ተወዳጇን ሊግ ስፖርት ጋዜጣን ቅዳሜ ያንብቧት
ሊግ ስፖርት በየሳምንቱ ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃ ጋዜጣ ስትሆን በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ የሚወዱትን ዘገባ ታቀርብሎታለች።
ሊግ ስፖርት ነገ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ የዋልያዎቹን ድል አስመልክቶና ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ከኮትዳቯር ጋር የፊታችን ስለሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ የቡድናችን ግብ ጠባቂ ተክለማሪያም ሻንቆ የሚለው ይኖራል።
የዋልያዎቹን ግብ ጠባቂ ከብቃቱ ጋር በተያያዘም ስለሚነሱበት ጉዳዮችም አናግረነው ምላሽን ሰጥቷል።
ምን ምን ጉዳዮችን ተናግሮ ይሆን ከእነዛ ውስጥ የቀድሞ ግብ ጠባቂዎች ከሚሰጣቸው ስልጠና አንፃር ግባቸው ውስጥ ቆመው ስለሚውሉ በርካታ ግቦችን ያስተናግዱ ነበር። አሁን ግን በረኛ እንደ ትርፍ ሰው ስለሚጫወት ብዙ ጎሎችን የሚያስተናግድበት እድሉ ጠባብ ነው። ይህ እንቅስቃሴ አዲስ ከመሆኑ የተነሳም እየተለማመድነውም ነው። ይህን እንቅስቃሴ ስንከተልም ስህተት ይኖራል ያም የሚታረም ነው በማለት በማዳጋስካሩ ጨዋታ ያን ያህል የጎላ የሚባል ስህተትን አልሰራሁም። የሰራሁት ስህተት ጥቂትና የሚታረም ስለሆነም አስተካክለዋለው ሲል ገልጿል።
ሊግ በባህር ማዶ ዘገባዋም ፖርቹጋልን ያለ ሮናሎዶና የማንቸስተር ዩናይትድ ተስፋ በሚል እና ሌላ ተጨማሪ ዘገባን አቅርባሎታለች።
ሊግ አታምልጦት። የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህን ይመስላል።
ተወዳጇን ሊግ ስፖርት ጋዜጣን ቅዳሜ ያንብቧት
ተመሳሳይ ጽሁፎች