Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“እግር ኳስን የሚያውቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ እኔን አይሰድበኝም”ጋዲሳ መብራቴ /ቅ/ጊዮርጊስ/

 

በተለይ ለሊግ ስፖርት

መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የቅ/ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ
ስፍራ ተጨዋች ጋዲሳ መብራቴ ከመከላከያ
ጋር በነበራቸው የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ
ዋንጫ ጨዋታ ቡድናቸው ከውድድሩ
ተሸንፎ መውጣቱ በጣም እንዳስቆጨው
በመግለፅ የዕለቱም ጨዋታ ላይ በእርሱ
ላይ የደረሰበት ተቃውሞና ስድብ ኳስን
ከሚያውቁ እውነተኛ የቅዱስ ጊዮርጊስ
ደጋፊዎች የመጣ ሳይሆን በግል ሌላ ችግር
ካለባቸው ኳስን ከማያውቁ ደጋፊዎች
የመጣም እንደሆነ ሀሳቡን ሀዘን
በተሞላበትም ስሜት ሊገልፅ ችሏል፡፡
የቅ/ጊዮርጊሱ ጋዲሳ መብራቴን
ከመከላከያ ጋር ተጫውተው ስለደረሳባቸው
ሽንፈት፣ የተወሰኑ ደጋፊዎች እርሱ ላይ
ስላደረሱበት ተቃውሞና ስድብ እንደዚሁም
ደግሞ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ
እያደረጉት ስላለው የውድድር ተሳትፎና
ሌሎችን ጥያቄዎች አንስተንለትም ምላሹን
እንደሚከተለው ሰጥቶናል፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ዘንድሮም የሊጉ
የውድድር ተሳትፎው ላይ ጥሩ አጀማመር
የለውም፤ ምክንያት ብለህ ብትጠይቅ
ምላሽህ ምንድነው የሚሆነው?
ጋዲሳ፡- የውድድሩ ጅማሬያችን ላይ
ክለባችንን ከወዲሁ ውጤት እያሳጣው
የሚገኘው ዋናው ነገር የእንግሊዛዊውን
አዲስ አሰልጣኝ የጨዋታ ታክቲክ
በፍጥነት ልንላመድና ልንግባባው
ስላልቻልን ነው፤ እንግሊዛዊው አሰልጣኝ
ስቲዋርት ለቡድናችን ይዞት የቀረበው
አጨዋወት ካለፈው አመት አሰልጣኝ ጋር
ሲነፃፀር አዲስና የተለየ ነው፤ የቡድናችን
ተጨዋቾችም የአጨዋወቱን ታክቲክ ገና
አልተረዱትም፡፡ ይህን የጨዋታ ታክቲክ
ለመላመድም ከልምምድ ሰዓታችን ጊዜ
አንስቶም ጠንክረን በመስራት አጨዋወቱን
ለመረዳት የተለያዩ ጥረቶችን እያደረግንም
ነው የሚገኘው፤ ታክቲኩን ለመልመድም
ጊዜ ስለሚያስፈልግ ሁሉንም ነገር
በትዕግስት ልንጠብቀውም ነው የሚገባን፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ የሊጉ ጀማሬው
ላይ ላጣቸው ውጤቶች ሌሎችስ ችግሮች
የሉበትም?
ጋዲሳ፡- አሉበት እንጂ፤ ይሄም
ሆኖ ግን ያንን ያህል የጎላ የሚባሉ
አይደሉም፤ በዘንድሮ የሊጉ ጅማሬያችን
ላይ በምናደርጋቸው ጨዋታዎችም ሆነ
በጥሎ ማለፉ ጨዋታ በመከላከያ ተሸንፈን
ከውድድሩ ለመውጣት እንድንችል ያደረገን
ዋናው ምክንያት ከላይ የጠቀስኩት ቢሆንም
ሌሎችም ችግሮች ነበሩብን፤ ለምሳሌ
አሰልጣኙ በሚከተለው የጨዋታ ታክቲክ
ስናጠቃ የሰው ቁጥራችንን አብዝተን
አንሄድም ነበር፤ ሌላው የመስመር
ተጨዋቾቻችንም ከዚህ በፊት የሌላ ክለብ
ተጨዋቾች እያሉ በአብዛኛው በመከላከሉ
ላይ ያመዝኑና በተወሰነው መልኩ ደግሞ
ያጠቁና አጥቂውንም ያግዙ ነበር አሁን ላይ
ግን ከመከላከል ወደ ማጥቃቱ ላይ ሲሄዱ
እንደበፊቱ ሳይሆን በሁለት መንገድ ላይ
የመቆም አይነትን እንቅስቃሴን ስለሚያሳዩ
እነዚያን ክፍተቶች በቀጣዮቹ ጊዜ
ልምምዶችና ታክቲኩን በደንብ ስንላመድ
የምናስተካክላቸው እና የምናርማቸው ነው
የሚሆነው፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ
በመጫወት ያልተላመዳችሁት
የእንግሊዛዊው አሰልጣኝ የጨዋታ ታክቲክ
ምንድነው? በፍጥነትስ ከታክቲኩ ጋር
የምትላመዱት ይመስልሃል?
ጋዲሳ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ
መጀመሪያ የነበረው አሰልጣኝ ኳስን መሰረት
አድርገን እንድንጫወት ይፈልግ ስለነበር
ከእሱ ጋር ከጊዜ በኋላ በደንብ ተዋህደን
ጥሩ ስራን እየሰራን መጥተን ነበር፤ የአሁኑ
አሰልጣኝ ደግሞ የሚከተለው የጨዋታ
ፍልስፍና በራስህ ሜዳ ላይ ኳስን ብዙ
ሳታቆይ የቀጥታ ኳሳችን /ዳይሬክት ኳስ/
ወይንም ደግሞ ረጅም ኳስ የበዛበትንም
አጨዋወት ነው የሚጠቀመውና ያንን
ለመላመድ ነው ጥረትን እያደረግን
የሚገኘው፤ ቀደም ሲል እንከተል ከነበረው
አጨዋወት ወጥተን አሁን አዲሱ አሰልጣኝ
ወደሚፈልገው አጨዋወት ለመግባት ጊዜ
ቢፈልግም የመከላከያ ዕለት ያሳየነውን
እንቅስቃሴ መድገም ከቻልን ግን በፍጥነት
ወደ ጨዋታው ታክቲክ የማንገባበት እና
የማንላመድበት ምንም አይነት ምክንያት
የለም፡፡
ሊግ፡- መከላከያን በተፋለማችሁበት
የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ
ተሸንፋችሁ ከውድድሩ ወጥታችኋል፤
ለሽንፈቱ ምክንያት ብለህ የምትጠቅሰው
ምንድን ነው፤ በተመዘገበው ውጤትስ ምን
ተሰማህ?
ጋዲሳ፡- ከመከላከያዎች ጋር በነበረን
ጨዋታ ምንም እንኳን ተሸንፈን ከውድድሩ
ብንወጣም በእንቅስቃሴው ደረጃ እኛ
የተሻልንበት ነበር፤ በጨዋታው ለአስር
ጊዜያት ያህል በብዛት እነሱ ጎል ጋር
ደርሰናል፤ ከእረፍት በፊት ብቻ ሁለትና
ሶስት ጎሎችን አስቆጥረን ማሸነፍም
እንችል ነበር፤ ቡድናችን ያን ዕለት በነበረው
ብቃት እንዲህ አጥቅቶም አያውቅም፤
ጎል ያለማስቆጠራችን ብቻ ለሽንፈትም
ዳርጎናልና የተመዘገበው ውጤት ለእኛ
የሚገባን አልነበረም፤ የውጤቱን ማጣት
ከሁሉም በላይ ያስቆጨን እና ያናደደን
እኛ ተጨዋቾችንም ነበር፤ በውጤቱ
ደጋፊዎቻችንም ያን ዕለት በጣም ሊያዝኑ
ችለዋል፤ በኳስ ጨዋታ ላይ ሊያጋጥም
በሚችል አይነት ሽንፈትም ነው ዕድለኛ
ሳንሆን ቀርተን እነሱ ያገኙትን የቅጣት
ምት በመጠቀምና ወደግብነትም በመለወጥ
አሸንፈውን ከውድድሩ ሊያስወጡን
የቻሉት፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ አንድ ተስተካካይ
ጨዋታ ቢቀረውም በሊጉ መሪ ኢትዮጵያ
ቡና በ6 ነጥብ ተበልጦ በ4ኛ ደረጃ ላይ
ተቀምጧል፤ አሁን ላይ ካላችሁ ወቅታዊ
አቋም በመነሳት ወደ ሻምፒዮናነቱ
ለምታደርጉት ጉዞ ይሄ ለናንተ እንቅፋትና
ስጋት ይሆንባችኋል?
ጋዲሳ፡- የሊጉ የውድድር ተሳትፎአችን
ሁሌም የሚያምረው አፈፃፀማችን እንጂ
አጀማመራችን አይደለም፤ በእዚህ በኩል
ለእኛ ቡድን ስጋት የሚሆንብን ክለብ
ፈፅሞ የለም፤ በመሪነትና በተከታይነት
ደረጃ ላይ የሚገኙት ቡድኖች ብዙ ጊዜ
ለዋንጫ የሚጫወቱ ክለቦች አይደሉም፤
የሊጉ ውድድርም ገና መጀመሩና በርካታ
ጨዋታዎችም የሚቀሩትም ነው፤ ከመሪው
ቡና ጋር አሁን ያለን የነጥብ ልዩነትም ገና
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረን 6 ብቻ
ነው፤ ልዩነቱም ብዙ የሚባል አይደለም፡
፡ ቅ/ጊ ዮርጊስ ደግሞ ከዚህ በፊት በሰፊ
የነጥብ ልዩነቶችም ተበልጦና ተመርቶ
ነጥቡን አጥቦ በመምጣት ውድድሮችን
ያሸነፈበት ጊዜያቶችም አሉና ያንን ታሪክ
ወደ ኋላ መለስ ብለን በማስታወስና
በማሰብ የቀጣይ ጨዋታዎቻችን ላይ
ትኩረትን ስለምናደርግ የሚያሳስበን
ምንም ነገር የለም፤ በሊጉ ውድድሮች ብዙ
ጨዋታዎችም በሜዳችን ጭምር ስላለን
ለእያንዳንዶቹ ግጥሚያዎቻችን ትኩረት
ሰጥተንና ጠንክረን ቀርበን የዘንድሮውን
ዋንጫ እኛ እናነሳለን፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ አንድአንድ
ደጋፊዎች መከላከያን በተፋለማችሁበት
ጨዋታ ሲቃወሙክ ብሎም ደግሞ
ጨዋታው ሲጠናቀቅ ሲሰድቡህ ነበር፤ ያኔ
ምንድን ነው የተሰማህ?
ጋዲሳ፡- የእግር ኳስ ጨዋታ እንዲህ
ነው፤ ዓምናም በዚህ ዙሪያ ተናግሬያለው፤
ኳስ ተጨዋች ስትሆን ሙገሳ እንዳለ
ሁሉ ተቃውሞ ስድብና ትችትም አለ፤
ያ ግን በአግባቡ ነው ሊሆን የሚገባው፤
ተቋውሞውና ስድቡ ግን መስመር አልፎ
ሲሄድ የክለብንም የሀገራችንንም እግር
ኳስ ነው የሚጎዳው፤ የእግር ኳስን
ስትጫወት የእግር ኳስን የማያውቅ ሰው
ሊናገርህ ይችላል፤ በግል ችግር ያለበት
ሰውም ሊናገርህ ይችላል፤ የመከላከያው
ጨዋታ ላይም በእኔ ላይ ይደርስ የነበረው
ተቃውሞና ስድብም በግል ከእኔ ጋር ችግር
ካለበት አካል የመጣ እንጂ የእግር ኳስን
ከሚያውቁ እውነተኛ የቅዱስ ጊዮርጊስ
ደጋፊዎች የመጣ ነው ብዬ አላስብም፤ ኳስን
የሚያውቅ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊ ያን ዕለት
እኔን ሰድቦኛል ብዬ አላስብም፤ የሰደቡኝ
በግል ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው፤ ገና
ለሟሟቅ ስሄድ ጭምር ነው ይሰድቡኝም
የነበሩት፤ ያኔም ራሴን የፀባይ ችግር
ያለበት የተቃራኒ ቡድን ተጨዋች ነኝ?
ወይንስ የተከበረውን የቅ/ጊዮርጊስን ማሊያ
አለበስኩም እንዴ እስከማለት ደረጃም
ራሴን እስከመጠራጠር አድርሶኝም ነበርና
በነገሩ በጣም ነው ልገረም የቻልኩት፤
በእኔ ላይ ይደረስ የነበረው ስድብ ከባድ
ነበር፤ አንድአንዶቹ ቃላቶችም በእጅጉ
ሞራልን የሚነኩ ነበሩ፤ የሐዋሳ ከተማ
ክለብ ውስጥ በነበረኝ የአራት አመታት
ቆይታዬ እግር ኳስን የተጫወትኩት
በጥሩ ብቃትና ችሎታዬ ነው፤ ያለኝን
ችሎታም በደንብ አድርጌ ጠንቅቄ ነው
የማውቀው፤ ወደቅዱስ ጊዮርጊስ ስመጣም
ይሄንን ብቃቴን ለምወደውና ልጫወትበት
ለምፈልገውም ውጤታማው ቡድን
ለማሳየት እና ብዙ ታዋቂ ተጨዋቾችም
ስላሉ ከእነሱም ጋር መፎካከርንም
ስለፈለግኩ ብመጣም ብዙ የመጫወት
እድሎችን ስላላገኘው የሚጠበቅብኝን
ያህል ግልጋሎት ለመስጠት አልቻልኩም፤
የዘንድሮ የውድድር ዘመን ላይ ግን ለክለቤ
ቅ/ጊዮርጊስ ምርጥ ብቃቴን ለማሳየት
በሚገባ ተዘጋጅቼና የመሰለፍ ዕድሉንም
በተደጋጋሚ ጊዜ ሳገኝ ምንያህል በጥሩ
ብቃት ላይ እንደምገኝ ለማሳየት በከፍተኛ
ፍላጎት ላይ በምገኝበት ሰዓት ተቀይሬ
በገባሁበት የመከላከያው ጨዋታ ላይ ገና
አንድ ኳስን አግኝቼ ያንን ወደ ግብነት
ሳልቀይር በመቅረቴ በእኔ ላይ ተቃውሞ
መነሳቱ ከምን ተነስቶ እንደሆነ አልገባኝም፤
የመከላከያው ተቀይሬ የገባሁበት ጨዋታ
እኮ ገና የመጀመሪያዬ ነው፤ ያኔ እኔን
ማበረታታት ሲገባ መቃወም ጥሩ ነው
ብዬ አላስብም፤ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ
የመጣሁት የሌሎች ክለቦችን ጥሪ ወደኋላ
አድርጌ ለቡድኑ ለመጫወትና ለመጥቀም
ነው በቡድኑ ብዙ የመጫወት እድልን
ስላላገኘው ግን በሚፈለገው መጠን ክለቡን
ማገልገል አልቻልኩም፤ ስለእኔ ወቅታዊ
ብቃት ማወቅ የሚቻለው ደግሞ ዘንድሮ
የልምምድ ሜዳ ላይ መጥቶ የሚያየኝ
ደጋፊና ተጨዋቾቻችን ናቸው፤ አሁን
በጥሩ ብቃት ላይ ነው የምገኘው፤ ከቅ/
ጊዮርጊስ ብወጣ እንኳን ሌላ ክለብ በደንብ
እንደምጫወት አውቀዋለው፤ ያን ዕለት
የደረሰብኝ ስድብ ለእኔ ብዙ ችግር የለውም
ወደፊት ግን ክለቡን ወደው ወደእኛ ቡድን
ለሚመጡ ተጨዋቾች ምን አይነት ስሜትን
ነው የሚፈጥርባቸው፤ ሁኔታውንስ
እንዴትስ ነው ሊቀበሉት የሚችሉትና
የተፈጠሩት ሁኔታዎች አፋጣኝ ርምት
ሊደረግባቸው የሚገባቸው ናቸው፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ
ለመጫወት አይመጥንም፤ ከዛ አልፎም
ራሱንም አይጠብቅም በማለት አንተን
የሚወቅሱ አካላቶች አሉ፤ ለዚህ ምላሽ
አለ…?
ጋዲሳ፡- ቅ/ጊዮርጊስን አይመጥንም
ያሉኝ አካላቶች እነማን ናቸው? በምን
መስፈርትስ ለክተውኝ ነው እንዲያ ሊሉ
የቻሉት፤ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ የመጣሁት እኮ
ለክለቡ ትጠቅማለህ ቡድኑንም ትመጥናለህ
ተብዬ ነው፤ ያኔ ብዙ ክለቦች በከፍተኛ
ክፍያ ሊወስዱኝ በፈለጉበት ሰዓት ላይም
ነው የእነሱን ጥያቄ አልቀበልም በማለት
ለክለቡ ልፈርም የቻልኩትና እኔ ለቅ/
ጊዮርጊስ የምመጥን ተጨዋች ነኝ፤ ለዚህ
ክለቡ ውስጥ ያሉት ተጨዋቾች ጭምር
በልምምድ ሜዳ ላይ ከማሳየው እንቅስቃሴ
በመነሳትም ምስክርነታቸውን ሊሰጡ
የሚችሉት፤ ብዙ የመጫወትና የመሰለፍ
እድሎችን በተደጋጋሚ ባላገኘሁባቸው
ጨዋታዎች ለክለቡ አይመጥንም የሚለውን
ነገር እኔ አልቀበለውም፡፡
የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ ባለሁበት
የአሁን ሰዓት ላይ እኔን አስመልክቶ ራሱን
አይጠብቅም ለሚለው የሰዎች አመለካከትም
ምላሼን የምሰጠው በአሁኑ ወቅት ለክለቤ
ቅ/ጊዮርጊስ ውጤት ማማርና የራሴንም
ብቃት በሜዳ ላይ የመሰለፍ እድልን
በተደጋጋሚ በማገኝባቸው ጨዋታዎች
ላይ ከሌላው ጊዜ በጣም በተሻለ መልኩ
ለማሳየት በከፍተኛ ዝግጅት ውስጥ
ያለሁበት ሰዓት ላይ ስለሆንኩ ራሴን
በደንብ እየጠበቅኩ ነው የምገኘው፤ የቅዱስ
ጊዮርጊስ ቆይታዬ ላይ ዘንድሮ በሁሉም
መልኩ ማለትም ልምምድ ላይ በማሳየው
ብቃትም ሆነ በማህበራዊ ህይወቱም በኩል
መልካም በሚባል ሁኔታ ላይም ስለምገኝ
ለዛም ደግሞ እንደ እነ ሳላህዲን ሰይድ፣
በኃይሉ አሰፋ ቱሳና አስቻለው ታመነን
የመሳሰሉት ተጨዋቾችም ባለኝ ለውጥ
ምስክርነታቸውን ስለሚሰጡና ከጎኔ ሆነው
ብዙ ነገርንም እያገዙኝም ስለሆነ የቅ/
ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በእኔ ችሎታ እምነት
የሌላቸውንም ሆነ እንደ ማንኛውም
ኳስ ተጨዋች ደግሞ ስሳሳት እንኳን
የሚቃወሙኝ ደጋፊዎች ካሉ የእነሱን
አመለካከት እንዲቀይሩ የማደርግበት
ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ የሰው ልጅ ሁሌም
ቢሆን ከወደቀበት መነሳቱ አይቀርም
በኳስ ጨዋታም ስህተት ሊኖር ይችላልና
ሁሉንም ነገር እኔ እንደአመጣጡም ነው
የምቀበለውና የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ
መጀመሪያ መቅደም ያለበት ትችት ሳይሆን
ማበረታታትም ነው ብዬ አስባለው፡፡
ሊግ፡- መከላከያን ዛሬም በድጋሚ
ትፋለማላችሁ፤ ምን ውጤትን
ትጠብቃለህ?
ጋዲሳ፡- መከላከያን የምንገጥምበት
የዛሬው ጨዋታ ለእኛ የክለባችንን ማንነት
የምናሳይበት ነው፤ ባለፉት ተከታታይ
ሁለት የጥሎ ማለፉ ጨዋታዎች እነሱ
ሊያሸንፉን ችለዋል፤ መከላከያን ቅ/ጊዮርጊስ
አይችለውም የሚለውም ነገር በጣም ነው
የሚያናድደኝ እና ዛሬ የሚኖረን ጨዋታ
የተጠና እና በውጤትም ደረጃ በማሸነፍ
ያማረም ይሆንልናል፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ የእዚህ ዓመት
የተጨዋቾች ስብስብ ዋንጫ ለማንሳት
የሚያስችላችሁ ነው? ቡድናችሁን በዓመቱ
መጨረሻ የት ላይ እናግኘው?
ጋዲሳ፡- የቅ/ጊዮርጊስ የእዚህ ዓመት
የተጨዋቾች ስብስብ ማንም ክለብ ጋር
የሌለ ነው፤ ስኳዳችን አስፈሪም ነው፤ የፊት
መስመሩ ላይ ብትሄድ እንኳን በተደጋጋሚ
ጊዜ የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ በመባል
የሚሸለመው ጌታነህ ከበደንና ሌላውን
የግብ አዳኝ ሳላዲን ሰይድን ይዘናል፤
ይሄ ሁሉ የተጨዋቾች ስብስብ እያለን
የፕሪምየር ሊጉ የውድድር ጅማሬያችን
ላይ ጥሩ ውጤት ባለማስመዝገባችን
ሊቆጨን ቢችልም ቡድናችን ተስተካክሎ
ወደለመደው ኃይልነት እንደሚመለስ ሙሉ
እምነት ነው ያለኝ፤ ቅ/ጊዮርጊስ አሁን
ላይ በሚፈልገው መጠን ውጤትን አጥቶ
የሚገኘው አዲሱን ታክቲክ ካለመላመድ
አንፃር እንጂ የተጨዋቾች ድክመት ኖሮበት
አይደለም፤ የሊጉን ውድድር አሁን ላይ
አንዱ ይመራል፤ በመቀጠል ደግሞ ሌላው
ይረከበውና ሊጉን በተራው ይመራል፤ ቅ/
ጊዮርጊስም የሆነ ወቅት ላይ መሪነቱን
ይጨብጣል ይሄ ሁሉ በሊጉ ሊከሰት
ቢችልም የእኛ ክለብ ግን በፈለገው ነጥብ
ሊጉን ሁሌም ማንም ይምራ ውድድሩን
እያከናወነ አስቀድሞ ሻምፒዮና እንደሚሆን
ያውቀዋልና የእዚህ አመቱ ባለድል
የምንሆነው እኛ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነን፡፡
ሊግ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት
ይከብዳል?
ጋዲሳ፡- በፍፁም አይከብድም፤
አንድ አንድ ሰዎች ናቸው አላስፈላጊ
ነገሮችን ይናገሩክና የግድ እንዲከብድህ
የሚያደርጉህ፤ የሃገሪቱ እግር ኳስ እኮ
ገና አልዳገም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ኳስን
መጫወት በጣም ቀላል ነው፤ ሰዎች
ናቸው የሚያከብዱት፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን
ግለፃቸው ብንል ምላሽህ ምንድን ነው
የሚሆነው?
ጋዲሳ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች
በሊጉም ሆነ በማንኛቸውም ጨዋታዎች
ላይ ቡድኑ በሜዳውም ከሜዳውም
ውጪ ሲጫወት በስፍራው በመገኘት
ድንቅ የሆነ ድጋፋቸውን ያለ አንዳችም
ስስት የሚሰጡን ደጋፊዎች ናቸው፤
ውጤት ስናመጣም ስናጣም ከጎናችን
ሆነውም ያበረታቱናል፤ ምርጥና
እውቀት ያላቸውም ደጋፊዎቻችንም
ናቸውና ለሚሰጡን ድጋፍ ያለኝ ምስጋና
ከፍ ያለም ነው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….
ጋዲሳ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
የመከላከያው ጨዋታ ዕለት ተቀይሬ
ገብቼ ተሰልፌ በእኔ ላይ የተሰነዘረብኝን
ስድብና ተቃውሞ ተገቢ አይደለም
በሚል ከጎኔ ሆነው አይዞህ እና በርታ
በማለት ስሜትህ እንዳይጎዳ በሚል
ድጋፋቸውን የሰጡኝ የቡድኔ አካላቶችና
ደጋፊዎች አሉና ለእነሱ በውጪ አገርም
ቢሆን የማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ እኔን
የሚቃወም ፅሁፍን የተመለከቱ ሰዎች
ሞራልህ እንዳይነካ በማለት ከጎኔ
የቆሙም አሉና እነሱን ለማመስገን
እፈልጋለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P