Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በኢትዮጵያ ቡና ተጠባባቂ ተጨዋችነቴን አምኜ ተቀብዬ ነበር”
እያሱ ታምሩ /ኢትዮጵያ ቡና/

በመሸሻ_ወልዴ

እያሱ ታምሩ ኢትዮጵያ ቡናን በሰርቢያዊው አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች እና በረዳቱ አሰልጣኝ አንዋር ያሲን የኃላፊነት ዘመን ላይ ቡድኑንበተቀላቀለበት ወቅት ጥሩ እንቅስቃሴን በሜዳ ላይ አሳይቷል፤ በኳስ ብቃቱ እና በእለኸኛነት ተጨዋችነቱም በብዙዎቹ ደጋፊዎች እይታ ውስጥም ቶሎ ለመግባት ችሏል፤ እያሱ ታምሩ በቡና ክለብ ውስጥ በነበረው የእስከአሁኑ የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው ደስተኛ መሆኑን እየተናገረ ሲሆን በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ የኃላፊነት ዘመን ላይ ያጣውን በቋሚ ተሰላፊነት የመጫወት እድልን በዘንድሮ የውድድር ዘመን ለማግኘት ራሱን በሚገባ እያዘጋጀ መሆኑን ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል፡፡
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከኢትዮጵያ ቡናው አማካይ እያሱ ታምሩ ጋር ተጨዋቹ በክለቡ ውስጥ ስለነበረው ቆይታ፣ በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ቡድን ውስጥ በቋሚነት ስላለመጫወቱ፣ ለዘንድሮ የውድድር ዘመን በምን መልኩ እየተዘጋጁ እንደሆነ፣ ከእዚህ ዓመት የሊግ ውድድር ምን ውጤትን ለማምጣት እቅድን እንደያዙና ሌሎችንም ጥያቄዎች አካተን ጠይቀነዋል፤ እሱም ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቶናል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡናን የእስካሁን ቆይታህ እንዴት ትገልፀዋለህ?
እያሱ፡-በክለቡ ውስጥ ስቆይ አሁን ላይ አምስተኛ ዓመቴን ይዣለሁ፤ በእዚህ ትልቅ ቡድን ውስጥም ገብቼ በመጫወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ በቡና በነበረኝ የእስካሁን ቆይታ በተደጋጋሚ ጊዜ የመሰለፍ እድልን አግኝቼ ለመጫወት ችያለሁ፤ ካለፈው ዓመት አንስቶ ደግሞ ውድድሩ በኮቪድ ወረርሽኝ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ በቋሚነት ያልተሰለፍኩባቸው ጊዜያት በርካታዎች የነበሩ ቢሆንም አሁንም ራሴን ወደ ጥሩ ብቃት ላይ አምጥቼ ለቡና በዘንድሮ የውድድር ዘመን ቆይታዬ ላይ በቋሚ ተሰላፊነት ገብቼ ለመጫወት እና ክለቤንም በጣም ለመጥቀም እየተዘጋጀው ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከመምጣትህ በፊት ለማን ለማን ቡድኖች ተጫውተህ አሳለፍክ፤ ልጅ በነበርክበት ሰዓትስ ስለ ኢትዮጵያ ቡና የምታውቀው ነገር ነበር?
እያሱ፡-ያኔ ልጅ ስለነበርኩ ስለ ቡናም ሆነ ስለሌሎች የሀገራችን ትላልቅ ቡድኖች ምንም የማውቀው ነገር አልነበረኝም፤ ከዛ ይልቅ እኔ አውቅ የነበረው ለእኛ በጣም ቅርባችን ስለነበረው እና ተወልደን ባደግንበት ወሊሶ ከተማ ውስጥ ስላሉት የነጋዴ እና የኮከብ ቡድኖች ነበር፤ ትንሽ አደግ ካልን በኋላ ግን ስለ ቡናም ሆነ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድኖች በደንብ ልናውቅ ቻልን፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ከመቀላቀሌ በፊት በተጨዋችነት እኔ ያሳለፍኩባቸው ቡድኖች ልጅ ሳለሁ በመጀመሪያ ለነቀምት ከተማ ነው፤ ከዛም ለወሊሶ ከተማ በኋላ ደግሞ ለሀላባ ከተማ ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ ገብተህ በመጫወትህ ምን ያስገኘልህ ጥቅም አለ?
እያሱ፡-ወደ ክለቡ ገብቼ ስጫወት ያገኘሁት ጥቅም ብዙ ነው፤ የመጀመሪያውም በእዚህ ታላቅ ቡድን ውስጥ ገብቼ በመጫወቴ ከፍተኛ እውቅናን፣ ዝናን በመቀጠል ደግሞ የደጋፊውን አድናቆት እና ፍቅርን ላገኝ ችያለሁ፤ ከዛ ውጪም በእንደዚህ ባለ ቡድን ውስጥ ኳስን ስትጫወትምበቋሚ ተሰላፊነት ወደ ሜዳ ገብቶ ለመጫወትም የፉክክር አይነት ስሜት ያለ እና በበርካታ ደጋፊዎች ፊትም ታጅበህ የምትጫወትበትንም እድል ታገኛለህና በእዛ ውስጥ እኔ እያለፍኩ በመሆኔ የተለየ አይነት ስሜትን ነው እየፈጠረልኝ ያለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና የተጨዋችነት ቆይታህ ላይ ቀደም ሲል በቋሚ ተሰላፊነት ትጫወት ነበር፤ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደ ቡድኑ ከመጣ በኋላ ግን የመሰለፍ እድሎችን ብዙ ለማግኘት አልቻልክም፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? ብዙ ባለመጫወትክስ ተከፍተሃል?
እያሱ፡-የእግር ኳስ ተጨዋች ስትሆን የለመድከውን የመሰለፍ እድሎችን ስታጣ መጀመሪያ ላይ ይከፈሃል፤ ምክንያቱም ማንኛውም ተጨዋች ሁሌም ቢሆን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ መጫወትን ይፈልጋልና ይሄ ደግሞ በእግር ኳሱ ዓለም ላይ ያለና የሚኖር ስለሆነ የግድ አምነህ ልትቀበለው ይገባል፤ በቡና ቆይታዬ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ከመምጣቱ በፊት በቋሚ ተሰላፊነት እጫወት ነበር፤ እሱ ሲመጣ ደግሞ የራሱ የሆነ የጨዋታ ፍልስፍና ስለነበረውና ያን የአሰልጣኝ ውሳኔን ደግሞ የግድ መቀበል ስለነበረብኝ ተሰልፌ ልጫወት አልቻልኩም፤ ለቡና መጀመሪያ ላይ ባለመጫወቴ ከፍቶኝ ነበር፤ ከጊዜ በኋላ ግን በኢትዮጵያ ቡና ተጠባባቂ ተጨዋችነቴን አሰልጣኙ እና ቡድኑ ከሚከተለውየአጨዋወት እንቅስቃሴ በመነሳት በቋሚ ተጨዋችነት አለመሰለፌን አምኜና ተቀብዬው ነበር፤ ለምንድነውስ? የማልሰለፈው በሚል አይነትም የቁጭት ስሜት ራሴን ለቡድኑ ብቁ አድርጌ ለማዘጋጀትም ሁሌም ጥረትን ሳደርግም ነበር፡፡
ሊግ፡-ባሳለፍነው ዓመት የውድድር ቆይታ ለቡና ሳትሰለፍ ስትቀር ለአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ለምንድን ነው የማልሰለፈው? የማልሰለፍበት ችግሬስ ምንድን ነው ብለህ ጠይቀኸው ታውቃለህ?
እያሱ፡-አዎን፤ በኢትዮጵያ ቡና ውስጥ ከአሰልጣኛችን ካሳዬ አራጌ ጋር ካለን ጥሩ ቅርርብ እና የመነጋገር ነፃነት አኳያም አይደለም ሳትሰለፍ ቀርተህ እየተሰልፈክም ቢሆን ያልገባህ ነገር ካለ እንደዚሁም ደግሞ ተሰልፈህ ለመጫወት ፈልገህ ቅሬታ ካለህም አሰልጣኝህን ትጠይቃለህ፤ አሰልጣኙ ጥሩ ከመሆኑ አንፃር እሱን ለመጠየቅ ምንም የሚያስፈራምነገር የለም፤ ከእዚህ በፊት በእኛ ሀገር ላይ የተለመደው ሳትጫወት ስትቀር ነበር ጥያቄን የምትጠይቀው፤ አሁን ተሰልፈህም አሰልጣኝ የመጠየቅ ልምድ ስለተፈጠረ ይሄ መቀጠል ነው ያለበት፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በታህሳስ ወር ላይ ይጀመራል፤ ለውድድሩ ራስህን በምን መልኩ እያዘጋጀከው ነው?
እያሱ፡-ያለፈው ዓመት ውድድር በአጋጣሚ በኮቪድ ተቋረጠ እንጂ ከእዚያን ጊዜ አንስቶ ነው ለዘንድሮ የውድድር ዘመን ራሴን በሚገባ እያዘጋጀሁት ያለሁት፤ ለኢትዮጵያ ቡና ባሳለፍነው ዓመት ብዙ የመጫወት እድልን አላገኘሁም ነበር፤ በእዚህ ዓመት ግን ይሄ እድል እንዲያመልጠኝ አልፈልግምና ለዛም ነው በበቂ ሁኔታ እንደግልም እንደ ቡድንም ለቡድኔ ጥሩ ለመጫወት እና ክለቤንም በውጤት ለመጥቀም እየተዘጋጀው የምገኘው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡናውን አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን በምን መልኩ ነው የምትገልፀው፤ የክለባችሁን አቋምስ እሱ ከያዘው ጊዜ ጀምሮስ በምን መልኩ አገኘኸው?
እያሱ፡- አሰልጣኙን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እንደተመለከትኩት ጥሩ ነው፤ የኳስ እውቀቱም ከፍተኛ ነው፤ የራሱ የሆነ አጨዋወትም አለው፤ ይሄ አጨዋወት ደግሞ ለቡና ባህሉ ጭምር ስለሆነም ነው ቡድኑ አሰልጣኙን ከአሜሪካ ሊያስመጣው የቻለውና ይሄ እንቅስቃሴ በክለቡ ውስጥ እንዲተገበር ነው በአሰልጣኙ እየተጣረ ያለውና ይሄን በእሱ ላይ ተረድቻለው፤ አሰልጣኙ ቡናን ከተረከበ በኋላ ሜዳ ላይ ስላለው የቡድኑ አቋም ደግሞ ይሄ ቡድን አዲስ ከመሆኑ አንፃርና አዳዲስ ተጨዋቾችንም በቡድኑ ውስጥ ከማካተቱ አኳያ ሲታይ ጅማሬው በጣም የሚያበረታታ እና ጥሩ ነው፤ ተስፋ ሰጪ ነገርም ይታይበታል፡፡ ትልቁ ነገር ቡድኑ የራሱ የሆነ አጨዋወት እንዲኖረው ማድረግ መቻል ነው፤ ከእዚህ በመነሳት ሌሎች ቡድኖችም የራሳቸው የሆነ አጨዋወት ቢኖራቸው ደስ ይለኛል፤ ለእግር ኳሱ እድገታችን ይሄበሁሉም ዘንድ ቢለመድም መልካም ነገርም ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮ የውድድር ዘመን በምን መልኩ ይቀርባል? ምን ውጤትንስ ለማምጣት ተዘጋጅቷል?
እያሱ፡-በፕሪምየር ሊጉ የአምናው ተሳትፎአችን በአዲስ አሰልጣኝ እና በአዲስ የጨዋታ ፍልስፍና እንደዚሁም ደግሞ በአዳዲስ ተጨዋቾችም የቀረብንበት ሁኔታ ስለነበር የቡድኑን የጨዋታ እንቅስቃሴ ለመረዳት ከመቸገር የተነሳ መጀመሪያ ላይ ነጥቦችን በመጣል የተቸገርንበት አጋጣሚ ነበር፤ ከዛ የቡድኑን አጨዋወት ወደመላመድ እያመራን ነበር፤ ከእዚህ በመነሳት ለዘንድሮ ቡድናችን እኛ ራሳችንን እያዘጋጀን ያለንበት ሁኔታ በጣም ጥሩ ነው፤ ቡና ለእዚህ ዓመት የሊግ ውድድሩ እየተዘጋጀ የሚገኘው ብዙ ተጨዋቾቹን ሳይለቅ ነው፤ በጨዋታ እንቅስቃሴ የተግባቡና አብረው የቆዩ ልጆቹም አሁንም በቡድኑ ውስጥ መኖራቸው ጥሩ ነው፤ ከዛ ባሻገር ጥቂት ቢሆኑም ቡድኑን ሊያጠናክሩ የመጡ ልጆችም አሉትና የእዚህ ዓመት ላይ ጥሩ ኳስን የሚጫወት እና የሊጉን ዋንጫ ሊያነሳ የሚችል ቡድንም ሜዳ ላይ ይዘን እንቀርባለን፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና የተጨዋቾች ስብስብ በአንተ እይታ ምርጥ የሚባል ነው?
እያሱ፡-አዎን፤ ምርጥ እና ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ ነው ያለን፤ በተለይ ደግሞ ክለባችን አንድ ላይ የቆዩ ልጆቹን በድጋሚ ሊያስቀጥል መቻሉም ሊያስደንቀው የሚገባው ነው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና ከክለቡ ነባር ተጨዋቾች ውስጥ የአራት ያህሉን ውል ለረጅም ጊዜ ኮንትራት በማስፈረም አራዝሟል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን አልክ?
እያሱ፡-ኢትዮጵያ ቡና ከእዚህ በፊት አዲስ ቡድንን ነበር በየዓመቱ የሚገነባው፤ አሁን ላይ ግን የክለቡን ተጨዋቾች ከማቆየት ባሻገር የረጅም ጊዜንም የኮንትራት ውል በማስፈረም እየተጓዘ ያለበት መንገድ ጥሩ እና ክለቡንም ለዋንጫ እንዲጫወትም የሚያደርገው በመሆኑ ይሄ እንደ ውጪ ሀገር ክለቦች በእኛ ሀገር ላይም ሊለመድ የሚገባው ነገር ነው፡፡
ሊግ፡- ከኢትዮጵያ ቡና ተለያይቶ የነበረው አማኑኤል ዩሃንስም ክለቡን መልሶ ለማገልገል ውሉን አድሷል፤ በእሱ ዙሪያስ ምን አልክ?
እያሱ፡- አማኑኤል የውል ጊዜውን ጨርሶ ከክለቡ ከተለያየ በኋላ በድጋሚ በመምጣት ለቡና ፊርማውን ለተጨማሪ አራት ዓመታት ሊያኖር በመቻሉ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ምክንያቱም ይሄ ተጨዋች ክለባችንን በጣም የሚጠቅም ነውና ከዛ ውጪ ለእኔም ደግሞ በጣም የቅርብ ጓደኛዬም ስለሆነ የእሱ መኖር በብዙ ነገሮች እንዳይደብረኝም ያደርገኛል፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ቡና ከመጫወትህ ውጪ አሁን ላይ ሌላ የምታስበው ነገር አለ?
እያሱ፡-አዎን፤ በእግር ኳስ ተጨዋችነቴብሔራዊ ቡድን ደረጃ ተመርጬ መጫወትን እና ራሴንም ማሳየት እፈልጋለው፤ ይሄን ማሳካቴ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ፤ አይቀሬ ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በዲ.ኤስ.ቲቪ ይተላለፋል፤ በእዚህ ዙሪያ ማለት የምትፈልገው ነገር ካለ?
እያሱ፡-የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች እንደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በዲ.ኤስ.ቲቪ ሊተላለፉ መሆናቸውን መስማት መቻላችን ለእግር ኳሳችን መልካም ዜናነው፤ከእዚህ ቀደምእኛ ይሄንን የማየት እድሉን አላገኘንም ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ከፍተኛ ተደራሽነት ባለው በእዚሁ ቻናል የሊግ ጨዋታዎቻችንን ልናይ መዘጋጀታችን ለሀገሪቱ እግር ኳስ እና ለተጨዋቾቻችንም እድገት የሚያበረክተው ትልቅ አስተዋፅኦ ስላለው አስደሳች ነገርን እየተመለከትን ነው፤ በተለይ ደግሞ የእነዚህ ጨዋታዎች መተላለፍ ከእዚህ በፊት ተጨዋቾቻችን ወደ ውጪ ወጥተው ለመጫወት እና የክለብ ሙከራን ለማድረግ ቪዲዮን አፈላልገው የሚልኩበትን ሁኔታ የሚያስቀርና በቀጥታም ጨዋታዎቹ ስለሚተላለፉም ያንን ፈላጊ ክለቦቹ እና የተጨዋቾች ወኪሎችም ስለሚያዩት ይሄ መሆን መቻሉ ለእኛ በጣም ጠቃሚው ነገር ነው፡፡
ሊግ፡-በኮቪድ ወረርሽኝ የእግር ኳሳችን ከተቋረጠበት ጊዜ አንስቶ የእረፍት ወቅትህን የት አሳለፍክ?
እያሱ፡-በአብዛኛው ረጅሙን ጊዜዬንከቤተሰቦቼ ጋር ነበር በተወለድኩበት የወሊሶ ከተማ ውስጥራሴን ለእዚህ ወረርሽኝ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ያሳለፍኩት፤ እዛ ስቆይም በተለይ ከታናናሽ ወንድሞቼ ጋር በመሆን ራሴን ለአዲሱ የውድድር ዘመን ማዘጋጀት ስለነበረብኝ ከእነሱ ጋር ልምምድን እሰራም ነበር፤ በግሌም ስዘጋጅ ቆይቻለው፡፡ ከዛ ውጪ ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር በመሆን እና እነሱን በማስተባበርም በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በመሰማራት ደም በመስጠት፣ አካባቢን በማፅዳት እና ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ ፕሮግራሞች ላይም ነበር የተሰማራሁት፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ ለወራቶች እድሜ ከኳሱ በራቅክበት ወቅት ምን አይነት ስሜት ነበር በውስጥህ የተፈጠረብህ?
እያሱ፡-መጀመሪያ ላይ ለእዚህን ያህል ጊዜ ከኳሱ እንርቃለን ብዬ ስላላሰብኩ ምንም ነገር አልመሰለኝም ነበር፤ ምክንያቱም ከእዚህ ቀደም ከኳስ መራቅ የተለመደው ቢበዛ ለአንድ ወር ነበርና ያንን ጊዜንም ቢሆን በሰፈር ውስጥ እየተጫወትክ የምታሳልፍበት ወቅት አለና፤ በኋላ ላይ ግን ረጅሙን ጊዜ በሰፈር ውስጥ ደረጃ እንኳን በማትጫወትበት ሁኔታ ያለ ኳስ ስናሳልፍ ከባድ ሁኔታዎች ነበር የገጠሙኝ፤ ዳግም ወደ ኳስ የምንመለስም አልመሰለኝም ነበር፤ ወደፊት ኳሱ ይኖር ይሆን እያልኩም አሰላስልም ነበርና ኳስ ከሌለ ምንም አይነት ነገር ስሜት ስለማይሰጥህ ለየት ያለ እና ከባድ ጊዜን ነበር ያሳለፍኩት፡፡
ሊግ፡- ከስድስት እና ከሰባት ወራቶች ቆይታ በኋላ ነበር ወደ ዝግጅት ውስጥ የገባችሁት፤ በዋናነት ናፍቆህ የነበረው ነገር ምን ነበር?
እያሱ፡-መጀመሪያ የናፈቀኝ እግር ኳስን እንደ ቡድን ተናኝተን ልምምድ መስራትና ኳስን መጫወት ነበር፤ ከዛ ደግሞ በቡና ደጋፊዎች ፊት ታጅበን መጫወትም ነውና ወደዛ ወደ ሁለቱ ሙሉ ለሙሉ ስንቃረብ ደስታዬ የበለጠ እጥፍ ድርብም ነው የሚሆነው፡፡
ሊግ፡-በኢትዮጵያ ቡና የፕሪ-ሲዝን ዝግጅት ለየት ያለ ነገርን ተመልክተሃል?
እያሱ፡-አዎን፤ይኸውም የዝግጅት ጊዜ ልምምዳችንን እየሰራን የምንገኘው እንደሌላው ጊዜ ራቅ ወዳለ ክልል እና ወይንም ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የመጫወቻ ስፍራዎች ላይ በመሄድ ሳይሆን እዛው በካምፓችን በሚገኘው ሜዳ ላይ ነው፤ ልምምድን ሰርተንም ከካምፕ አንወጣም፤ በፊት ግን ሻይ ቡና ለማለት እንወጣ ነበር፤ አሁን ግን ከኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ ግዴታ እና ራሳችንንም መጠበቅ ስለሚገባን ሁሉንም ነገር የምናከናውነው በካምፓችን ውስጥ ነው፤ ይሄ ነው የዘንድሮ ዝግጅታችንን ለየት የሚያደርገው፡፡
ሊግ፡- እንደ ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋችነትህ ወደ ትውልድ ክልልህ ወሊሶ ስታመራ የሚቀርቡልህ ጥያቄዎች አሉ?
እያሱ፡- አዎን፤ ለእረፍት ብዙ ጊዜ ስሄድ የሚያጋጥመኝ የማልያዎች ጥያቄ ነው፤ እኔ ከዛ ክልል ወጥቼ ለቡና በመጫወቴ የክለቡ ደጋፊዎች የሆኑ ሰዎች አሉ፤ ብዙ ጊዜ የቡናን ማልያ እንፈልጋለን አምጣልን ይሉኛል፤ ለእነሱ የወሰድኩላቸውም ጊዜ አለ፤ ለሁሉም ጠያቂዎች ግን ሁሌም ስለማትችል አንድአንዴ ሳልወስድላቸው የቀሩባቸውም ጊዜያቶች አጋጥመውኛል፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን በተወለድክበት ክልል ልጅ ሆነህ ስትጫወት አድንቀህ ወይንም ተምሳሌት ያደረግከው ተጨዋች አለ? ከውጪዎቹስ ማንን አድንቀህ አደግክ?
እያሱ፡- በወሊሶ ከተማ ውስጥ ያኔ ስጫወት ያደነቅኳቸው ብዙ ተጨዋቾች ነበሩ፤ ከሁሉም ግን ሞዴሌ /ተምሳሌቴ/ አድርጌው የነበረው ተጨዋች ኤፍሬም አስራትን ነው፤ በውጪ ሀገር ደረጃ ደግሞ ያደነቅኩት ተጨዋች የአርሰናል ደጋፊ ነበርኩና ሴስክ ፋብሪጋስን እና ቴሪ ዳንኤል ኤነሪን ነው ያደነቅኩት፡፡
ሊግ፡-በእግር ኳስ አብረህ ተጣምረሃቸው ስትጫወት ደስታን የሚሰጡህ ተጨዋቾች እነማን ናቸው?
እያሱ፡-በኢትዮጵያ ቡና የተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ አብሬያቸው ስጫወት ደስታን የሚሰጡኝ ተጨዋቾች አቡበከር ናስር፣ ሚኪያስ መኮንን እና አማኑኤል ዩሃንስ ሲሆኑ ከበፊት ተጨዋቾች ደግሞ መስዑድ መሐመድ ነው፤ በተለይ መስዑድ መሐመድ በሜዳ ላይ ብዙ ነገርን በመመሪያ ደረጃ መልዕክት በማስተላለፍ ጥሩ ነገር እንድታደርግ እና በችሎታህ ላይም መሻሻል እንድታሳይ ይመክርሃልና እነዚህን ተጨዋቾች ነው የምጠቅሰው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ አብረሃቸው በመጣመር ለመጫወት የምትፈልጋቸው ተጨዋቾችስ?
እያሱ፡-ከሙሉዓለም ረጋሳ እና ከዳዊት እስጢፋኖስ ጋር፤ ሙሉዓለምን በተመለከተ ኳስ በማቆሙ የተነሳ ይህን እድል የማግኘት እድሌ አክትሟል፡፡
ሊግ፡- ባህሪይ እንዴት ይገለፃል?
እያሱ፡-ዝምተኛ ነኝ፤ ከሰዎች ጋር ስቀራረብም የእውነት ነው የምቀርበው፤ ከዛም መግባባት እችላለው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ቡና ካምፕ እነማን ተጨዋቾች ያዝናናቹሃል?
እያሱ፡- እኛን በጣም የሚያዝናኑን ታፈሰ ሰለሞን፣ ሚኪያስ መኮንን እና ሀይሌ ናቸው፤ ቀልድና ጨዋታን በጣም ይችላሉ፡፡
ሊግ፡- ከኢትዮጵያ ቡና መዝሙር በጣም የምትወደው?
እያሱ፡- ተወዳጅ ዝነኛው ክለባችን የሚለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….?
እያሱ፡-ከሁሉ በፊት ለማስተላለፍ የምፈልገው የመጨረሻ መልዕክቴ በአሁን ሰዓት በአገራችን የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተከፈተው ጦርነት ለእኛ የማይጠቅምና ወገን ወገኑም ላይ እየጨከነ ያለበት ሁኔታ ላይ ስለሆነ ይህን ድርጊት ሁላችንም ልናወግዘው ይገባል፤ ሰላም ሲኖርም ነው ሁሉም ነገርም የሚኖረው፤ እንደ ስፖርትም ስንሄድ ሰላም ከሌላ ስፖርቱ አይኖርም፤ ስለዚህም ሁላችንም በየተሰማራንበት ሙያ የአገራችንን ሰላም ለማስጠበቅ ልንንቀሳቀስ ይገባናል፤ ፈጣሪ ኢትዮጵያን በመጠበቅም ሰላም ያድርጋት፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P