Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለኢትዮጵያ ቡና የሚመጥነንን ውጤት ባናስመዘግብም አሁንም ከዋንጫው አልራቅንም” “ኮትዲቯር ላይ እንገናኝ፤ ከእንግዲህ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ብዙ ዓመትን አንጠብቅም” አማኑኤል ዮሃንስ /ኢትዮጵያ ቡና/

“ለኢትዮጵያ ቡና የሚመጥነንን ውጤት ባናስመዘግብም አሁንም ከዋንጫው አልራቅንም”
“ኮትዲቯር ላይ እንገናኝ፤ ከእንግዲህ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ብዙ ዓመትን አንጠብቅም”
አማኑኤል ዮሃንስ /ኢትዮጵያ ቡና/
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /ዋልያዎቹ/ እና ለኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን የመሀል ሜዳው ላይ ጥሩ ግልጋሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል፤ ከዛ ውጪም በኢትዮጵያ ቡና ክለብ ውስጥ እስካሁን ድረስ ቆይታን በማድረግና የሌላ ክለብ መለያን ባለማጥለቅም በብዙዎች ዘንድ ተለይቶም ይታወቃል፤ ይኸው አማካይ አማኑኤል ዮሃንስ ሲባል ዋልያዎቹ በካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎአቸው ቆይታን ባደረጉበት ጊዜ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየቱ አድናቆትን ከማትረፉ ባሻገር የጨዋታ ኮከብ ተብሎም ሊሸለም ችሏል፤ አማኑኤል በአፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎ ኳሶችን በተሳካ መልኩ ለቡድን አጋሮች ካቀበሉ ጥቂት የየሀገሩ የቶርናመንቱ ተጨዋቾች መካከልም አንዱ የነበረ ተጨዋች ሲሆን ይህን በወቅታዊ አቋሙ ጥሩ የሆነውን ተጨዋች የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ በብሔራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ዙሪያና ስለ ራሱ እንደዚሁም ደግሞ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ስለነበረው የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎና ስለ ቀጣዩ የሁለተኛው ዙር የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተንለት ምላሹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፤ መልካም ንባብ፡፡
ሊግ፡- የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎአችሁን ወደ ኋላ ዞር ብለህ ስትመለከተው በምን መልኩ አገኘኸው? የአንተስ የውድድሩ ጉዞ የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል?
አማኑኤል፡- መጀመሪያ እንደ ሀገር ወደ ውድድሩ ስፍራ ስናመራ እንደ እቅድ ያሰብነው ጥሩና አሪፍ ነገር ነበር፤ ይኸውም ከምድባችን ማለፍን ነበር የፈለግነው፤ ያም ሆኖ ግን በነበረን ጨዋታ ላይ ያስመዘገብነው ውጤት ብዙም ደስ የሚል አልነበረምና ያ መሆን መቻሉ ከፍቶናል፤ ወደ ራሴ ስመለስ ደግሞ ምንም እንኳን ብሔራዊ ቡድናችን ያስመዘገበው ውጤት ባያረካኝም ቢያሳዝነኝም በግሌ ባደረግኳቸው ግጥሚያዎች ግን በእያንዳንዱ እንቅስቃሴዎች ላይ ቁጥሮች ወጥተው ኳሱን የተቆጣጠርኩበት መንገድና ለጓደኞቼም ያቀበልኩበት ሁኔታ የተሳካ እና በአንዱ ጨዋታም ላይ የግጥሚያው ኮከብ ተጨዋች ተብዬ የተሸለምኩበት ሁኔታም ለእኔ ትልቅ ነገርም ሆኖልኝ ስለነበር በግሌ ጥሩ ጊዜን አሳልፌያለሁ ብዬ አስባለው፡፡
ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው ጥሩ ጥሩ እና የተሳኩ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ካቀበሉ ጥቂት የአፍሪካ ሀገራት ምርጥ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሆነህ አልፈሃል፤ በእዚህ ምን አይነት ስሜት ተሰማህ? ይሄንስ አሳካለው ብለህ ጠብቀህ ነበር?
አማኑኤል፡- እናሳካለን ብዬ ያሰብኩትና ሲያስጨንቀኝ የነበረው የቡድኑ ውጤት እንጂ በግል ስለማደርገው እንቅስቃሴና ምርጡ ተጨዋች ስለመባል አልነበረም፤ ቅድሚያም የሰጠሁት ለሀገር ውጤት ነበር፤ በእዛ ውስጥ ሆኜም ግን ኳሶች እንዳይበላሹብኝ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እጫወት ስለነበር የኮከብነቱን ሽልማት በአንዱ ጨዋታ ላይ እንደዚሁም ደግሞ እንደ አጠቃላይም ጥሩ እንቅስቃሴን ካሳዩ የአፍሪካ ሀገራት ተጨዋቾች መካከልም አንዱ ሆኜ ስሜ ሊጠራ በመቻሉም በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ሊግ፡- ዋልያዎቹ ካደረጓቸው የአፍሪካ ዋንጫው ጨዋታ ተሳትፎአቸው ምን ምን ነገሮችን ማሻሻል ይኖርባችኋል?
አማኑኤል፡- እንደ ቡድን ከራሳችን ተነስተን ማሻሻልና ማስተካከል አለብን ብዬ የማስበው ቅድሚያ የአካል ብቃታችንን ነው፤ በእዚህ በኩል እኛ በእግር ኳሱ ከፍ ባለ ደረጃ ላይ ከተቀመጡት ሀገራት ጋር መስተካከል አንችልምና ያለንን ነገር የበለጠ ማሳደግ ነው የሚኖርብን፤ ከእዛ ውጪም በውድድሩ ተሳትፎአችን ላይ የአየሩም ሞቃታማነትን እንደ ምክንያት ለማቅረብ ሳይሆን አስቸግሮን ስለነበርም ቀድመን ወደ ካሜሮን ከመሄዳችን አኳያ ጨዋታዎችንም ያለ ብዙ ድካም መጨረስ ይገባንም ነበርና እነዚህ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ነገሮች ናቸው፡፡
ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫ፣ በዓለም ዋንጫ እና በሌሎች መሰል የማጣሪያ ውድድሮች ላይ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲሸነፍ በምክንያትነት የተለያዩ ሰበቦች ይቀርቡ ነበር፤ አሁን ላይስ ያን ሰበብ የምታቀርቡበት ሁኔታ አለ? ከሌለ የሽንፈታችን ምክንያትስ ምንድን ነው ትላለህ? የሚያሸንፉንን ሀገራትስ ምን ብናደርግ እኛስ ልንረታቸው እና በእግር ኳሱስ ከፍ ባለ ደረጃ ላይ ልንገኝ እንችላለን?
አማኑኤል፡- አሁን ላይ ውጤት ስናጣ በምክንያትነት የማስቀምጥልህ ነገር ምንም የለም፤ ከዛ ይልቅ ወደ ራሳችን መመለስና ወደ ኋላም ዞር ብለን ራሳችንን መመልከት አለብን ብዬ ነው የማስበው፤ ሁሌም በአሰልጣኛችን እና በኮቺንግ ስታፉ የሚሰጠንን ተገቢ የሆነ ስልጠናን በአግባቡ ተከትለንም ልምምዳችንን መስራት እና ያመንበትንም እንቅስቃሴ በሜዳ ላይ መተግበር አለብንም ብዬ ነው የማስበው፤ በእግር ኳስ ጨዋታ እኮ ጥሩ ነገር ሰርተህ ልትሸነፍ ትችላለህ፤ ዋናው ቁም ነገሩ ግን ከእኛ የሚጠበቀውንና ያለንን ነገር አውጥተን አለመጫወት መቻልም ነውና ያን ሳታደርግ ስትቀር ነው የራስህ የሆነ ክፍተትም የሚባለውና ያለንን ነገር በጨዋታው ላይ ስላላሳየንም ጭምር ነው እንዴት ልበልህ….. /ንግግሩን እንደ ማቋረጥ ሲል/
ሊግ፡- ቀጥል አልኩት…..ከእኛ የሚጠበቀውን ነገር ስላላሳየንም ብለሃል…?
አማኑኤል፡- አዎን፤ ቡድናችን ላይ ደካማ ጎኖች አሉ፤ በእግር ኳስ ጨዋታ ብዙ ቡድኖች ጥሩ ሆነው ሊሸነፉ ይችላሉ፤ እኛን በቅርቡ የገጠመን ነገር ደግሞ የዓለም ዋንጫው የማጣሪያ ጨዋታ ላይ የነበረንን ጠንካራ ጎን በአፍሪካ ዋንጫው ላይ መድገም ስላልቻለን ነው ውጤትን ሊያሳጣንና ዋጋንም ሊያስከፍለን የቻለው፡፡
ሊግ፡- በዋልያዎቹም ሆነ በክለቦቻችን የኢንተርናሽናል ጨዋታ ተሳትፎች ላይ ብዙ ጊዜ የውጤት ማጣታችን ከአካል ብቃት ችግር ጋር ይያያዛል፤ የአካል ብቃት ችግር ብቻ ነው ውጤትን እያሳጣን ያለው? በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?
አማኑኤል፡- የአካል ብቃት ሲባል ብዙ ጊዜ ለእኔ አይገባኝም፤ ይሄ ልዩነት ከሌሎች ሀገራት ጋር ወደፊትም የሚቀጥል ነገር ነው ብዬም አስባለው፤ ከአቅም እና ከጉልበት ጋር ከሆነ መቼም እነሱ ላይ የመድረስ ብቃታችን ደካማ ነው ብዬም ነው የማስበው፤ ግን እንደ ራሴ አስተሳሰብ እኔ የምለው እኛ የራሳችን ነገር አለን፤ ያንን የራሳችንን በተለይም ከኳሱ ጋር ያለንን ነገር ማጠንከር እና ማጎልበት ነው እንጂ የሚያስፈልገው በአካል ብቃት ላይ እኛ እነሱ ላይ ስለማንደርስ ከጉልበት ጋር በተያያዘ ስላለው ነገር ባናስብ ጥሩ ነው፤ ከሆነ የማይታሰብ ነው የራሳችንን ነገር ማጎልበት ነው የሚያስፈልገው፤ በተለይም ደግሞ በአፍሪካ ዋንጫው ላይ የታዩብንን ድክመቶች በኮቺንግ ስታፉም ቢሆን ወደ ኋላ ተመልሶ በማየት ጠንካራ ጎኖችን እያበረቱ በደካማ ጎን ላይ ደግሞ አካል ብቃቱን ጭምር እየሰራን በመሄድና ጨዋታን ያለመጨረስ ችግራችንንም በማስተካከል የምንጓዝ ከሆነ የተሻለ የሚባል ብሔራዊ ቡድንን እንገነባለን፡፡
ሊግ፡- እኛ አለን የምንለው ነገር እነሱ የላቸውም ብለህ ታስባለህ?

አማኑኤል፡- እኛ ያለን ነገር እነሱ የላቸውም ሳይሆን እኛ ባለን ነገር ነው መቅረብ የምንችለው፤ እነሱ የኳስ ብቃቱ አላቸው፤ እኛ ግን ያለንን እንጂ የሌለንን ነገር አይደለም ማሳየት ያለብን፤ እነሱ ሁለቱም ነገር ቢኖራቸው እኛ ያለንን ነገር ደግሞ በደንብ አጠንክረን ልንችላቸው፤ እንደዚሁም ልንቋቋማቸው እንችላለን ብለን በምናስበው የራሳችን የሆነውን መንገድ የበለጠ ማጎልበት አለብን፤ የዓለም ዋንጫው ማጣሪያ ላይ እንዳሳየነው ዶሚኔት ያደረግንበትን የራሳችንን የሆነ ነገርን ማጠንከር አለብንም ብዬ ነው የማስበው፡፡
ሊግ፡- ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎ ካደረጓቸው ግጥሚያዎች ውስጥ የቱ ግጥሚያ አበሳጨህ?
አማኑኤል፡- እኔ በመጀመሪያው ጨዋታ እውነቱን ለመናገር ካሰብነው የውድድሩ ዓላማና እቅዳችን አንፃር አንድ ተጨዋቻችን ማለትም ተከላካዩ ያሬድ ባየህ በጊዜ በቀይ ካርድ ከሜዳ በመውጣቱና በእዚህ ጨዋታም ልናገኝ የምንችለውን ውጤት ማጣታችንን ሳየው በመሸነፋችን በጣም ነበር የተናደድኩት፤ ምክንያቱም ያን ጨዋታ ማሸነፍ እንችልና መጨረሻ ላይ ያደረግነውን ግጥሚያ ደግሞ አቻ ስለተለያየን በአራት ነጥብ ወደ ተከታዩ ዙር ለማለፍ እንችልም ነበር፤ ነገር ግን በኳስ እንዲህ ያሉ ነገሮች የሚያጋጥሙም ነገሮች ናቸውና ምንም ነገርን ማድረግ አትችልም፡፡
ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው ከአስተናጋጇ ሀገር ካሜሮን ጋር በነበረን የሁለተኛው ጨዋታ ቅድሚያ ግብ አስቆጠርን፤ ሁላችንም በደስታም ፈነጠዝን፤ ወዲያውም ደግሞ አቻ ሆንን፤ በኋላ ላይ ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ተከታታይ ጎሎች ተቆጠረብንና ውጤታችን ሳያምር በሰፊ ግብ ተሸነፍን፤ በጨዋታው ዙሪያ የምትለን ነገር ካለ?
አማኑኤል፡- ይሄ ጥያቄ ይለፈኝ፡፡
ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው በእግር ኳሱ ትላልቅ ከሚባሉት ሀገራት ጋር እኛ በብቃታችን ርቀት አለን?
አማኑኤል፡- በጣም የራቅን አይደለንም፤ ከእዚህ መድረክ ውጪ በሌሎች ጨዋታዎች ላይ እነሱን ተፋልመን አይተናቸዋልና፤ ያም ሆኖ ግን ብዙ መስራት እንዳለብንም ያሳየን ግጥሚያዎችም ሆነዋል፡፡
ሊግ፡- ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ከዚህ ቀደም 31 ዓመታት ፈጀብን፤ በመቀጠል ደግሞ 8 ዓመታት፤ ከእዚህ በኋላስ ስንት ዓመታት ይፈጅብናል?
አማኑኤል፡- ዓላማችን ብዬ የማስበው በየቶርናመንቱ የማጣሪያ ውድድሮች ላይ ተጫውተን ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፍ መቻል ነው፤ ለ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ኮትዲቯር ላይ እንገናኝም ብዬአለው፤ ከእንግዲህ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍም ብዙ ዓመትንም አንጠብቅም፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ ባሳለፍከው የእስካሁን መንገድ የኢትዮጵያ ቡናን እና የዋልያዎቹን መለያ በማጥለቅ እየተጫወትክ ነው የሚገኘው፤ በኳሱ የመጨረሻ ግብህን የት ላይ አስቀመጥክ?
አማኑኤል፡- በኳሱ የመጨረሻ ግቤ ከሀገር ወጥቶ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት መጫወት መቻል ነው፤ ለእዚህም ከአፍሪካ ዋንጫው በኋላ የጀመርኳቸው ፕሮሰሶች አሉና ፈጣሪ እነሱን ሲያሳካልኝ የምጫወትበት አጋጣሚው ይኖረኛል፡፡
ሊግ፡- አሁን ደግሞ ወደ ክለባችሁ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎ እናምራ፤ ኢትዮጵያ ቡና በአንደኛው ዙር የነበረው የውድድር ቆይታ ምን ይመስላል?
አማኑኤል፡- እንደ ኢትዮጵያ ቡና ከአምናው አንፃር ውጤቱ ብዙም ደስ አይልም፤ ደካማ ውጤትና የሚመጥነንን ውጤትም አይደለም እያስመዘገብን የምንገኘው፤ ያም ሆኖ ግን አሁንም ከዋንጫው ፉክክር አልራቅንምና በአዳማ ላይና በባህርዳር ከተማ ላይ በሚኖረን የውድድር ቆይታ ራሳችንን በተሻለ አቋም ላይ በማስቀመጥ እንደ ቀድሞው እልማችንና ግባችን ሁሉ አሁንም ዋንጫውን ለማንሳት እንጫወታለን፤ ያ ካልተሳካም የሚመጣውን ውጤት በፀጋ እንቀበላለን፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ቡና ጥሩ የነበረው የሐዋሳ ቆይታው ወይንስ የድሬዳዋ ቆይታው?
አማኑኤል፡- ከሜዳ እና ጥሩ ከመጫወት አንፃር የተሳካና አሪፍ ጊዜን ለማሳለፍ የቻልነው በድሬዳዋ ላይ በነበረን ቆይታ ነው፤ ከውጤት አንፃር ከሆነ ደግሞ ምንም እንኳን የሚመጥነን ባይሆንም 9 ያህል ጨዋታዎችን ያደረግነው ሐዋሳ ላይ ስለነበር ያ ቆይታችን ነው ሊጠቀስልን የሚችለው”፡፡
ሊግ፡- ቤትኪንጉን ቅ/ጊዮርጊስ እየመራ ነው፤ ከተከታዮቹ ክለቦችም በተቀራረበ ነጥብ ላይ ይገኛል፤ የቅ/ጊዮርጊስ የእናንተን ቡድን በ11 ነጥብ ያህል ሊጉን መምራት ልታመጡት ካሰባችሁት ስኬት አንፃር ስጋትን ፈጥሮባችኋል…….?
አማኑኤል፡- ለእኔ ምንም አይነት ስጋትን አልፈጠረብኝም፤ በሁለታችን መካከልም የተወሰነ የጨዋታ ልዩነትም ነው ያለው፤ ይኸውም የ11 ነጥብ ነው፤ ከሌሎቹ ክለቦች ጋርም ከዛ ባነሱ የነጥብ ልዩነቶችም አንሰንም ነው የምንገኘውና ከላይ ካሉት ሁሉም ቡድኖች ጋር እርስ በርስ የምንገናኝበት ጨዋታ ስላለም ከእኛ የሚጠበቀውን ነገር በማድረግ ይኸውም ጨዋታዎችን በማሸነፍ ወደ ሻምፒዮናነቱ ፉክክር የማንመጣበት ምክንያት ምንም የለም”፡፡
ሊግ፡- ባሳለፍነው የውድድር ዘመን አቡበከር ናስር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የተሳካ ጊዜን አሳልፎ ነበር፤ የኮከብነትን ሽልማቶችም ጠራርጎ ወስዶ ነበር፤ እስካሁን ባለው የአንደኛው ዙር ውድድርስ የቱ ተጨዋች ለአንተ ጎልቶ ወጥቶብሃል?
አማኑኤል፡- ይሄ ከባድ ጥያቄ ነው፤ ለእዚህ መልስ አልሰጥህም፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዘንድሮ ለየት ብሎ የቀረበብህ ቡድን ማን ነው?
አማኑኤል፡- በውጤትም ቀዳሚ ስፍራ ላይ ስላለ እና በአንድም ጨዋታ ላይ ስላልተሸነፈም ቅ/ጊዮርጊስ ነው ዘንድሮ ለየት ብሎ የቀረበብኝና ጥሩ ቡድኑ፡፡
ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እስካሁን ካደረጋችሁት ጨዋታዎች መካከል ያስቆጨ ጨዋታ አለ?
አማኑኤል፡- አዎን፤ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረግነው ግጥሚያ በራሳችን መዘናጋት ግብ ተቆጥሮብን የተሸነፍንበት ስለነበር ያ ጨዋታ ያስቆጨኛል፤ በእዚህ ፍልሚያ ቢያንስ አቻ መለያየት እንችል ነበር፡፡
ሊግ፡- አሁን ለሁለተኛው ዙር እየተዘጋጃችሁ ከመሆናችሁ አንፃር ምን ነገርን ከእናንተ እንጠብቅ?
አማኑኤል፡- ኢትዮጵያ ቡና የጨዋታ ሀሳብ ያለው ክለብ ነው፤ በዛም ላይ እየሰራበትም ነው፤ በያዝነው ነገርም እንቀጥላለን፤ በእዚህም በመጓዝ ጥሩ ጨዋታን ከማራኪና ከምንፈልገው ውጤት ጋር ለማምጣት ስራችንን እየሰራን ይገኛል፡፡
ሊግ፡- ስለ ደጋፊዎቻችሁ አንድ ነገርን በልና እናጠቃል?
አማኑኤል፡- ስለ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ሁሌም ነው የምለው፤ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ አብረውንም ነው ያሉት፤ ለሚሰጡንም ድጋፍ እናመሰግናችኋለን፤ የተሻለ ነገር ሰርተን በመምጣትም በውጤት ልናስደስታቸውም እንፈልጋለን፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P