Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለኢት. ቡና ከፍተኛ ጥቅም ልሰጥ የምችለው በተከላካይ ስፍራ ሳይሆን በመሀል ሜዳው ላይ ስጫወት ነው” አስራት ቶንጆ (ኢት.ቡና)


ኢትዮጵያ ቡናን ከሶስት ዓመት በፊት የተቀላቀለው አስራት ቶንጆ በእስካሁኑ የክለቡ ቆይታው በተለያዩ ስፍራዎች ላይ ከሚጫወት ይልቅ በመሀል ሜዳ ላይ ብቻ ቢጫወት ቡድኑን በጣም እንደሚጠቅምና ውጤታማም እንደሚያደርገው ለዝግጅት ክፍላችን አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከተጨዋቹ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ላይም ቆይታን ያደረገ ሲሆን፤ የተጨዋቹ ምላሽም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡


ሊግ፡- በኮቪድ 19 ለአምስት ወራት ከሜዳ ርቅሃል፤ ይህን ተንተርሶ በአንተ እና በቤተሰቦችህ አካባቢ የተመለከትካቸው አንኳር ነገሮች ምን ምን ናቸው?
አስራት፡- በእዚህ ዙሪያ ሁለት አይነት ነገሮችን መጥቀስ እፈልጋለው፤ የመጀመሪያው ከዚህ በፊት ከቤተሰቦቼ ጋር ለረጅም ጊዜያት አብሬያቸው እና ተገናኝቼያቸው አላውቅም ነበርና አሁን ላይ ወቅቱን ከእነሱ ጋር እያሳለፍኩ ነው፤ ሌላው ከዛ ውጪ ያለው ደግሞ በቤት ውስጥ በመወሰን በምታሳልፍበት ሰዓት ስራ ካልሰራህ በምንም ነገር ደስተኛ እንደማትሆንና ስራዬንም በአግባቡ መስራት እንዳለብኝም ነው የተመለከትኩት፤ ይህም ማለት የእግር ኳስን ሳትጫወት ዝም ብሎ ወርሃዊ ደመወዝ ሲከፈልህ ማየት ደስታን የማይሰጥህ መሆኑም ነውና ያ አይነት ስሜትም እየተሰማኝ ይገኛል፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ለረጅም ጊዜያት ከኳሱ የራቅክበት አጋጣሚዎች አለ?
አስራት፡- በፍፁም የለም፤ የአሁኑም የመጀመሪያዬ ነው፤ ከዚህ በፊት ውድድር ከጨረስን በኋላ በእረፍት ጊዜዬ ከኳሱ ርቅ የነበረው ወይ ለአንድ ወር አልያም ደግሞ ወር ከአስራ አምስት ቀን ነው፤ የአሁኑ ግን ኮቪድ በሀገራችን እየተስፋፋ ስለሆነና ወደ ውጪ ወጥተህም የእግር ኳሱን ከጓደኞችህ ጋር የምትጫወትበት አጋጣሚው ስለሌለህና ኳስን ሳትጫወት ስፖርትን ብቻ መስራቱ ደግሞ ብዙም ስሜት ስለማይሰጥ ከቤት ሳልወጣ ነው አስቸጋሪ የሆነውን ወቅት እያሳለፍኩ የምገኘው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳሱን አለመጫወት እና ስፖርትን ብቻ መስራት መቻል አሁን ላይ ስሜትን አይሰጥም ብለሃል፤ በጉዳዩ ዙሪያ አንድ ነገር ብትል?
አስራት፡- የእግር ኳስን ሳትጫወት ስፖርትን መስራት እና መሮጥ ብቻ ምንም አይነት ትርጉም እና ስሜትንም አይሰጥም ያልኩት በአካባቢያችን ሰበታ ከተማ ተፈጥሮ በነበሩት ችግሮች እና እዛም ቦታ ላይ በቅርበት የማገኛቸው ብዙም ኳስን የሚጫወቱ ተጨዋቾችም ስለሌሉ ነው ኳስን ሳትጫወት ስሜትን ማግኘት ከባድነቱን ልናገር የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና የተጨዋችነት ቆይታህ ደስተኛ ሆነህ ነው የኳስ ጊዜያቶችህን እያሳለፍክ የምትገኘው?
አስራት፡- አሁን ካለኝ የሜዳ ላይ ብቃት እና አቅም አንፃር ደስተኛ ነኝ ማለት አልችልም፤ ምክንያቱ ደግሞ ቡና በፈለገው መልኩ እያጫወተኝ እንጂ እኔ በምፈልገው መልኩ እየተጫወትኩ ስላልሆንኩ ነው፤ ያም ሆኖ ግን በክለቡ ቆይታዬ ከመጫወቻ ቦታ ጋር በተያያዘ ደስተኛ ባልሆንም በተባልኩት እና በታዘዝኩት መልኩ ግን አቅሜ በሚፈቅደው መልኩ ሁሉ ለክለቤ ጥሩ ግልጋሎትን እያበረከትኩ ስለሆነ ይሄንም መጥቀስ ነው የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና የእስካሁን ቆይታህ በምፈልገው መልኩ እየተጫወትኩ አይደለውም፤ በዛም ደስተኛ ልሆን አልቻልኩም ስትል በክለቡ በምን አይነት ሁኔታ ነው መጫወትን የምትፈልገው?
አስራት፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና ካመራሁበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም አሰልጣኝ የተለያየ ቦታ ላይ ነው የተጫወትኩት፤ ክለቡ በፈለገው መልኩም ነው ሲያጫውተኝ የነበረው፤ እኔ ደግሞ ከልጅነቴ ዕድሜ ጀምሮና ሌሎች ክለቦች ውስጥም ስገባ በመሀል ሜዳው ላይ ነው ለመጫወት የቻልኩት፤ በቡና ቆይታዬ ግን አብዛኛውን ጊዜ በመስመር ተጨዋችነት /ፉልባክ/ ላይና በተከላካይ ስፍራው /ስቶፐር/ ላይ ሆኜ የተጫወትኩባቸው አጋጣሚዎች በዝተዋልና ለእዚህ ቡድን መጫወት የምፈልገው እና ክለቡንም በጣም ልጠቅም የምችለው በመሀል ሜዳው ላይ ለመጫወት ስችል እና ለእኔም ምቾት በሚሰጠኝ መልኩም ቡድኑን ባገለግለው ነው ዋንኛ ምርጫዬ መሆኑን ለመናገር የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና የመሀል ሜዳ ተጨዋች ሆነህም እኮ ክለቡን ያገለገልክበትም ወቅት አለ….?
አስራት፡- አዎን፤ ለተወሰነ ጨዋታ ስለሆነ እንጂ እሱንማ አልክድም፤ በዛ መልኩ ስጫወትም ለጓደኞቼ ጥሩ የግብ ኳስን ከማቀበል በተጨማሪ ራሴም የተቃራኒ ቡድን ተጨዋቾችን ባለኝ የግል ችሎታ አብዶ ሰርቼ /ፔኔትሬት/ አድርጌ ጎል ያስቆጠርኩበት አጋጣሚም አለና ያን ፈፅሞ አልረሳውም፤ ለዛም ነው ለቡና አሁን ላይ በመስመር የተከላካይ ስፍራው ከምጫወት ይልቅ በመሀል ሜዳው ላይ ብጫወት ክለቡን በከፍተኛ ሁኔታ እጠቅመዋለው እያልኩ ያለሁት፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና በተጫወትክባቸው ጊዜያቶች የመሀል ሜዳው ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን ያሳየክባቸው ጨዋታዎች የትኞቹ ናቸው?
አስራት፡- አንዴ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ስንጫወት ነው፤ ሌላው ደግሞ ከባህር ዳር ከተማ ጋር በተጫወትንበት እና በእነሱም ላይ ከፍተኛ ግብ አስቆጥረን ባሸነፍንበት ጨዋታ ሲሆን ከእነዛ በተጨማሪም በሌሎች ጥቂት ግጥሚያዎችም ላይ ጥሩ ልንቀሳቀስ በቅቻለው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና ያለቦታህ መጫወትህን ተከትሎ ከአሰልጣኛችሁ ካሳዬ አራጌ ጋር የተነጋገርክበት አጋጣሚስ አለ?
አስራት፡- አዎን፤ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ክለቡን በእዚህ ዓመት እንደመረከቡ በጉዳዩ ዙሪያ አውርተንበታል፤ ያን ብናወራም እኔ በምጫወትበት የተከላካይ ስፍራው ላይ ግን እጫወታለው ብዬ ፈፅሞ አልጠበቅኩም ነበር፤ ምክንያቱም የካቻምናው ውድድር ወደ መጠናቀቁ ሲቃረብ ለክለቤ በመሀል ሜዳው ላይ ገብቼ እየተጫወትኩ ጥሩ ስንቀሳቀስ ነበር፤ ጎልም አስቆጥሬ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን አሰልጣኙ በፈለገው ስፍራ ላይ ሊያጫውተኝ በመፈለጉና እኔም እንደ እግር ኳስ ተጨዋች ያለኝ አማራጭ እሱን መረዳትም በመሆኑ የሚሉኝን ነገር በመስማት እና ስራዬንም ጠንክሬ በመስራት ልጫወት ችያለው፤ አሰልጣኝ ካሳዬ እኔ ልጫወት በማልፈልግበት ስፍራ ላይ ሊያጫውተኝ የቻለው ከዚህ በፊት የነበሩ ጨዋታዎቼን ስላልተመለከተ እና ወይንም ደግሞ አስራት የሚጫወተው በእዚህ ቦታ ላይ ነው የሚል መረጃዎች ተነግሮት ሊሆን ይችላል፤ ያም ሆኖ ግን በቦታው ላይ እኔ ጥሩ ስለተንቀሳቀስኩና በዛ ቦታ ላይ ሌላ አማራጭ ተጨዋች ስላልነበረው በዛ መልኩ እያጫወተኝ ይገኛል፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ከመጫወት ውጪ የተለየ የሚባል የጊዜ ማሳለፊያ እና የመደሰቻ መዋያ ቦታዎች አለ?
አስራት፡- አዎን፤ ብዙ ጊዜ ከቤቴ አልወጣምና እዛ ነው የሚያዝናኑኝንና የሚያስተምሩኝን ፊልሞች የምመለከተው፤ መፅሀፍትንም አነባለው፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ቤተክርስቲያን በመሄድም ፀሎቴን ለፈጣሪ የማደርስበት የመዋያ ፕሮግራሞች አሉኝና እነዛ ነገሮች ናቸው እኔን የሚያስደስቱኝ፡፡
ሊግ፡- በቤተሰባችሁ ስፖርተኛው አንተ ብቻ መሰልከኝ?
አስራት፡- አልተሳሳትክም፤ የቤቱ ኳስ ተጨዋች እኔ ብቻ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ አንድ አንድ ተጨዋቾች ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት መቻልን ብቻ የመጨረሻ ግባቸው ያደርጉታል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ? የአንተ የመድረሻ ግብህስ የት ድረስ ሄዶ መጫወት ነው?
አስራት፡- አንድ አንድ ተጨዋቾች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ተጨዋቾች ናቸው በርካታ ደጋፊዎች ላላቸው እና በስታድየም ውስጥም በእነሱ ፊት ታጅቦ ኳስን መጫወት መቻል የተለየ አይነት የደስታ ስሜትን ስለሚሰጥ ያንን ታሳቢ በማድረግ ነው ወደ ሁለቱ ክለቦች ብቻ ገብቶ በመጫወት የኳሱ የመጨረሻ ግባቸውን የሚያደርጉትና እንደ አንድ እግር ኳስ ተጨዋች ግን እነዚህ ተጨዋቾች ከዚህ ስሜት ሊወጡና ራሳቸውን በኳሱ ትልቅ ደረጃ ላይ ለማድረስ ወደ ባህር ማዶም በመሄድ በፕሮፌሽናል ኳስ ተጨዋችነት ሊጫወቱ የሚችሉበትን እድል ሊፈጥሩ ነው የሚገባቸው፤ ወደ ሌላው ጥያቄ ሳመራ የአንተስ ግብና እልምህ ለተባልኩት በፈጣሪ ፈቃድ ከአሁን በበለጠ በምታውቅበት የመሀል ሜዳው ላይ በመጫወት እና የተሻለም የሀገሪቷ ተጨዋች በመባልና ለብሔራዊ ቡድንም ደረጃ በመመረጥ የኳስ ደረጃዬን አሳድጌ እና የሀገሬንም ስም በማስጠራት ወደ ውጪ ወጥቼ መጫወትንም ነው የማልመው፡፡
ሊግ፡- ለብሔራዊ ቡድን የመመረጥ እድሉን አግኝተህ ታውቃለህ?
አስራት፡- አዎን፤ ባለፈው ምርጫ ተጠርቼ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን የተመረጥኩት በተከላካይ ስፍራው /ስቶፐር/ ላይ በመሆኑ ያን ሳውቅ በጣም ገርሞኝም ነበር፡፡
ሊግ፡- ለምንድን ነው የተገረምከው?
አስራት፡- በኳሱ ብዙ የምታወቀው የመሀል ሜዳው ላይ ሆኜ ስጫወት ነው፤ እኔ ለብሔራዊ ቡድን የተጠራሁት ግን በተከላካይ ስፍራው ላይ ሆኜ ስጫወት ብቻ አሰልጣኙ ስለተመለከተኝ ነውና ያ ነው በውስጤ ጥያቄ እና አግራሞትን ሊፈጥርብኝ የቻለው፤ ያም ሆኖ ግን ቀደም ሲል በተጨዋትኩበት የመሀል ሜዳው ቦታ ላይ ለመጠራት ብችል ለሀገሬም ጥሩ ጥቅምንና ግልጋሎትን እንደምሰጥ በጣሙን እርግጠኛ ነው ለመሆን የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነት እንድታመራ የጥርጊያ መንገዱን የከፈተልህ ሁኔታ ምን ነበር?
አስራት፡- ለእኔ ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነት መምጣት የመጀመሪያው ዋንኛ ምክንያት የሆነኝ 2006 ላይ በዓለም ገና አካባቢ ተዘጋጅቶ የነበረው የፉትሳል ውድድር ነው፤ ያኔ እዛ ስጫወት ቡድናችን የውድድሩ አሸናፊ እንዲሆን ትልቁን አስተዋፅኦ ከማበርከቴ ባሻገር በኮከብ ተጨዋችነትም ስለ ተሸለምኩ በዛ ታይቼ ነው አንተማ ለሰበታ ከተማ ገብተህ መጫወት አለብህ በሚል አዘጋጅ አካሎቹ ገፋፍተውኝ እና ለቡድኑም እንድሞክር ቢያደርጉኝም ያለ ኦርጅናል ትሴራ እንዴት ለክለቡ ሊጫወት ይችላል በሚል አንድ አንድ ሰዎች ሊቃወሙኝ ቢችሉም ባሳየሁት ጥሩ ብቃት ግን የቡድኑ ደጋፊዎች መፈረም አለበት ብለው ቢከራከሩም ይሄ ወደ ቡድኑ እንዳላመራ አድርጎኝ ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ለኦሮሚያ ሻምፒዮና ሰበታ ከተማን ወክዬ በሄድኩበት ሰዓት እና ቀጥሎም ለመላው ኢትዮጵያ ጨዋታም ኦሮሚያን ወክዬ በምጫወትበት ሰዓት ከዛ በኋላ ነው ሰበታ ከተማ ከፍተኛ ፍላጎት አሳድሮ ቡድኑን ልቀላቀል የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- ሰበታ ከተማን በተቀላቀልክበት ሰዓት በቡድኑ ውስጥ የነበረህ ቆይታ ምን ይመስል ነበር?
አስራት፡- በሰበታ ከተማ የነበረኝ የሁለት ዓመት ቆይታ የመጀመሪያው ዓመት ላይ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ሆኜ ለክለቡ በስድስት ጨዋታዎች አራት ግቦችን ለማስቆጠር ችዬ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን በጊዜው የደረሰብኝ የጉልበት ጉዳት ቡድኑን በምፈልገው መልኩ እንዳላገለግለው አድርጎኛል፤ ያኔ በእኔ ላይ የደረሰው ጉዳት እስከ ቀዶ ጥገና /ሰርጀሪ/ የሚያደርስ እንደሆነ ሊነገረኝ ቢችልም በእምነት እና በፀበል ድኜ ዳግም ወደ ቡድኑ ተጨዋችነት የተመለስኩበት ወቅት ነበርና በእዚህ መልኩ ነው ክለቡ ውስጥ ተጫውቼ ያሳለፍኩት፡፡
ሊግ፡- ወደ ጅማ አባጅፋርም አምርተህ ነበር፤ እዛስ የነበረ ቆይታ?
አስራት፡- ከሰበታ ከተማ ተጨዋችነቴ በኋላ ቀጥዬ ያመራሁበት ክለብ ጅማ አባጅፋር ነበር፤ እዛም በነበረኝ ቆይታ ለቡድኑ ጥሩ ከመጫወት ባሻገር ክለቡንም ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ ያደረግንበት ወቅት ስለነበር ቆይታዬን ወድጄዋለው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ አሁን ላይ ባለህ ችሎታ እና ብቃት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነው የምገኘው ብለህ ታስባለህ? በኳስ ህይወትህስ ደስተኛ ነህ?
አስራት፡- በኳሱ አሁን ከደረስኩበት ስፍራ እና ብዙ አሰልጣኞችም ችሎታዬን አድንቀው ከሚነግሩኝ ነገር በመነሳት በዚህ ሰዓት የምገኝበትን ደረጃ እኔ ገና ነኝ ብዬ ነው የማስበው፤ ያን ለማለት የፈለግኩትም በቡና ቆይታዬ አሰልጣኞች እኔን ከመሀል ሜዳ ተጨዋችነት ይልቅ በመስመር ላይና በተከላካይ ስፍራው ላይ ስላጫወቱኝ ችሎታዬ ከዚህ በፊት ከነበረው አኳያ ወርዷል ብዬ ስለማስብ ነው፤ ሆኖም ግን በቀጣዩ ጊዜ ፈጣሪ ፈቅዶ በመሀል ሜዳ ላይ ብጫወት ብዙ ነገርን ለክለቡ እንደምሰራ እርግጠኛ ነኝ፤ ያኔም ነው ከዚህ በፊት ስጫወትበት እና ደስተኛም ሆኜ ወደ ቆየሁበት የመሀል ሜዳ ተጨዋችነቴ ስመለስ በቡና በጣም ደስተኛ የምሆነው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ከተመለከትካቸው ተጨዋቾች የአንተ ምርጡ ማን ነው?
አስራት፡- ብዙ ተጨዋቾች አሉ፤ ሆኖም ግን አስቻለው ታመነ ለእኔ በጣም ምርጡ ተጨዋች ነው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና ስትጫወት ለአንተ ምቾት የሰጠህ ተጨዋች ማን ነው?
አስራት፡- ሁሉም፤ ምክንያቱም በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ አጨዋወት ውስጥ የሚፈለገው የህብረት ስራን እንድትሰራ እንጂ አንድ ሰው ተነጥሎ የሚወጣበት ነገር ስለሌለ ነው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና የሊጉን ዋንጫ መቼ ወደ ቡድኑ ማምጣት ይችላል?
አስራት፡- ያን ለማሳካት አሰልጣኙ ይዞ የመጣው የጨዋታ ፍልስፍና ጥሩ ሆኖ ሳለ ምርጥ እና የተሻለ የተጨዋቾች ስብስብ ሊኖረው ይገባል፤ በተለይ ደግሞ በቋሚነት የሚሰለፈው ተጨዋች ከሜዳ ተቀይሮ ሲወጣ ሌላው የሚገባውም ጥሩ ችሎታ ሊኖረው እና የእሱን ፍልስፍናም በደንብ አድርጎም በሜዳ ላይ ሊተገበር ይገባልና ያኔ ነው ውጤታማ ለመሆን የሚቻለው፡፡
ሊግ፡- የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ካለማንሳትህ አኳያ ድሉ አልናፈቀህም?
አስራት፡- ይናፍቃል እንጂ፤ በቡና ቆይታዬ ግን ይሄን ከዓመታት በፊት ለማሳካት ተቃርቤ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታ የአዲስ አበባ ስታድየም ጨቅይቶ መጫወት ሳይኖርብን ተጫውተን ነጥብ ልንጥልና ከዛ በኋላ ያለውን ጨዋታም ስለተሸነፍን ያ እልማችንን እንዳናሳካ እና የውድድር ዓመቱንም በሶስተኝነት ደረጃ እንድናጠናቅቅ አድርጎናል፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን ከሌሎች ክለቦች ምን ይለየዋል?
አስራት፡- ደጋፊውንና ቡድኑ ሊከተል የሚፈልገውን የአጨዋወት ሀሳቡን፤ ደጋፊውን በተመለከተ ኳስን አስተውሎ የሚመለከት እና በስሜት ሆኖም በመጨፈርና በማበረታታት ለክለቡ ውጤት ማምጣት ጥረት የሚያደርጉ ናቸው፤ አጨዋወትን በተመለከ ደግሞ የቡድኑ ተጨዋች ስትሆን ቢያንስ እንደዚህ ተጫወቱ ትባላለህ፤ ይህን የምልህ ለእኔ ነው፤ ከዚህ በፊት እግር ኳስን በዚህ መልኩ ተጫወቱ ተብለን ሳይሆን ዝም ብለን ወደ ሜዳ እንገባና ክሮስ ታደርጋለህ፤ የራስህን መንገድም ነው የምትከተለው፤ አሁን ግን እግር ኳስን በስርዓት እንድትጫወት የሚያደርግ ባለሙያ ስላለ ቡናን ይሄ ይለየዋል፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ….?
አስራት፡- ቤተሰቦቼ በኳሱ ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ስፍራ ያደረጉልኝ አስተዋፅኦ ከፍ ያለ ነውና እነሱን እንዴት አድርጌ እንደማመሰግናቸው አላውቅም፤ በተለይ ደግሞ እናቴ ትጥቆችን እና ጫማዎችን በመግዛት ከዛም ውጪ የትራንስፖርት ብርም በመስጠት ለእኔ ስትል ብዙ መስዋትነትን ከፍላለችና ልትመሰገንልኝ ይገባል፡፡ ሌላው ኮቪድ 19 ወደ አገራችን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ሰዎችን በሞት አሳጥቶናል፤ ይሄ ወረርሽኝ ይጠፋል፤ ሊጨምርም ይችላል፤ ከዛ ውጪም የሊጉ ውድድር ላይካሄድም ይችላል በሚል ብዙ እየተባለ ባለበት የአሁን ሰዓት ላይ ፈጣሪ አምላካችን በቸርነቱ አገራችንን እንዲጎበኛትና በሽታውን እንዲያጠፋላት ከዛም ውጪ እግር ኳሱ ወደነበረበት እንዲመለስ እና በሞት ቤተሰቦቻቸውን ላጡ አካላትም መፅናናትን እመኝላቸዋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P