Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጪ ካሉ ክለቦች ጋር የምታገኘው አንድ ዋንጫ ትልቅ ስኬት ነው” “መቻል ከያዘው ስብስብ አንጻር የምንጫወተው ለዋንጫ ነው” አስቻለሁ ታመነ / መቻል/

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች  ከኳሱ ሲገለሉ የሚሰሩት ስራ የለም የተጨማሪ ሙያ ወይም ሌላ የቢዝነስ አማራጭ ስለማያስቡ ርዳታ ሲጠየቅላቸው ይታያሉ ተብሎ  ይታማሉ .. በተጨዋችነት ዘመን  ያገኙትን  ሀብት ለሌላ ገንዘብ አመንጪ ቢዝነስ አይጠቀሙም ተብሎም ይተቻሉ…. በርግጥ ይህን ትችት ካሸነፉና ከተጨዋችነት ሲገለሉ የፋይናንስ ጥያቄ የማይነሳባቸው   ተጨዊቾችም አሉ…. ይሄን መንገድ  ከተከተሉ  ተጨዋቾች መሃል አንዱ ደግሞ አስቻለሁ ታመነ በምሳሌነት ይጠቀሳል….  ከመቻል ጋር የሊግ ዋንጫ  ለማንሳት እንደሚያቅዱ የሚናገረው አስቻለሁ  በቅርቡ የከፈተውን  “አስቻለሁ ታመነ ስፔሻል ስጋ ቁርጥ” ሆቴሉን ቅዳሜና እሁድ ያስመርቃል…. ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ  ጋር ቆይታ ያደረገው ጠንካራው የመሃል ተከላካይ  አስቻለሁ ታመነ ስለ መቻል፣ ስለ አዲሱ ቢዝነሱ፣ ስለ ዋሊያዎቹ፣ ስለ አዲሱ የበጀት  ገደብ  ደንብና ሌሎች ጉዳዮች ለቀረበለት ጥያቄዎች  ምላሹን ሰጥቷል።

ሊግ:-  ለ2017 እንኳን አደረሰህ …የአመቱን ጅማሮ እንዴት አገኘኧው ..?

አስቻለሁ:- ከሁለት ቦታ ከፍለን እናውራ… ከቤተሰብ ጋር ከረጅም ጊዜ በኋላ አዲስ አመትን በማክበሬ ደስ ብሎኛል። ባለ ትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነኝ በቤተሰቤም ደስተኛ ነኝ  አዲስ አመትን ተቀብያለሁ ለሌሎች ቤተሰቦች ልጆችን ትምህርት ማስገቢያ  ነው ወጪም ብዙ የሚኖርበት ጊዜ ነው  እንደ በዓል  ጥሩ ጊዜ ነበር ያሳለፍኩት  ከክፍለሃገርም ቤተሰቦቼ መጥተው ስለነበር ጥሩ ጊዜ ነበረን .. ብዙ ጊዜ በአልን ከቤተሰብ ጋር የማክበር እድሉ አልነበረኝም ስፖርተኛና ወታደር  ብዙ ጊዜ ከቤተሰብ ጋር አይይገኙምና ዘንድሮ ግን እድሉን አግኝቼ በማክበሬ ደስተኛ  ነኝ ክለቡ ዕረፍት ሰጥጦቶን ያገኘሁት  ዕድል ነው  ጥሩ የበአል አከባበር ነበረኝ ሁለተኛው ከመቻል ጋር ተያይዞ  አዲስ አመት እንደመሆኑ የመጀመሪያ ጨዋታችንን ፎርፌ ብናገኝም በሲዳማ ቡና ነጥብ ጥለናል.. አሁን ደግሞ  ወላይታ ድቻን አሸንፈናል ስህተትን  ማረም አለብን በርግጥ  ባሰብንበት ደረጃ ለመገኘትም  ገና  ነን  አዲስ አመት በመሆኑ በቀጣየቹ ጊዜያት የምናስበውን የምናሳክበት ጊዜ አለን ብዬ አምናለሁ..ወደፊት ጥሩ ጊዜ ይኖረናል ብዬ አምናለሁ 2017 እንዲህ ነው የጀመርነው

ሊግ:-  በፕሪሚየር  ሊግ ደረጃ 2007 ጀመርክ ዘንድሮ 10ኛ አመትህን እየያዝክ ነው …?

አስቻለሁ አዎ ትክክል ነው ….

ሊግ:-  በ10 አመት ቆይታህ ያካበትከውን ሀብት  ሰብስበህ ቁርጥ ቤት ቦሌ ላይ ከፈትክ …ባለሀብት መሆንህን እያሳየኧን ነው ..?

አስቻለሁ:– /ሳቅ በሳቅ/  ባለሀብት ሆኜ ሳይሆን ለቀጣይ ኑሮ ቢዝነሴን መሞከር የግድ ስለሆነ ነው፡፡

/ሳቅ/ የግል ስራዎችን እሞክራለሁ  ያገኘሁትን ገንዘብ ንብረት ላይ ቶሎ  ብዬ ስለማውል ጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ እግዚአብሄር  ይመስገን… እንዳልከው ቦሌ ላይ ስጋ ቤት ከፍቻለሁ “አስቻለሁ ታመነ ስፔሻል ቁርጥ” ይላል   ቦሌ ሴላቪ በርገር ጀርባ ይገኛል በዚህ አጋጣሚ   የስፖርት ቤተሰቡም ይሁን  ይህን ቃለምልልስ የሚያነብ በሆቴሉ ተገኝቶ  እንዲጠቀም  ጥሪ አደርጋለሁ ብዙ ቢዝነሱ አልተለመደም ያም ሆኖ ብዙ ገንዘብ ወጥቶበታል መጥታችሁ ተጠቀሙ እላለሁ../ ቃለምልልሱን የሰራነው ባለፈው  ማክሰኞ ምሽት ነው /

ሊግ:- ለተጨዋቾቹ የምትለው ነገር አለ..?

አስቻለሁ:– አዎ ምክርማ አለኝ … እንደ መነሻ  ቢዝነስን ስትጀምር መድፈርን ይጠይቃል ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶበት ኪሳራም ይሁን ትርፍ ሊከሰት ይችላል ያም ሆኖ መድፈር  ይጠይቃል እግርኳስ ተጨዋች በመሆን ባገኘሁት ገንዘብ ቢሆንም የማሰራው   እግርኳስን እድሜ ልክ መጫወት አንችልም  ነገን የተሻለ ለማድረግ መድፈር አለብን ፈር እየያዘ ሲሄድ ትልቅ ለውጥ ይፈጥራልና  ጓደኞቼን ወዳጅ ዘመዶቼን ባለሙያዎችን አማክሬ ቁርጥ ቤቱን ከፍቻለሁና  የሙያ ጓደኞቼም ነገን እንዲያስቡና ቢዝነሱን  እንዲሞክሩ እመክራለሁ  አጽንኦት ሰጥቼ ለጓደኞቼ  የምናገረው  እግርኳስ ረጅም አመት የምትጫወትበት አይደለም ከበዛ 15 አመት ብትጫወት ነው ብዙ ጊዜ የሚሰማው የተጨዋች ውድቀት ነው እገሌ ለተባለው ተጨዋች ገንዘብ አዋጡ መባል የተለመደ ሆኗል ይሄ  መቅረት አለበት እግዜር በሰጠን ገንዘብ መጠቀም መቻል አለብን ጥሩ ክፍያ ነው የምናገኘውና ነገን አስበን ገንዘባችንን ተገቢ ቦታ ማዋል  አለብን በርግጥ ወደ ተሻለ ቢዝነስ ለመቀየር አማካሪ ሊኖረን ይገባል፡፡  የግድ ግን  ስፖርቱ ውስጥ  ያሉ አማካሪ መሆን የለባቸውም  በነገራችን ላይ ቀድመው  የበሰሉ ሆቴል ከፍተው ጥሩ ቢዝነስ እየሰሩ ያሉ ተጨዋቾች … እነ አዳነ ግርማ ሽመልስ በቀለ ጥሩ ምሳሌ ናቸው በሀዋሳ ሆቴልና እንግዳ ማረፊያ ከፍተው የሚሰሩ.. አርአያነታቸውን ማየት አለብን እንደነሱ ልባም መሆን ይጠበቅብናል ዛሬያችንን መጠቀም ለነገው ጉዟችን ወሳኝ ነው  ይሄን  መልዕክት ነው  የማስተላልፈው …

ሊግ:- ወደዚህ ቢዝነስ ዞር ማለትህ ከእግርኳሱ ልትሰናበት እንደምትችል ማሳያ ይሆን…..?

አስቻለሁ:– / ሳቅ / ኧረ በፍጹም … ገና ሳልጀምር ለማቆም ማሰብ አይታሰብም ለማቆምም ማሳያ አይደለም  እግርኳስ ዋና ስራዬ ነው በፊትም ቢሆን ክፍለሀገር ላይ ንግድ ምናምን እሞክራለሁ አሁን የጀመርኩት  አይደለም   እኔ በመጣሁበት ወቅት ገንዘቡ ጥሩ ስለነበር  ያገኘሁትን ወደ ቢዝነስ ላይ ማዋል እመርጣለሁ  የከፈትኩት ሆቴል የሚያሳየው ያገኘሁት ገንዘብ  መጥፎ ቦታ ላይ አለመዋሉን  እንጂ ኳስ  ላቆም እንደሆነ አይደለም /ሳቅ/  ገና  የመጫወትና ማሳካት የምፈልገው ነገር ያለኝ ተጨዋች ነኝ እግርኳስ ዋናና ዋና ስራዬ ነው ሀብት ያፈራሁት በምወደው በዚህ ሙያዬ ነው እግዜር እድሜ በሰጠኝና ጤነኛ  እስከሆንኩ ድረስ እጫወታለሁ ብዬ አምናለሁ እኛ ሀገር ረጅም ጊዜ ፊትህን ካዩ ብዙ የሚሰጥ ስም ይኖራል እንጂ ገና ነኝ፡፡

ሊግ:- የምትጫወትበትን ዘመን  በቁጥር መገመት ትችላለህ …?

አስቻለሁ:- በፍጹም አልገድበውም ጤነኛ ሆኜ መጫወት ችዬ አቅሜን እስካሳየሁ ድረስ  እጫወታለሁ ብዬ አምናለሁ እግርኳስ የሜዳ ላይ ስፖርት ነው የሚታይ… እንድቀጥልም እንዳቆምም የሚያደርገኝ ሜዳ ላይ የሚታይ በመሆኑ መቼ አቆማለሁ ብዬ ማሰብም አልፈልግም፡፡  እግዚአብሄር ይመስገን ፊቴ በተደጋጋሚ  ለረጅም ጊዜ መታየቱ ካልሆነ በቀር  ለመጫወት ገና ነኝ  የምገድበው ዘመን የለም ረጅም አመት ገና እጫወታለሁ።

ሊግ:-  የመጀመሪያ የሆቴልህ ምርቃት ላይ ሙሉ የመቻል ተጨዋቾች ተገኝተዋል …መደገጋገፋችሁን  ያሳያል ..?

አስቻለሁ:- አዎ ምን ጥርጥር አለው ገና ለአንድ አላማ አይደል የምንጫወተው … በእለቱ የክለቤ ተጨዋቾች ሌሎች ጓደኞቼም ተገኝተዋል። ያኔ ጥሪ ያደረኩት በማህበራዊ ሚዲያ ነበር፡፡ በቲክቶክ ጥሪዬን ሲያስተጋቡ የነበሩ ጓደኞቼንም በዚህ አጋጣሚ አመሰግናለሁ  ከዚያ ውጪ ያ ምርቃት  በማህበራዊ ሚዲያ በመሆኑ ብዙ ሰው አልተገኘም አሁን ደግሞ ለመጪው ቅዳሜ  በጥሪ ካሮድ እንዲገኙልኝ ጥሪ አደርጌያለሁ፡፡ ትላልቅ እንግዶች በተገኙበት አርቲስቶች ፣ የስፖርት ሰዎች፣ በእግርኳሱ  ላይ ያሉና   ሚዲያዎች በተገኙበት  በትልቅ ደረጃ ይመረቃል በዚህ አጋጣሚ ይህን ቃለምልልስ ያየ ያነበበ ሁሉ ጥሪ አልደረሰኝም ብሎ  ሳይቀር መጥቶ እንዲመርቁ  ጥሪ አደርጋለሁ፡፡

ሊግ:-  አምና መቻል ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የተመዘገበ ትልቅ ውጤት ነው…አንተስ እንዴት አየኸው..?

አስቻለሁ:- አናዶኛል እንጂ አላስደሰተኝም ሀዋሳ ላይ በነበረው ውድድር ከሻሸመኔ  ከተማ ጋር  ተጫውተን የጣልነው ነጥብ ያበሳጫል፡፡ በርግጥ እግርኳስን ወደኋላ መመለስ አትችልም በሻሸመኔ ጨዋታ ነጥብ ባንጥል ብዬም ሰበብ እየሰጠሁም አይደለም  ድሬዳዋ ላይ  በመድን ነጥብ ስንጥል ባለቀ ሰአት በተቆጠረብን ግብ ነው፡፡ እነዚያ ውጤቶች አናደውኛል፡፡ ያም ሆኖ እግዜር  የፈቀደው ነው የሆነው፡፡

ሊግ:- አምና የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው ያሸነፈው .. ዘንድሮ  የሊጉን  ዋንጫ  የማሸነፍ ተራው የመቻል  ነው  እንበለው ..?

አስቻለሁ:-  ግዴታ ነው መቻል ከያዘው ስብስብ አንጻር የምንጫወተው  ለዋንጫ ነው  በርትተን እንፋለማለን  አምና የተቆጨንበትን ዋንጫ ዘንድሮ ከአሰልጣኞቻችን በሚሰጠን አመራር  ከጓደኞቼና ከቦርዱ ጋር  ሆነን ለማምጣት  ጠንክረን እንሰራለን ከእግዜር ጋር ለማሳካትም እንጥራለን፡፡

ሊግ:- ቦርዱና አስተዳደር ክፍሉ በደንብ እየደገፏችሁ ነው…?

አስቻለሁ:- አዎ በደንብ  ነው የምንደገፈው  ምንም ችግር የለብንም  ..መቻል ሳንገባም ውጪ ሆነን  የምንሰማው ምርጥ መሆኑን ነው ያን እያየን ነው ጥሩ ድጋፍ አለን የሚጠበቀው የኛ ጥረት ብቻ ነው፡፡

ሊግ:-  ከፋይናንስ  ገደቡ ጋር ተያይዞ ምን የምትለው ነገር አለ…?

አስቻለሁ:-  ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ  እንደ ህግ የተቀመጠው ነገር ተጨዋቾች ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ከባድ ነው  በዚያ አካሄድ  ሳይቀጥል ተጨዋች ላይ የሚያርሰው ጉዳት ተታይቶ ማስተካከያ ይደረጋል ብዬ አምናለሁ .. እግርኳስ ተጨዋች ረጅም አመት አይጫወትም፡፡  ከ10-12  አመታት ነው  በጣም ከበረታ ነው 15 አመት ነሚጫወተው … በዚህ ዘመን ነው የእድሜ ልኩን ሀብት የሚፈጥረውና  መታገዝ  አለበት እግርኳስን  እስከ 35 አመት ተጫውቶ  ቢያቆም  ከዚያ በኋላ ላለው ህይወቱ ነው የሚሰራውና ሊግ ኩባንያውና ፌዴሬሽኑ ይህን አይተው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ያስተካክሉታል ብዬ  ተስፋ አደርጋለሁ።

ሊግ:-  በዋሊያዎቹ  የመሃል  ተከላካይ ክፍል ደጀን የሆነው አስቻለሁ ታመነ ጠፋሳ..?

አስቻለሁ:- አዎ ጠፍቻለሁ… አምና ሊጉ ሊያልቅ በጉዳት ረጅም ጨዋታ አምልጦኛል..  በዚህ ምክንያት ነው ከዋሊያዎቹ ውጪ የሆንኩት ዘንድሮ ግን በሙሉ ጤንነት ሰርቼ ዳግም ወደ ዋሊያዎቹ ስብስብ እመለሳለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡

ሊግ:–  በ2017  ምን ለማሳካት አቅደሃል ..?

አስቻለሁ:-  በእግርኳስ ብዙ ነገር  አሳክቻለሁ  በአገር ደረጃ ያሉ ዋንጫዎችን አንስቻለሁ የፕሪሚየር ሊግ  የጥሎማለፍና የሲቲካፕ ዋንጫዎችን አሳክቻለሁ ለአፍሪካ ዋንጫ  ባለፈው ስብስብ  ውስጥ አለሁበት ብዙ ታሪክ  ሰርቻለሁ፡፡ ይህን ስኬት በመቻል መድገምም እፈልጋለሁ … በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ያገኘኋቸው የሊግ ዋንጫ ድሎችን በመቻል መድገም እፈልጋለሁ፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ  ያሳካሁትን  ስኬት  ከመቻል ጋር  ሆኖ  አንዴ ማሳካት ዕድለኝነት ነው  ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጪ  ካሉ  ክለቦች ጋር የምታገኘው አንድ ዋንጫ  ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ዋንጫ አንሰቶ ከማያውቅ ቡድን ጋር  አንዴ  የሊጉን ዋኔጫ ማሳካት ድሉ የተለየ ነውና ያንን ማሳካት እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ:-  ውጤታማ የነበረውና  በአሸናፊነቱ  የሚታወቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የውጤት መንገራገጭ ገጥሞት ስታይ ምን ተሰማህ ..?

አስቻለሁ:-  በጣም አዝኛለሁ ….ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለበት ሁኔታ አሳዛኝ ነው፡፡ የተሻለ ነገር ኖሮኝ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የሆነ ነገር ባደርግ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ጊዮርጊስ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም ነገ  ከነገ ወዲያ ግን በፋይናንስ ተጠናክሮ ዳግም እንደማገኘው ተስፋ  አደርጋለሁ፡፡ በፈረሰኞቹ ቤት ተጫውቶ  እንዳለፈ እንደማንኛውም  ተጨዋች እያሳለፈ ባለው ውጣ ውረድ አዝኛለሁ።

ሊግ:- ጨረስኩ ….የመጨረሻ  ቃል  ካለህ …?

አስቻለሁ;– ዋና ስራዬ እግርኳስን መጫወት ነው .. ከመቻል ጋርም የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት እፈልጋለሁ..  ያንን እንደማሳካ  ተስፋ አደርጋለሁ።  ቢዝነስ ውስጥ ደግሞ ገብቻለሁ  ቦሌ የሚገኘው አስቻለሁ ታመነ  ስፔሻል ቁርጥ ቤትን ቅዳሜ አስመርቃለሁ በካርድም ጥሪ ያደረኩላችሁ ሁኑ ያላደረኩላችሁ በዚህ አጋጣሚ  ቅዳሜና እሁድ  ተገኝታችሁ እንድትመርቁልኝ  ጥሪ አደርጋለሁ እኔን መደገፍ ማበረታታት የሚፈልጉ ማንኛውም ስጋን የሚወድ ሁሉ መጥቶ እንዲመገብና ቤቴን እንዲመርቅልኝ ጥሪ አደርጋለሁ፡፡

ሊግ:- አመሰግናለሁ  በኳሱም በቢዝነሱም  እንዲሳካልህ እመኛለሁ…

አስቻለሁ:– አመሰግናለሁ እግዜር ይስጥልኝ…

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P