Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቤትኪንጉን እስከ ሶስተኛ ባለ ደረጃ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድን ይዘናል” “የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ሜዳ ሁሉንም ክለቦች እኩል ያደረጋቸው ይመስለኛል” አለልኝ አዘነ /ባህርዳር ከተማ/

 

በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚመራው ባህርዳር ከተማ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎው ትናንት ከሊጉ መሪ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረገውን ጨዋታና እንደዚሁም ደግሞ መከላከያዎችም ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ግጥሚያ ውጤት ሳይጨምር በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በአምስተኛ ስፍራ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ የስምንተኛ ሳምንት የጨዋታ መርሃ ግብር ደግሞ ከአምናው ሻምፒዮና ፋሲል ከነማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በከፍተኛ ጉጉት ከወዲሁ ተጠብቋል፤ ባህርዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ሁሌም ደርቢ ከመሆኑ አኳያ ለጨዋታው ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው የታወቀ ቢሆንም የዛሬው እንግዳችንና አንድ አንድ ተጨዋቾች ደግሞ ግጥሚያውን እንደ መደበኛ ጨዋታ እንደሚመለከቱትም ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡

ባህርዳር ከተማ በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና የትናንቱን ጨዋታ ውጤት ሳይጨምር ባለፉት ስድስት ግጥሚያዎች ሶስቱን አሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቶና በሁለቱ ተሸንፎ 10 ነጥብን ያስመዘገበ ሲሆን በቡድኑ የውድድር ተሳትፎ ዙሪያና በራሱ የኳስ ህይወት ዙሪያ በአሁን ሰዓት ለክለቡ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ ከሚገኘው የቡድኑ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች አለልኝ አዘነ  ጋር የሊግ ስፖርት አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ቆይታን አድርጎ ምላሽ ተሰጥቶታል፤ ሊግ ስፖርትና አለልኝ ያደረጉት ቆይታም በሚከተለው መልኩ ሊቀርብ ችሏል፡፡

ሊግ፡- በቅድሚያ ስለ ውልደትህና እድገትህ ብትነግረን?

አለልኝ፡- የተወለድኩት በአርባምንጭ ከተማ በተለምዶ አጠራር አርባምንጭ ልማት ሰፈር በሚባለው አካባቢ ነው፤ በእዛ ስፍራም ነው ከህፃንነት ዕድሜዬ አንስቶ ኳስን እየተጫወትኩ ያደግኩት፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን የታዳጊነት ዕድሜህ ላይ ሆነህ ስትጫወት የቤተሰብ ፍቃድን ታገኝ ነበር?

አለልኝ፡- በፍፁም፤ ለትምህርቴ ትኩረት እንዳደርግ ስለሚፈለግ እንድጫወት አይፈቀድልኝም ነበር፡፡

ሊግ፡- የቤተሰባችሁ ስፖርተኛው አንተ ብቻ ነህ? ስንት ወንድምና እህቶችስ አሉ?

አለልኝ፡- በእኛ ቤተሰብ ውስጥ ስፖርተኛው አዎን እኔ ብቻ ነኝ፤ ሁለት ወንድሞችና አራት እህቶችም ናቸው ያሉኝ፡፡

ሊግ፡- ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነት የመጣህበት መንገድ ምን ይመስላል?

አለልኝ፡- የመጀመሪያ መነሻዬ የገረመው የታዳጊ ፕሮጀክት ቡድን ነው፤ እሱ ጋርም ነበር እየሰለጠንኩ ኳሱን በጥሩ ሁኔታ እጫወት የነበረው፤ ትንሽ ከፍ ካልኩ በኋላ ደግሞ ከዚሁ የፕሮጀክት ቡድን ተጨዋቾች ውስጥ ወደ አርባምንጭ ከተማ ወጣት ቡድን ለመግባት በተሰጠን የሙከራ ዕድል አራት የምንደርስ ተጨዋቾች አለፍንና ቡድኑን ልቀላቀል ቻልኩ፤ ወደ ኳሱ የመጣሁበት ሁኔታም  በአጭሩ ይህንን ይመስላል፡፡

ሊግ፡- ወደ እግር ኳሱ በጥልቀት ያመራኸው የዩንቨርስቲ ትምህርትህን ጥለህ መሆኑንም ሰማን?

አለልኝ፡- አዎን፤ ያኔ ውጤት መጥቶልኝ አርባምንጭ ዩንቨርስቲ ገብቼ ነበር፤ ወደ ዋናው ቡድን ያደግኩበት ዓመት ላይም ነበር፤ ለአንድ ወር ያህል ከተማርኩ በኋላ ግን ዊዝድሮ ሞላውና በኳስ ተጨዋችነቴ ልቀጥልበት ቻልኩ፡፡

ሊግ፡- በታዳጊነት ዕድሜህ ኳስን ተጫውተህ ስታሳልፍ የማን አድናቂ ሆነህ አደግክ?

አለልኝ፡- መጀመሪያ ያደነቅኩት ተጨዋች የሰፈሬ አርባምንጭ ልማት አካባቢ ተጨዋች ስለነበርና ሲጫወትም ያስደስተኝ ስለነበር አመለ ሚልኪያስን ነው ተምሳሌቴና ሞዴሌ ያደረግኩት፤ ይህ ሰፈር ደግሞ እንደ እነ ቢያድግልኝ ኤልያስና አበባው ቡታቆ የመሳሰሉ ተጨዋቾችንም ያፈራ ስለነበር የሚታወቅም አካባቢ ነው፡፡

ሊግ፡- ከባህርማዶ ተጨዋቾችስ የማን አድናቂ ነበርክ?

አለልኝ፡- የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ እንደመሆኔ ፖል ስኮልስንና ማይክል ካሪክን ነበር የማደንቃቸው፡፡

ሊግ፡- ወደ እግር ኳስ ተጨዋችነቱ ባታመራ ኖሮ አንተን በምን ሙያ ላይ እናገኝ ነበር?

አለልኝ፡- ያው ከላይ እንደገለፅኩት ወደ ኳሱ ያመራሁት የዩንቨርስቲ ትምህርቴን ትቼ በመሆኑ ኳስ ተጨዋች ባልሆን ተምሬና ተመርቄ በሌላ የስራ አለም ውስጥ ነበር እገኝ የነበረው፡፡

ሊግ፡- አርባምንጭ ከነማ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ክለብህ ነው፤ በቡድኑ ውስጥ የነበረ ቆይታ መልካም የሚባል ነው?

አለልኝ፡- አዎን፤ በእዚህ ቡድን እያለው ጥሩ ጊዜን ነበር ያሳለፍኩት፤ በተለይም ደግሞ በወቅቱ የቡድናችን አሰልጣኝ የነበረው በረከት ደሙ // በወጣት ተጨዋቾች ላይ ያለው እምነት ጥሩና የመሰለፍ እድልንም ያስገኝልን ስለነበር ያ በጣሙን ያስደሰተኝ ነው፤ ከዛም ባሻገር በእዚህ ቡድን ቆይታዬም ሐዋሳ ላይ ተዘጋጅቶ የነበረውን የደቡብ ሲቲ ካፕ ዋንጫንም በወጣትነት ዕድሜዬ ከቡድን አጋር ጓደኞቼ ጋር ስናነሳም የተለየ የደስታ ስሜትም ነው የተሰማኝና እነዚህ የማይረሱኝ ናቸው፡፡

ሊግ፡- በአርባምንጭ ክለብ ቆይታህ በጣም ተከፋሁበት የምትለው ወቅትስ?

አለልኝ፡- በጊዜው የቡድኑ አባልና መጫወትም የጀመርኩበት ሰዓት ነበርና ከፕሪምየር ሊጉ ወደ ከፍተኛው ሊግ ስንወርድ በጣም ነው ያዘንኩት፤ ምክንያቱም የእኛ መውረድ የብዙ ታዳጊ ተጨዋቾችን ሞራልም ነበር የጎዳው፤ ያም ሆኖ ግን ይሄ ቡድን አሁን ተመልሶ ሊጉን በመቀላቀሉ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል፡፡

ሊግ፡- በፕሪምየር ሊግ ደረጃ የመጀመሪያ ግጥሚያህን ታስታውሳለህ? ያኔ ምን ስሜትስ ነበር የተፈጠረብህ..?

አለልኝ፡- የመጀመሪያ ግጥሚያዬን ያደረግኩት በ2009 በሐዋሳ ስታድየም ከሐዋሳ ከተማ ጋር ነው፤ በጨዋታው የእኔው ክለብ አርባምንጭ በመሸነፉ ይክፋኝ እንጂ በወጣትነት እድሜዬ ግጥሚያውን ለማድረግ በመቻሌ ደስ ሊለኝ ችሏል፡፡

ሊግ፡- ወደ አሁኑ ክለብህ ባህርዳር ከተማ ከማምራትህ በፊት ለሐዋሳ ከተማም ስትጫወት አይተንሃል፤ በዛ ቡድን ውስጥ ስለነበረህ ቆይታ የምትለን ነገር ካለ?

አለልኝ፡- ለሐዋሳ ከተማ ለመጫወት ፊርማዬን ባኖርኩበት የሁለት ዓመታት ጊዜያቶች ውስጥ የእኔን ቆይታ በተመለከተ የምገልፀው በሁለት አይነት መንገድ ነው፤ የመጀመሪያውና አንዱ በዳኛ ላይ ያልተገባ ባህሪይን በማሳየቴ ለአንድ ዓመት እንድቀጣ ተደርጎ ያሳለፍኩትንናየተፀፀትኩበትን የኳስ ጊዜያቴን ሲሆን ሌላው ደግሞ ጥሩ ጊዜን ያሳለፍኩበትን የኳስ ቆይታዬን ነው፡፡

ሊግ፡-  ወደ ሐዋሳ ከተማ እንደተዘዋወርክ የአንድ ዓመት ቅጣት የተጣለብህ ሐዋሳ ከተማ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ነበር?

አለልኝ፡- አዎን፤ በእዛው በመቐለ ከተማ በተደረገው ጨዋታ ላይ ነበር ኢንተርናሽናል አልቢትር ብሩክ ፋውል ሳልሰራ ሰርተሃል ብሎ ፊሽካ በነፋብኝ ሰዓት 2-0 እየተመራንም ስለነበር ስሜታዊ ሆኜ ኸረ ጥፋት አልሰራውም በማለት ወደ እሱ በጣም ተጠግቼበማመራ ሰዓት በቴስታ የመታሁት ያህል ተደርጎ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ በቀይ ከመውጣቴ በተጨማሪ ከሁለት ሳምንት በኋላ በወጣው ኮሚኒኬም ዳኛውን መትቶታል ተብዬ ለአንድ ዓመት በመቀጣቴ በጣም ነው ያዘንኩት፤ ያን ዕለት የእውነት እኔ ዳኛውን ስሜታዊ ሆኜ በመቃወም ተጠጋሁት እንጂ በቴስታ አልመታሁ?ትም፤ የአንድ ዓመት ቅጣትም መቀጣት አልነበረብኝም፤ ያም ሆነ ይህ ግን አላጠፋሁም አላልኩም፤ ስሜታዊ ሆኖ ዳኛን መቃወም በራሱ ጥፋት ነውና ከዛ ጨዋታ የተማርኩት ብዙ ነገርም አለ፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ባህርዳር ከተማን ዘንድሮ ለመቀላቀል ችለሃል፤ ለውድድሩ ስላደረጋችሁት ዝግጅትና ስለ እስካሁን የጨዋታ ጉዞአችሁ ምን ትላለህ?

አለልኝ፡- ባህርዳር ከተማ ለዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎው  የቅድመ ዝግጅቱን ያደረገው መጀመሪያ ላይ ያለምንም የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነበር፤ በኋላ ላይ በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ላይ ተሳትፎ አድርጎና በመጨረሻም ላይ መከላከያን በሜዳው በማሸነፍና ሻምፒዮና በመሆንም አቋሙን በሚገባ ተመልክቶበታል፤ ወደ ዋናው የሊጉ ውድድር ከገባ በኋላ ደግሞ በመጀመሪያዎቹ ሁለትና ሶስት ጨዋታዎች ላይ ጥሩና አስተማማኝ የሚባል ነጥብን መያዝ ቢጀምርም መልሶ ባደረጋቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ደግሞ የጣላቸው ነጥቦች መዋዥቅ ውስጥ ከትቶት ነበር፤ አሁን ደግሞ የትናንቱን ጨዋታ ውጤት ሳይጨምር ወደ አሸናፊነት የመጣበት መንገድ ለቡድናችን ጥሩ ሊሆንልን ችሏልና በእዚሁ ልንቀጥልበት ነው ዝግጁ የሆንነው፡፡

ሊግ፡- ባህዳር ከተማ ያለው ጠንካራና ክፍተት ጎኑ ምንድን ነው?

አለልኝ፡- የእኛ ጥንካሬያችንና ለየት እንድንል የሚያደርገን ነገር እንደ ቡድን ወደፊት ፕሬስ አድርገን መጫወት መቻላችንና እንቅስቃሴያችንን ባለቀቀ መልኩም የራሳችን የሆነ አጨዋወት ያለን መሆኑ ነው፤ በክፍተት ደረጃ የማነሳው ደግሞ ስንከላከል እንደ ቡድን አልነበረም፤ በመነጣጣል ነበር ስንከላከል የነበረውና ይሄን ጅማ አባጅፋርን ባሸነፍንበት ጨዋታ ላይ አርመንና አስተካክለነው ለመምጣት መቻላችን መሻሻላችንን ሊያሳየን ችሏል፡፡

ሊግ፡- ባህርዳር ከተማን በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ምን ውጤትን ያመጣል ብለን እንጠብቀው? አንተስ የውድድር ዘመኑን በምን መልኩ ታሳልፋለህ?

አለልኝ፡- ባህርዳር ከተማ ከዝግጅት ጊዜ አንስቶ የእዚህ ዓመት የውድድር ተሳትፎውን  ሊያጠናቅቅ ያቀደው ሊጉን ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ባለው ደረጃ ላይ ሆኖ ለመጨረስ ነው፤ እኔም በእዚህ ቡድን ውስጥ በሚኖረኝ ቆይታዬ በግሌ ጥሩ ነገሮችን በመስራት ክለቤ ውጤታማ እንዲሆን እፈልጋለውና ያን በተግባር ለማሳየት ጠንክሬ ነው የምሰራው፡፡

ሊግ፡- ባህርዳር ከተማን በተቀላቀልክበት እና እየተጫወትክ ባለህበት የአሁኑ ወቅት ክለቡን ለየት ያደርገዋል የምትለው ነገር አለ?

አለልኝ፡- አዎን፤ ደጋፊውም ቡድኑም ዋንጫን ይፈልጋል፤ ይሄን ተመልክቼያለው፡፡

ሊግ፡- ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዘንድሮ እንዴት ተመለከትከው?

አለልኝ፡-የሊጉን የፉክክር ደረጃ  በተመለከተ መጀመሪያ የምነሳው ከመጫወቻው ሜዳ ነው፤ የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ሜዳ ኳስን ለመቀባበል አመቺ ካለመሆኑ የተነሳ የዘንድሮ  ሁሉንም ተሳታፊ ቡድኖችን እኩል አድርጓቸዋልና ከአምናው አንፃር ጠንካራ ፉክክርን ነው እያየን የምንገኘው፤ ከዛም ባሻገር ውድድሩ እንደ በፊቱ ለአንዱ እላይ ለሌላኛው እታች የሆነ ግምትንም ፈፅሞ ሳትሰጥም ነው ለሁሉም ክለቦች እኩል ግምትን ሰጥተህ በሜዳ ላይም የምትጫወተው፤ ክለቦች ተጠናክረውም መጥተዋልና ይሄንንም ነው ለመመልከት የቻልኩት፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ስምንተኛው ሳምንት ፋሲል ከነማን ትፋለማላችሁ ስለ ጨዋታው ምን ትላለህ?

አለልኝ፡- ከእነሱ ጋር የሚኖረን ጨዋታ የደርቢ ፍልሚያ ነው፤ ስለ ደርቢ ግጥሚያ ደግሞ ከዚህ ቀደም የሚታወቅ እና ተጫውተን ያለፍንም ልጆች ስላለን ብዙ ሊነገረን የሚገባ አይደለም፤ ስሜቱንም እናውቀዋለን፤ በደርቢ ጨዋታ ማሸነፍ ሁሌም ቢሆን በጣም ነው ደስ የሚለው፤ ፋሲልን ለማሸነፍም ነው ወደ ሜዳ የምንገባው፤ ያም ሆኖ ግን ለግጥሚያው የምንዘጋጀው በጣም የተለየ ዝግጅት አድርገን ሳይሆን ለሌሎች ክለቦች እንደምንሰጠው ትኩረት ነው፡፡

ሊግ፡- የአንተ ባህሪይ እንዴት ይገለፃል?

አለልኝ፡- ቁጡም ዝምተኛም አይደለሁም፤ ከሁለቱ በመሀል ሰፋሪ ላይ የሚገኝ ባህሪይ ነው ያለኝ፡፡

ሊግ፡- በጣም የማትረሳው አጋጣሚ የቱ ነው?

አለልኝ፡- በአንድ ወቅት አርባምንጭ እያለው ከባንክ ጋር  ባደረግነው የአዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታ ላይ በግብ ጠባቂያችን ጃክሰን ፊጣ ላይ የደረሰበት አደጋ በጣም ያስደነግጥና እንዲህ ያለ አደጋም አይቼ ስለማላውቅ እሱን አልረሳውም፡፡

ሊግ፡- የእረፍት ጊዜን በምን ታሳልፋለህ?

አለልኝ፡- በመተኛትና ፊልም በማየት፡፡

ሊግ፡- ወደ ግል ህይወትህ እናምራ የውሃ አጣጪህን አገኘህ?

አለልኝ፡- አዎን፤ ወደ ጋብቻው ባናመራም፤ የ7 ዓመት ፍቅረኛ አለችኝ፤ አዴይ ጌታቸው ትባላለች፤ ለእኔ ሁሉም ነገሬ ነች፤ እሷ ስከፋም ስደሰትም ከጎኔ በመሆን ብዙ ነገሮችን የምታደርግልኛና ዛሬ ላይ ለምገኝበት የኳስ ደረጃም ጥሩ ነገሮችን እያደረገችልኝ ስለሆነ ከልቤ ላመሰግናት እፈልጋለው፤ በጣምም እወዳታለው፡፡

ሊግ፡- በምን እናጠቃል?

አለልኝ፡- በምስጋና ነዋ!  መጀመሪያ አሁን ለምገኝበት ደረጃ የድንግል ማሪያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስን በመቀጠል ቤተሰቦቼን በተለይ እናቴን፣ ፍቅረኛዬን፣ ጓደኞቼን ከስር ጀምሮ እስካሁን ያሰለጠኑኝን ታሪኬን፤ በረከት ደሙን /ፈየራ/፣ የባህርዳር ከተማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱና ኮቺንግ ስታፉን እንደዚሁም ደግሞ አመራሮቹንና ደጋፊዎቹን አመሰግናለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P