Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የዘንድሮው የሠሜን አሜሪካ ስፖርት ፌስቲቫል በአትላንታ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል “ተወዳጁ ጠ/ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ በመክፈቻው ፕሮግራም ላይ ቢገኙልን ደስታችን ወደር የለውም” አቶ አብይ ኑርልኝ የESFNA ፕሬዝዳንት

በተለይ ለሊግ ስፖርት
በአለምሰገድ ሰይፉ

“አሁን በኢትዮጵያ ፀሃይ ወጥቷል፤ ለዚህ ስኬት ላበቁን ጓዶችና በተለይ ደግሞ ለተወዳጁ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ
አህመድ ላቅ ያለ ክብር አለን” ይላሉ በሰሜን አሜሪካ ባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን የ/ESFNA/ ፕሬዝዳንት አቶ አብይ ኑርልኝ፡፡

ያኔ ከለውጡ በፊት ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው መግባትን እየናፈቁ እንዳይመጡ በታፈኑበት ጊዜ ይህ በአሜሪካ የሚገኘው
ፌዴሬሽን ኢትዮጵያኖችን በማቀራረብና በማገናኘት የማይዘነጋ ውለታን ከፍሏል፡፡ ከምንም በላይ ዛሬ ሁላችንም ለኮራንበት
አንፀባራቂ ለውጥ መገኘት በአሜሪካ የሚገኘው ማህበረሰብ የከፈለው ውለታ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡
ይሄን ለውጥ መንከባከብ ብቻ ሳይሆን ሂደቱ እንዳይቀለበስ ሁላችንም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን መሰለፍ አለብን የሚሉት አቶ አብይ
ኑርልኝ የነገዋን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለማነፅ ከስፖርቱ ባሻገር ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ለማገዝ ከፍተኛ ተነሳሽነት አላቸው፡፡
ከምንም በላይ በአሁኑ ጊዜ የተወዳጁ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ባለቤት ቀዳሚዊት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በበጎ ተግባራት ላይ እያደረጉ
ያለውን እንቅስቃሴ የሰሜን አሜሪካው ፌዴሬሽን እገዛ በማድረግ እና አብሮ በመስራት የለውጡ አንዱ አካል የመሆን ፍላጎቱ
እንዳለቸው የESFNA ፕሬዝዳንት አቶ አብይ አዲስ አበባ በነበራቸው ቆይታ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር
አለምሰገድ ሰይፉ አውግተውታል፤ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነው ቆይታም ይሄንን ይመስላል፡፡

ሊግ፡- ፌዴሬሽናችሁ ከተመሰረተ ዘንድሮ ስንተኛ አመቱን አስቆጠረ?

አቶ አብይ፡- ፌዴሬሽኑ እንደአውሮፓ አቆጣጠር በ1984 የተመሰረተ ሲሆን፤ ዘንድሮ 36ኛ አመቱን ይዟል፡፡
ሊግ፡- በየአመቱ በሰሜን አሜሪካ የሚደረገው ታላቅ ውድድር የሚፈጀውን በጀት ማወቅ ይቻለኛል?
አቶ አብይ፡- በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ያነሳከው፤ ይህ ፌዴሬሽን በውስጡ 9 የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት አሉት፤ እነዚህም
ምክትል ሊቀመንበር፣ ፀሃፊ፣ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፣ ገንዘብ ያዥ፣ የንግድ ማዕከላቱን የሚቆጣጠር፣ ፋይናንስ ቼር፣ ቶርናመንት
ኮርዲኔተርና የውስጥ ኦዲተር ናቸው፡፡ እነዚህ ዘጠኝ የኮሚቴ አባላት በየጊዜው እየተገናኙ ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ ማስኬጃ
የሚያስፈልገውን ወጪ ከማሰናዳት ባሻገር ውድድሩ በጥሩ ሁኔታ መካሄድ የሚችልበትን መንገድ የማመቻቸት ሃላፊነት አለባቸው፡፡
ከእኛ በተጨማሪም ከየቲሙ የተውጣጡ 31 የቦርድ አባላት አሉ፡፡ በመሆኑም የቀረፅነውን አጀንዳ ለእነርሱ አቅርበን
አስተያየታቸውን በማዳመጥ ወደ ተፈፃሚነት እናመራለን፡፡
ሊግ፡- የወጪውን ጉዳይ አላነሱልኝም?
አቶ አብይ፡- በየአመቱ የሚደረገውን ይህን ውድድር ለማካሄድ በጣም በትንሹ ከ500 መቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊየን ዶላር
ይፈጃል፡፡ ወጪው የሚለያየው እንደከተማው ውድነትና የኑሮ ሁኔታ ነው፡፡ በአነስተኛ ከተሞች በምናዘጋጅበት ጊዜ ከ550 እስከ
650 ሺህ ዶላር ይጠይቃል፤ ውድ ከተሞች በሚባሉት የአሜሪካ የምስራቅ ግዛቶች በምናዘጋጅበት ጊዜ ደግሞ ከ1 ሚሊየን ዶላር
በላይ ወጭ ይጠይቃል፡፡


ሊግ፡- ይህ ከፍተኛ የሆነ ወጪ በምን በምን ላይ የሚውል ነው?
አቶ አብይ፡- እንግዲህ እነዚህ ወጪዎች ለዳኞች፣ ለዕቃ፣ ለፅዳት፣ ለስቴድየም ኪራይ፣ ለተዋናይ፣ ለአርቲስቶችና ዘፋኞች፣
ለመጓጓዣ፣ ለሆቴሎችና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎች የሚከፈል ነው፡፡
ሊግ፡- ቀደም ብለው እንደገለፁልኝ በየአመቱ የምታወጡት ወጪ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ከየት አምጥታችሁ ነው ይሄን ወጪ
የምትሸፍኑት?
አቶ አብይ፡- እንዳልከው በየአመቱ ለዚህ ውድድር ማስኬጃ የምናወጣው ገንዘብ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ይሄን ክፍተት
ለመድፈን አንዳንዴ ስፖንሰሮችን እንፈልጋለን፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አመት ያደረግነው ውድድር ወጪውን ለመሸፈን እንዲረዳን ሰቨን

ኢለቨን ከተባለ ድርጅት ጋር የስፖንሰር ስምምነት ላይ በመድረስ ድጎማ አድርጎልን የተለያዩ ወጪዎችን ከመሸፈን ባሻገር በነፃ ውሃ
ያቀርቡልናል፡፡
እንደሚታወቀው በየአመቱ ከሚሳተፉት 31 ቡድኖች ውስጥ 800 የሚደርሱ ተጨዋቾች አሉ፡፡ የሚደረጉት 74 ግጥሚያዎች
ከመሆናቸው አንፃር ተጨዋቾቹ ውሃ ስለሚያስፈልጋቸው በስፖንሰር ሺፕ የሚያግዘን ኩባንያ ይህን ወጪ ይሸፍንልናል፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ ደግሞ ኡበር የተባለው ኩባንያ የምናካሂደውን እንቅስቃሴ በደንብ አይተውና ገምግመው እንዲሁም ጥቅምና ጉዳቱን
መዝነው “ይህ በጣም መደገፍ የሚገባው ዝግጅት ነው” በማለት መቶ ሺህ ዶላር ሰጥተውን ወጪያችንን ለመሸፈን ችለናል፡፡
ከእነርሱ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ድርጅቶች ያግዙን ነበር፤ ለምሳሌ ሃበሻ ሲሚንቶ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣
ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የመሳሰሉ ኩባንያዎች አንዳንድ ድጋፍ ያደርጉ ነበር፤ ሆኖም በወቅቱ ሃገሪቱ ውስጥ በነበረው ችግር
ምክንያት እዚህ አሜሪካ ሃገር መጥተው በፕሮግራሙ ላይ አልተሳተፉም፡፡
እናም ይሄን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈን ይቻል ዘንድ ከስፖንሰር አድራጊ ኩባንያዎች ከምናገኘው ገንዘብ ባሻገር በዝግጅቱ ላይ
ድንኳኖችን በመሸጥ ለምሳሌ የደረቅና የምግብ አቅርቦት እንዲሁም የበጎ አድራጎት ድንኳኖች እናዘጋጃለን፡፡ ቢያንስ በአንድ ውድድር
ላይ እስከ 80 የሚደርሱ ድንኳኖችን እናከራያለን፡፡ እኛ ለዚህ ድንኳን ወደ 30 ሺህ ዶላር የሚጠጋ ወጪ እናደርጋለን፡፡ ከዚያም
ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚያልቅ አገልግሎት ለሚሰጡ ድርጅቶች እናከራያለን፡፡ በተረፈ ከኢትዮጵያ ለሚመጡ በጎ አድራጎት
ድርጅቶችም ድንኳኑን የምንሰጠው በነፃ ነው፡፡
ሊግ፡- ለምሳሌ መጥቀስ ይቻላል?
አቶ አብይ፡- ሜቅዶንያ፣ መሰረት ሂውማኔቲሪያል፣ሲስተር ዘቢደርና ሌሎችም በርካታ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን እንደጉማለን፡፡
የተቀሩት አትራፊ ለሚባሉት ቢያንስ 20 ፐርሰንት ጨምረን ድንኳን እናከራያቸዋለን፡ ይሄን የምናደርገው በአሉን ለማክበር
የሚመጣው ህዝብ እንዳይጉላላና በዛው ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው ነግደው ለማትረፍ የሚፈልጉ ወገኖችን ለማገዝ ነው፡፡
ሊግ፡- ዝግጅቱ ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ለዚህ የምታውሉት ጊዜ የግል ስራችሁን አይበድልባችሁም?
አቶ አብይ፡- በጣም ከባድ ስራ ነው፡፡ ነገር ግን የሚያቀለው ምንድነው በአሜሪካ አገር የሚኖሩና በተለያየ የሙያ ዘርፍ
ተሰማርተው የሚሰሩ ኢትዮጵያኖች አሉ፡፡ አካውንታንት፣ ነጋዴ፣ ሃኪም አሊያም ማርኬቲንግ ዳይሬክተር ናቸው፡፡ እነዚህ ቀና
ኢትዮጵያኖች ከምናወጣው ወጪ በበለጠ በጉልበታቸውና በእውቀታቸው ከሚገባው በላይ ያግዙናል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ለሚሰጡት
አገልግሎት ይከፈላቸው ቢባል ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ ለአንድ ውድድር የምናወጣው ከ500 እስከ 1 ሚሊየን ዶላር
የሚደርሰው ወጪ በእጥፍ ይጨምር ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እዛ ያለነው ዘጠኙም የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከጊዜም
ባሻገር ሁሉንም ወጪ ከኪሳቸው አውጥተው ነው ለዚህ የተቀደሰ አላማ በጋራ የሚንቀሳቀሱት፤ እናም በገንዘብ በማይተመነው
ነፃ ግልጋሎት ድጋፍ ባይኖረን ኖሮ ውድድሩ በየአመቱ እውን ባልሆነ ነበር፡፡
ሊግ፡- 36 አመታትን ያስቆጠረው የሰሜን አሜሪካ የባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን በእስካሁኑ ጉዞ ምን የሚታይ ነገር አስመዝግቧል
ማለት ይቻላል?
አቶ አብይ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ በስፖርቱ ዘርፍ ያለፉ ወጣቶች እዚህ አሜሪካ ሃገር መጥተው ልምዳቸውን የበለጠ
አዳብረውበታል፤ ከዚህም ባሻገር ወጣቶች ያላቸውን ችሎታ አሳድገው በስኮላርሺፕ እዚህ አሜሪካ ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች
እንዲጫወቱ በር ከፍተናል፡፡ ከስፖርቱ ባሻገር ደግሞ በባህሉ ዘርፍ ሃገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች መገኛ ሃገር
ከመሆኗ አንፃር በበአሉ ላይ አንድ ቀን ሪዘርቭ በማድረግና “የኢትዮጵያ ቀን” በሚል ስያሜ ስለሃገራችን ባህልና ወግ
የምንወያይበትና የምንመካከርበትን ዝግጅት እናደርጋለን፡፡ በዚህ ረገድም በጣም ስኬታማ ሆነናል ማለት ይቻላል፡፡
በንግዱ በኩል ደግሞ ይሄን አመታዊ በአል ተንተርሶ በሚደረገው የንግድ እንቅስቃሴ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ትርፋማ እንዲሆኑ
አስችለናል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ እዚህ የሚገኙት ሚዲያዎች ለምሳሌ ኢሳት፣ አባይ ሬዲዮና ሌሎችንም እዛ ውድድር ተገኝተው
ድጋፍ እንዲደረግላቸውና እንዲያድጉ በማስቻል የምንችለውን ነገር ሁሉ አድርገናል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የእኛ ፌዴሬሽን አትራፊ
ተቋም ባለመሆኑ ከተዘጋጀው ውድድር ላይ የሚተርፈውን ገንዘብ ወደአገራችን በመላክ ለምሳሌ በኤች አይ ቪ በሽታ ወላጆቻቸውን
ላጡ ህፃናት፣ ውሃ በሌለባቸው ገጠራማ ከተሞች የውሃ ጉድጓዶችን በማስቆፈር፣ ለአበበች ጎበና ህፃናት ማሳደጊያ ገንዘብ በመላክ
እንደዚሁም በጦርነት ምክንያት ተሰደው ለሚንከራተቱ ዜጎች 150ሺህ ዶላር በመላክ የቅርብ አጋርነታችንን እና ብሄራዊ
ተቆርቋሪነታችንን በተግባር አሳይተናል፡፡ ወደፊትም በዚሁ እንቀጥላለን፤ በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ በሃገራችን የተደረገውን
አንፀባራቂ ለውጥም እንደግፋለን፡፡
ሊግ፡- ከለውጡ በፊት በርካታ ዜጎች ወደሃገራቸው መግባት በማይችሉበት ጊዜ እናንተ ኢትዮጵያውያንን በማቀራረቡ ረገድ
የነበራችሁ ሚና እንዴት ይገለፃል?

አቶ አብይ፡- እንግዲህ እኛ ኢትዮጵያኖች ብዙ ከመሆናችን አንፃር በሃይማኖት፣ በአመለካከትና በፖለቲካ አቋም ልዩነቶች ቢኖሩም
ለበአሉ በሚኖረን የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተቻችለንና ተነጋግረን ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን እንደሆነና አባቶቻችን ያስረከቡንን
ታላቅ አገር ማገዝ እንዳለብን እንነጋገራለን፡፡ እኛ ምንም እንኳን ያለነው አሜሪካ ቢሆንም መንፈሳችን ግን ሁሌም ሃገራችን
ውስጥ ነው፡፡ በመሆኑም ሃገራችንን ከማሰብ ባሻገር ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በማስተዋወቅ ብዙ ሰርተናል፡፡ የተለያዩ
የፖለቲካ ፓርቲዎች በግንባር ቀርበው እንዲገናኙ በማስቻል የላቀ ሚና ተጫውተናል፡፡ ቢያንስ ላለፉት 36 አመታት ኢትዮጵያዊነትን
በመስበክ፣ ባንዲራችንን ከፍ አድርገን በማውለብለብና ባህላዊ ምግባችንን ፕሮሞት በማድረግ ኢትዮጵያዊነት ከሀገር ውጪም
ጎልቶ እንዲታይ ለማስቻል ብዙ ለፍተናል፡፡ ምክንያቱም ለማናችንም ቢሆን ከኢትዮጵያ በላይ ማንም የለምና፡፡
ሊግ፡- ዘንድሮ አትላንታ ላይ የሚደረገው የስፖርት ፌስቲቫል በሃገራችን ከተፈጠረው ለውጥ ማግስት የሚደረግ ከመሆኑ አንፃር ምን
አዲስ ነገር ይኖራል?
አቶ አብይ፡- በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፤ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ ዘንድሮ በአትላንታ የሚደረገው ዝግጅት ለ36ኛ ጊዜ ነው፡፡
በፌዴሬሽናችን የእስካሁኑ ጉዞ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ አዲስ የተሾሙት አምባሳደር ክቡር አቶ ፍፁም ይገኛሉ፤ እንዲሁም
ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ፡፡ የዚህ አይነቱ አሰራር ከአሁን በፊት ተደርጎ አይደለም
ተሞክሮ እንኳን አያውቅም፤ ከመንግስትም እውቅና አግኝተን አናውቅም ነበር፡፡ ከባለፈው ጊዜ ጀምሮ ግን እጅግ ተወዳጁ ጠቅላይ
ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ ከመጡ ጊዜ ጀምሮ እዚህ እየሰራን ላለነው ነገር እውቅና በመስጠት አጋርነታቸውን
አረጋግጠውልናል፡፡ እውቅና መስጠት ብቻ ሳይሆን እሳቸው ራሳቸው በበአሉ ላይ በመገኘት አጋርነታቸውን ለማሳየት የተነሳሱበት
ሁኔታም ተፈጥሮአል፡፡


እውነት ነው የምልህ በቁማችን እያለን ይሄን የመሰለ ነገር በማየታችን ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ አሁን በአገራችን ፀሃይ
ወጥቷል፡፡ ይሄን ለውጥ ማገዝ ደግሞ የሁላችንም ሃላፊነት ነው፡፡ እኛ ደግሞ በአሜሪካ በርካታ ደጋፊዎች ስላሉን እነርሱን
በማስተባበር ሃገራችንን መቶ ፐርሰንት ለመደገፍ ቆርጠን ተነስተናል፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህች ውድ አገር ማንነት ላይ የሚደራደር
የለም፡፡ አሁን የተፈጠረው አንፀባራቂ ለውጥ የብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ ደስታ የፈጠረ ቢሆንም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ይሄን ለውጥ
ለመቀልበስ የሚንደፋደፉ አንዳንድ ወገኖች እንዳሉ እናውቃለን፤ እናም ይሄ ነገር እንዲቆም ለማስቻል ስፖርታዊ ጨዋነት
ተመክሮአችንን ይዘን በመምጣት ከህዝባችን ጋር ተቀላቅለን የመስራት ከፍተኛ ፍላጎት አለን፡፡ ሃገራችንንም በሚገባ እናግዛታለን፡፡
ባለፈው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሲናገሩ በአንድ ቀን አንድ ዶላር ለምትወዷት አገራችሁ ብትለግሱ ባሉት መሰረት እኛ ይህን
የተቀደሰ አላማ የሚያራምደው አካል ኤጀንት መሆን ነው የምንፈልገው፡፡
ይህ አሁን እሳቸው የተናገሩትን ነገር ከአሁን በፊት እኛ ውስጥ ለውስጥ እናደርገው የነበረው የድጋፍ አይነት ነው፡፡ ለምሳሌ በየአመቱ
የክብር እንግዶችን እንጠራለን፡፡ ስፖርተኛ የሆኑትንም ያልሆኑትንም፤ ለምሳሌ ከስፖርተኞች መካከል እነ አባተ ስዩም፣ ሰውነት
ቢሻውን ስንጋብዝ ከነይድነቃቸው ጀምሮም በርካታ ስፖርተኞችን ጋብዘናል፡፡
ከዚህ ባሻገር ስፖርተኞች አገራቸውን ጠቅመው ካለፉ በኋላ አስታዋሽ የላቸውም፤ እናም ለእነዚህ ወገኖች የገንዘብ ድጎማ
እናደርጋለን፡፡ ምንም እንኳን በወቅቱ በነበረው የአመለካከት ልዩነት የፖለቲካ ሰዎችን መጋበዝ ከባድ ቢሆንም እኛ ግን ለአገራቸው
ውለታ ፈፅመዋል የምንላቸውን ፖለቲከኞች ሳይቀር በድፍረት እየጋበዝን እውቅናና ክብር ሰጥተን እንሸኛቸዋለን፡፡
ሊግ፡- በደማቅ ሁኔታ በሚከበረው የአትላንታው ፌስቲቫል ላይ የለውጡን ሃዋሪያ ዶክተር አብይ አህመድን ለመጋበዝ
አላሰባችሁም?
አቶ አብይ፡- በባለፈው አመታዊ ስብሰባችን ላይ ትልቁና ዋነኛ አጀንዳችን ሆኖ የቀረበው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር
አብይ አህመድ ጉዳይ ነበር፡፡ ዳላስ ላይ በተሰናዳው አመታዊ ፌስቲቫል ላይ እሳቸው ቢመጡ በሚለው አጀንዳ ላይ ስንነጋገር
የተዘጋጀው ስታድየም የደረጃ ጥራት፣ የሴኩሪቲ ጉዳይና አንዳንድ ነገሮች የተመቻቹ ስላልነበሩ መሆን አልቻለም፡፡
ምክንያቱም እኚህ በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ፍቅር የሚለገሳቸው ተወዳጅ መሪ እሳቸውን በሚመጥን ፕሮቶኮልና ክብር
ሳንነፍግ በትክክለኛው መንገድ ለማስተናገድ ባለመቻላችን እናዝናለን፡፡
በወቅቱ ደግሞ እንዲመጡ የታሰበበት ጊዜ አጭር ስለነበርና ትክክለኛ ስራ ላንሰራ እንችላለን የሚል ጥርጣሬ ስላደረብን በዛ
ምክንያት ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ ሆኖም አሜሪካ በመጡ ጊዜ በተዘዋወሩባቸው የአሜሪካ ስቴቶች በአጠቃላይ እየዞርን ዝግጅቱን
ከመሳተፍም ባሻገር አጋርነታችንን አሳይተናል፡፡ እናም ሁሌም ቢሆን እኚህ ተወዳጅ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ቢገኙልን ደስ ይለናል፤
እንደውም ዘንድሮ አትላንታ ላይ በምናዘጋጀው ደማቅ ድግስ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ቢያደርጉልንና ኳሱን መትተው
ቢያስጀምሩልን ደስታችን ወደር የለውም፡፡
ሊግ፡- የግብዣ ወረቀቱን ልትልኩላቸው አስባችኋል?

አቶ አብይ፡- እንዳልኩህ እዚህ አሜሪካ የሚገኘው ሰፊው ማህበረሰብ ለእኚህ የለውጥ አባት ያለው ፍቅርና ከበሬታ የተለየ ነው፡፡
እናም ጥረታችን ይቀጥላል፡፡ እርግጥ ነው ስራ በጣም እንደሚበዛባቸው እናውቃለን፡፡ ሆኖም በፕሮግራሙ ላይ ይገኙልን ዘንድ
ኢንቪቴሽን ፔፐሩን ከመላክ ወደኋላ አንልም፡፡ ጥሪያችንንም ተቀብለው እንደሚመጡ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ሊግ፡- አሁን የተፈጠረውን አመቺ ሁኔታ በመጠቀም አንድ ውድድር ኢትዮጵያ ውስጥ ለማድረግ አልታሰበም?
አቶ አብይ፡- ታስቧል፡፡ ነብሳቸውን ይማረውና በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸው ካለፈው አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ጋር አንዳንድ
ነገሮችን ጀምረን ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በሃገራችን በርካታ ብቃት ያላቸው አለም አቀፍ ስታንዳርድ የሚያሟሉ ስቴድየሞች
ስላሉ ይሄን ለማድረግ ይቻላል፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ 800 ተጨዋቾችን ነው የምናጓጉዘው፡፡
ከእነርሱ በተጨማሪ የቦርዱ አባላትና ደጋፊዎች አሉ፡፡ እናም ይሄን አብቃቅተን ውድድሩን ወደዚህ ካመጣን ፕሮግራሙ እንዴት
መከናወን አለበት? በሚለው ነጥብ ላይ እየተወያየን ነው፡፡ ይህ የእኔ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የሁሉም የቦርድ አባላትና ደጋፊዎቻችን
ስሜት ነው፡፡ ከምንም በላይ ወደዚህ መጥተን የዚህ የለውጡ አካል በመሆን ድጋፋችንን ለማሳየት ጊዜው አሁን ነው፡፡
እስካሁን በነበረው ሁኔታ ለ35 አመታት ያህል እውቅና አላገኘንም፡፡ ከዚህም ባሻገር በጊዜው በነበረው የፖለቲካ ችግር ምክንያት
ወደዚህ መምጣት አላሰብንም ነበር፡፡ አሁን ግን በአገራችን ደማቅ ፀሃይ ወጥቷል፤ እናም ወደዚህ ሀገር መጥተን ውድድሩን
የማናካሂድበትና የማንሳተፍበት ምንም አይነት ምክንያት የለም፡፡ እግረ መንገዳችንን ለሀገራችን ኢኮኖሚ እገዛ እናበረክታለን፡፡
ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ በየዓመቱ ወደተለያዩ ስቴቶች ስንዘዋወር በብዙ መቶ ሚሊየን ደረጃ የሚገመት ብር ነው የሚጠፋው፡፡
ተጨዋቾች መኪና ይገዛሉ፣ትኬት ይቆርጣሉ፣ ሆቴል ይይዛሉ፣ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ እናም ያ ገንዘብ ለአንድ ከተማ እድገት
የሚጫወተው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡
በመሆኑም እዛ የምናጠፋውን ገንዘብ ወደሃገራችን ብናመጣው ጠቀሜታው ሁለትዮሽ ነው፡፡ በመሆኑም በሂደት አንዱን ውድድር
ወደዚህ የማምጣት ሃሳብ አለን፡፡
ሊግ፡- አዲስ አበባ ላይ ቅርንጫፍ ቢሮ የመክፈት ሃሳቡስ የላችሁም?
አቶ አብይ፡- በሚገባ አለን እንጂ፤ አንደኛው ወደዚህ የምንመጣበት አላማ ይህ ነው፡፡ ፌዴሬሽናችን ከአሁን በፊትም የተለያዩ
ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ሲወጣ ነው የቆየው፡፡ ወደፊትም እገዛውን ከማሳደግ ባሻገር ለወጣቱ መዋያ የሚሆን
መዝናኛ ስፍራና ላይብረሪ የማቋቋም ሃሳብ ስላለን እዚህ ቅርንጫፍ ቢሮ የመክፈት ሃሳብ አለን፡፡ ይሄንንም ለማሳካት በስፋት
እየተነጋገርን ነው፡፡
ሊግ፡- ደጋግመው ሲናገሩ እንደሰማሁት በሃገራችን በተፈጠረው ለውጥ በእጅጉ መደሰታችሁን ገልፀውልኛል፡፡ ይህ ለውጥ እስርዎ
ለሚመሩት ፌዴሬሽን ፋይዳው እንዴት ይገለፃል?
አቶ አብይ፡- ከአሁን በፊት በነበረው ሁኔታ በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን፣ አድሎ እንዳይኖር፣ አንዱ ጎሳ በሌላው ጎሳ ላይ ሳይነሳ
ሁላችንም በእኩልነት እንድንጓዝ ለማስቻል በኢትዮጵያዊነት ከመክፈቻው እስከመዝጊያው ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ቀን ስንሰብክ
ነው የነበረው፡፡ ይሄን በማድረጋችን ብዙ መስዋዕትነትን ከፍለናል፡፡ ከዛም አልፎ ተርፎም የተለየ የፖለቲካ አቋም የነበራቸው
ወገኖች እኛን የፖለቲካ ድርጅት እንደሆንና አሊያም ደግሞ እንደ ሽብርተኛ እየተቆጠርን ለአገራችን ከምናደርገው ድጋፍ ይልቅ
ጥፋታቸው ይበልጣል የምንባልበት ጊዜ ነበር፡፡ አሁን ግን ያ ዘመን ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር
እየተነጋገርን እነርሱም ድጋፍ እያደረጉልን ሃሳብ በማመንጨት ይሄን ብታደርጉ በማለት እየተመካከርን በጋራ እየሰራን ነው ያለነው፡፡
ይህም በመሆኑ በውጪ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሃገሩን ለመርዳት የሚፈልግ በመሆኑ እኛ ለ36 አመት ያገኘነውን የስራ ልምድ
ወደዚህ በማምጣት ስፖርቱን ማገዝ፣ አገራችንን ማሳደግና ለውጡን በመደገፍ ላይ ነው ትኩረት አድርገን እየሰራን ያለነው፡፡
ሊግ፡- በ36ኛው የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ፕሮግራም ላይ ምን አዲስ ነገር ታቅዷል?
አቶ አብይ፡- አትላንታ ላይ ያቀድነው ከ35 አመት ታሪካችን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተገኝተው የበአሉ
ታዳሚ ይሆናሉ፡፡ ከአሁኑ በፊት በነበረው ሁኔታ ግን ማንም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጥሪ ብናደርግላቸውም አይገኙም
ነበር፡፡ ሌላውን ተወውና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ብንወስድ እዚህ መጥተው ውድድሩን በመዘገብ ለህዝቡ እንዲያስተላልፉ ጥሪ
ብናደርግላቸውም ፈፅሞ አይገኙም ነበር፡፡ አሁን ሁሉ ነገር ተለውጧል፡፡ ከፍተኛ የሆነ ስሜትም አለ፤ ኢንተርቪው እንደልብ
እንሰጣለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ እንደውም በቅርቡ ለስራ ጉዳይ ወደሃገር ቤት በመጣሁ ጊዜ በኢቲቪ ቀርቤ የሚሰማኝን ነገር በነፃነት
ከማውራትም ባሻገር በአገራችን የተፈጠረውን አንፀባራቂ ለውጥ በከፍተኛ ደረጃ እንደምደግፍ ተናግሬያለሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለኢቲቪ
ጣቢያና በወቅቱ እኔን አፈላልጎ በማግኘት ጥሩ ሊባል የሚችል ቃለ-ምልልስ ላደረገልኝ ጋዜጠኛ ማንደፍሮ ታደሰ ላቅ ያለ
ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ በአጠቃላይ በአትላንታ በሚደረገው አመታዊ ውድድር ከለውጡ በኋላ የሚደረግ የመጀመሪያ
ፕሮግራም በመሆኑ የተመረጡ የመንግስት ሃላፊዎች እንዲገኙ ይደረጋል፡፡

በመሆኑም ይህ ፕሮግራም የአንድነት ስሜት የተላበሰና የይቅርታ ጊዜ የሚሰበክበት በመሆኑ የአትላንታው ፕሮግራም ከሌላው ጊዜ
በተለየ ደማቅ ይሆናል ብለን እናስባለን፡፡
ሊግ፡- በየአመቱ እንግዶችን እንደምትጋብዙ ይታወቃል፤ የዘንድሮው የESFNA የክብር እንግዳ ማነው?
አቶ አብይ፡- እንግዳ የምንመርጥበት መስፈርት የተለያየ ነው፡፡ በየአመቱ የሚጋበዙ እንግዶችን የሚጠቁም ኮሚቴ አለ፡፡ ይህ
ኮሚቴ እንግዶች የሚጋበዙበትን ቅድመ ሁኔታ ጥናት ያደርግና ለቦርድ አባላቱ ያቀርባል፡፡ ቦርዱ ደግሞ የተጠቆመው እንግዳ ከአሁን
በፊት ያለውን አስተዋፅኦ መለስ ብሎ በማየት ጥናት ያደርጋል፡፡ እናም መስፈርት የሚሆነው ምንም አይነት አድሎ በሌለበት ሁኔታ
ለአገራቸው ስፖርት ማደግ የጎላ አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር እንይዝና በትክክለኛው መስፈርት በዚህ ዓመታዊ
ውድድር ላይ የሚሳተፉ እንግዶች ይመረጣሉ፡፡ በዘንድሮው የአትላንታ ውድድር ላይ ሶስት እንግዶችን ለመጋበዝ አስበናል፡፡ በዋናነት
የክብር እንግዳችን የሚሆነት አቶ ሃይለማሪያም ሻሾ ናቸው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ የቀድሞ ሯጭ የነበሩትና በአውሮፓ የሚኖሩት ሻምበል
መህመድ ከድር ሲሆኑ ቀሪው ደግሞ በ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለብሄራዊ ቡድናችን ተሰልፈው ዋንጫ ያገኙትና በግብ ጠባቂነት
የተሳተፉትን አቶ ጊላ ሚካኤልን ነው፡፡
ሊግ፡- እናንተ ወደዚህ ሃላፊነት ከመጣችሁ ምን ያህል ጊዜ ተቆጠረ?
አቶ አብይ፡- በእኛ ፌዴሬሽን አሰራር መሰረት እያንዳንዱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁለት ተርም አለው፤ ፕሬዝዳንት ሆኖ
የሚመረጠው ግለሰብ ለሶስት አመት ያክል ያገለግላል፡፡ ከዚያ ከእንደገና ምርጫ ይደረግና ፕሬዝዳንቱ በድጋሚ ከተመረጠ ለሁለተኛ
ተርም ያገለግላል፡፡ ከፕሬዝዳንቱ ሌላ ፀሃፊውና ቢዝነስ ማኔጅመንቱ ሶስት ሶስት አመት የስራ ተርም ሲኖራቸው ሌሎች ስራ
አስፈፃሚዎች ግን ሁለት አመት የስራ ዘመን አላቸው፡፡ ነገር ግን አንድ ተመራጭ ከሁለት ተርም ውጪ በሃላፊነት መቆየት
አይችልም፡፡ እኔ ወደዚህ ሃላፊነት ከመጣሁ ደግሞ ይህ የመጀመሪያ ዓመቴ በመሆኑ ሁለት ቀሪ የስራ አመታት አሉኝ፡፡
ሊግ፡- ይህ ፌዴሬሽን አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያስቻሉ ግለሰቦችን እንዴት ነው የምትዘክሯቸው?
አቶ አብይ፡- ይህ ፌዴሬሽን እንዲመሰረት ጥንስስ ከጣሉት ግለሰቦች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት አቶ ብርሃኑ ወልደ
ማሪያም ናቸው፡፡ እሳቸው ሁሌም በየአመቱ በሚደረገው ውድድር ላይ የክብር እንግዳችን ናቸው፤ እኚህ ግለሰብ ከዛሬ 35 አመት
በፊት አስበው በአራት ቲሞች መካከል የጀመሩት ፕሮጀክት ይኸው አሁን ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሶ 31 ቡድኖች በውድድሩ ላይ
እየተሳተፉ ናቸው፡፡ እናም ለእኚህ ታላቅ ሰው እውቅና መስጠት ስላለብን በየአመቱ እየጋበዝናቸው ሽልማት እንዲሰጡልንና ምስጋና
እንዲደርሳቸው እናደርጋለን፡፡ ከእሳቸው በተጨማሪ በዚህ ፌዴሬሽን የምስረታ ጉዞ ላይ በርካታ ሰዎች አሻራውን አኑረዋል፡፡ ከእነርሱ
መካከል አቶ ፍስሃ ወልደ አማኑሄል፣ እነ አቶ ተስፋዬ፣ አቶ ሽመልስና ሌሎችም ያልጠቀስኳቸው ግለሰቦች ለዚህ ፌዴሬሽን
ምስረታና በሁለት እግሩ እንዲቆም ለማስቻል ለከፈሉት መስዋዕትነት ከፍ ያለ ክብርና ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ፡፡
ሊግ፡- በአውሮፓ ከሚገኘው ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ለመስራት ያሰባችሁት ነገር አለ?


አቶ አብይ፡- አለ፡፡ ብዙ ጊዜም እንደዛ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ የመጓጓዝና የቪዛ ችግር ይኖራል፡፡ ከአሁን ቀደም
ከአውሮፓ እየመጡ አሜሪካ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ነበሩ፤ ሆኖም ቦታው ባለው ርቀትና በቪዛ ምክንያት ብዙ ተጨዋቾች ወደዚህ
ለመምጣት ያዳግታቸዋል፡፡ በዛ ምክንያት የምንደክምበት ስራ ፍሬአማ መሆን አልቻለም፡፡
ከዚህ ውጪ ግን የእኛን ተሞክሮ በማጋራትና እነርሱ ጥያቄ ካላቸው እያቀረቡልን ብዙ ምክክሮችን እናደርጋለን፡፡ እናም በተቻለን
አቅም ልምዳችንን በማጋራት የምንችለውን አድርገናል፡፡
ሊግ፡- ልንሰነባበት ነውና አንድ እድል ልስጥዎት?
አቶ አብይ፡- ይህ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ፌዴሬሽን ካለው ስብስብና የሰው ሃብት አንፃር በሂደት የአገራችንን ስፖርት ያሳድጋል
ብለን ነው የምናስበው፡፡ በዚህ በኩልም ከስፖርት ኮሚሽኑ ጋር ተነጋግረን እዚህ መጥተው ተጨዋቾቹን እንዲገመግሙና አገር
ውስጥም መጥተው ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ከዚህ በተረፈ በእጅጉ የምንወዳት አገራችንን ባህልና ወግ
ማስተዋወቅ ነው፡፡ በዚህ ረገድም ተሳክቶልናል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን የመጣውን ለውጥ መደገፍ ነው፤
ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡
ሊግ፡-ውድ ጊዜዎን ሰውተው ለሊግ ስፖርት ጋዜጣና ዌብሳይት ተከታታዮቻችን ይህን የመሰለ ቃለ-ምልልስ ስለሰጡኝ ላቅ ያለ
ምስጋናዬን አቀርባለሁ?
አቶ አብይ፡- እኔም በምስረታ አንጋፋ በሆነችውና ለአገር ውስጥ ስፖርት በተለየ ትኩረት ሰጥታ በምትሰራው ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ላይ
እንግዳ ሆኜ በመቅረቤ በጣም አመሰግናለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P