Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“የልምድ እጦትና ልጅነት ለትልቅ ደረጃ እንዳልደርስ አድርጎኛል፤ መጪው ጊዜ ግን የእኔ ይሆናል” ቡልቻ ሹራ /አዳማ ከተማ/

በመሸሻ_ወልዴ

ቡልቻ ሹራን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ቆይታው የአዳማ ከተማን የአጥቂ ስፍራ ሲመራ ብዙዎቹ ያውቁታል፤ ተጨዋቹ ከተስፋ ቡድን አንስቶም ለስድስት ዓመታት ያህል በክለቡም ቆይታን አድርጓል፤ በተጨዋችነት ዘመኑም ለአዳማ ተስፋ ቡድን በሚጫወትበት ሰዓት ክለቡን ለድል እንዲበቃ ከማድረግ ባሻገር የውድድር ዘመኑም ኮከብ ተጨዋች ተብሎ ተሸልሟል፤ ቡልቻ ሹራ በእግር ኳስ ተጨዋችነት ቆይታው ተስፋ የሚጣልበትን እንቅስቃሴ ይዞ ወደ ሊጉ ቢመጣም በሚፈልገው ደረጃ ግን የላቀ ደረጃ ላይ አለመድረሱን በራሱ አንደበት ይናገራል፤ ያም ሆኖ ግን በቀጣዩ ጊዜ የኳስ ህይወቱ አሁን ላይ የተማራቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ተስፋን ሰንቋል፤ ይሄን ተጨዋች ባሳለፈው የኳስ ህይወት ቆይታው እና በክረምቱ ወራት የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከክለቡ ጋር የውል ጊዜውን መጨረሱን አስመልክተን ከአዳማ ከተማ ጋር ስለመቀጠሉ እና አለመቀጠሉን በማስመልከት አናግረነዋል፤ እሱም ተገቢውን ምላሽ በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡


ሊግ፡- ለአዳማ ከተማ ከተተኪው ቡድን አንስቶ ለመጫወት ችለሃል፤ በኳሱ መድረስ ያለብህ ቦታ ላይ ተገኝተሃል?
ቡልቻ፡- እንደዛ ብዬ እንኳን አላስብም፤ ከዛ ይልቅ ግን እስካሁን መጫወት በምፈልግበት ክለብ ውስጥ ለመጫወት በመቻሌ ብቻ በጣሙን ደስተኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- በኳሱ መድረስ ያለብህ ቦታ ላይ እንዳትደርስ ያደረጉህ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ቡልቻ፡- አንደኛው እና የመጀመሪያው ምክንያት ጥሩ ችሎታው እና አቅሙ ኖሮኝ እነዛን በምፈልግበት መልኩ ለማሳየት አለመቻሌ ነው፤ እነዛ እንዳይሳኩም ገና ያልበሰልኩ እና የልጅነት እድሜዬም የሸወደኝ ተጨዋች ስለሆንኩ የራሴ ችግሮች ናቸው በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንዳልደርስ እና እንዳልገኝም ያደረገኝ፡፡
ሊግ፡- ከእዚህ በኋላስ በኳሱ ትልቅ ደረጃ ላይ ትደርሳለህ?
ቡልቻ፡- ያለምንም ጥርጥር ነዋ! ምክንያቱም አሁን ላይ ያወቅኳቸው እና የተማርኳቸው ብዙ ነገሮች አሉና፤ በፊት ግን ኳሱን ስጫወት ያው ልጅነቱም ጭምር ስላለ ለስራህ እንደምትሰጠው ያህል ከፍተኛ ትኩረት ለኳሱ አትሰጥም ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ኳሱ ስራዬና እንጀራዬ መሆኑን ሳውቅ ከዛም በተጨማሪ ደግሞ አንተን የሚያውቁ ሰዎች በችሎታ ያለህን አቅም በተደጋጋሚ ጊዜ ሲነግሩህ በምን መልኩ መበርታት እንዳለብህ ስለምትረዳህ እኔም ያን አወቄ ነው በኳሱ ጥሩ ደረጃ ላይ እደርሳለሁ ያልኩት፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳሱ የቀጣይ ጊዜ የኳስ ቆይታህ ምን ምን ነገሮችን ለማሳካት ነው የምትፈልገው?
ቡልቻ፡- ፈጣሪ ፈቅዶ እና ኮቪድንም አጥፎቶልን የእግር ኳስ ውድድራችን ሲጀመር እኔ በዋናነት ለማሳካት የምፈልጋቸው ነገሮች ብዙ ናቸው፤ ከእነዛም መካከል አዳማ ከተማን ለቀቅኩም በክለቡ ቆየውም ከምጫወትበት ቡድን ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እፈልጋለው፤ ኮከብ ግብ አግቢ መባልን እፈልጋለው፤ በአጠቃላይ ጉዞዎቼ ሁሉ ከስኬት ጋር እንዲሆንም ነው የምመኘው እና እነዚህ መሳካታቸውም አይቀሬ ነው፡፡
ሊግ፡- ካልተሳሳትኩ በስተቀር እስካሁን በአዳማ ከተማ ክለብ ውስጥ ነው ቆይታህን ያደረግከው?
ቡልቻ፡- ልክ ነህ፤ በተጨዋችነት ዘመኔ ከአዳማ ውጪ የሌላ ክለብ ማሊያን ሳለብስ ነው እየተጫወትኩ የቆየሁት፤ በእዛ በነበረኝ ቆይታም ለዋናው ቡድን አምስት ዓመት ለተተኪው ቡድን ደግሞ አንድ ዓመት በአጠቃላይ ደግሞ ለስድስት ዓመት ነው ለመጫወት የቻልኩት፡፡


ሊግ፡- በአዳማ በነበረህ የተጨዋችነት ቆይታ ያሳለፍካቸውን ጊዜያቶች እንዴት ነው የምትገልፃቸው?
ቡልቻ፡- በቆይታዬ መልካም እና መልካም ያልሆኑ ጊዜያቶችን ለማሳለፍ ችያለው፤ መግለፅ የምፈልገው ግን ጥሩ ጊዜያቶችን ብቻ ስለሆነ እነዛን ብል ብቻ እመርጣለሁ፤ አዳማ የምወደው ክለቤ ነው፤ ቡድኑም እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ ያደረገኝ እናት ክለቤም ስለሆነ በቆይታዬ ደስተኛ መሆኔን ነው ለመናገር የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- የውል ዘመንህን ከመልቀቅህ ጋር ተያይዞ አዳማ ከተማን በዝውውሩ መስኮት የምትለቅ ይመስልሃል?
ቡልቻ፡- አሁን ላይ ሆኜ በእዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምንም ነገርን ባልል እመርጣለው፤ የእኔ ከክለቡ ጋር መቀጠልም አለመቀጠልም ሊታወቅ የሚችልው በእዚህ የዝውውር መስኮት ከሌሎች ክለቦችም ጥሪው እየቀረበልኝ ስለሆነ ይሄን በተመለከተ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምላሽን የምሰጥበት ነው የሚሆነው፤ ምክንያቱም በተጨዋችነት ዘመኔ ሁኔታዎች ካላስገደዱኝ በስተቀር ከአዳማ ከተማ ጋር ባልለያይ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ግን የተለያዩ ክለቦች ከሚደውሉልኝ ስልክ የተነሳ እና አሁን ላይ ደግሞ ቤተሰብም መስርቼ የምኖርና የልጅ አባትም ከመሆኔ አኳያ የራሴን ህይወትም መለወጥ እና ስለ ልጄና ስለ ባለቤቴም ማሰብ ስላለብኝ የመጪው ዘመን ቡድኔን በቅርቡ የማሳውቅ ነው የሚሆነው፡፡


ሊግ፡- ከአንተ የእግር ኳስ ህይወት ጀርባ እነማን አሉ(
ቡልቻ፡- ቤተሰቦቼ እና ባለቤቴ እንደዚሁም ደግሞ ከልጅነቴ ጀምሮ ያሰለጠኑኝ አሰልጣኞች እና ሌሎች ስማቸውን ጠቅሼ የማልጨርሳቸው በርካታ ሰዎች አሉ፡
ሊግ፡- ባለቤትህን በሚመለከት ስለ እሷ ምን የምትለው ነገር አለ( የልጅ አባትስ ሆነሃል(
ቡልቻ፡- ባለቤቴ እየሩሳሌም ስዩም ትባላለች ፤ በፍቅር ለአምስት ዓመታት ያህል አብረን ቆይተናል፤ ከዛ ውጪም በመስከረም ወር ላይም ልንጋባ ችለናል፤ እሷ ማለት ለኳሱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሴ ትልቅ አስተዋፅኦን ያደረገችልኝ ነች፡፡ የልጅ አባት ነህ ላልከኝ አዎን፤
ኤምራኬል ቡልቻ ትባላለች ገና የወራት ዕድሜን ያስቆጠረችም ናት፡፡

ሊግ፡- በቤተሰቦችህ ዘንድ በእግር ኳሱ እዚህ ደረጃ ላይ ትደርሳለህ ብለህ ጠብቀውህ ነበር(
ቡልቻ፡- አልተጠበቅኩም፤ እነሱ እንድማር ነበር የሚፈልጉት፤ በኋላ ላይ ግን ከዘጠነኛ ክፍል በኋላ ለኳሱ የነበረኝ ፍቅር ነው በራሴ ፍላጎት ወደ ተጨዋችነቱ ላመራ የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ማንን ነው ተምሳሌት አድርገህ የመጣከው(
ቡልቻ፡- ከሀገር ውስጥ ሳላህዲን ሰይድን፤ እሱ የተሻለ አጥቂም ነው፤ በጣም ነው የምወደው፤ ከውጪ ደግሞ ክርስቲያኖ ሮናልዶን፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት የመጨረሻው ግብህ ምንድን ነው?
ቡልቻ፡- በመጀመሪያ ከሀገር በላይ ምንም ነገር የለም፤ ስለዚህም በእዛ ደረጃ ሄጄ መጫወትን እፈልጋለው፡፡ የተሻለ የሀገሪቱ ተጨዋችም መባልንና የኮከብ ግብ አግቢነትን የግብ ሪከርዶችንም መስበርም ነው የምፈልገው፡፡ እነዚህን ካሳከው ደግሞ የውጪ እድሎች ይመጡልኛል፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ የታዳጊ፣ የወጣት፣ የኦሎምፒክ እና የዋናው ብሄራዊ ቡድን ደረጃ ከዚህ ቀደም የመመረጥ እድሉን አግኝተሃል?
ቡልቻ፡- በአሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ ዘመን የተመረጥኩበት አጋጣሚ ነበር፤ ያኔም ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ለሆኑት ቡድን ነበር የተመረጥኩት፤ ከደደቢት ጋር ባደረግነው ጨዋታ ላይም ነበር ጥሩ መንቀሳቀሴን ተመልክተው እኔን ሊመርጡኝ የቻሉት፤ ያም ሆኖ ግን ለቡድኑ ከተመረጥኩ በኋላ የተሰራልኝ ፓስፖርት ዕድሜዬን ያሳለፈ ስለነበር ልመለስ ችያለው፤ ከዛ ውጪም አንድ ጊዜ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱም ቡድኑን ተረክቦ በነበረበት ሰዓት ልመረጥ ብችልም አሁንም በድጋሚ በፓስፖርት ችግር ልመለስ ችያለው፡፡
ሊግ፡- አብዛኛዎቻችን በሜዳ ላይ ስንመለከት ያለህ ተክለ ሰውነት ጥሩ የሚባል ነው፤ ይሄ የመጣው ከተፈጥሮ ነው ወይንስ ከስራ?
ቡልቻ፡- ከስራ ነው፤ በአዳማ ከተማ የተተኪ ቡድን ውስጥ እያለው በጣም እሰራ ነበር፤ በግሌ ጥሩ ትንፋሽ እንዲኖረኝ ብዙ እሮጣለው፤ ከዛ ውጪ ጂም ጭምርንም እለማመድም ነበርና የስራ ውጤቶችም ናቸው ሰውነቴን እንዳዳብር ያደረገኝ፡፡
ሊግ፡- ኮቪድ 19 ብዙዎችን ከሜዳ አርቋል፤ ያ መሆን መቻሉ በአንተ እና በቤተሰቦችህ ዘንድ ምን ነገሮችን ፈጥሮባችኋል?
ቡልቻ፡- እኔ ጤነኛ ካልሆንኩ የተሸለ ነገር አልሰራም ራስህን ከእንዲህ ነገ እንደምንመለስ እርግጠኛ ነኝ፤ ቤተሰቦቼም ራሰሳቸውን ተብቀዋል፤ ሰፈር ውስጥ ነው ጊዜን የምናሳልፈው፡፡
ሊግ፡- አዳማ ከተማ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለአንዴም ለማንሳት አልቻለም፤ ያኔ ምን አይነት ስሜት ነው በውስጥህ ሊፈጠርብህ የቻለው?
ቡልቻ፡- በጣም ነው የተበሳጨሁት በተለይ ደግሞ 2010 ላይ፤ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ላለማንሳትቻን የተጨዋች ችግር ወይንም የአመራር ችግር አይደለም፤ አንድ ቡድን የራሱ የሆነ መዋቅር አለው፤ ደጋፊውም ከጎን ሆነ እያገዘን ሳለ አንድ አንድ አመራሮች ናቸው ከጎናችን ስላልነበሩ ውጤትን ልናጣ የቻልነው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ በጣም የቅርብ ጓደኛ ማን ነው( እሱን እንዴትስ ነው የምትገልፀው(
ቡልቻ፡- ጓደኛዬ በረከት ደስታ ነው፤ ጥሩ ተጨዋች ነው እንደወንድምም እንተያያለን፤ እንደማመጣለን፤ በረከት በተጨዋችነቱ ምርጥ የሀገሪቱ ተጨዋች ነው፤ አንድ አንድ ተጨዋች በጣም የሚታይ እና የማይታይ ችሎታ ቢኖረውም፤ እሱ ግን ጓደኛዬ ስለሆነ ሳይሆን እንደ አንድ ጥሩ ተመልካች ስመለከተው ሙሉ የሆነ ተጨዋች ነው፡፡

https://t.me/Leaguesport
spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P