Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በአገር ውስጥ ሊግ ብቻ መወሰን አልፈልግም፤ ታላቅና ፕሮፌሽናል ተጨዋች የመሆን ሕልም አለኝ”አቡበከር ናስር /ኢትዮጵያ ቡና/

በመሸሻ ወልዴ

በኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለኢትዮጵያ ቡና በአጥቂ ስፍራ ላይ በመጫወት አንፀባራቂ ኮከብ ተጨዋችነቱን እያስመሰከረ የሚገኘው አቡበከር ናስር በሊጉ ተሳትፎው ቡድኑ እየተጓዘ ስለመጣበት ሁኔታ እና ከራሱ ጋር በተያያዙ እንደዚሁም ደግሞ ሌሎችንም ጥያቄዎች የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አቅርቦለት ምላሽን ሰጥቶታል፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው ላይ ቡድኑ በትናንትናው ዕለት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ውጤት ሳይጨምር በአጠቃላይ 19 ግቦችን ለማስቆጠር የቻለው እና ለሶስት ጊዜያትም ሀትሪክን በመስራት በሊጉ ያለፉት 24 ዓመታት የውድድር ታሪክ ብቸኛው ተጨዋች መሆኑን ያስመሰከረው አቡበከር ናስር ምንአልባትም በሊጉ የውድድር ታሪክ አሁን ባስቆጠራቸው 19 ግቦች ላይ ተጨማሪ 7 ግቦችን ከዚህ በኋላ ማስቆጠር ከቻለም በጌታነህ ከበደ የተያዘውን የ25 ግብ ሪከርድ የሚሰብርበት አጋጣሚም ሊኖር እንደሚችልም ሊታወቅ ችሏል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡናው አንፀባራቂ ኮከብ ተጨዋች አቡበከር ናስር ጋር ሊግ ስፖርት ጥያቄዋን የጀመረችው ቡድኑ ባሳለፍነው ሳምንት በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሽንፈትን ካስተናገደበት ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ነው፤ ቃለ-ምልልሱም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡

ሊግ፡- ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገው የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ቡና ውድድሩን በሚመራው ፋሲል ከነማ ተሸንፏል፤ ጨዋታው በአንተ እይታ ምን ይመስላል? ስለደረሰባችሁስ ሽንፈት ምን ትላለህ?

አቡበከር፡- ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረግነው ጨዋታ ሁለታችንም ውጤቱን አጥብቀን ከመፈለጋችን አኳያ በጣም ከባድ ነበር፤ ክብደቱ በተለይም ደግሞ ለእኛ ነበር፤ ከእነሱ ጋር ባደረግነው ጨዋታ ፋሲሎች ተደጋጋሚ የግብ እድሎችን በመፍጠሩ በኩል ከእኛ የተሻሉ እና ጥሩ ነበሩ፤ ከዛ ውጪ እኛን በእንቅስቃሴ ደረጃ ለማቆም የመረጡት አግሬሲቭ የሆነ አጨዋወታቸውና ከእረፍት በኋላም በአብዛኛው የጨዋታ እንቅስቃሴያቸው መከላከል ላይ ያተኮረን እንቅስቃሴን ስለተከተሉ እና እኛም ደግሞ ያን አጨዋወታቸውን ልንሰብር የምንችልበት አቋም ላይ ስላልነበረን ሽንፈትን ልናስተናግድ ችለናል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በፋሲል ከነማ ለደረሰበት ሽንፈት በዋነኝነት ምክንያት የማደርገው የራሳችንን ድክመት ነው፤ በዕለቱ ጨዋታ ግጥሚያውን ለመርታት የምንችለውን አድርገናል፤ ያም ሆኖ ግን ከሌላው ቀን አጨዋወታችን አኳያ በጥንቃቄ ለመጫወት ያለመቻላችን ዋጋን እንድንከፍልም አድርጎናል፤ ስለዚህም ለሽንፈታችን ራሳችንንም ነው እየወቀስን የምንገኘው፤ ሽንፈት በእግር ኳስ ላይ የሚያጋጥም ነው፤ እኛም ያን ሽንፈታችንን አምነን ልንቀበል ብንችልም በመሸነፋችን ግን በጣም ነው ላዝን የቻልኩት፡፡

ሊግ፡- ከሽንፈቱ ውጪ ያዘንከው ለቡድንህ ጎልን ጭምር ስላላስቆጠርክም ነው?

አቡበከር፡- አይደለም፤ እኔ ያዘንኩት በጨዋታው ላይ ውጤትን ስላጣን እንጂ ጎልን ስላላስቆጠርኩ አይደለም፤ በኳስ ሁሌም ቅድሚያ የምሰጠው ቡድኔ አሸንፎ በሚወጣበት ጉዳይ ላይ እንጂ እኔ ወይንም ደግሞ የቡድን አጋር ጓደኞቼ ግብን አስቆጠሩ አላስቆጠሩ በሚለው ላይ አይደለም፤ ስለዚህም የተከፋሁት እና ያዘንኩት ፋሲልን ባለማሸነፋችን ብቻ ነው፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በኢትዮጵያ ቡና ላይ የመሪነቱን ግብ ያስቆጠረው ገና በጊዜ እና በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ነበር፤ የአቻነትን ግብ የምታስቆጥሩበት ሰፊ ሰዓት ቢኖራችሁም ያን ለማድረግ አልቻላችሁም፤ ተደጋጋሚ የጎል እድሎችንም ለመፍጠር አልቻላችሁም፤ በዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ….?

አቡበከር፡- የእውነት ነው፤ የሁለታችን ጨዋታ ላይ ከላይ እንደገለፅከው ቡድናችንም ሆነ እኔ እንደሌላው ጊዜ ጎሎችን ለማስቆጠርም ሆነ የግብ እድሎችን ለመፍጠር የነበረን ዕድል በጣም ጠባብ ነበር፤ ይሄም ሊሆን የቻለው በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ለእኛ ከባድ በሆነብን የፋሲሎች ማርክ የማድረግ አጨዋወት እና ግብም የመፍጠር እድላቸው አኳያ ያን ማድረግ ሳንችል ቀርተናል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቡድናችን ላይ የተቆጠረብንም ግብ ቶሎ እንዳንነቃም አድርጎናልና ይሄና ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደግሞ የፋሲሎች ውጤትን ከማስከበር አኳያ የመረጡት የመከላከል አጨዋወትም ነው እኛን ግብ እንዳናስቆጥርም ያደረገን፡፡

ሊግ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ መሸነፋችሁን ተከትሎ በነጥብ እየራቃችሁ ነው፤ ከዋንጫው ፉክክር ወጣችሁ ማለት ይቻላል?

አቡበከር፡- በፍፁም፤ ውድድሩ እኮ ገና ነው፤ በርካታ ጨዋታዎችም ከፊት አሉ፤ በእግር ኳስ ምን እንደሚፈጠርም አታውቅም፤ ስለዚህም ዋናው ነገር አንተ ራስህን ለየዕለት ጨዋታዎችህ በብቃት አዘጋጅተህ የሚመጣውን ነገር መጠበቅ ነው ያለብህ፡፡

ሊግ፡- ሻምፒዮና የመሆን ዕድሉ አሁንም አለን እያልክ ነው?

አቡበከር፡- ለምን አልልም፤ እስከመጨረሻው ጨዋታም ድረስ ይህን ስኬት ለመጎናፀፍ ጥረትን እናደርጋለን፤ ይህን ስል ግን ከፊት ለፊት ያሉብንን ጨዋታዎች ማሸነፍ እንዳለብን ሳልረሳ ነው፡፡ ለዛም በጥንቃቄ እያንዳንዱን ጨዋታዎች እናደርጋለን፡፡

ሊግ፡- ሻምፒዮና ለመሆን ባትችሉስ?

አቡበከር፡- አሁን ላይ እንደዛ ብለን የምናስብበት ጊዜ ላይ አይደለንም፤ ሻምፒዮና ለመሆንም ነው የምንጫወተው፤ ለምንስ ሻምፒዮና አንሆንም? ምንአልባት ግን ያ እድል ካልገጠመን እንኳን ኢትዮጵያ ቡናን በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ተሳትፎ ላይ የሚካፈልበትን ውጤት እንዲያስመዘገብ እናደርገዋለን፡፡

ሊግ፡- የአቡበከር ናስር ጎል ማስቆጠር በቀጣይ ጨዋታዎቹስ ላይ ይቀጥላል?

አቡበከር፡- ባለፈው ጨዋታ ላይ ጎል ባላገባም የቀጣይ ፍልሚያዎቻችን ላይ ይሄን የሚከለክለኝ ማንም የለም፤ ምክንያቱም በጥሩ አቋም ላይም ነኝ፡፡

ሊግ፡- ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረጋችሁት ጨዋታ የታፈሰ ሰለሞን በጊዜ ተቀይሮ መውጣት ቡናን አቀዛቅዞት እንደነበርና አንተም ጎል እንዳታገባ በብዙዎች ዘንድ በምክንያትነት የተጠቀሰበት ሁኔታ ነበርና በዚህ ዙሪያ ምን አልክ?

አቡበከር፡- ታፈሰ ሰለሞን የቡና ብቻ ሳይሆን የሀገርም ትልቁ ተጨዋች ነው፤ ያን ዕለት እሱ እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ቢኖርም ይጠቅመንም ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ሌሎችም የሚጠቅሙን ተጨዋቾችም ስለነበሩ ላጣነው ውጤትና ለእኔ ግብ አለማስቆጠር የእሱ አለመኖር ብቻ ምክንያት አይሆንም፤ ይህን ለማለት የወደድኩትም ኢትዮጵያ ቡና እንደ ቡድን የሚንቀሳቀስ ክለብም ነውና፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማን በዛን ዕለት ጨዋታ በምን መልኩ ገመገምካቸው?

አቡበከር፡- ፋሲሎችን ከተጨዋቾች ስብስባቸው አንስቶ ሜዳ ላይ ባላቸው ነገር እንደተመለከትኳቸው በጣም ጠንካራ እና አሪፍ የሆነ ቡድን ነው፤ ጥሩም አሰልጣኝ አላቸው፤ በእንቅስቃሴ ደረጃ ግን እኛ ከእነሱ የተሻልን ነን፡፡

ሊግ፡- በቅዳሜው ዕለት ጨዋታ የአንተ እና የፋሲሉ ተከላካይ ከድር ኩሊባሊ የአንድ ለአንድ ፍጥቻ የብዙዎቹን ትኩረት ከመሳብ ባሻገር አላፈናፍን ብሎህም ቆይቷል፤ እሱ አንተ ላይ በሰራው ተደጋጋሚ ጥፋትም የቢጫ ካርድ ማስጠንቀቂያን ሊመለከት ችሏል፤ በዚህ ዙሪያስ ምን አልክ?

አቡበከር፡- ፋሲል ከነማዎች እኛን ለማሸነፍ ያን ዕለት በመረጡት አግሬሲቭ የሆነ ጨዋታቸውና በኋላም ላይ በተከተሉት ውጤትን የማስከበር እንቅስቃሴያቸው እኔ ብዙም ቅሬታ የለኝም፤ እንደዛም ሆኖ ግን የቡድናቸው ተከላካይ የሆነው ከድር ኩሊባሊ አንዴ ይሁን እሱ ግን እኔ ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ፋውልን እየሰራብኝ የዕለቱ አልቢትር በዝምታ ማለፉና በኋላ ላይ ቢጫ ካርድን ብቻ መስጠቱ ጨዋታው ምን ያህል ከብዶት እና አስፈርቶት እንደነበር ያሳየኝ ነውና ስለ ዳኝነቱ መናገርን እፈልጋለው፤ ዳኞች እንደ እኛው ሰዎች ናቸው፤ ሊሳሳቱ እንደሚችሉም አውቃለው፤ እንደዛም ሆኖ ግን ሁሌም አንድ ጨዋታን ሊመሩ ሲገቡ ጠንከር እና ቆፍጠን ብለው መግባት እንዳለባቸውም ከተመለከትኩት ነገር በመነሳት መልዕክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ፡- በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሌላኛው ወንድማችሁ ጅብሪል ናስርም ለወልቂጤ ከተማ ተቀይሮ በመግባት ተጫውቶ መልካም ጅማሬን አሳይቷል፤ በእሱ ዙሪያ ምን ትላለህ?

አቡበከር፡- ስለ ጅብሪል ወንድምህ ስለሆነ እንዳይባል እንጂ ስለ እሱ ብዙዎች ናቸው ምስክርነታቸውን እየሰጡለት የሚገኙት፤ ጅብሪል ጎበዝ ኳስ ተጨዋች ነው፤ በራሱ አቅምና ደረጃ ላይም ነው ገና የመጫወት እድሉን ባገኘበት ጨዋታ ላይ ጥሩ ለመንቀሳቀስ የቻለው፤ እሱ በኳሱ የመጫወት እድልን በተደጋጋሚ ጊዜ ያግኝ እንጂ ብዙ ነገሮችን መስራትም ይችላል፤ ለጨዋታ ሁሌም ዝግጁ ነው፤ ወደፊት ሀገሩን ሊጠቅማት የሚችልበት እምቅ ብቃትም አለው፡፡

ሊግ፡- በዛ ላይ ደግሞ ከቤተሰባችሁ ውስጥ በጣም ቀልደኛ እንደሆነም ይነገራል፤ የእውነት ነው?

አቡበከር፡- አዎን፤ ጅብሪል ካለ ሳቅና ጨዋታ አለ፤ ትልቁ ብቃቱ ደስተኝነቱ ነው፤ ካልተቀላለደ ብዙ ነገር ደስ አይለውም፤ ከቤታችን ወጣ ያለ ባህሪህ ያለውም እሱ ነው፤ ቤታችን አንድአንዴ ዘመዶቻችን ሊጠይቁን ሲመጡና ሲሰበሰቡም ደስታን እንዲሰጣቸው ጅብሪልን ጥሩልንም ነው የሚሉትና በሁሉም ነገሩ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ እመኝለታለው፡፡

ሊግ፡- ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉን እንደ አጠቃላይ ስትመለከተው ግን እንዴት አገኘኸው?

አቡበከር፡- ውድድሩ ጥሩ ቢሆንም ጨዋታው ግን በየ3 ቀኑ የሚከናወን በመሆኑ ከፍተኛ ድካም አለው፤ ግጥሚያው ለብዙዎቹ እየከበዳቸው መጥቷል፤ ጉልበትን የፈጀም ውድድር ነው፤ ይሄ በመሆኑም አሁን ላይ ምንም እንኳን ቀጣዩ ውድድር ለ21 ቀናት እረፍት የተበተነ ቢሆንም አወዳዳሪው አካል ግን ከጤናም አንፃር በመመልከት ሊያስብበት ይገባል፡፡

ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና በቤት ኪንግ ተሳትፎው በተለየ መልኩ ቀርቧል ማለት ይቻላል?

አቡበከር፡- በሚገባ፤ የእኛ ቡድን የራሱን የሆነ የጨዋታ ይዘት ሳይለቅ ነው በየጨዋታው ሲፋለም የነበረው፤ በርካታ ግቦችን ካስቆጠሩ ጥቂት የሊጉ ክለቦች ውስጥም ስሙ በጉልህ የሚጠቀስ ነው፤ ተመልካቹ የሚወደውን ጥሩ እግር ኳስንም በመጫወት ጎልቶ ታይቷልና ይሄ እሱን ይለየዋል፡፡

ሊግ፡- ወንድምህ ጅብሪል እኛ ቤተሰብ ውስጥ ኳስን ስንጫወት የሚፈራት የለም፤ ሁላችንም ጋር ያለው የራስ መተማመንም ነው እያጫወተን ያለው ሲል ተናግሯል፤ በዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ይኖራል?

አቡበከር፡- ይሄ እኛ ቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከሰፈራችንም ጉቶ ሜዳ አካባቢ ጭምር ነው፤ በእኛ አካባቢ ማህበረሰብ ለኳስ የሚጨነቅ የለም፤ ኳስን እንደ መዝናኛ ጭምርም ነው የምንመለከተው እና በዚህ ተለይተን እንታወቃለን፡፡

ሊግ፡- በችሎታህ ሁሉንም እያሳመንክ መጥተሃል፤ እንደዛም ሆኖ ደግሞ አንድአንዴ የነጭናጫነትን ባህሪም እያሳየህ መጥተሃል?

አቡበከር፡- የእውነት ነው፤ ይህን የማደርገው ግን ከክፋት ወይንም ደግሞ ከሌላ ነገር ተነስቼ አይደለም፤ ኳስ ጨዋታ የሚያመጣው ባህሪህ ነው፤ አንድአንዴ የእኛ ቡድን ተመርቶ በሚገኝበት ሰዓት ላይም ነው ተጨዋቾች ሰዓት ሲገሉ ሳይና ጥፋትም በእኔም ሆነ በቡድናችን ተጨዋቾች ላይ በሚፈፀምበት ሰዓት ይሄንን ባህሪህ የማሳየው፤ ሜዳ ላይ ስትሆን እኮ አንድአንዴ ሽንፈትን ካለመውደድ አኳያ ስሜታዊ የምትሆንበት ጊዜ አለ፤ ከሜዳ ስትወጣ ደግሞ ያደረግከው ነገር ስህተት ሆኖ ከታየ ይህን አድርጌያለው ብለህ ትፀፀታለህና በእንደዚህ ውስጥ ያለሁኝ ተጨዋች ነኝ፤ በየትኛውም ጨዋታዎች ላይም ግጥሚያው ከተጠናቀቀ በኋላም ከብዙዎቹ ተጨዋቾች ጋር ብተዋወቅም ባልተዋወቅም ሰላምታ ተለዋውጬም መውጣትንም ነው የምፈልገው፡፡

ሊግ፡- ብዙዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለህን ብቃት ተንተርሰው በእዚህ ሊግ ደረጃ ብቻ መጫወት የለበትም እያሉህ ነው፤ ከወዲሁ ያሰብከው ነገር አለ?

አቡበከር፡- አዎን፤ የኳስ ህይወቴ በዚህ ሊግ ደረጃ ብቻ እንዲጠናቀቅ አልፈልግም፤ የእኔ እልም በፕሮፌሽናል ደረጃም ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ መጫወት እና በግብ ማስቆጠሩ እና ጥሩ በመጫወቱ በኩል እዚህ የምሰራውን ገድል እዚያም ሄጄ በመስራት ታሪካዊ ኢትዮጵያዊ ተጨዋች መባልንም ነው የምፈልገው፡፡

ሊግ፡- አሁን ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ተብሎ ተቋርጧል፤ ስለ እሱስ ምንን እያሰብክ ነው?

አቡበከር፡- በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ የእኛ የማለፍ ዕድል ምንም እንኳን ጠባብ እና በራሳችን ሁለት ግጥሚያዎች ላይ የሚወሰን ቢሆንም ከወዲሁ ለማንም እጅን አንሰጥም፤ ከማዳጋስካር ጋር በቅርቡ ጨዋታ አለን ይህን ግጥሚያም የምናደርገው በሜዳችን ነው፤ ጨዋታውንም እናሸንፋለን፤ ከኮትዲቯር ጋር የሚኖረንን ግጥሚያ ደግሞ ከሜዳችን ውጪ የምናደርግ ቢሆንም እዛም ጨዋታ ላይ የአቅማችንን አውጥተን በመጫወት የሚመጣውን ማናቸውንም ነገሮች ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P