፡- የአሁን ሰአት ላይ እኛ እያሰብን የምንገኘው ሁሉንም ጨዋታዎች ስለማሸነፍ ነው፡፡ በሜዳችንም ከሜዳችን ውጪም ግጥሚያዎችን ማሸነፍ አለብን፡፡ ከሜዳ ውጪ የምናደርጋቸውን ጨዋታዎች ፈፅሞ መሸነፍም የለብንም፡፡ በሜዳችን ላይ ብቻ ማሸነፍ ሻምፒዮና አያደርግምና ይሄን ነው እየሰራን የምንገኘው፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታን ከሌሎች ቡድኖች ምን ይለየዋል?
ያሬድ፡- ከሁሉም ቡድን በተለየ መልኩ የተለያየ አይነት የአጨዋወት ስልቶች አለን፤ በዛም እንለያለን፤ ስንፈልግ ኳስ ይዘንና ተቆጣጥረን እንጫወታለን፡፡ ከፈለግን በመልሶ ማጥቃት እንጫወታለን፡፡ አንድ አይነት አጨዋወት ስለሌለን በዚሁም ውጤታማም እንሆናለን፡፡
ሊግ፡- የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎችን እንዴት ትገልፃቸዋለህ?
ያሬድ፡- የእኛ ደጋፊዎች በአሁን ሰአት ከሚሰጡን ድጋፍ በመነሳት ስመለከታቸው የኢትዮጵያ አርማ ብላቸው ደስ ይለኛል፤ ሌሎቹ ደጋፊዎች ከእኛ ቢማሩም ደስ ይለኛል፡፡ እዚህ መጥተህ በሰላም ነው ተጫውተህ የምትሄደው፡፡ ተደግፈህም ነው የምትሸኘው፡፡ የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊንም በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር በሜዳችሁ ስትጫወቱ ነጥብ ጥላችሁ ነበር፤ ለእዚያ እንደምክንያት የምትጠቅሰው ነገር አለ… የቡናን አጨዋወትስ በምን መልኩ ነው የምትገልፀው?
ያሬድ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር ስንጫወት የተጎዱብን አንዳንድ ተጨዋቾች አልተሰለፉልንም ነበርና እነሱ አለመኖራቸው እኛን አጉለውናል፤ ከእዛም በመነሳት ቡናዎች በመሃል ሜዳው ላይ በልጠውንም ተጫውተዋል፤ ኢትዮጵያ ቡናዎች በእዚያን እለት ኳስን ይዘው ቢጫወቱም ጎል በማስቆጠሩ ግን ቅድሚያን የወሰድነው እኛ ነበርን፡፡ እነሱ የአቻነቷን ግብ ሲያስቆጥሩብን ጫና ተፈጠረብን በተለይ ደግሞ ሰአቱ እየገፋ ሲሄድ የደጋፊው ጫና አንተ ጋር ይመጣልና ስህተቶችን ስንፈጥር ነበር ቡና በዛ ዕለት ጨዋታ ብዙም አልበለጡንም፡፡ በእዛ ላይ ቡድናችን ብዙም አልተዋሃደም ነበር፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡናን አጨዋወት እንደተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ስታየው የምትወደው አይነት ነው?
ያሬድ፡- የቡና አጨዋወት ከሚጫወቱበት ሜዳ አንፃር ጥሩ ነው፤ አሁን ሜዳው መቐለ ላይ ስለነበርም ነው ጥሩ ሊጫወቱ የቻሉት፤ ግን በሌላ ብዙዎቹ የክልል ሜዳዎች ላይ ሄደው እንዲህ ልጫወት ቢሉ ለእነሱ ጥሩ አይደለም ብዬ ነው የማስበው፤ እንጂ አጨዋወታቸው ኳስ ይዘውም ስለሆነ ጥሩ ነውና ሌሎችንም አማራጮች ሊጠቀሙም ይገባል፡፡
ሊግ፡- የመቐለ 70 እንደርታው ያሬድ ከበደ እንዳለው የኳስ ብቃትና ለቡድኑ እንደሚያበረክተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያልተዘመረለት ጀግና ነው የሚል ነገርን ሰማን፤ ይሄን አባባል እንዴት ትቀበለዋለህ ስለቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወትስ ምን ትላለህ?
ያሬድ፡- /እንደመሳቅ ካለ በኋላ/ እኔንጃ እኔ የእግር ኳስን ስጫወት ሁሌም እንደቡድን ነው የማስበው ቡድኑ ማሸነፍ አለበት እንጂ የግል ነገርን አላስብም፡፡ አሰልጣኙም እንደዛ ነው ያስተማረኝ፡፡ ጥሩ ተጨዋች ሆኜ እኔ የምመኘው ነገር ስኮር ማድረግ ነው፡፡ ኮከብ ግብ አግቢ መሆንን ነው የምፈልገው፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስን ታውቀዋለህ ጎል ባገባ ነው የጣረን የሚያስበው የለም፡፡ በተለይ ክልል ከወጣ ማንም ሰው አያይህም በስም ካልሆነ በስተቀር አንተ የምትጠረው ነገር አይታይም፤ መቀሌ ውስጥ ስትጫወት የመቀሌ ህዝብ ነው የሚያየኝ የአዲስ አበባውም እንደዛ እኔ ለዛ ነው እንጂ እንደ ቡድን ነው መጫወት ይምፈልገው ለሃገሬም ወደፊት ጥሩ ነገር አሰራለው ብዬም አስባለው
ሊግ፡- በመጨረሻ…..?
ያሬድ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በአሁን ሰአት የሚታየው ነገር በጣም ደስ ይላል፡፡ የእግር ኳሱ ላይ ጥሩ ነገር ተሰርቷል፡፡ እንደፈለግክ ወጥተህ ተጫውተህ ነው የምትመጣው እና በእዚሁ እንቀጥል በጣም ደስ ይላል፤ ይሄም ነው እግር ኳስ ማለት፡፡

እናንተ ወደ ይርጋም ተጉዛቹሁ ሲዳማ ቡናን ማሸነፍ ችላችሁ ነበር፡፡ የእዚያን ፍልሚያ እና ድል በምን መልኩ ነው ልትገልፁት የምትችሉት?
ያሬድ፡- ሲዳማ ቡናን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ልናሸንፈው የቻልነው ባለን ህብረት እና አንድነት ነው በእነሱ ጨዋታ በፊት ከቡና ጋር በነበረን ግጥሚያ ነጥብ ጥለን ቁጭትም ስለነበረብን ነው የግድ ይሄን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን በሚል ወደ ሜዳ ተነጋግረን በመግባት የጨዋታው ባለድል ልንሆን የቻልነው፡፡
ሊግ፡- የመቀሌ 70 እንደርታ ደጋፊዎችን እንዴት ትገልፃቸዋለህ?
ያሬድ፡- የእኛ ደጋፊዎችን በአሁን ሰአት ከሚሰጡን ድጋፍ በመነሳት ስመለከታቸው የኢትዮጵያ ግርማ ባላቸው ሌሎቹ ደጋዎች ሌሎቹ ቢማሩም ደስ ይለኛል፡፡ እዚህ መጥተህ በሰላም ነው ተጫውተህ የምትሄደው፡፡ ተደግፈህም ነው የምትሸኘው፡፡ የመቀሌ 70 እንደርተ በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵይ ቡና ጋር በሜዳችሁ ስትጫወቱ ነጥብ ጥላችሁ ነበር ለእዚይ እንደምክንያት የምትጠቅሰው ነገር አለ የቡናን አጨዋወትስ በምን መልኩ ነው የምትገልፀው?
ያሬድ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር ስንጫወት የተጎዱብን አንዳንድ ተጨዋቾች አልተሰለፉልንም ነበርና እንሱ አጉለውናል፡፡ በእዛም በመነሳት ቡናዎች በመሃል ሜዳው እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያ ቡናዎች በእዚያን እለት ኳስ ይዘው ቢጫወቱም ጎል በማስቆጠሩ ግን ቅድሚያን የወሰድነው እኛ ነበርን፡፡ እነሱ የአቻነቷን ግብ ሲያስቆጥሩ ግን ጫና ተፈጠረብን በተለይ ደግም ሰአቱ እየገፋ ሲሄድ ጫናው አንተ ጋር ብቻ አይደለም አንድ ስህተት ተፈጠረ፡፡ ብዙም አልበለጡም፡፡ ከእዚያ ላይ ብዙም አልተዋሃድንም ይሄ ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና አጨዋወት?
ያሬድ፡- የቡናን አጨዋወት ኳስ ሜዴው ጥሩ ነው ሌላ ቦታ ሄደህ እንዲህ ልጫወት ብትል ጥሩ አይደለም ብዬ ነው፡ የማስበው አጨዋወታቸው ደስ ይላል፡፡ አካሄዳቸው ደስ ይላል ሜዳም መፍቀድ አለበት፡፡
ሊግ፡- የመቀሌ 70 እንደርታው ያሬድ ከበደ እንዳለህ የኳስ ብቃትና ለቡድኑ እንደሚያበረክተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያልተዘመረለት ጀግና ነው የሚል ነገርን ሰማን፡፡ ይሄን አባባል እንዴት ትቀበለዋለህ ስለቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወትስ ምን ትላለህ?
ያሬድ፡- /እንደመሳቅ ካለ በኋላ/ እኔንጃ እኔ የእግር ኳስ ስጫወት ሁሌም እንደቡድን ነው የማስበው ቡድኑ ማሸነፍ አለበት እንጂ የግል ነገርን አላስብም፡፡ አሰልጣኙም እንደዛ ነው ያስተረማኝ፡፡ ጥሩ ተጨዋች ሆኜ እነ የምመኘው ነገር ስኮር ማድረግ ነው፡፡ ኮከብ ግብ አግቢ መሆንን ነው የምፈልገው፡፡ እግር ኳስ ታውቃለህ ጎል ካገባ ነው የጠፋ የሚያስብ የለም፡፡ በተለይ ክልል ከወጣ ማን አይድንም በስም ከሆነ እንጂ መቀሌ ውስጥ ተጫውተህ የመቀሌ ህዝብ ነው የሚያየኝ የአዲስ አበባውን እንደዛ እኔ እንደ ቡድን ነው የምጫወተውም ጥሩ ነገርን ለሃገሬም ለቡድኔም ለመስራት እፈልጋለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P