Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ያዘጋጀው የስፖርት ጨዋነት ምንጮች የምክክር መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መረን
እየለቀቀና ለሀገር ስጋት እየሆነ የመጣውን
የስፖርታዊ ጨዋነት የመደፍረስ አደጋን
ለመከላከል ይቻል ዘንድ አንጋፋው የቅ/
ጊዮርጊስ ክለብ በሸራተን ሆቴል ያዘጋጀው
የሁለት ቀናት የፓናል ውይይት በስኬት
ተጠናቋል፡፡ የሰላም፣ የባህልና ቱሪዝም
ሚኒስትርና የኢትዮጵያ እግር ኳስ
ፌዴሬሽን በአጋርነት በተገኙበት በዚህ
ታላቅ የፓናል ውይይት ላይ በሀገሪቱ
አሉ የሚባሉና ጉዳዩ የሚመለከታቸው
የስፖርት ቤተሰቦች የተሳተፉ ሲሆን
በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ደረጃ ከፊታችን
የተጋረጠውን አደጋ በእንጭጩ መቅጨት
ይቻል ዘንድ በርካታ ገንቢ ሃሳቦች ተነስተው
ተንሸራሽረዋል፡፡ በዚህ ታላቅና ሀገር አቀፍ
ደረጃ ለተሰናዳው ትልቅ መድረክ የቅ/
ጊዮርጊስ ክለብና በተለይ ደግሞ የቦርድ
ሰብሳቢው አቶ አብነት ገ/መስቀል ላሳዩት
ከፍተኛ የሆነ ተነሳሽነት ተሳታፊዎቹና
የመንግስት ተወካዮች ላቅ ያለ ምስጋና
አቅርበዋል፡፡ በዚህ መድረክም ላይ የተለያዩ
ሃሳቦች ከተሰነዘሩ በኋላ የሚመለከተው
የአቋም መግለጫ ወጥቷል፡-
የአቋም መግለጫ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር
ዶክተር አብይ አህመድ “በኢትዮጵያዊያኖች
መካከል ውይይት መባዛት አለበት” ባሉት
መሠረት በሚያዝያ 14 እና 15/2011
ዓ.ም በሼራተን አዲስ ሆቴል ለሁለት ቀን
የተካሄደው “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች”
የውይይት መድረክ የሚቀጥለውን የአቋም
መግለጫ ለኢትዮጵያ መንግስት እንዲቀርብ
በጋራ ተስማምቷል፡፡
በቅድሚያም ጉባኤው፡-
1) የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም
ሚኒስቴር እና የባህል ቱሪዝም ሚኒስቴር
በውይይቱ ላይ በመካፈላቸው፣ እንዲሁም
2) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም
በመተባበሩና ለውጥ ፈላጊ መሆኑን
በመግለፁ የተሰማውን ደስታ እየገለፀ፤
3) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር
በራስ ተነሳሽነትና የጠቅላይ ሚኒስትሩን
መመሪያ በመከተል የውይይቱን መድረክ
ስላዘጋጀ ምስጋናውን እያቀረበ፤
4) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨዋታ
አካባቢ የሚፈጠረው ረብሻ በጎሳ፣ በብሄር
ወይም በቋንቋ ልዩነት ላይ የተመሠረተ
እየሆነ መምጣቱን በመረዳት፣
5) ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች
መካከል የፖለቲካ አመለካከቶቻቸውን
የሚያንፀባርቁ ስሞች፣ አርማዎችና ልዩ
ልዩ ምልክቶች ያሏቸው መኖራቸውን
በመገንዘብ፣
6) ክልሎችም ሆኑ ከተሞች እግር
ኳስን የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ መሣሪያ
ማድረጋቸውን በማስተዋል፣
7) በእነዚህ ምልክቶች የተነሳም፣
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨዋታ አስጊና
አሳዛኝ ሁኔታ ላይ በመገኘቱ፣
8) ዘርን የተመለከቱ የኦሊምፒክ
ቻርተርና የኢንተርናሽናል ፌዴሬሽኖች
ደንቦች እየተጣሱ በመሆኑ፣
9) የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ
አስተዳዳሪዎች በሙያና በችሎታ ሳይሆን
በብሔር ተዋፅኦ የሚመረጡበት አሠራር
በመኖሩ፣
10) የትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች
ስፖርት እንቅስቃሴ መዳከም በመጉላቱ፣
11) ያም ሆኖ የእግር ኳስ ክለቦችን
አቅም በመመዘንና ያገሪቱን ኢኮኖሚ
በማገናዘብ፣
12) የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠነክር
በትና ሕዝቡም የሚዋሐድበት የስፖርት
እንቅስቃሴው መሆኑን በማመን፣
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ መንግስት የስፖርት እንቅስቃ
ሴውን ችግሮች በመረዳትና ዓለማቀፍ
የስፖርቶቹን ሕጎች እና ደንቦች ለማክበር
ይቻል ዘንድ ተገቢውን እርምጃዎች ለመ
ውሰድ እንዲረዳ የውይይቱ መድረኩ በሚከ
ተሉት አቋሞች ላይ በጋራ ተስማምቷል፡-
1) የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ
ውስጥ የዘር ልዩነት እንዲጠፋና የኦሊ
ምፒክ ቻርተርና የኢንተርናሽናል ስፖርት
ፌዴሬሽኖች ደንቦች እንዲከበሩ እንዲደረግ፤
2) ዘራቸውን ወይም ብሔራቸውን
መሠረት አድርገው የተቋቋሙት የእግር
ኳስ ክለቦች ስማቸውን እንዲቀይሩ፤
3) የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና
የልዩ ልዩ ስፖርት ፌዴሬሽኖች መሪዎችና
አባሎች በዘራቸው ሳይሆን በሞያቸውና
በችሎታቸው ብቻ እንዲመረጡ፤
4) የትምህርት ሚኒስቴር ስፖርት
በትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች እንዲ
ስፋፋ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ፤
5) የኢትዮጵያ ስፖርት እንቅስቃሴ
አገልጋዮች በጎ ፈቃደኞች መሆናቸውን
በመገንዘብ የወጣቱ ትውልድ በበጎ ፈቃደ
ኝነት እንዲሰለፍ እንዲበረታታ፤
6) የኢትዮጵያ ስፖርት ድርጅቶች
ለማገልገል የሚመኙ ሁሉ በስነ ምግባር
ኮሚቴዎችና በመንግስት ፀጥታና ደህንነት
አገልግሎት እንዲሁም በፖሊስና በፀረ
ሙስና ኮሚሽን እንዲመረመሩ፤
7) ኢትዮጵያን በዓለም ስፖርት
ጉባኤዎች የሚወክሉት መልዕክተኞች ቢያ
ንስ አንድ የውጭ አገር ቋንቋ አጣርተው
የሚያውቁና ውይይቱን መከታተል የሚ
ችሉ መሆናቸው እንዲረጋገጥ፤
8) የፖሊስና የደህንነት ድርጅቶች
የስፖርት ውድድሮችን በተለይ እግር
ኳስ ጨዋታን በፀጥታና በጥበቃ መስክ
ከፌዴሬሽኖቹ ጋር በመተባበር የሚሰሩ
ቋሚ ኃላፊዎች በየከተሞቹ እንዲመደቡ
አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ፤
9) በኢትዮጵያ ያሉት የስፖርት
ስታዲየሞችና መጫወቻ ስፍራዎች
ተገቢ የእሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም
የሕክምናና የአምቡላንስ አገልግሎትና በቂ
የመፀዳጃ ስፍራዎች እንዲኖራቸው፤
10) የአልኮል መጠጥ ከስታዲየሞች
ውስጥ እንዳይሸጥና ሲጃራ ማጨስ ክልክል
መሆኑን እንዲታወጅ፤
11) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚዘጋጁት
ውድድሮች ፎርማት ለክለቦች ተስማሚና
ለስፖርት ዕድገት የሚጠቅም እንዲሆን
እንዲደረግ፤
12) ይህን የአቋም መግለጫ ለክቡር
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያቀርቡልንና
መንግስትም ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት
ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የኢትዮጵያ ስፖርት
እንቅስቃሴ ኦሎምፒክ ቻርተር አክባሪ
እንዲሆን ተገቢውን ውሳኔ እንዲያስተላልፉ
ክብርት የሰላም ሚኒስትርንና ክብርት
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርን በአክብሮት
እንጠይቃለን፡፡
አዲስ አበባ
ሚያዝያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም
የስፖርት ጨዋነት ምንጮች
የውይይት መድረክ

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P