Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ባሳለፍኩት የኳስ ህይወት መቆጨት ሳይሆን ተምሬበታለሁ” “በኳሱ ላልደረስኩበት ትልቅ ስፍራ ማንም ሰው ላይ ጣት ሳልቀስር ራሴን ነው ተጠያቂ የማደርገው” “ወደ በፊቱ ስምና ዝናዬ ዳግም እመለሳለሁ” ሮቤል ግርማ /አዲስ አበባ ከተማ/

“ባሳለፍኩት የኳስ ህይወት መቆጨት ሳይሆን ተምሬበታለሁ”
“በኳሱ ላልደረስኩበት ትልቅ ስፍራ ማንም ሰው ላይ ጣት ሳልቀስር ራሴን ነው ተጠያቂ የማደርገው”
“ወደ በፊቱ ስምና ዝናዬ ዳግም እመለሳለሁ”
ሮቤል ግርማ /አዲስ አበባ ከተማ/
በከዚህ ቀደም የእግር ኳስ ህይወቱ የተሳካና ምርጥ የሚባል የጨዋታ ጊዜን አሳልፏል፤ በተለይም ደግሞ ባደገበት የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ቡድን ውስጥ በነበረው የኳስ ቆይታው በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፎለት ወደ ኢትዮጵያ ቡናም እንዲዘዋወር የጥርጊያ መንገድም አመቻችቶለት መቆየቱና ወደ ቡድኑም መግባቱ ይታወሳል።
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኑ የግራ መስመር የኮሪደር ስፍራውን በመሸፈን በጥሩ ሁኔታ ይጫወት የነበረው ሮቤል በኳሱ ላይ ቀድሞ የነበረውን ስምና ዝና ከኢትዮጵያ ቡና ከለቀቀ በኋላ ያጣ ሲሆን በኳሱ ላይ ለትልቅ ደረጃ ተጠብቆ በአስፈላጊው ስፍራና ቦታ ላለመገኘቱም ራሱን ተጠያቂ እያደረገም ይገኛል።
ሮቤል በእዚህ ጉዳይ ዙሪያ ላይ ሲናገርም “” ይህንንም ብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎው በአስራ አራተኛ ስፍራ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣዩ ዙር ላይ ተጠናክሮ በመቅረብ አመርቂ ውጤት እንደሚያስመዘግብና እሱም ዳግም የቀድሞ ስሙንና ዝናውን እንደሚመልስም እየተናገረ ይገኛል።
የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ከአዲስ አበባ ከተማው ተጨዋች ሮቤል ጋር ያደረገው ቆይታም እንደሚከተለው ይቀርባል። መልካም ንባብም ብለናል። ተከታተሉት።
ሊግ፦ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የአንደኛው ዙር የውድድር ቆይታችሁ እና ተሳትፎአችሁ ምን መልክ ነበረው?
ሮቤል፦ በሐዋሳ የነበረን የውድድር ቆይታ አጀማመራችን እና አካሄዳችን ከሞላ ጎደል አሪፍ እና ጥሩ ነበር። ከሐዋሳ ለቀን ወደ ድሬዳዋ ከተማ ስንጓዝ ግን ለእኛ ቡድን በምንፈልገው መልኩ ውጤትን እንድናስመዘግብ ስላላደረገንና ውጤታችንሞ አስደሳች ስላልነበር በምንፈልግበት ሁኔታ ለመጓዝ አልቻልንም፤ ከእዛም በመነሳት እንደ መዲናዊቷ /ከተማችን/ ክለብ የሚያስፈልገን ነገር ላይ በመስራት በቀጣዩ ዙር ላይ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ እየተዘጋጀን ይገኛል”።
ሊግ፦ በቤትኪንጉ ተሳትፎአችሁ በጥንካሬና በድክመት ደረጃ የምታነሳው ዋናው ነገር ምንድን ነው?
ሮቤል፦ ከጥንካሬው ስነሳ በስኳድ /በስብስብ/ ደረጃ ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች በቡድናችን ውስጥ ስላሉን ኳሱን በህብረት መጫወታችን ጥሩ ጎናችን ሆኖ ሳለ አብዛኛውን ጊዜ ጎል ጋር ደርሰን ያገኘናቸውን የግብ አጋጣሚዎች ለመጠቀም አለመቻላችን እና የልምድ ማነስ ሁኔታን በክፍተት ደረጃ የማነሳው እና ዋናውም ችግራችን ነበር።
ሊግ፦ የአንደኛው ዙር ለአንተ በጥሩ ጊዜ ያለፈ ነው?
ሮቤል፦ እንደ ማንኛውም ተጨዋች ቅድሚያ ለቡድኑ ነው የምሰጠው። እንደ ግለሰብ ደስተኛ የምትሆነው ቡድኑ ውጤት ሲኖረው ነው ብቻህን የምትፈጥረው ነገርሞ የለም አንድ ላይ ቡድኑ በህብረት ውጤት ሲኖር የምታሳልፈው ቆይታና ጊዜ አሪፍ ይሆናል እንደ ውጤት ማጣታችን ጥሩ ጊዜን አላሳለፍኩም ብዬ አላስብም።

ሊግ፦ ዘንድሮ ጎሎችን ለማስቆጠር ችለሃል፤ እነዛን ሁኔታዎች እንዴት ነው የምትመለከታቸው፤ ምርጧ ጎልህስ የትኛው ነች?
ሮቤል፦ የመጀመሪያ ጎሌን ሐዋሳ ላይ ነበር ያስቆጠርኩት፤ ለእኔ ምርጥና ማራኪ የነበረችው ጎል ግን በሰበታ ከተማ ላይ ያስቆጠርኳት የቅጣት ምት ግብ ነች።
ሊግ፦ በእግር ኳሱ በመጣህበት መንገድ ጥሩ ጅማሬህ ነበረህ፤ ያንን አካሄድህን ግን በትልቅ ስፍራ ላይ እንድትደርስ ብዙ ተጠብቆብህ ለማስቀጠል አልቻልክም፤ በአንተ ከፍ ባለ ደረጃ ላይ አለመገኘትም የተቆጩ አሉ፤ በእዚህ ዙሪያ የምትለው ነገር ካለ?
ሮቤል፦ የእውነት ነው ብዙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎችና እኔን የሚያደንቁኝ ተመልካቾች ባሰቡኝ እና በጠበቁኝ መልኩ በትልቅ ደረጃ ላይ እንዳልገኝ ስላላደረገኝ የምወቅሰው እኔው ራሴን ነው። ህብረተሰቡ ባሰበኝ መልኩም ላለመድረሴም በምክንያትነት የምጠቅሰው ያኔ ልጅነት ስለነበረኝና ከአጠገቤም እንደ ታላቅ ሆኖ የሚመክረኝ ወንድም ስላልነበረኝ ያ በጣሙን ሊጎዳኝም ችሏል። ታላቅ ወንድም ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ እሆን ነበር። ልጅነቱ ማንንም አልጎዳም እኔኑን ነው የጎዳኝ፤ አሁን ብዙ ነገር አስተምሮኝ እንደ በፊቱ ሳይሆን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ በዲስፕሊን ብቻ ሳይሆን በዕድሜም በመልካም ሁኔታ ላይ ስለምገኝ በብዙ ነገርም ጥሩ ሆኜ ለመቅረብ ዝግጁ ነኝ፤ በእዛም ደረጃ ለመቅረብ ልምምዴን በአግባቡም እየሰራሁ ነው። ያለፈውን ስህተቴንም በስራም እክሳለሁ።
ሊግ፦ አብዛኛዎቹ የሀገራችን እግር ኳስ ተጨዋቾች መልካም ጅማሬያቸው ወደ አልሆነ አቅጣጫ እና ጎዳና ሲሄድ ጥፋቱን ወደ ሌላ አካል በማዞር ሲወስዱት ይታያሉ፤ አንተ ግን ራስህን ተጠያቂ አድርገህ ስትወቅሰው ሰምተናል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ?
ሮቤል፦ አዎን እኔ በራሴው ስህተት ራሴን ነው ተወቃሽና ተጠያቂ ያደረግኩት። እከሌ እንዲህ አድርጎኛል ብዬም ሰዎችን ተጠያቂ አድርጌ አስቤም አላውቅም። መጀመሪያ አንተ ለሁሉም ነገር ዝግጁ ስትሆን ነው ሁሉንም ነገር የምታውቀው። አንተ ያላስተካከልከውን ነገር መንገድ አሳይተህ መንገዱ ሲበላሽብህ ሰው ላይ ማመካኘት ሀሳብ ነው ብዬ አልደግፈውምና ላለፉት ስህተቶቼ ራሴን ነው የምወቅሰው።
ሊግ፦ በቀጣይ ጊዜው የኳስ ህይወት የበፊቱን ሮቤል ግርማ መመልከት እንችላለን?
ሮቤል፦ አዎን፤ ለእዛ አትጠራጠር። የሚያስፈልገኝን ነገር ከልምምድም ሆነ ከዲስፕሊን አንፃር የተማርኳቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ወደ በፊቱ አቋሜ እንደምመለስ እርግጠኛ ነኝ።
ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በምን ውጤት የሁለተኛው ዙር ላይ እንጠብቃችሁ? የውድድር ዘመኑ ሲጀመርስ በምን ውጤት ነው ሊጉን እናጠናቅቃለን ብላችሁ ያሰባችሁት?
ሮቤል፦ ከከፍተኛው /ብሔራዊ/ ሊግ እንደመምጣታችን የመጀመሪያው እቅዳችን የነበረው ሊጉ ላይ መቆየት ነበር። ያን ለማሳካትም አንደኛው ዙር ብዙ መስታወትም ሆኖናል። ብዙ ክፍተቶችና የልምድ ማነስ ችግሮች ነበሩብንና ለሁለተኛው ዙር ጥሩ ጅማሬ እንዲኖረን መማሪያም ሆኖናልና ሊጉ ሲጠናቀቅ እኛም በእዚሁ የሊግ ተሳትፎ ላይ እንደምንቀር በጣም እርግጠኛ ነኝ።
ሊግ፦ አምና አቡበከር ናስር በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ጎልቶ ወጥቶ ነበር። አሁንስ በአንደኛው ዙር ላይ የቱን ተጨዋች በተሻለ ብቃትና አቋም ላይ አግኝተከዋል?
ሮቤል፦ በአንደኛው ዙር ላይ እንደ ጨዋታ አጀማመራችን በብዙ ጎኑ በምርጥ እና ወጥ በሆነ አቋም ላይ በመገኘት ጎልቶ ወጥቷል የምለው ተጨዋች ባይኖረኝም የቅዱስ ጊዮርጊሱ የአብስራ ተስፋዬ፣ ሌላው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጨዋች ጋቶች ፓኖም፣ የሲዳማ ቡናው ይገዙ ቦጋለ እና የኢትዮጵያ ቡናው ዊሊያም ሰለሞን ጥሩ ለመንቀሳቀስ ችለዋል ብልም ከሁሉም ተጨዋቾች በተሻለ ደግሞ የአብስራ ተስፋዬ ነው ለእኔ በጣም ጥሩ የሆነ ጊዜን ያሳለፈው።
ሊግ፦ ባሳለፍከው የእግር ኳስ ህይወት ትቆጫለህ?
ሮቤል፦ በኳስ ህይወቴ መቆጨት ሳይሆን ተምሬበታለሁ። ቁጭት ሳይሆን ያሳለፍኩት ነገር መማሪያም ነው የሆነኝ። ፈጣሪ ይመስገን የተለየ ያጋጠመኝ ነገርም የለም። አሁን ድረስ ከኳስ ህይወትም አልወጣሁም። ብዙ ጊዜ የብሄራዊ ቡድን ውስጥ የመመረጡን ዕድል አግኝቼ ነበርና እነዛን ዕድሎች ባለመጠቀሜ ብቻ ነው የተቆጨሁት። ከእዛ ውጪ በኳሱ ህይወቴ ምንም የጎደለብኝ ነገር የለም፤ ለዛም ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁኝ። በሱፐር ሊጉም ላይ
ሁለት ዓመት ያህል ለቤንች ማጂ ዞንና ለአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን በመጫወቴ ብዙ ትምህርቶችን አግኝቼበታለሁና ከእዛም በመነሳት ኳሱን ያቆሙ ብዙ ጓደኞቼም አሉና እነሱንሞ ባለኝ አቅም እየረዳዋቸው ስለሆነም ከራሴ ካሳለፍኩት ህይወቴና ከጓደኞቼም የተማርኳቸው ብዙ ሁኔታዎች ስላሉ ሁሉም ነገሮች ለእኔ መማሪያዬ እንጂ መቆጫዬ አይደሉም።
ሊግ፦ የአንተ ምርጡ የእግር ኳስ ህይወት በየት ክለብ እያለህ ያሳለፍከው ነው ?
ሮቤል፦ በአብዛኛው ባደግኩበት ክለብ መብራት ሀይል ውስጥ የነበረኝን ነዋ! ምርጡን የኳስ ጊዜዬ እዛ እያለሁ ለተከታታይ አራት ዓመታት ላሳልፍ ችያለሁ። ወደ ኢትዮጵያ ቡናም ካመራሁ በኋላም ለሁለት ዓመታት ቆይታን ሳደርግም ጥሩ ጊዜን ነው ለማሳለፍ የቻልኩት።
ሊግ፦ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ስታመራ ከአንተ ብዙ ነገር ነበር የተጠበቀው፤ ከላይ እንደገለፅከው ጥሩ ጊዜን ከማሳለፍህ ጋር በተያያዘ ባሰብከው መልኩ ነው የሄደልህ?
ሮቤል፦ አዎን፤ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ስሄድ በጣም ጥሩ ጊዜን ነው በወቅቱ ያሳለፍኩት። ያኔ ክለቡም በአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው /ማንጎ/ እየተመራ ሳለ የሊጉ መቋረጥና አንድ አንድ ከፌዴሬሽን ጋር ያለ የጨዋታ መርሀ ግብር ራሱን ይዞ ባለመሄዱ ሁለተኛ እንዲወጣም ምክንያት ሆኗል ብዬም አስባለው እንጂ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በተጠበቀብኝ መልኩ ጥሩ ጊዜን ነው ያሳለፍኩት።
ሊግ፦ 2003 ላይ ኢትዮጵያ ቡና የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ አንተ የመብራት ሀይል ተጨዋች ሆነህ ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር በተደረገው እና አቻ በተለያያችሁበት ጨዋታ ባሳየከው ምርጥ ብቃት ዋንጫውን እንድናነሳ የጥርጊያ መንገዱን አመቻችቶልናል በሚል የክለቡ ደጋፊዎች አሁንም ድረስ ስምህን እየጠሩ ያነሱሃል፤ በእዛ ግጥሚያ ዙሪያ ወደ ኋላ መለስ ብለህ የምትለው ነገር ካለ?
ሮቤል፦ የሚገርምህ ያን ጨዋታ ያደረግኩት ኢትዮጵያ ቡናን ብቻ ሀስቤ ሳይሆን ከሊጉ ላለመውረድ ይጫወት የነበረውን ክለባችንን መብራት ሀይልንም ጭምር በማሰብ ነበር። ከእነሱ ላይ ያገኘነው ነጥብም ለእኛ በጣም አስፈላጊያችንም ነበር። በአጋጣሚ ፈጣሪ ሲረዳን እኛ እነሱን ነጥብ ስናስጥልለት በሰዓቱ ለኢትዮጵያዋ ቡና አጋጣሚው ስለተስተካከለለት ወደ ሻምፒዮንነት እንዲያመራም በርን ከፍቶለታል። ያኔም የውድድር ዘመኑ ከተጠናቀቀ በኋላም የእኛ ከሊጉ ያለመውረድ ጥረታችን በመሳካቱና ኢትዮጵያ ቡናም ዋንጫ በመብላቱ በጣም ደስተኛ ነበርኩ፤ ባደረግኩት የጨዋታ እንቅስቃሴም ጭምር የተደሰትኩበት ጊዜ ስለነበር የማይረሳ ጊዜን ነው ለማሳለፍ የቻልኩት፤ ለእኔ ያኔ ድርብ ድልም ነበር።
ሊግ፦ አንተ የመብራት ሀይል ተጨዋች ሆነህ ነው ኢትዮጵያ ቡና የሊጉን ዋንጫ በማንሳቱ ተደስቻለሁ ያልከው፤ የኢትዮጵያ ቡናዎች ደጋፊ ነበርክ ማለት ነው?
ሮቤል፦ አዎን ከልጅነቴ ዕድሜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ነኝ፤ አሁንም ጭምር የምናገረውም ነው። ያም ሆኖ ግን ለጨዋታ ወደ ሜዳ ስገባ ኳስ መጫወቱ ስራዬ ስለሆነ ለቀጠረኝ ክለብ አቅሜን ሳልሰስት የሚጠበቅብኝን ብቃት በማሳየት ለማልያዬ እሞታለሁ።
ሊግ፦ ስለ ቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወትህ ምን ትላለህ? እግር ኳስን ጠግበህ ተጫውተሃል?
ሮቤል፦ የእግር ኳስን እንደፈለግኩት ተጫውቼያለሁ ብዬ አላስብም። በአንድ አንድ ልጅነት ያጠቃኝ በነበሩ የራሴ የሆኑ ባህሪዎች ካለኝ ነገር እንደ ልቤ በሚገባኝ ደረጃ ኳሱን ተጫውቻለሁ ብዬ አላስብም። ያው ፈጣሪ ዕድሜና ጤናውን ሰጥቶኝ ባለችኝ ዕድሜ ጥሩ ጊዜን አሳልፌ በፍቅር፣ በሰላም እና በጤና የእግር ኳስ ጊዜዬን መጨረስ ነው የምፈልገው።
ሊግ፦ ብዙ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ጉዳቶች፣ የስነ-ልቦና ችግሮች እና ሌሎች መሰል ነገሮች ከሜዳ አጥፍቷቸው ኳስን እስከ ማቆም ደረጃ ያደርሳቸዋል? በተለይም ደግሞ ጉዳት አንተን ለእዛ ደረጃ ሊያጋጥምህ የተቃረበበት ወቅት ነበር?
ሮቤል፦ በፍፁም፤ እኔ በጤና ደረጃ ፈጣሪ ይመስገን ተጎድቼ አላውቅም፤ ኳስን ጉዳት ደርሶብኝም ከሜዳ አርቆኝም አያውቅም። እስካሁን ያለኝ የጤና ሁኔታም መቶ ፐርሰንት በአካል ብቃትም ሆነ በጤና ከሚገባው በላይ ጥሩ ነገሮችን ለመስራት ዝግጁ ነኝ። ያለፈውን ህይወቴንም መድገም ሳልፈልግ ባለኝ የኳስ ህይወት ጥሩ ጊዜን አሳልፌ ደስተኛ ህይወትን መኖር እፈልጋለሁ።
ሊግ፦ ወደ ውሃ አጣጪ ህይወት ገባህ?
ሮቤል፦ አዎን። እንደ ማንኛውም ሰው ገብቼበታለሁ። እናቴ አሁን በህይወት የለችም፤ ካረፈችም ዘጠኝ ወር ሆኗታል። እሷ እያለች ወደ እዚህ መስመር ውስጥ እንድገባ ትነግረኝም ነበር የእኔ ወደ እዛ ህይወት መግባት እሷ ካለፈች በኋላ መሆኑ ቢያስቆጨኝም ግዴታ ከአንድ ወደ ሁለት መግባት በብዙ ነገሮች ህይወትን ለመቀየር ይቻላልና ለእዛ ዝግጁ ነኝ ፈጣሪ የፈቀደም ቀን ሁሉንም ነገር የእሷን ስም ጨምሮ በይፋም አወጣዋለሁኝ።
ሊግ፦ የውሃ አጣጪህ ስሟ በይፋ ባይገለፅም ከአንተ የእግር ኳስ ህይወት ጀርባ እንዴት ትገለፃለች?
ሮቤል፦ እንደ ማንኛውም ሰው ትዳር ስትይዝ ጠንካራ ጎንህ የትዳር አጋርህ ነች። እሷ ለእኔ በብዙ መንገድ ከፍተኛ ነገርም አድርጋለች፤ ከወላጅ እናቴና ከእህቶቼም ቀጥሎ ብዙ የምትጨነቅም ነበረች። ብዙ ያስተካከለችልኝም ነገር አለ። ከጎኔ በመሆኗም ህይወቴ ተስተካክሏል ብዬም አስባለው። በጣምም ቅን ሰውም ናት።
ሊግ፦ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን እንዴት ተመለከትከው?
ሮቤል፦ የውድድሩ ይዘት ወደ እኛ ሀገር ከመጣ በኋላ ብዙ መሻሻሎችና ለውጦች አሉ። ግን የሜዳ አለመመቸት እና የዳኝነት ችግሮች ሊቀረፉ አለመቻላቸው በክፍተት ደረጃ የማነሳው ነው። እነዚህ ክፍተቶች መስተካከል ከቻሉ ብዙ ለውጦች እንደሚመጡ ማሳያ ነገሮች አሉና ባለው የውድድር ጉዞ በጣም ደስተኛ ነኝ።
ሊግ፦ ወደ ማጠቃለሉ እናምራ፤ በመጨረሻ ምን ትላለህ?
ሮቤል፦ በእግር ኳስ ህይወቴ እስካሁን ለእኔ ጥሩ ነገሮችን ተመኝታችሁልኝ ባሰባችሁት ደረጃ ላይ ባለመድረሴ ትልቅ ይቅርታን እጠይቃለሁ። በቀጣዩ ጊዜም የራሴን አቋም በማስተካከል እና ወደ ቀድሞ ብቃቴም ሙሉ ለሙሉ በመመለስ ያዘነብኝን ደጋፊም ማስደሰት እፈልጋለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P