Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“አስደሳች የውድድር ዓመትን እያሳለፍን እንገኛለን፤ አሳዳጊ ክለቤን በምንፋለምበት የዛሬው ጨዋታ ጥሩ ፉክክር ይታያል”ሳለአምላክ ተገኝ /ባህር ዳር ከተማ/

 

የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የፕሪምየር ሊጉን በተቀላቀለበት የዘንድሮ የውድድር ዘመን እያስመዘገበ
የሚገኘው ጣፋጭ እና አበረታች ውጤት በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶለታል፤ ክለቡ በዚህ ዘመን
ተሳትፎው የሀገሪቱን ታላላቅ ቡድኖችም ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የሊግ መሪውንም መቐለ 70 እንደርታን
በሳለአምላክ ተገኝ ብቸኛ ግብ ማሸነፉም የቡድኑን ደጋፊዎች እንዲደሰቱም አድርጓል፤ የባህር ዳር ከተማ
ለእዚህ ውጤት እንዲበቃ የቡድኑ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው /ማንጎ/ እና የተጨዋቾቹ ጥምረት ለስኬት
ያበቃው ሲሆን የቡድኑን የውድድር ጉዞና ስለ ራሱ የኳስ ሕይወት ከክለቡ ውጤታማ ተጨዋች ሳለአምላክ
ተገኝ ከጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ጋር ቆይታ አድርጎ ተጨዋቹ ምላሹን ሰጥቷል፡፡

ሊግ፡- “አማራው” ተብለህ ነው የምትጠራው፤ ለምን ተባልክ? ስሙንስ ማን አወጣልህ?
ሳለአምላክ፡- “አማራው” የሚለውን ስም ያወጣልኝ ኢትዮጵያ ቡና በነበርኩበት ጊዜ አሰልጣኝ በያን ሁሴን
ነው፤ ይሄ ስም ሊወጣልኝም የቻለው የ2007 ዓ.ም ላይ ከዋናው ቡድን ጋር ለ15 ቀን ልምምድ ሠርቼ
ነበርና በአንድ ልምምድ ላይ የእኔ ስም ለበያን ይጠፋዋል፤ ያኔ ክለባችን ውስጥ ከጋምቤላ እና ከተለያዩ
ክልሎች የመጡ ተጨዋቾችም ነበሩና እኔን ሊጠራኝ ፈልጎ ስሜ ሲጠፋበት ጊዜ ከየት ክልል እንደመጣው
አውቆ በጓደኞቼ አማካኝነት አማራው ብሎ አስጠራኝና ከዚሁ ጊዜ በኋላ ነው በስሙ ልጠራበት የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ጨዋታ ጅማሬህ ምን ይመስላል?
ሳለአምላክ፡- የእር ኳስ መጫወት የጀመርኩት ተወልጄ ባደግኩበት የባህር ዳር ከተማ ውስጥ ነው፤ እዛው
ነው ከህፃንነቴ እድሜዬ አንስቶ በድሮው የአየር ማረፊያ በኋላ ላይ ደግሞ መስቀል አደባባይ የሚል ስያሜ
በተሰጠው የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ላይ ኳስን ማንከባለል የጀመርኩት፡፡
ሊግ፡- የትውልድ ስፍራህንና እድገትህን እንዴት ነው የምትገልፀው?
ሳለአምላክ፡- የባህር ዳር ከተማ ውስጥ የሚገኘው እና በልዩ ስሙም ጊሽ አባይ ተብሎ የሚጠራው የትውልድ
ስፍራዬ ለእኔ ከምንም ነገር አስበልጪ የምወደው ቦታ ነው፤ በዛም ቦታ ላይም ሳድግ ኳስን በመጫወት ነው
ያሳለፍኩት፡፡
ሊግ፡- የልጅነት እድሜህ ላይ ኳስ ስትጫወት ተምሳሌትህ ማን ነበር?
ሳለአምላክ፡- የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ እንደመሆኔ የልጅነቴ እድሜዬ ላይ ኳስ ስጫወት ያደነቅኩት
ተምሳሌቴምያደረግኩት ተጨዋች ቢኖር ክርስትያኖ ሮናልዶን ነው፤ በእኛ ሀገር ደረጃ ደግሞ አሸናፊ ግርማን ነው
አድንቄ ያደግኩት፡፡
ሊግ፡- የቤተሰባችሁ አባላት ውስጥ የእግር ኳስ ተጨዋች አንተ ብቻ ነህ? ስንት ወንድምና እህት አለ?
ሳለአምላክ፡- በቤተሰባችን ውስጥ ያሉት እህቶቼ እና ወንድሞቼ ሲደመሩ አስር ናቸው፤ 5 ወንድም እና 5
እህቶችም አሉኝ፡፡
ሊግ፡- አንድ ቡድን ልትሰሩ አንድ ልጅ ጎደላችሁ ማለት ነው?
ሳለአምላክ፡- (ሳቅ ካለ በኋላ) አዎን፤ እንደዛ በለው ከቤተሰባችሁ አባላት ውስጥ የእግር ኳስ ተጨዋች
አንተ ብቻ ነህ ወይ ላልከኝ በፊት እኔ ብቻ አልነበርኩም፤ ታላቅ እህቴም ኳስ ትጫወት ነበር፤ በኋላ ላይ ግን
ወላጅ አባቴ ትምህርት ላይ እንድታተኩር ነገራትና ኳስን መጫወት በማቆም በትምህርቷ ቀጥላ የአሁን ሰዓት
ላይ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ሙያ ልትመረቅ ችላለች፡፡ ስለዚህ የአሁን ሰአት ላይ ኳሱን የምጫወተው እኔ
ብቻ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የህፃንነት እድሜዬ ላይ ሳለህ የእግር ኳስ ተጨዋች እሆናለሁ ብለህ ጠብቀህ ነበር? የቤተሰብ
አመለካከትስ ምን ይመስል ነበር?
ሳለአምላክ፡- የእግር ኳስ ተጨዋች ለመሆን እንደምችል ማሰብ የጀመርኩት ገና ልጅ እያለሁ ነው፤ ይህንንም
ለሰፈሬ ልጆች እነግራቸውም ነበር፤ ያኔ ኳስን በጣም ከማፍቀሬ የተነሳ አንድ ቀን ጥሩ ደረጃ ላይ እደርሳለሁ
በሚልም በርትቼ ስለሰራሁ የምፈልገውን ተጨዋች ለመሆን ችያለሁ፤ ቤተሰቦቼ በኳሱ ላይ ያላቸው
አመለካከት እነሱ በትምህርት ጥሩ ደረጃ ላይ እንድንደርስ እንጂ ማንም ኳስን እንድጫወት አይፈልጉም ነበር፡፡
ብዙ ጊዜ ኳስን በተደጋጋሚ የምጫወተው እኔ ስለነበርኩም ወላጅ አባቴ አጥብቆ ይቆጣኝም ነበር፡፡ አባቴ
በተለይ ኳስን እንዳልጫወት እና በትምህርቴ ገፍቼ ጥሩ ደረጃ ላይ እንድደርስም ከመፈለግ ከመንግስት ት/ቤት
አስወጥቶ ጥሩ ትምህርት እንዳገኝም በሚል የግል ትምህርት ቤት ያስገባኝ ሁኔታም ነበርና ይሄን አልረሳውም፤
እሱ ኳስን ልጫወት ብል እንኳን በትምህርት ቤት ውስጥ ብቻ እንድጫወትም ነበር የሚፈቅድልኝ፡፡
ሊግ፡- ለመጀመሪያ ጊዜ የእግር ኳስን የት ክለብ ገብተህ ተጫወትክ?
ሳለአምላክ፡- የኢትዮጵያ ቡና የተስፋ ቡድን ውስጥ ገብቼ ነው የተጫወትኩት፤ ከዛ በፊት በፕሮጀክት ደረጃ
እንኳን አልተጫወትኩም፤ ወደ ቡና ተስፋ ልገባ የቻልኩት አዲስ አበባ ላይ ተዘጋጀቶ በነበረው የ2005ቱ
የመላው ኢትዮጵያ የትምህርት ቤቶች ውድድር ላይ ባህር ዳርን ወክዬ በመጣሁበት ወቅት በሜዳ ላይ ባሳየሁት
ጥሩ ብቃት ልመለመል በመቻሌ ነው፡፡
ሊግ፡- ወደ ኢትዮጵያ ቡና ስትመጣ ምልመላውን ያደረገልህ አሰልጣኝ ማን ነው? ክለቡን ስትቀላቀልስ ምን
አይነት ስሜት ተሰማህ?
ሳለአምላክ፡- ኢትዮጵያ ቡናን በተስፋ ቡድን ደረጃ እንድቀላቀል ምልመላውን ያደረገልኝም ሆነ ወደ ቡድኑ
ያስመጣኝ አሰልጣኝ በያን ሁሴን ነው፤ እሱ ያኔ እኔን ጠርቶ ሲያናግረኝም ወደ የት ክለብ እንደምገባም

የክለቡን ስም ጠቅሶ አልነገረኝም ነበርና ትንሽ ግራ ወደ መጋባት ደረጃ ደርሼ ነበር፤ በኋላ ላይ ግን አንተ
ገብተህ የምትጫወትበት ክለብ ለኢትዮጵያ ቡና የተስፋ ቡድን ነው ብሎ ሲነግረኝ በጣም ነበር የተደሰትኩት፤
ያኔ የ11ኛ ክፍልም ተማሪ ነበርኩ፤ ወደ ቡና መግባቴን ለቤተሰቦቼም ስናገር አባቴም ሰምቶ ነበርና በፍፁም
አይሆንም፤ ወደ እዛም አትሄድም ትምህርትህን ተማር ሲለኝ የእኔ የኳስ ስሜት ከፍተኛ በመሆኑ እና
የገባሁበት ክለብ ደግሞ በታሪክ ትልቅም ነውና ይሄ እድል በፍፁም እንዲያመልጠኝ አልፈለግም ብዬው ከብዙ
ጭቅጭቅ በኋላ እህቶቼን ጨምሮ አንዳንድ እሱን የሚያውቁትም ሰዎች ልጅህ ጥሩ የእግር ኳስ ተሰጥኦ
አለው፡፡ እንዲጫወትም ፍቀድለት ሲሉት በኋላ ላይ ነው እሺ በማለቱ የቡናን የተስፋ ቡድን ተቀላቅዬ ልጫወት
የቻልኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን ከመጫወት ውጪ በትምህርቱ ላይስ እንዴት ነበርክ?
ሳለአምላክ፡- ጥሩ እና ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ፤ ወላጅ አባቴም ያንን ስለሚያውቅም ነበር ኳሱን ትቼ
በትምህርት ብቻ እንድገፋ ይፈልግ የነበረው፤ በጊዜው በትምህርቱ ላይ የነበረኝ ውጤትም ጥሩ የሚባል ነበር፤
የ10ኛ ክፍል ትምህርቴን ያጠናቀቅኩትም 3.8 በማምጣት ነበር፤ ከዛ በኋላ ግን በትምህርቱ ለመቀጠል
ሁኔታዎች አመቺ ስላልሆኑልኝ ልቀጥል አልቻልኩም፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጰያ ቡና ቆይታህ እንዴት ይገለፃል?
ሳለአምላክ፡- የኢትዮጵያ ቡና ቆይታዬ የ2006 ዓ/ም አንስቶ ነው፤ ወደ ቡና ስገባም በመጀመሪያ ለተስፋ
ቡድኑ ተጫወትኩ፤ የ2007 ዓ.ም ላይ ደግሞ ወደ ዋናው ቡድን አደግኩና እዛ ቆይታ አደረግኩ፡፡ ያም ሆኖ ግን
በፕሪምየር ሊጉ ደረጃ የመጫወት እድሉን ላገኝ ስላልቻልኩ ቡድኑ የ2008 ላይ በውሰት ለባህር ዳር ከነማ
ስጠኝና እዛ መጫወት ጀመርኩ፤ በኋላ ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናዎች ሰርቪያዊውን አሰልጣኝ ፓፓዲችን
በቀጠሩበት ጊዜ ለእኔም ወደ ቡድኑ ተመልሼ እንድመጣ ጥሪው ደረሰኝ እና በእሱ ስር የመጫወት እድሉን
ሳገኝ ጊዜ በክለቦች በደንብ የመታየት እድልን ስላገኘው በኋላ ላይ ለቡና በቀጣይነት ለመጫወት ባልችልም ወደ
ባህር ዳር ከነማ በመግባት ከቡድኑ ጋር ጥሩ የጨዋታ ጊዜን ላሳልፍ ቻልኩ፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ከተማ ክለብ ወስጥ በነበረህ ቆይታ ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማሳለፍ ችላችኋል፤ ዘንድሮ
ደግሞ የሊጉም ጠንካራ ተፎካካካሪ መሆን ቻላችሁ፤ የሁለቱን ስሜት በምን መልኩ ትገልፀዋለህ?
ሳለአምላክ፡- የባህር ዳር ከተማ ክለብን ከሚወዳደርበት የከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ከማስገባት ባሻገር
የፕሪምየር ሊጉም ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን በማስቻላችን ለእኔ ከሁሉም በላይ ያስደሰተኝ ዋንኛው ጉዳይ
ቢኖር ቡድኑ የትውልድ ክልሌ በመሆኑ ነው፡፡ ከዛ ውጪም ዘንድሮ “አስደሳች የውድድር ዓመትን እያሳለፍን
እንገኛለንና ይሄም ለእኔ ልዩ የሆነ ጊዜያት ሆኖልኛልና ደጋፊዎቻችንም በራሱ የተለዩ ስለሆኑም የባህር ዳር ከተማ
ተጨዋች መሆን መቻሌ በራሱ ልዩ የደስታ ስሜት እንዲሰማኝ ነው ያደረገው፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳሱ የቀጣይ ጊዜ ራዕይህ እና ግብህ ምንድነው?
ሳለአምላክ፡- የእግር ኳሱን ስጫወት የእኔ ዋንኛ ራዕዬም ግቤም ክለቤን ባህር ዳር የፕሪምየር ሊጉ ጠንካራ
ተፎካካሪ በማድረግ ለታላቅ ደረጃ ላይ ማብቃት እና ወደ ውጭ ሃገርም ሄዶ የፕሮፌሽናል ተጨዋች መሆን ነው፡፡
ከዛ ውጪ ለሃገሬ ብሄራዊ ቡድንም በተደጋጋሚ በመመረጥ መጫወትም እፈልጋለሁ፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ከተማን የዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ተሳትፎን እንዴት ነው የምትገልፀው?
ሳለአምላክ፡- የፕሪምየር ሊግ የእዚህ አመት ተሳትፎአችን ከታችኛው ሊግ እንደመምጣታችን ጥሩ እና
ከጠበቅነው በላይ ነው፤ ለብዙ ክለቦችም አስፈሪ ሆነናል፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የእዚህ አመት እቅዳችሁ ምን ነበር?
ሳለአምላክ፡- የእኛ እቅድ የነበረው ክለባችንን ጠንካራ ተፎካካሪ አድርጎ በሊጉ ላይ ማቆየት መቻል ነበር፤
አሁን ላይ ግን በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠን ጥሩ የሚባል ውጤትን እያስመዘገብን ይገኛል፡፡
ሊግ፡- ባህር ዳርን የውድድር አመቱ ሲጠናቀቅ ምን ደረጃ ላይ እንጠብቀው?
ሳለአምላክ፡- በሊጉ ውድድር አሁን ላይ የምንገኝበት ደረጃም ሆነ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴያችን ጥሩ የሚባል
ነውና እንደራሴ አመለካከት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነን ሊጉን ከአንድ እስከ አራተኛ ባለው ደረጃ ውስጥ ሆነን
እንጨርሳለን፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ጠንካራ እና ክፍተት ጎኑ ምንድነው?
ሳለአምላክ፡- ጠንካራው ጎናችን በመከላከሉ ላይ ጥሩ ነን፤ ከአንድ በላይም ጎል አይቆጠርብንም፤
በማጥቃቱ ላይ ስንጫወትም ለእዚህ አሰልጣኙ ተጨዋቾችን ቦታ እያቀያየረ የሚያጫወትበት የራሱ
ፍልስፍናም አለውና ያ ሊጠቅመን ችሏል፡፡ ክፍተት ጎንን በተመለከተ ከታችኛው ሊግ እንደመምጣታችንና ጥሩ
ውጤትም እያስመዘገብን ስለሆነን ብዙም አልታየኝም፡፡
ሊግ፡- ባህር ዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን ሲያሸንፍ የድሉን ግብ አስቆጥረሃል፤ ጨዋታው ምን ይመስላል?
ጎል በማስቆጠርክስ ምን ተሰማህ?
ሳለአምላክ፡- የመቐለ 70 እንደርታ ጋር የነበረን ጨዋታ ጥሩ ፉክክር የተደረገበት ነበር፤ የተሻለ
ስለተጫወትንም ግጥሚያውን አሸንፈናል፤ በእዚህ ጨዋታ እኔም የድሉን ጎል ስላገባሁ እና ደጋፊዎቻችንም
ይህን ጨዋታ ማሸነፍ መቻልን በጣም ይፈልጉት ነበርና ግጥሚያውን በማሸነፋችን የተሰማኝ ስሜት ከፍ ያለ
ሆኗል፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ከተማ ውስጥ አሁን ላይ ተከላካይ ሆነህ ነው የምትጫወተው፤ ከእዚህ በፊት በነበረህ የእግር
ኳስ ህይወት ደግሞ የመስመር አጥቂ እና አጥቂም ሆነህ ተጫውተህ ነበር….?

ሳለአምላክ፡- የእግር ኳስን መጫወት ከጀመርኩባቸው ጊዜያቶች አንስቶ የመስመር አጥቂ እና አሁን ለይ
ደግሞ ተከላካይ ሆኜ ነው በመጫወት ላይ የምገኘው፤ በእነዚህ መጫወቻ ቦታዎች ላይም ጥሩ ለመንቀሳቀስ
ችያለሁ አምና የመስመር አጥቂ ሆኜ ስጫወት ለክለቤ አምስት ጎሎችን አስቆጥሬያለሁ፤ ዘንድሮ ደግሞ
ተከላካይ ሆኜ 2 ጎሎችን ለማስቆጠር ችያለሁና ይሄ የሚያስደስተኝ ነው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር ዛሬ የሚኖራችሁን ጨዋታ እንዴት ትጠብቀዋለህ? ምን ውጤትስ ይጠበቅ?
ሳለአምላክ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚኖረን ጨዋታ ለእኔ የቀድሞ አሳዳጊ እና ለዛሬም እዚህ ደረጃ ላይ
መድረሴ የጥርጊያውን በር የከፈተልኝን ቡድኔን በተቃራኒነት የምፋለምበት ጨዋታ ስለሆነ እንደዚሁም
ሁለቱም ቡድኖች በርካታ ደጋፊዎችም ስላላቸው በሜዳ ላይ ጥሩ ጨዋታን እናሳያለን ብዬ ነው ስለግጥሚያው
የምገልፀው፤ ከጨዋታው በኋላ የሚመጣውን ውጤት በተመለከተ ጥሩ እና ተሽሎ የተጫወተው ቡድን
ያሸንፋል ከማለት ውጪ ምንም የምለው ነገር የለም፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….
ሳለአምላክ፡- የእግር ኳስ ደረጃዬን ዛሬ የምገኝበት ስፍራ ላይ እንዳስቀምጥ እስካሁን እኔን በማሰልጠንም ሆነ
በመምከር ጥሩ አስተዋፅኦን ያበረከቱልኝ አካላቶችን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ እነዚህም በመጀመሪያ ወደ ቡና
ተስፋ ቡድን እንድመጣ እና እንድጫወት መንገድ የከፈተልኝን አሰልጣኝ በየነ ሁሴንን ነው የማመሰግነው፤
በመቀጠል ባህር ዳር በነበርኩበት ጊዜ እኔን ያሰለጠኑኝ እንዳለ ጥላሁን እና አራዶምን በተለይ ደግሞ እንዳለ
የጨዋታው ዘይቤዬን አይቶ አንተ የመስመር አጥቂ ሆነህ ብትጫወት ትልቅ ቦታ ትደርሳለህ ብሎኝ ነበርና በዛ
ቦታ እንድጫወት መንገዱን ስለከፈተልኝ እንደዚሁም ቤተሰቦቼን የባህር ዳር አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው
/ማንጎ/ እና ደጋፊዎቻችንን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P