Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ደስታዬ ሙሉ ይሆን የነበረው ኒጀርን እዛም ብናሸንፍ ነበር”
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካፒቴን ጌታነህ ከበደ


ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው የማጣሪያ ጨዋታ ላይ ዋልያዎቹ የኒጀር አቻቸውን 3-0 ድል ሲያደርጉ አንዷን ግብ ለማስቆጠር የቻለው ጌታነህ ከበደ በቀጣዮቹ ሁለት የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ እድላቸውን በራሳቸው ብቻ በመወሰን ለአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ከፍተኛ ትረቶችን እንደሚያደርጉ እየተናገረ ይገኛል፡፡
የዋልያዎቹ ካፒቴን ኒጀርን ድል ባደረጉበት ጨዋታ አገራችን ጥሩ መንቀሳቀሷን ተናግሮ ውጤት የሚገባቸው እንደሆነና የኒያሚውንም ግጥሚያ አሸንፈው ቢሆን ኖሮ ደስታው የበለጠ ሙሉ ይሆን እንደነበርም ሀሳቡን ሰጥቷል፤ በዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዙሪያና ሌሎችን ጥያቄ ለጌታነህ አንስተንለት ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፡፡


ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኒጀርን በሜዳዋ 3-0 ለማሸነፍ ችላለች፤ ድሉን እንዴት አገኘኸው?
ጌታነህ፡- ማክሰኞ ዕለት በተደረገው ጨዋታ የኒጀር ብሔራዊ ቡድንን ያሸነፍንበት ውጤት በጣም አሪፍ እና የጠበቅነውም ነበር፤ ያም ሆኖ ግን በእዚህ በተመዘገበው የድል ውጤት እኔ እንደ እግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪው ያህል በጣሙን አልተደሰትኩም፤ ምክንያቱም ይህን ድል እንደምንጎናፀፍ እነሱ ሀገር ላይ ካደረግነው ጨዋታ በመነሳት እናውቅ ነበር፤ በኒያሚው ጨዋታ ምንም እንኳን እኛ ሽንፈቱ ቢገጥመንም ያላቸውን አቋም በሚገባ ተመልክተን ነበር፤ ከዛም በመነሳት በኒጀሩ ጨዋታ ቢያንስ አንድ ነጥብ ካልሆነ ደግሞ ብናሸንፍ ኖሮ ደስታዬ ሙሉ ይሆንልኝም ነበር፡፡
ሊግ፡- የጨዋታውን ውጤት ያጠናቀቃችሁት 3-0 በሆነ ውጤት ነበር፤ ይህን ያህል ግብስ በእነሱ ላይ እናስቆጥራለን ብላችሁ ጠብቃችሁስ ነበር?
ጌታነህ፡- በእርግጠኝነት በቁጥር ደረጃ ይህንን ያህል ግብ እናስቆጥራለን ብለን ባናቅድም የመጀመሪያው የኒያሚ ጨዋታችን ላይ ካገኘናቸው በርካታ የግብ ዕድሎች አኳያ የግብ ቁጥሩ ከእዛ በላይም ሊሆን ይችል ነበር፡፡
ሊግ፡- በኒጀር ስላጋጠመን የ1-0 ሽንፈት ምን ትላለህ?
ጌታነህ፡- የተመዘገበው ውጤት ለእኛ ፈፅሞ አይገባንም፤ ምክንያቱም እዛ በነበረን ጨዋታ ጥሩ ተጫውተናል፤ ወደ እነሱ የግብ ክልልም በተደጋጋሚ ጊዜ ደርሰናል፤ ያገኘናቸውን የግብ እድሎችንም ከመጓጓት የተነሳ ሳንጠቀምባቸውም ቀርተናል፤ በዛ ጨዋታ በተለይ ደግሞ እንደነበረን የኳስ ብልጫ ቡድናችን በእነሱ ሜዳ ላይ ሲጫወት ግጥሚያውን ለማሸነፍ በሚል ብቻ መጫወት ጀመረ እንጂ የአቻ ውጤትን አስመዝግበን አንድ ነጥብን ይዘን ለመውጣት ብንጥር ኖሮ መልካም የሚባል ውጤትን ይዘን መውጣት እንችል ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶችና እነሱም ባስቆጠሩት ተገቢ ያልሆነ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ በጨዋታው ዕድለኛ ሳንሆን ቀርተን ሽንፈትን ልናስተናግድ ችለናል፡፡
ሊግ፡- በኒያሚ በተደረገው ጨዋታ የኒጀር ብሔራዊ ቡድንን ለማሸነፍ እንዳንችል በዋናነት የምትጠቅሰው ሌላስ ምክንያት አለህ?
ጌታነህ፡- አዎን፤ የመጀመሪያው ከእዚህ ከመጓዛችን በፊትየአቻ ውጤትን ብናስመዘግብ የሚለው ምኞታችን እና እሳቤያችን ነው በቡድናችን ተጨዋቾች ላይ ተንፀባርቆ ስለነበር ያንን ብቻ ማሰባችን የጎዳን፤ ሌላው ከእዚህ ጨዋታ በፊት ያደረግናቸውን የአቋም መለኪያ ግጥሚያዎችን አለማሸነፋችንም ከስነ-ልቦናው አኳያ የፈጠረው ተፅህኖ አለ፤ ከዛ ውጪ ደግሞ በጨዋታው ሜዳ ላይ ከእንቅስቃሴያችን በመነሳት በተደጋጋሚ ጊዜ እያጠቃን ስለነበርና ከላይ እንደገለፅኩትም ማሸነፍን ብቻም ስለፈለግን ቢያንስ በአቻ ውጤት ልናጠናቅቅ የምንችልበትን ውጤት ነው ልንጠቀምበት ያልቻልነው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ የኒጀር አቻዋን ባሸነፈችበት ቀን ጨዋታ ኮትዲቯርና ማዳጋስካር አቻ ሊለያዩ ችለዋል፤ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚኖረው ዕድል ይሄ ውጤት መመዝገቡ ለእኛ መልካም ነገር ነው?
ጌታነህ፡- በአንድ ጎኑ አዎን፤ የበለጠ ግን ለእኛ ጥሩ ሊሆንልን ይችል የነበረው ኮትዲቯር ማዳጋስካርን ብታሸንፍልን ነበር፤ ምክንያቱም በቀጣይነት በሚደረገው ጨዋታ እኛ የምንገጥመው ማዳጋስካርን ነውና፤ እነሱን እዚህ ከአንድ ግብ በላይ ልዩነት ካሸነፍን በኋላ የመጨረሻ ግጥሚያችንን የምናደርገው ከኮትዲቯር ጋር ነው፤ እዛ የትኛውም ውጤት ቢመዘገብ ወደ አፍሪካው ውጤት ማለፋችን አይቀሬ ስለሚሆን ነው፡፡
ሊግ፡- ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከእዚህ በኋላስ የሚኖረን ሌላኛው ዕድል የቱ ነው?
ጌታነህ፡- አሁንማ በሚቀሩን ሁለት ጨዋታዎች ነው ዕድላችንን የምንወስነው፤ የሌላ ቡድኖችን ውጤትም መጠበቅ አይኖርብንም፤ በራሳችን ዕድል ተወስነን ነው ግጥሚያዎቹን ለማሸነፍ እና ካልተቻለ ደግሞ ከእነዚህ ጨዋታዎች አንዱን አሸንፈንና በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተን አራት ነጥብን ይዘን ለመውጣት መጫወትም የሚኖርብን፤ ይሄን ካሳካንም ወደ አፍሪካው ዋንጫ እናልፋለን፡፡
ሊግ፡- ማዳካስካር ኮትዲቯርን አሸንፋ ቢሆን ኖሮስ?
ጌታነህ፡- ይሄ ውጤት ቢመዘገብ ኖሮ ደግሞ ለእኛ መልካም አልነበረም፤ ይሄን ለማለት የቻልኩትም ማዳጋስካር አሸነፈች ማለት ነጥቧን 9 ስለምታደርስና የመጨረሻ ግጥሚያዋን ደግሞ 6 ግቦችን ካስቆጠረችባት ኒጀር ጋር ስለምታደርግ እንደዚሁም ደግሞ ኮትዲቯር ቀጣዩን ጨዋታ ከኒጀርና የመጨረሻውን ጨዋታ ደግሞ ከእኛ ጋር ስለሚያደርግ ፍልሚያው ለእኛ አስቸጋሪ ስለሚሆንብን ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የተጨዋቾች ስብስብ እንዴት እና በምን መልኩ እያየኸው ነው?
ጌታነህ፡-ጥሩ የተጨዋቾች ስብስብ እንዳለን አምናለው፤ ያም ሆኖ ግን የአሁኑ ቡድናችን አዳዲስ እና ወጣት ተጨዋቾችን ጨምሮ የያዘ ስለሆነ ትንሽ የልምድ ማነስ እና የአሰልጣኙን የጨዋታ ታክቲክም በፍጥነት የመላመድ ችግርን ልመለከትበት ችያለው፤ እንደዛም ቢሆን ግን አሁን ላይ ሁሉም ተጨዋች በአሰልጣኙ የሚሰጠውን ታክቲክ ለመላመድ በከፍተኛ ጥረት ላይ ነውና ከጊዜ ሂደቶች በኋላ በጣም ጥሩ እና ጠንካራ ቡድን እንደሚኖረን ከፍተኛ እምነቴ ነው፡፡
ሊግ፡-ከእዚህ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታው ከአራት ወራት በኋላ ዳግመኛ እንመለሳለን፤ እስከዛ ቡድናችን ምን ምን ነገሮችን መስራት ይኖርበታል?
ጌታነህ፡-የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሁን ላይ ብዙ ነገሮችን እየሰራ ይገኛል፤ ከእነዛም መካከል የሊጉን ውድድር በታህሳስ ወር ላይ ይጀምራልና ይሄ መሆን መቻሉ ለብሔራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሌሎች ተጨዋቾችን ከውድድሩ ላይ እንዲመርጥ ስለሚያስችለው እና በምርጫውም ወቅት በምንም ነገር እንዳይቸገርም ስለሚያደርገው በሚሰራቸው ጠንካራ ስራዎች ጭምር ካለፈው የተሻለ ቡድን እንዲኖረው ያደርገዋል፤ ከዛም በተጨማሪ የብሔራዊ ቡድኑ ሌሎች የወዳጅነት /የማጠናከሪያ/ ግጥሚያዎችን ማድረግም ይኖርበታልና እነዚህን ነገሮች ነው ልንሰራቸው የሚገባን፡፡
ሊግ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኃላፊነት ዘመን ላይ ከተቀላቀልክ በኋላ በአቋም መለኪያም ሆነ በዋናው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ግጥሚያ ላይ ጎሎችን ማስቆጠር ጀምረሃል፤ ይሄ ሲታይ ወደበፊቱ ወይንም ደግሞ ብዙዎቹ ወደሚያውቁህ አቋምህ እና ብቃትህ ዳግም እየተመለስክ ነው ማለት ይቻላል?
ጌታነህ፡- የዋልያዎቹን ተጨዋችነቴን በተመለከተ በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱም ወቅት መጀመሪያ ላይ የቡድኑ አባል ነበርኩ፤ ከዛም ጉዳት ከቡድኑ እንድርቅ አደረገኝ፤ በእዛን ሰዓትም ድኜ ወደሜዳ በፍጥነት እንድመለስ አብርሃም ይደውልልኝም ነበር፤ ከዛም በኋላ ወደጤንነቴ ከተመለስኩ በኋላም ለክለቤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኮቪድ ወደ አገራችን ገብቶ ሊጋችንን እስካቋረጠበት ሰዓት ድረስ ጥሩ መንቀሳቀሴን በተከታተለው አዲሱ የብሔራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ዳግም ዋልያዎቹን እንዳገለግል በተጠራው ሰዓት ጥሩ ለመንቀሳቀስ መቻሌ በጣሙን እያስደሰተኝ ነው የሚገኘው፤ በዋልያዎቹ የአሁኑ የተጨዋቾች ስብስብ ከላይ እንደገለፅከው ከአቋም መለኪያ ጨዋታ ጀምሮ ኒጀርን በገጠምንበት የማክሰኞው ዕለት ጨዋታ ግብ ለማስቆጠር በቅቻለው፤ ከዛም ባሻገር ነጥብ ለመጋራት እና የመከላከል ጨዋታን ይዘው መጥተው ለነበሩት የኒጀር ብሔራዊ ቡድን ላይም ሌሎችን ተጨማሪ ግቦችን እንድናስቆጥርም ለሌሎች ተጨዋቾቻችን ቦታ በማስከፈት ጭምር ጥሩ የተንቀሳቀስኩበትም ሁኔታ አለና ይሄ የሚያሳየው ወደ ቀድሞው ምርጥ ብቃቴ እየተመለስኩ መሆኑም ነው፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተጨዋችነት ዘመን ቆይታህ እስካሁን አቋምህን ጠብቀህ ለመጫወት የቻልክበት ዋንኛው ምክንያት ምንድን ነው?
ጌታነህ፡- በእዛ ደረጃ የእግር ኳስን ለመጫወት የቻልኩት ከፕሮጀክት ተጨዋችነት ዘመኔ አንስቶ በየተጫወትኩባቸው ክለቦች ውስጥ ሁሌም ስራዬን አክብሬ ስለምሰራ ነው፤ ከዛም በተጨማሪ አሰልጣኞች ከሚሰጡኝ ልምምዶች ባሻገር በግሌም የምለማመድበት ሁኔታና ጂምም በደምብ ስለምሰራ እነዚህ በጣሙን ጠቅመውኛል፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ጥሩ ተስፋን የጣልክባቸው ተጨዋቾች አሉ?
ጌታነህ፡-አዎን፤ ለምሳሌ የቡናው አቡበከር ናስር እንደዚሁም ደግሞ ሁለቱ የኮሪደር ስፍራ ተጨዋቾች ረመዳንና ሱሌይማን ጥሩ ተስፋን የጣልኩባቸው ተጨዋቾች ናቸው፤ ከእነሱ በተጨማሪም በተከላካይ ክፍሉ ላይ ጠንካራ ብቃታቸውን እያሳዩ ያሉት አስቻለው ታመነና ያሬድ ባየህ እንደዚሁም ደግሞ ግብ ጠባቂያችን ተክለማሪያም ሻንቆም ኳስን በእግር በመጀመር እንቅስቃሴያችንን የሚያስቀጥልበት መንገድ ጥሩ በመሆኑ ተጨዋቾቹን በጣም እያደነቅኳቸውም ነው የሚገኘው፡፡
ሊግ፡- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደዚሁም ደግሞ ለክለብህ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ በኋላ ምን ልትሰራላቸው ዝግጁ ነህ?
ጌታነህ፡-በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመን ቆይታዬ ከእዚህ በኋላ ጉዳት ካላጋጠመኝ በስተቀር ለሀገሬም ሆነ ለክለቤ ጥሩና የተሻለ የስኬት ስራዎችን ለመስራት ሁሌም ራሴን አዘጋጃለው፤ በተለይ የእኔ ዋንኛ እልም ሀገሬን ለአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ ክለቤን ደግሞ የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና በማስደረግ ወደለመደበት የአፍሪካ የክለቦች ውድድር እንዲመለስና በእዛም የውድድር ተሳትፎው ከእዚህ በፊት አስመዝግቦት ከነበረው ውጤት አንድ ደረጃ ከፍ ያለ ድልን እንዲጎናፀፍም ነው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ?
ጌታነህ፡-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለአፍሪካ ዋንጫው በማሳለፍ የአገራችንን ህዝብ ወደለመደው አንድነቱ፣ ወንድማማችነቱ መመለስ የእኛ ተጨዋቾች ትልቅ የቤት ስራ ነውና ከወራቶች በኋላ ለእዚህ አገራዊ ግዳጅ ሁላችንም ከፍተኛ ጥረታችንን ልናደርግ ይገባል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P