Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ደቡብ ፖሊስን ከሊጉ እንዳይወርድ ማድረግ ቀዳሚው ግቤ ነው”

ሄኖክ አየለ /ደቡብ ፖሊስ/

ሊግ፡- ደቡብ ፖሊስ ከፕሪምየር ሊጉ ላለመውረድ ይጫወታል፤ አንተ ደግሞ ለክለቡ  ተደጋጋሚ ጎሎችን እያስቆጠርክ ለኮከብ ግብ አግቢነቱ እየተፎካከርክ ይገኛል፤ እነዚህን ሁኔታዎች እንዴት  ነው የምትመለከታቸው?

ሄኖክ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎአችን ላይ  እስካሁን በተደረጉት ጨዋታዎች ለክለቤ 10 ያህል ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክሩ ውስጥ ብገኝም የእግር ኳሱን በአሁን ሰዓት ላይ እየተጫወትኩ የምገኘው በወራጅ ቀጠናው ላይ የሚገኘውን ቡድኔን ከወራጅ ቀጠናው ላይ በማዳን የመጪው ዓመት የውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ ነውና ይሄን እቅዴን ለማሳካት እስከመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ድረስ ከፍተኛ ጥረትን አደርጋለው፡፡

ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ ውድድር በወራጅ ቀጠናው ላይ ለሚገኘው ደቡብ ፖሊስ  10 ግቦችን ለማስቆጠር ችለሃል፤ ጎሎቹ በቂ ናቸው? ወይንስ ከእዚህም በላይ ግቦችን ማስቆጠር ትችል ነበር?

ሄኖክ፡- ደቡብ ፖሊስን ዘንድሮ ከተቀላቀልኩበት ጊዜ አንስቶ እኔ ያስቆጠርኳቸው የግብ ብዛቶች ከተጫወትኳቸው ጨዋታዎች አንፃር የሚታዩ ከሆነ ብዙ ናቸው፤ ይሄን ለማለት የቻልኩትም ቡድኑን በተቀላቀልኩበት ጊዜ ተቀይሬ ከመግባት በዘለለ ብዙ የመሰለፍ እድሉን የማላገኝ ስለነበርና ክለባችን ደግሞ የፍፁም ቅጣት ምት በሚያገኝበት ሰዓት በአሰልጣኛችን ውሳኔና ትህዛዝ መሰረት የክለቡ አንደኛ መቺ አበባው ቡታቆ እንጂ እኔም ስላልሆንኩ ከእዚያ በላይ ማስቆጠር እየቻልኩ ያን ማድረግ አልቻልኩምና እስከአሁን ያገባዋቸው ግቦች ለእኔ በቂ ናቸው፡፡ ከእዚህ በኋላ በሚኖሩት ጨዋታዎች ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ግቦችን እኔም ሆንኩኝ የቡድን ጓደኞቼ በማስቆጠር ቡድኔ ከሊጉ እንዳይወርድና የሚተርፍበትንም ስኬታማ ስራን በጋራ ለመስራት ተዘጋጅቻለው፡፡   

ሊግ፡- የእግር ኳስን ተጫውተህ ባሳለፍክበት የእስካሁን ህይወትህ ደስተኛ ነህ?

ሄኖክ፡- በጣም እንጂ፤ የእግር ኳስ ተጨዋች መሆን የልጅነት እልሜ ነበር፤ ያን ስላሳካሁትም ነው ደስተኛ የሆንኩት፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን በብዙ አጋጣሚዎች ስትጫወት  የሚከፋህ ምን ጊዜ ነው?

ሄኖክ፡- ብዙ ጊዜና በተደጋጋሚ የሚከፋኝ የምጫወትበት ቡድኔ  ውጤት ሲያጣና ሽንፈት ሲያጋጥመው ነው፤ ከእዛ ውጪ ተደጋጋሚ የሆኑ ጉዳቶች ሲያጋጥሙኝ እና ከሜዳ ሲያርቁኝም ይከፋኛል፤ ከእነዚህ ውጪ ግን እስካሁን በነበረኝ የኳስ ሕይወት በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡  

ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመንህ ላይ ብዙ ጊዜ የተለያዩ ጉዳቶችን ያስተናገድክ ይመስለኛል፤ እስኪ ስለ ጉዳቶችህ አንድ አንድ ነገር በለን?

ሄኖክ፡- አልተሳሳትክም፤ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውስጥ ገብቼ ኳስን መጫወት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በእኔ ላይ የደረሱት ጉዳቶች ብዙ እና የተለያዩም ናቸው፤ በእኔ ላይ የደረሰው ጉዳትም በሌላ ተጨዋች ላይም የደረሰ አይመስለኝም፤ የእግር ኳስን ስጫወት የመጀመሪያ ጉዳቴን ያስተናገድኩት የ2003 የውድድር ዘመን ላይ ለክለቤ አዳማ ከተማ በታህሳስ ወር ላይ ስጫወት ነበር፤ ያኔ ቡድናችን ከትራንስ ኢትዮጵያ ጋር ለመጫወት ወደ አዲግራት ተጉዞ ነበርና እኔ ህክምናዬን አዲስ አበባ መጥቼ አደርግ ስለነበር  በዛ ጨዋታ ላይ ሳልሰለፍ ቀርቻለው፤ ያኔ እኔ አዲስ አበባ ላይ ህክምናዬን ብከታተልም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የቡድናችን ተጨዋቾች በሰርቪስ ሲመለሱ አዲግራት ላይ በደረሰው የመኪና መገልበጥ አደጋ የቡድናችንን ተጨዋቾች ለጉዳት እና አንዱን ለሞት እንዲሁም በቡድናችን መሪ ላይ የሞት አደጋ በመድረሱ በጊዜው በጣም ነበር ያዘንኩት፡፡ የእግር ኳስ ተጨዋችነት ዘመኔ ላይ ሌላ ጉዳትን ያስተናገድኩበት ዘመን የ2004 ዓ/ም ላይም ለሲዳማ ቡና ስጫወት የደረሰብኝ ከፍተኛ አደጋ ነው፤ ያኔ ኦፕራሲዮን እስከመደረግ ደረጃም ላይ ደርሼ ነበርና ለሁለት ዓመት ያህል ከኳሱ አንድ አንዴ በመሀል ሻል ሲለኝ ልጫወት ብችልም ለመራቅ ችዬ ነበር፤ ሌሎች የደረሱብኝ ጉዳቶች በድጋሚ ወደ አዳማ በገባሁበት ጊዜ ስጫወት የደረሰብኝ ጉዳት እና በኋላ ላይ ደግሞ 2009 ላይ ለወልቂጤ ከተማ ክለብ በተጫወትኩበት ወቅት ከድሬዳዋው ናሽናል ሲሚንት ጋር ስንጫወት ከእነሱ ተከላካይ ጋር በመጋጨት መሬት ላይ ስወድቅና ጭንቅላቴም በተመታበት ሰዓት ምላሴን እስከመዋጥ እና ወደ ጭንቅላቴም ደም ፈሶኝ ለ9 ደቂቃ ያህል ራሴን እስከመርሳት ደረጃ አድርሶኝ ለህክምና ወደ አቤት ሆስፒታል የተወሰድኩበት     ወቅትም ነበርና እነዚህ ጉዳቶቼ እና በኋላም ላይ በፈጣሪ እርዳታ እና እገዛ ከጉዳቶቹ ድኜ ወደ እግር ኳሱ ዳግም የተመለስኩባቸውን ጊዜ መቼም ቢሆን አልረሳቸውም፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት የጀመርከው በምን መልኩ ነው? ለማን ለማን ቡድኖችስ ተጫውተህ አሳለፍክ? በቆይታህስ ምን አይነት ጊዜያቶችን ነው ያሳለፍከው?

ሄኖክ፡- የእግር ኳስን ለመጀመሪያ ጊዜ መጫወት የጀመርኩት ልጅ ሆኜ ተወልጄ ባደግኩበት የወንዶ ገነት ከተማ በኬላው አካባቢ ነው፤ ያኔ ልጅ ሆነን በፕሮጀክት ደረጃም ነው ስንጫወት የነበረው፤ በኋላ ላይ ሳድግ ለትምህርት ወደ ሐዋሳ መጣውና እዛም በፕሮጀክት ደረጃ ከእነ ሽመልስ በቀለ ጋር ኳስን አብረን በጋራ መጫወት ጀመርን፤ ከሐዋሳ የፕሮጀክት ቆይታዬ በኋላ ደግሞ በክለብ ደረጃ የተጫወትኳቸው ቡድኖች የደቡብ መምህራን ኮሌጅ የደቡብ ፖሊስ የአዳማ ከተማ የሲዳማ ቡና የወልቂጤ ከተማ የዲላ ከተማ እና አሁን በድጋሚ እየተጫወትኩበት የሚገኘው የደቡብ ፖሊስ ቡድኖች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግና የከፍተኛ ሊግ የተጨዋችነት  ቆይታዬም ላይ ኳስን እስካሁን ደረጃ ስጫወት ያሳለፍኳቸው ጊዜያቶች ጥሩ የሚባሉ ናቸው፤ ለአዳማ ከተማ ስጫወት 13 ጎል እስከማስቆጠር የደረስኩበትን ጊዜ መቼም የማልረሳው ነው፤ በሌሎች ክለቦች ቆይታዬም ሙሉ ጤነኛ ሆኜም ህመም እየተሰማኝም ሌሎች ጎሎች ያስቆጠርኩባቸውም ጊዜያቶችም አሉና እነዛ የሚያስደስተኝ ናቸው፡፡

ሊግ፡- የደቡብ ፖሊስ የአሁን የተጨዋችነት ቆይታህ ላይ ለኮከብ ግብ አግቢነቱም እየተፎካከርክ ይገኛል፤ ኮከብ ግብ አግቢነቱን የምታሸንፍ ይመስልሃል?

ሄኖክ፡- የደቡብ ፖሊስ  ተጨዋችነቴ ላይ በቀሪዎቹ ጨዋታዎች ወደ ሜዳ የምገባው ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢ ተብዬ ለማሸነፍ ሳይሆን ቡድኔን ከወራጅ ቀጠና ለማዳን ነው፤ ስለ ኮከብነት የማስበው ከዛ በኋላ ነው፡፡

ሊግ፡- በፕሪምየር ሊጉ ነገ እሁድ ቅ/ጊዮርጊስን ትገጥማላችሁ፤ ስለ ጨዋታው ምን ትላለህ? ምንስ ውጤት ትጠብቃለህ?

ሄኖክ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብን የምንፋለምበት የእሁዱ ጨዋታ ከተጋጣሚያችን ትልቅነት አንፃር ለእኛ በጣም ፈታኝ የሚሆንብን ሲሆን ለእዚህ ጨዋታም ለሌሎች ክለቦች እንደምንሰጠው ዝቅተኛ ግምት ሳይሆን ከፍተኛ  ግምት ሰጥተን ወደ ሜዳ በመግባት ግጥሚያውን በጥሩ ውጤት ማለትም የአሸናፊነት ውጤትን ወይንም ደግሞ የአቻ ውጤትን አስመዝግበንበት ከሜዳ ለመውጣት ተዘጋጅተንበታል፡፡

ሊግ፡- ደቡብ ፖሊስ በፕሪምየር ሊጉ የወራጅ ቀጠናው ላይ ይገኛል፤ ዘንድሮ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት እንዴት ነው የምትመለከተው? የዓመቱ ውድድር ሲጠናቀቅስ ቡድናችሁን የት ስፍራ ላይ እናግኘው?

ሄኖክ፡- ደቡብ ፖሊስ የፕሪምየር ሊጉ የውድድር ተሳትፎ ላይ ዘንድሮ እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤትና በአሁን ሰዓት ላይ የሚገኝበት ደረጃ ፈፅሞ  የሚገባው አይደለም፤ ከዛ ውጪም የወራጅ ቀጠናው ላይ መገኘታችንም ካለን ጥንካሬ አንፃር ይሄም ማለት ቡድናችን ብዙ ጎል ያልተቆጠረበትም ቡድን ከመሆኑም አንፃር ምንም ነገርን እንዳላምንም አድርጎኛልና ይሄን ቡድን ከእዚህ ደረጃ አውጥተን የሚገባው ስፍራ ላይ ልናስቀምጠው ይገባል፤ ደቡብ ፖሊስ ውድድሩ ሲጠናቀቅ የሚገኝበት ደረጃም ከወራጅ ቀጠና የሚወጣበት ስፍራም ይሆናል፡፡

ሊግ፡- የእግር ኳስን መጫወት ስትጀምር ተምሳሌትህ ማን ነበር?

ሄኖክ፡- ከባህር ማዶ ተጨዋቾች ፈረንሳዊው የአርሴናል ተጨዋች የነበረው ዳንኤል ቴሪ ኦንሪ ሲሆን ከእኛ ሀገር ደግሞ ሳላህዲን ሰይድ ነው፤ የሁለቱ ተጨዋቾች አጨዋወት በጣም ነበር ደስ የሚለኝ በችሎታቸው ጥሩ አቅም ያላቸው ስለነበሩም አድናቂያቸው በመሆንም ነው ያደግኩት፡፡  

ሊግ፡- በቤተሰብ አካባቢ የእግር ኳስን ስትጫወት ተፅህኖ ነበረብህ?

ሄኖክ፡- ልጅ ሆኜ አዎን፤ በፍፁም ኳስን አትጫወትም እባል ነበር፤ ከዛ በኋላ ግን የሐዋሳ የድሮ ሜዳ ላይ የክለቦች ጨዋታ ሲካሄድና እኔም ስጫወት አባቴ ተደብቆ ይመለከተኝ ነበርና ጎል ሳገባና ጥሩ ስጫወት አይቶኝ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ኳሱን እንድጫወት ፈቀደልኝ፡፡  

ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት እልሞችህ ምንድን ናቸው? ከችሎታህ መካከል ማሻሻል የምትፈልገውስ ምንድን ነው?

ሄኖክ፡- የእግር ኳስን ስጫወት የእኔ ዋንኛ እልሞች የነበሩት ከሀገር ወጥቼ በመጫወት የፕሮፌሽናል ተጨዋች መሆን ነበር፤ እነዚህ እቅድና ፍላጎቶቼ በተደጋጋሚ ጊዜ ይደርስቡኝ በነበሩት ጉዳቶች አማካኝነት በተደጋጋሚም ከሜዳ የራቅኩባቸው ጊዜያቶች ስለነበሩ ሳላሳካቸው ቀርቻለው፤ አሁን ላይ ግን ኳሱን በጥሩ ጤንነት ላይ ሆኜ እየተጫወትኩና ለቡድኔም ጎሎችን እያስቆጠርኩም ስለሆነ አሁን የምገኝበት ደረጃም ለእኔ በቂ ስላልሆነ በችሎታዬ ላይ ያሉብኝን አንድ አንድ ክፍተቶች በማሻሻል ለብሔራዊ ቡድን በመመረጥ ሀገሬን ማገልገል እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- በመጨረሻ…?

ሄኖክ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነቴ ዘመኔ ላይ ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ እኔን በማሰልጠኑም ሆነ በመምከሩ  በጥሩ ጤንነት ላይ እያለውም ሆነ ጉዳት በደርሰብኝ ሰዓት ከአጠገቤ ሆነው የረዱኝን አካላቶች ማመስገን እፈልጋለው፤ በመጀመሪያ ፈጣሪዬን ነው የማመሰግነው፤ ከዛ በመቀጠል ቤተሰቦቼን፣ ከፕሮጀክት አንስቶ እስከ ክለብ ደረጃ ያሰለጠኑኝን አሰልጣኝ ተስፋዬን፣ የዘላለም ሽፈራው /ሞውሪኖ/ ወንድም ፍፁም ሽፈራውን፤ ተመስገን ዳናን በክለብ ደረጃ ደፍሮ የመጫወት እድልን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰጠኝን ዘላለም ሽፈራውን፤ ጓደኞቼን እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት በመማር ተመርቆ የወጣውን ወንድሜን እርቂይሁንን ለማመስገን እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P